Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
Open in Telegram
እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
Show more233 788
Subscribers
+2 93424 hours
+2 7417 days
+7 99530 days
Posts Archive
Ads.
የፖለቲካ ምልከታዎችን ከቻናላችን ይከታታሉ።
- ሀገራዊ
- አለምአቀፋዊ
-አካባቢያዊ መረጃዎች ይቀርባሉ subscribe አድርጉን።
Ethio 547
https://youtube.com/@ethiopianlink99?si=QcKcSJHvOKaWW8d-
❤ 15🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሳዑዲ አረቢያከ19,500 በላይ የህግ ተላላፊዎችን በቁጥጥር ስር አዋለች!
📌57 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው።
የሳዑዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ባለፈው ሳምንት (ከዲሴምበር 4 እስከ ዲሴምበር 10) ባለው ጊዜ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች እና በተዛማጅ የመንግስት አካላት በተደረጉ የጋራ ፍተሻዎች 19,576 ህገወጥ ነዋሪዎች ተይዘዋል።
ይህ ሰፊ ዘመቻ በሶስቱ ዋና ዋና የህግ ጥሰት ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነበር፡
📌 12,506 የመኖሪያ ፈቃድ ህግ ተላላፊዎች
📌 4,154 የድንበር ደህንነት ህግ ተላላፊዎች
📌 2,916 የሠራተኛ ህግ ተላላፊዎች
በዚሁ ጊዜ ውስጥ ድንበር ጥሰው ወደ መንግሥቱ ለመግባት ሲሞክሩ 1,418 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከተያዙት ውስጥ፡
📌 57% ኢትዮጵያውያን
📌 41% የመን አገር ዜጎች
📌 2% ሌሎች ዜግነቶች
በተጨማሪም 24 ሰዎች መንግስቱን ለቀው ለመውጣት ሲሞክሩ ተይዘውበታል፣ እንዲሁም 16 ሰዎች ለህግ ተላላፊዎች የትራንስፖርት፣ የመጠለያና የስራ ዕድል በማመቻቸት ተሳትፈው ተይዘዋል።
ጠቅላላ 30,427 የሚሆኑ የውጭ ዜጎች
📌 28,718 ወንዶች እና
📌 1,709 ሴቶች
በአሁኑ ጊዜ ህጋዊ እርምጃዎች እየተወሰደባቸው ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት በተከናወነው የህግ ማስፈጸሚያ ሂደት፡
📌 12,365 ተላላፊዎች ከሀገር ተባርረዋል
📌 21,803 ተላላፊዎች የጉዞ ሰነድ ለማግኘት ወደ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖቻቸው ተልከዋል
📌5,202 ተላላፊዎች የጉዞ ቦታ ማስያዣቸውን እንዲያጠናቅቁ ተመላክተዋል
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ህገወጥ ግለሰቦች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ የሚያመቻች፣ የሚያጓጉዝ፣ መጠለያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ድጋፍ የሚሰጥ ማንኛውም ሰው እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት፣ እስከ 1 ሚሊዮን የሳዑዲ ሪያል (SR1M) በሚደርስ ቅጣት፣ እንዲሁም ለትራንስፖርት ወይም ለመጠለያ አገልግሎት የዋሉ ንብረቶች በመውረስ እንደሚቀጣ አስጠንቅቋል። የሳዑዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ መረጃውን ያጋራው ጉርሻ ነው።
❤ 189😱 22👍 19😢 11💔 6🕊 3🏆 3🍾 3
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ደሴ
ስልክ 0937411111
0938411111
ሊንክ:
https://t.me/+ACPCPoXDK4JlMjA0
❤ 16👍 1
የፌስታል ክልከላ‼
ከመጭው ጥር ጀምሮ ፌስታል መጠቀም በፍፁም የተከለከለ ይሆናል።
ፌስታል ይዞ መገኘት ከ5 -10 ሺህ ብር ያስቀጣል።
አምራቾች፣ የተሰጠው የ6 ወር የመሸጋገሪያ ጊዜ በቂ አይደለም እያሉ ነው።
የአካባቢ ጥበቃ ግን የተሰጠው መሸጋገሪያ ጥር 23 ስለሚያበቃ ወደ እርምጃ እሄዳለሁ ብሏል።
በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማመረት እና ወደ አገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ይታወሳል።
በአዋጁ መሠረት የፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር ገንዘብ ይቀጣል።
በተመሳሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ለገበያ ማቅረብ፣ መሸጥ ወይም ለንግድ ዓላማ ማከማች ከሃምሳ እስከ መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል። ከዚህ በተጨማሪም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ አዋጁ ላይ ሰፍሯል።
አነዚህን "የወንጀል ድርጊቶች" የፈጸመው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ቅጣቱ ሦስት እጥፍ እንደሚሆን የፀደቀው አዋጅ ያትታል።
❤ 153🤣 80👏 10😱 10🙊 10🤔 8😢 5😎 5😍 3🤝 3👌 2

Attention‼️
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው
#ቴምርሪልስቴት
‼️ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል
👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ
20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን
‼️አዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉 1መኝታ 78ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
👉3 መኝታ 117ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 2.6ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን
👉 157ካሬ =
20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
#ልብይበሉ
#ቀሪውን 80% በ 15ዙር ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
❤ 27
"አይቀርም እናመጣዋለን"ጀኔራሉ
"አሰብን በጋራ መጠቀም አለብን። የኤርትራ መሪዎች ሞኞች ናቸው ''
አምባሳደር ጀኔራል ባጫ ደበሌ
<<የሚያስቡ ከሆነ አሰብን በጋራ ጥቅም ማዋል'' ለጋራ ጥቅም ካላዋልክ ደግሞ አይቀርም እናመጣዋለን።አሰብን አስቀራለሁ ስትል ይጠፋል።
በውጊያ የመሄድ ፍላጎት የለንም፣ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንሄዳለን።
የነሱ ሃሳብ ኢትዮጵያን በማመስ ኤርትራ በሰላም ትኖራለች የሚል ፖሊሲ ነው ያላቸው። ይህ ደግሞ የሞኞች ፓሊሲ ነው አንተ የሰው ቤት እየበጠበጥክ በሰላም አትኖርም ሰውን ሰላም አሳጥተህ አንተ በሰላም አትኖርም።
አንተ መስታወት ቤት ውስጥ ቁጭ ብለህ ድንጋይ ብትወረውር ምን ሊያመጣ እንደሚችል ይታወቃልና የኢትዮጵያ የባህር በር የማገኘት ጉዳይ ምንም ጥርጥር የለውም"።
አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ
ሰሞኑን በተካሄደ የመፅሃፋቸው ምረቃ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ
❤ 219🤣 71👏 33🏆 15🥴 7😱 6🕊 6🤝 5🎉 4💩 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
አነጋጋሪው የፈስ ግብር🤭😳
በ 2030 መጣል የሚጀምረው የፈስ ግብር ወይም ፍላቱንስ ታክስ እንግዲህ የተለያዩ ሀገራት የታክስ መሰረታቸውን ለማስፋት የሚጠቀሙባቸው በጣም አስገራሚ የሆኑ የተለያዩ አካሄዶች አሉ።
በዚህ ረገድ ዴንማርክ በ 2030 ትተገብረው የተባለው ይሄ የፈስ ግብር የሚባለው ነገር በጣም አነጋጋሪ ይሆናል። ይሄ ነገር እንግዲህ ምንድነው አካባቢ ጥበቃን መነሻ ያደረገ ነው።
ኖርማሊ ከብቶች በፈስ መልክ የሚለቁት ሜታን የሚባለው ነገር አካባቢን በመረበሽ ረገድ፣ ፖሊውት በማድረግ፣ በመበከል ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ተብሎ በበርካታ ጥናቶች የተረጋገጠ በመሆኑ መንግስት ይህንን ከከብቶች በሚለቀው ፈስ ምክንያት አካባቢ ላይ የሚደርስ መበከል ለማረም እና ኢንቫይሮመንቱን ለመጠበቅ ይህን ካሏቸው ገበሬዎች ይህንን ፍላቱንስ የተባለ ግብር መሰብሰብ አስፈልጎታል ማለት ነው።
ስለሆነም ይሄ ግብር ከ2030 ጀምሮ የሚሰበሰብ ሲሆን በቶን 300 የዴንማርክ ክሮን የመክፈል ግዴታ ተጥሎበታል ገበሬው። ይህ እንግዲህ በተወሰኑ መልኩ የግብርን መሰረት ለማስፋትም አካባቢንም ለመጠበቅ የተደረገ ነው ተብሏል።አሁን ይሄ ነገር ኢትዮጵያ ቢተገበርስ?😳🤭
https://www.facebook.com/61585267550889/posts/pfbid02eGHyvpr4besA1zTnyzZTZUbveWUsgrsYiEePgNGZEaZczoc5MUR8fpE1iooyHpkLl/
🤣 146❤ 128🙉 18🤔 9😘 7😱 4🙈 4😢 3💩 3🍾 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ደሴ
ስልክ 0937411111
0938411111
ሊንክ:
https://t.me/+ACPCPoXDK4JlMjA0
❤ 15👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተፈጠረው ውጥረት አሳስቦኛል" የአውሮፓ ህብረት
የኢትዮጵያና የኤርትራ “ሉዓላዊነት፣ ነጻነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር” ብሪታኒያና ቱርክን ጨምሮ አምስት ሀገራት በጋራ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሐምሌ 2010 በተፈራረሙት “የሰላም ሥምምነት መንፈስ ማንኛውም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላምና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ” ጠይቀዋል።
የካናዳ፣ ጃፓን፣ ኖርዌይ፣ ቱርክና ብሪታንያ መንግሥታት ጥሪውን ያቀረቡት የአልጀርስ ሥምምነት የተፈረመበትን 25ኛ ዓመት በማስመልከት ትላንት አርብ ባወጡት መግለጫ ነው።
ሀገራቱ በ1993 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአልጀርስ የተፈራረሙትን ሥምምነት፣ ሥምምነቱ የሚያራምዳቸውን መርሆዎችና በሥምምነቱ የተቋቋመው ኮሚሽን የወሰናቸውን ድንበሮች እንደሚደግፉ በጋራ መግለጫቸው ጠቁመዋል።
የአውሮፓ ኅብረት “የአልጀርስ ሥምምነትንና በድንበር ኮሚሽኑ የተወሰነውን” የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር “ሙሉ በሙሉ” እንደሚደግፍ አስታውቋል።
በ1993 በአልጀርስ እንዲሁም በ2010 በአስመራ በተፈረሙት ሥምምነቶች መሠረት ኢትዮጵያና ኤርትራ አንዳቸው የሌላቸውን “ሉዓላዊነት፣ ነጻነትና የግዛት አንድነት” እንዲያከብሩ የአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አቅርቧል።
ሁለቱም ወገኖች “ማንኛውንም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ” ጥሪ ያቀረበው የአውሮፓ ኅብረት፤ “ይህ ለቀጠናው መረጋጋት ቁልፍ” እንደሆነ አሳስቧል።
ሀገራቱ የአልጀርስ ሥምምነትን በማስታወስ ያወጧቸው መግለጫዎች በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እንዳሳሰባቸው የሚጠቁሙ ናቸው።Via DW
❤ 103🤣 29😱 9❤🔥 8🕊 8😍 5🔥 2🎉 2😘 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሙስሊም ከሆናችሁ ሊኖራችሁ ከሚገቡ ቻናሎች መካካል አንዱ ይሄ ቻናል ነው። ሊንኩን ከታች አስቀምጥላቹኋለው ተቀላቀሉ።
❤️አሁኑኑ ጆይን ይበሉ🔥
👇👇↴↴
╰┈➤@Quran_post18
╰┈➤@Quran_post18
❤ 43👍 24🥰 3😁 2
ንግድ ባንክ ከቴሌ ብር ብድር ወስደው ያልመለሱ ሰዎች አካውንት እያገደ መሆኑን በውስጥ የደረሱኝ ጥቆማዎች አመልክተዋል።
😁 57❤ 40🤪 22🙏 11🤣 7😍 4🏆 3😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
ረጅም የመንገድ ኔትዎርክ ያላቸው 10 ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት
1)- ደቡብ አፍሪካ - 750,000 ኪ.ሜ
2)- ናይጄሪያ – 195,000 ኪ.ሜ
3)- ኢትዮጵያ - 161,452 ኪ.ሜ
4)- ኬንያ - 161,000 ኪ.ሜ
5)-ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ - 152,000 ኪ.ሜ.
6)- ታንዛኒያ - 145,000 ኪ.ሜ
7)- አልጄሪያ - 141,000 ኪ.ሜ
8)- ማሊ – 139,000 ኪ.ሜ
9)- ዚምባብዌ - 97,000 ኪ.ሜ
10)-ደቡብ ሱዳን - 90,000 ኪ.ሜ
Great Africa-
❤ 88👏 17🏆 6👍 5🙉 4😍 3😎 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
Attention‼️
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው
#ቴምርሪልስቴት
‼️ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል
👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ
20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን
‼️አዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉 1መኝታ 78ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
👉3 መኝታ 117ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 2.6ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን
👉 157ካሬ =
20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
#ልብይበሉ
#ቀሪውን 80% በ 15ዙር ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
❤ 27😱 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኮንዶም ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ‼
ቻይና ኮንዶምን ጨምሮ በተለያዩ የወሊድ መከላከያዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መጣል ልትጀምር ነው‼
ቻይና ከፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮ የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶችና ምርቶች ከታክስ ነፃ እንደማይሆኑና የ13 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሚጣልባቸው አስታውቃለች።
ቻይና ከ1980 እስከ 2015 ጥንዶች አንድ ልጅ ብቻ እንዲኖራቸው ታደርግ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ በ2015 ወደ ሁለት ልጆች ከዛም በ2021 ይህንኑ ቁጥር ወደ ሶስት ከፍ አድርጋ ነበር።
የሚወለዱ ህፃናትን ቁጥር በእነዚህ ጊዜያት ለመቀነስም የወሊድ መከላከያ ከ30 አመታት በላይ ከታክስ ነፃ ሆኖ ነበር።
በ2024 9.5 ሚሊየን ህፃናት በቻይና ሲወለዱ በ2019 ከተወለዱት 14.7 ሚሊየን ህፃናት አንድ ሶስተኛው ብቻ እንደማለት ነበር።
የሞት ቁጥር ከሚወለዱት የበለጠባት ቻይና ብዙ ህዝብ የሚኖርባት የሚለውን ስያሜም በ2023 በህንድ ተነጥቃለች።
በ2020 በቻይና በአጠቃላይ 5.4 ቢሊየን ኮንዶሞች ጥቅም ላይ ሲውሉ ባለፉት ተከታታይ 11 አመታትም ጭማሪ አሳይቷል።
በ2022 በቻይና 9% የሚሆኑ ጥንዶች ኮንዶም ይጠቀሙ ነበር ሲባል ታክስ መጣሉ የወሊድ መከላከያዎችን ቢያስወድድም ልጅ ለማሳደግ ከሚወጣው ወጪ አንፃር ኢምንት በመሆኑ ውልደት ላይ ያን ያህል ተፅዕኖ አይፈጥርም ተብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ የታክስ ጭማሪው ሰዎችን ለተላላፊ በሽታዎች እንዳያጋልጥ ተሰግቷል።
❤ 94🤣 40👍 15🥰 4🤔 3😱 3🎉 2🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
መቐለ‼
መቐለ ከተማ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ቅርንጫፍ ትናንት ምሽት በተማው መረጃ መሰረት የህውሃት ሰዎች በበርካታ ተሽከርካሪዎች ገንዘብ ሲጭኑ ታይተዋል።በጉዳዩ ላይ ከመንግስት አካል የተሰጠ መረጃ የለም።
❤ 39👍 32😱 11😁 9🏆 4🕊 2😢 1🎉 1💩 1
Ads.
የፖለቲካ ምልከታዎችን ከቻናላችን ይከታታሉ።
- ሀገራዊ
- አለምአቀፋዊ
-አካባቢያዊ መረጃዎች ይቀርባሉ subscribe አድርጉን።Ethio 547
https://youtube.com/@ethiopianlink99?si=QcKcSJHvOKaWW8d-
❤ 8👏 1😱 1😢 1
የጊዜያዊ ከለላ መብት‼
📌ኢትዮጵያዊያን በ60 ቀናት ከሃገሯ እንዲወጡ አሜሪካ አሳስባለች።
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰጥታ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት አንስታለች።
የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም ለኢትዮጵያ ተሰጥቶ የነበረው የጊዜያዊ ከለላ መብት መነሳቱን አስታውቀዋል።
አሜሪካ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ወደ ሃገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎች ጊዜያዊ ከለላ( Temporary protected status) ትሰጥ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያም ይኸው መብት ነበራት።
አሜሪካ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሃገሯ የሚኖሩ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ጦርነትን ጨምሮ በአንዳንድ ምክንያቶች ወደመጡበት ሃገር መመለስ ለማይችሉ ሰዎች ይህንን ከለላ መስጠት ጀምራ ነበር።
ይህ ከለላ የሚሰጣቸው ዜጎችም የሃገራቸው ሁኔታ እስኪሻሻል በአሜሪካ የመኖርና የመስራት መብት ሲሰጣቸው ከአሜሪካ ከመባረር ይጠበቁ ነበር።
አሜሪካ" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች ደህንነት ላይ ስጋት አይፈጥርም" ያለች ሲሆን በዚህም የተነሳ ይኸው ከለላ መነሳቱን አስታውቃለች።
አሜሪካ ሌሎች በአሜሪካ ለመቆየት ህጋዊ መሰረት ካላቸው ኢትዮጵያውያን ውጪ የኢትዮጵያ ዜጎች በ60 ቀናት ከሃገሯ እንዲወጡ አሳስባለች።
ቀድመው ከአሜሪካ ለሚወጡ የትኬት ወጪያቸው እንደሚሸፈን፣ የ1000 ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥና ለወደፊቱ ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድል እንደሚኖራቸው ገልፃለች።
ከፈረንጆቹ የካቲት 13 በኋላ ከለላው እንደሚያበቃ ገልፃ ያለ ከለላው በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደምታስር እና ከሃገሯ እንደምታባርር አስጠንቅቃለች።
አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተመሳሳይ ከለላ የነበራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜጎችን መብትም ማንሳቷ ይታወሳል።
❤ 97😱 13👍 9👏 8🕊 6🙉 6😢 3🏆 3