uz
Feedback
ATC NEWS

ATC NEWS

Kanalga Telegram’da o‘tish

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

Ko'proq ko'rsatish
127 765
Obunachilar
-1624 soatlar
-287 kunlar
-65030 kunlar
Postlar arxiv
#MoE #ExitExam ትምህርት ሚኒስቴር በጥር ወር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ይሰጣል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል። እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈሉበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማቸው ለየትምህርት ክፍላቸው መላክ ይጠበቅባቸዋል። የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት ደግሞ በራሳቸው እንደሆነ ተገልጿል። ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ምዝገባቸውን https://exam.ethernet.edu.et ላይ ማከናወን ይችላሉ። የምዝገባ ሒደቱን የሚያሳይ ቪዲዮ👇 https://youtu.be/C9KkQ9AHd2o ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ERMP የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ተጀምሯል፡፡ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህክምና ዲግሪ ያላቸውንና የስፔሻሊቲ ስልጠና በ2018 ዓ.ም መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን በብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የዘንድሮው ስልጠና በ22 የማሰልጠኛ ተቋማት እና በ23 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ይሰጣል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ታህሳስ 06-20/2018 ዓ.ም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (https://www.moh.gov.et) ላይ በመግባት በምትፈልጉት የጤና ስፔሻሊቲ መስክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#MekelleUniversity በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም) መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል። የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
DATA_TEMPLATE_LATEST_2018_UPDATED_PRIVATE.xlsx0.20 KB
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በዓመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለማካሔድ የታቀደ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ሰርኩላር ገልጿል፡፡ በዚህም አስፈታኝ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ተፈታኞች እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከታች በተያያዘው ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን በተጠቀሱት ቀናት ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንደታስገቡ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ! የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
🚨2 ቀን ቀረዉ 😰 አሁኑኑ ተቀላቅላችሁ , በ4 ወር ዉስጥ ጥሩ የሚባል የ Cyber Security እውቀት ይያዙ . 🧑‍💻 አሁኑኑ ተመዝገቡ 👨‍💻 🆘LINK: https://course.geezsecurity.com/course/gtst ✅ ለበለጠ መረጃ ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 ℹ️ info@geezsecurity.com #geeztech #gtst @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🚨2 ቀን ቀረዉ 😰 አሁኑኑ ተቀላቅላችሁ , በ4 ወር ዉስጥ ጥሩ የሚባል የ Cyber Security እውቀት ይያዙ . 🧑‍💻 አሁኑኑ ተመዝገቡ 👨‍💻 🆘LINK: https://course.geezsecurity.com/course/gtst ✅ ለበለጠ መረጃ ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 ℹ️ info@geezsecurity.com #geeztech #gtst @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ወደ ትምህርት ቤታችሁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ለ9ኛ ክፍል የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ወዘተ) ➫ የመኝታ አልባሳት (አንሶላ እና ብርድ ልብስ) ➫ ስትማሩ ከነበረበት ትምህርት ቤት መሸኛ እና የትምህርት ውጤት ዩኒፎርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ከያዘበት አቅራቢ ድርጅት በራሳችሁ ወጪ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ወደ ትምህርት ቤቶቹ መሔድ እንደማይቻል ተገልጿል።
Hammasini ko'rsatish...
Ethical Hacking በአማርኛ እየተየቃቹ ከ0 ጀምራችሁ ተማሩ ✅ ይሄን በመንካት ይመዝገቡ 🔗 https://course.geezsecurity.com/course/gtst Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#DillaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ አዳያኣ ግቢ፣ ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ሀሴደላ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#WolaitaSodoUniversity ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል። የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም እና በቦዲቲ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 01/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ C-R የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ S-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ C-S የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ T-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመምህራን የሥራ ቦታ ዝውውር ሊያስጀምር ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የመምህራን እና ትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር በዚህ ዓመት ሊጀመር መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል። የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር መመሪያ መሻሻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ዝውውር ለማድረግ ገዳቢ የነበሩ ችግሮች በተሻሻለው መመሪያ ምላሽ ማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታጠፉ የትምህርት ዓይነቶች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን አዲስ በተመደቡበት የትምህርት ዓይነት ዝውውራቸው የሚፈፀም መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በዘርፉ የሚታየውን የሰው ሃይል ስምሪት ምጥጥን ለማረጋገጥም ያስችላል ተብሏል፡፡ ዝውውሩ ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት በተሻሻለው መመሪያ ላይ በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ከታህሳስ 30/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የዝውውር ፎርም እንደሚሞሉ ተገልጿል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
Ethical Hacking በአማርኛ እየተየቃቹ ከ0 ጀምራችሁ ተማሩ ✅ ይሄን በመንካት ይመዝገቡ 🔗 https://course.geezsecurity.com/course/gtst Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ይመዝገቡ! ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 02-12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ArsiUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 4 ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#WachemoUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ ስማችሁ ከ A-H የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ሆሳዕና ከተማ ➫ ስማችሁ ከ I-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዱራሜ ካምፓስ ፣ ዱራሜ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ A-L የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ሆሳዕና ከተማ ➫ ስማችሁ ከ M-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዱራሜ ካምፓስ ፣ ዱራሜ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 8 ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
GTST ማሠልጠን ከጀመርን 3 ዓመት ሞላን 🎉 አሁኑኑ በመመዝገብ በCYBER SECURITY CERTIFIED በሆኑ እና ልምድ ባላቸዉ አሰልጣኞች ይማሩ✅ ይሄን በመንካት ይመዝገቡ 🔗 https://course.geezsecurity.com/course/gtst Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#BongaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 6 ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በክረምት የትምህርት ፕሮግራሞች በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በሦስተኛ ዲግሪ በመደበኛ መርሐግብር የትምህርት ፕሮግራሞች ትምህርት ይሰጣል፡፡ በሁለተኛ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች፦ ➫ Public Policy and Leadership ➫ Political Economy ➫ Project Management ➫ Peace and Development ➫ Law and Economics ➫ Urban Leadership በሦስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች፦ ➫ Public Policy and Leadership ➫ Political Economy and Governance ➫ Peace and Security በ2018 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ትምህርት ለመማር ፍላጎት ያላችሁና በትምህርት ሚኒሰቴር የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትናችሁ ያለፋችሁ በዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 61 በመቅረብ ወይም በኦንላይን https://forms.gle/At98CD7A3bGjsriT9 እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ 0918707648 / 0918231240 / 0918767516 ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...