fa
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

رفتن به کانال در Telegram

نمایش بیشتر
352 559
مشترکین
+19024 ساعت
+9017 روز
+3 27330 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
#ተጨማሪ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። ተማሪዎች ወደየተመደባችሁበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ስትሔዱ ከወላጅ፣ ከአሳዳጊ ወይም ኃላፊነት ካለው ተጠሪ ጋር መሆን እንዳለበት ተገልጿል። ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተጠሪው ግለሰብ በትምህርት ቤቱ የተዘጋጀውን የስምምነት ሰነድ ፈርመው ለትምህርት ቤቱ አመራር ማስረከብ ይኖርባቸዋል ተብሏል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
78👍 19😱 3🙏 2🥰 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ምዝገባው እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል። እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈላችሁበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማችሁ ለየትምህርት ክፍላችሁ መላክ ይጠበቅባችኋል፡፡ 🔔 የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት በራሳችሁ ነው፡፡ ፈተናውን በድጋሜ የምትወስዱ ይመዝገቡ 👇 https://exam.ethernet.edu.et የምዝገባ ሒደቱን የሚያሳይ ቪዲዮ👇 https://youtu.be/C9KkQ9AHd2o @tikvahuniversity
نمایش همه...
119👍 26👎 6😢 6👏 2🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵 ሰኞ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም 16ኛው እና የመጨረሻው ዙር ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፆቻችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ1,000,000 ብር ዕድለኛ ከሻሸመኔ ሆኗል። ሌሎች የ100 ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም Story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን። 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot #SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #furtheraheadtogether #besh
نمایش همه...
26👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ERMP የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ተጀምሯል፡፡ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህክምና ዲግሪ ያላቸውንና የስፔሻሊቲ ስልጠና በ2018 ዓ.ም መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን በብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የዘንድሮው ስልጠና በ22 የማሰልጠኛ ተቋማት እና በ23 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ይሰጣል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ታህሳስ 06-20/2018 ዓ.ም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (https://www.moh.gov.et) ላይ በመግባት በምትፈልጉት የጤና ስፔሻሊቲ መስክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
46
Photo unavailableShow in Telegram
የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ እና ሲኒማቶግራፊ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 Photography, Videography, Cinematography, Graphic Design እና Video Editing በአንድ ላይ 👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
نمایش همه...
31🥰 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MekelleUniversity በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም) መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል። የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
73👍 15👏 3🙏 3😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ተጨማሪ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም እንደሆነ መገለፁ ይታወቃል። ➫ ወሊሶ የተመደባችሁ የምትሄዱት አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ፦ 0920189695 ➫ ቡኢ የተመደባችሁ የምትሄዱት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፦ 0943165470 ➫ ቦንጋ የተመደባችሁ የምትሄዱት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፦ 0913192165 ➫ ጅግጅጋ የተመደባችሁ የምትሄዱት ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፦ 0922648636 ➫ ጋምቤላ የተመደባችሁ የምትሄዱት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፦ 0911590938 በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወል አስፈላጊ መረጃዎችን መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
81🙏 6🥰 2👍 1👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ይስጡ! የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ በተከታዮቹ ሦስት ሰነዶች ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ ➫ በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ 👇 https://forms.gle/RXsuSUGtFFYrkAMQ9 ➫ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ 👇 https://forms.gle/TZTSPZrJzgEnY2Rq9 ➫ የተፋጠነ ትምህርት መርሐግብር አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ 👇 https://forms.gle/16CDaGfzkXDF6fwt6 ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ/ደንብ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ፣ በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ያግኙ፣ ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ Submit የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ እንደምትችሉ ተገልጿል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
39👎 3👍 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ #AAU በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር እና የፊልም ጥበባት ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም በሁለተኛው ሴሚስተር በቀን መርሐግብር የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ተዘጋጅቷል፡፡ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች፦ 1. MA in Multimedia Theatre 2. PhD in Performing Arts በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ (www.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱ መስፈርቶችን በማሟላት ማመልከት ይቻላል ተብሏል፡፡ ከላይ ለተገለፁት ሁለት የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የማመልከቻ ቀናት የሚያበቃው ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች ውጤታችሁን https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በማየት ከታህሳስ 28 እስከ ጥር 06/2018 ዓ.ምhttps://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms ማመልከት ይችላላችሁ ተብሏል። በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስረከቢያ ቦታ አ.አ.ዩ. ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 መሆኑ ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
51
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል) ለተመደቡ ተማሪዎች ዘግይተው ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡ ምስል፦ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity
نمایش همه...
21
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ 🔔 በምዝገባ ላይ ነን! BSc Fields of Study: → BSc in Medical Laboratory Science → BSc in Pharmacy → BSc in Nursing TVET Programs: → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Accounting and Finance → Hardware & Networking Service → Radiography የCPD ማዕከል አገልግሎት ☎️ 0929969696 / 0996828282 አድራሻ፦ 📍 መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ 📍 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ Telegram: @Yanet6kiloc
نمایش همه...
25🙏 1
በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ
نمایش همه...
DATA_TEMPLATE_LATEST_2018_UPDATED_PRIVATE.xlsx0.20 KB
56😢 10👍 5👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በዓመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለማካሔድ የታቀደ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ሰርኩላር ገልጿል፡፡ በዚህም አስፈታኝ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ተፈታኞች እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከታች በተያያዘው ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን በተጠቀሱት ቀናት ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንደታስገቡ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
90🥰 9👍 2🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!! 🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተኑበት   👉 በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ 👉 ስልጠናው በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል። ☎️  0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
نمایش همه...
53🥰 4👍 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ! የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 220 118👎 23😢 14🥰 11👏 5😱 4🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል። የህጻናት መጻሕፍት፣ የታሪክ መጻሕፍት፣ ልብወለዶች፣ የፍልስፍና መጻሕፍት እና ሌሎችም በተመጣጣኝ ዋጋ በአውደ ርዕዩ ያገኛሉ። በዋናው ግቢ (6ኪሎ) የባህል ማዕከል የተከፈተው አውደ ርዕይ፤ ዛሬ ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል። ይጎብኙ፣ ይሸምቱ! 🕙 እስከ ከሰዓት 11:00 ሰዓት @tikvahuniversity
نمایش همه...
41
Photo unavailableShow in Telegram
🎓 ለተማሪዎች እና ለሥራ ፈላጊዎች! የእርስዎ የሥራ ፍለጋ ጉዞ ከእኛ ጋር ቀላል፣ ፈጣን እና ተስፋ የተሞላበት ይሆናል! የኛን አገልግሎት ተጠቅመው ከሚያገኙዋቸው ጥቅሞች፦ ⚡የሙያ ብቃት፣ ልምድ እና የግል መረጃዎችን ያካተተ ፕሮፌሽናል የሥራ መግለጫ (Profile) መፍጠር፣ ⚡በሚመርጡት የሥራ ዘርፍ አዲስ ማስታወቂያ ሲወጣ ፈጣን የቅፅበት ማሳወቂያዎች (Notifications) ይደርስዎታል፣ ⚡የቅጥር ሂደትን መከታተል የሚያስችልዎ፣ ⚡በሰው ሰራሽ ክህሎት (AI) የተፈጠሩ መልዕክቶችን መፃፍ፣ ⚡ሥራዎችን በቦታ፣ በሙያ ብቃት እና በሥራው ዓይነት መሠረት መፈለግና ማጥራት (Filter) ማድረግ፣ ⚡በቦቱ በኩል ከአሠሪዎች ጋር በቀጥታ መገናኘት! ⚡የትርፍ ጊዜ (Part-time)፣ የሙሉ ጊዜ (Full-time)፣ የልምምድ (Internship) እና የርቀት ሥራ (Remote) አማራጮች የሚያገኙባቸው፣ 👇🏾 ይህን ሊንክ በመጫን AfroJobLink ን ይቀላቀሉ! ፈጣን የሥራ ቅጥር ያድርጉ! 🌐  https://t.me/afrojoblink ለበለጠ መረጃ፦ 0911745927 / 0911632184
نمایش همه...
62👍 4👏 2😱 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ወደ ትምህርት ቤታችሁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ለ9ኛ ክፍል የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ወዘተ) ➫ የመኝታ አልባሳት (አንሶላ እና ብርድ ልብስ) ➫ ስትማሩ ከነበረበት ትምህርት ቤት መሸኛ እና የትምህርት ውጤት ዩኒፎርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ከያዘበት አቅራቢ ድርጅት በራሳችሁ ወጪ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ወደ ትምህርት ቤቶቹ መሔድ እንደማይቻል ተገልጿል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
130👍 17👎 13🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
የፋይዳ መታወቂያ ያውጡ! ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡ ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
87👎 75👍 18😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በመጪው ዓመት የማሪታይም ስልጠና መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት የስርዓተ ትምህርት ቀረጻ እያካሔደ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀጣይ ዓመት ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ የሀገሪቱን የገበያ ፍላጎት በማጥናት ከደረጃ ስድስት እስከ ደረጃ ስምንት (ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ፒኤችዲ) ደረጃ የሆኑ አዳዲስ ስልጠናዎች በኢንስቲትዩቱ እየተሰጡ እንደሚገኙ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ አዲስ ከተጀመሩ የስልጠና መስኮች መካከል የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ የኒው ኢነርጂ ቬሂክል፣ ባዮ-ሜዲካል ቴክኖሎጂስ እና ሳይበር ሴኪውሪቲ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። #ኢፕድ @tikvahuniversity
نمایش همه...
22🙏 5👏 1