352 583
المشتركون
+19024 ساعات
+9017 أيام
+3 27330 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ
ጥምር የማስተርስ እና የፒኤችዲ ፕሮግራም ትምህርት እድል ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ!
ፕሮግራሙ (Joint MA and PhD Program Global Studies: Peace and Security in Africa) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በሌፕዚግ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚሰጥ ነው፡፡
በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ሦስት ተርሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና አንድ ተርም በሌፕዚግ ዩኒቨርሲቲ ቆይታ ይኖርዎታል፡፡ ሁሉም ኮርሶች በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ናቸው፡፡
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
የኦንላይን ቃለመጠይቅ፦ መጋቢት 2018 ዓ.ም
የመጨረሻ ቅበላ ውሳኔ፦ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም
ተጨማሪ ያንብቡ 👉 bit.ly/48Mvn9A
@tikvahuniversity
❤ 38👍 9👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሀገር አቀፍ የግእዝ ጉባኤ ከሚያዚያ 15-17/2018 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡
ለጉባኤው የሚሆኑ የምርምር ጽሑፎችን ከስር በተገለፁት የምርምር ጭብጦች ዙሪያ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡
የምርምር ጭብጦች፦
➫ የጊዜ እሳቤ እና የዘመን መንፈስ በፍልስፍና እና በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፣
➫ የዘመን ስሌትና ጥንታዊ የሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ምርምር፣
➫ ሰው መሆን፣ ባህል፣ እምነት እና ጊዜ በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፣
➫ የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር በግዕዝ ድርሳናት፣
➫ የአቡሻኽር የዘመን አቆጣጠርና የእቆጣጠሩ ብልኃት፣
➫ የዘመን አከፋፈልና የጊዜ እሳቤ በሥነ ተፈጥሮ ጥናት በቅዱስ ያሬድ ሥራዎች፣
➫ የግዕዝ የሒሳብ ስሌት ከዘመናዊ የሒሳብ ስሌት ጋር ሲነፃፀር፣
➫ የግዕዝ ፊደልና ቀመረ ፊደል፣
➫ የገዳማት አስተዋጽኦ በጥንታዊው የዘመን ስሌት፣
➫ የግእዝ ስነ-ጽሁፋዊ ሀብቶች ጥበቃ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣
የአኅጽሮተ ጽሑፍ ማስረከቢያ ጊዜ፦
ከታህሳስ 1-20/2018 ዓ.ም
የተመረጡ የምርመር ጽሑፎች ማሳወቂያ ጊዜ፦
ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም
ሙሉ ጽሑፍ ለጉባኤው አዘጋጆች የሚላክበት ጊዜ፦
ከመጋቢት 25-30/2018 ዓ.ም
የምርምር ሥራዎች የሚላኩበት አድራሻ፦
➫ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አቶ መኮንን ከፋለ
ስልክ ቁ. 0933225306
ኢሜይል፦ mokewwa@gmail.com
➫ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የባህል፣ ታሪክ እና ቋንቋ ልማት ማዕከል
ኢሜይል፦Zemeneworkyohannes19@gmail.com
የሚቀርቡ ጥናቶች ከዚህ በፊት ያልቀረቡና ያልታተሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 14👏 3👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
📣 የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ (ፎረም ህንጻ) እና በአቡነ ጴጥሮስ ግቢ ህንጻ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል።
🏢 የሚከራዩ ቦታዎችና አገልግሎት የሚገኙባቸው ግቢዎች፦ ፎረም ህንጻ (12 ቤቶች) እና አቡነ ጴጥሮስ ህንጻ (11 ቤቶች)።
የሚውሉባቸው አገልግሎቶች፦ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቅ፣ ለቢሮ፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለሾው ሩም፣ ለጂም እና ለዲስፕሌይ ሥራ።
📝 የጨረታ ሰነድ ለማግኘት፦ ተጫራቾች የቦታ ስፋትና የኪራይ መነሻ ዋጋን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን በሚከተለው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ።
AAU ድረ-ገጽ፦ https://shorturl.at/C1uSu
አድራሻ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ 6 ኪሎ ዋናው ግቢ፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣ ቢሮ ቁጥር 314።
ለተጨማሪ ጥያቄ፦ 251-111220001 ወይም 0998656426 ላይ ይደውሉ።
❤ 6
Photo unavailableShow in Telegram
Entrepreneurship, Marketing, Leadership, Human Resource Management & Business Management ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 የሽያጭ መንገዶች እና ቢዝነስ ፕሮፖዛል አዘገጃጀት ብቃትን የሚያገኙበት
👉 ዲጂታል ማርኬቲንግ በተግባር የሚሰጥበት
👉 በተጨማሪነት የቢዝነስ አመራር እና Seራ ፈጠራ (Entrepreneurship) ስልጠናን በውስጡ አካቷል
👉 ለመክፈት የሚያስቡትን ቢዝነስ ከስልጠና እስከ ማማከር አካቶ የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 8🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ተጨማሪ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።
ተማሪዎች ወደየተመደባችሁበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ስትሔዱ ከወላጅ፣ ከአሳዳጊ ወይም ኃላፊነት ካለው ተጠሪ ጋር መሆን እንዳለበት ተገልጿል።
ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተጠሪው ግለሰብ በትምህርት ቤቱ የተዘጋጀውን የስምምነት ሰነድ ፈርመው ለትምህርት ቤቱ አመራር ማስረከብ ይኖርባቸዋል ተብሏል።
@tikvahuniversity
❤ 93👍 22😱 3😢 2🙏 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam
በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ምዝገባው እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል።
እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈላችሁበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማችሁ ለየትምህርት ክፍላችሁ መላክ ይጠበቅባችኋል፡፡
🔔 የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት በራሳችሁ ነው፡፡
ፈተናውን በድጋሜ የምትወስዱ ይመዝገቡ 👇
https://exam.ethernet.edu.et
የምዝገባ ሒደቱን የሚያሳይ ቪዲዮ👇
https://youtu.be/C9KkQ9AHd2o
@tikvahuniversity
❤ 125👍 29👎 7😢 6🙏 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
ሰኞ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም 16ኛው እና የመጨረሻው ዙር ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፆቻችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ1,000,000 ብር ዕድለኛ ከሻሸመኔ ሆኗል።
ሌሎች የ100 ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም Story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን።
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 27👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ERMP
የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ተጀምሯል፡፡
ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህክምና ዲግሪ ያላቸውንና የስፔሻሊቲ ስልጠና በ2018 ዓ.ም መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን በብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የዘንድሮው ስልጠና በ22 የማሰልጠኛ ተቋማት እና በ23 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ይሰጣል፡፡
የምዝገባ ጊዜ፦
ታህሳስ 06-20/2018 ዓ.ም
ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (https://www.moh.gov.et) ላይ በመግባት በምትፈልጉት የጤና ስፔሻሊቲ መስክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 47
Photo unavailableShow in Telegram
የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ እና ሲኒማቶግራፊ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Photography, Videography, Cinematography, Graphic Design እና Video Editing በአንድ ላይ
👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 33🥰 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MekelleUniversity
በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም) መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል።
የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል።
@tikvahuniversity
❤ 74👍 15👏 3😱 3🙏 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ተጨማሪ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም እንደሆነ መገለፁ ይታወቃል።
➫ ወሊሶ የተመደባችሁ የምትሄዱት አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ፦ 0920189695
➫ ቡኢ የተመደባችሁ የምትሄዱት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፦ 0943165470
➫ ቦንጋ የተመደባችሁ የምትሄዱት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፦ 0913192165
➫ ጅግጅጋ የተመደባችሁ የምትሄዱት ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፦ 0922648636
➫ ጋምቤላ የተመደባችሁ የምትሄዱት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፦ 0911590938
በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወል አስፈላጊ መረጃዎችን መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
❤ 83🙏 6🥰 2👍 1👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ይስጡ!
የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ በተከታዮቹ ሦስት ሰነዶች ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡
➫ በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ 👇 https://forms.gle/RXsuSUGtFFYrkAMQ9
➫ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ 👇
https://forms.gle/TZTSPZrJzgEnY2Rq9
➫ የተፋጠነ ትምህርት መርሐግብር አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ 👇
https://forms.gle/16CDaGfzkXDF6fwt6
ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ/ደንብ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ፣ በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ያግኙ፣ ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ Submit የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ እንደምትችሉ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
❤ 40👎 3👍 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ
#AAU
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር እና የፊልም ጥበባት ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም በሁለተኛው ሴሚስተር በቀን መርሐግብር የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ተዘጋጅቷል፡፡
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች፦
1. MA in Multimedia Theatre
2. PhD in Performing Arts
በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ (www.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱ መስፈርቶችን በማሟላት ማመልከት ይቻላል ተብሏል፡፡
ከላይ ለተገለፁት ሁለት የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የማመልከቻ ቀናት የሚያበቃው ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡
የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች ውጤታችሁን https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በማየት ከታህሳስ 28 እስከ ጥር 06/2018 ዓ.ም በ https://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms ማመልከት ይችላላችሁ ተብሏል።
በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስረከቢያ ቦታ አ.አ.ዩ. ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 መሆኑ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 52🥰 1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል) ለተመደቡ ተማሪዎች ዘግይተው ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡
ምስል፦ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲ
@tikvahuniversity
❤ 21
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ
🔔 በምዝገባ ላይ ነን!
BSc Fields of Study:
→ BSc in Medical Laboratory Science
→ BSc in Pharmacy
→ BSc in Nursing
TVET Programs:
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Accounting and Finance
→ Hardware & Networking Service
→ Radiography
የCPD ማዕከል አገልግሎት
☎️ 0929969696 / 0996828282
አድራሻ፦
📍 መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ
📍 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ
Telegram: @Yanet6kiloc
❤ 25🙏 1
በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ
DATA_TEMPLATE_LATEST_2018_UPDATED_PRIVATE.xlsx0.20 KB
❤ 56😢 10👍 5👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA
የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በዓመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለማካሔድ የታቀደ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ሰርኩላር ገልጿል፡፡
በዚህም አስፈታኝ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ተፈታኞች እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡
ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከታች በተያያዘው ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን በተጠቀሱት ቀናት ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንደታስገቡ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 90🥰 9👍 3🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!!
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተኑበት
👉 በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ
👉 ስልጠናው በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 55🥰 4👍 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam
በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ!
የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦
ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም
የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል።
@tikvahuniversity
👍 220❤ 118👎 23😢 14🥰 11👏 5😱 4🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል።
የህጻናት መጻሕፍት፣ የታሪክ መጻሕፍት፣ ልብወለዶች፣ የፍልስፍና መጻሕፍት እና ሌሎችም በተመጣጣኝ ዋጋ በአውደ ርዕዩ ያገኛሉ።
በዋናው ግቢ (6ኪሎ) የባህል ማዕከል የተከፈተው አውደ ርዕይ፤ ዛሬ ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
ይጎብኙ፣ ይሸምቱ! 🕙 እስከ ከሰዓት 11:00 ሰዓት
@tikvahuniversity
❤ 41
