ግጥም ብቻ 📘
Open in Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Show more65 864
Subscribers
-2424 hours
-667 days
-28630 days
Posts Archive
ልቡ ግን ምን አለ
አዳም ሄዋንን ልክ እንዳያት፣
ተዋት አታግኛት
ወይ ደግሞ አፍቅራት፣
ትሂድ ወይ ልቀቃት
ወይስ ደግሞ ሳማት፣
ሂድ እቅፍ አድርጋት
ወይንስ ትሁንክ ሚስት።
እንጃ ምን እንዳለክ፣
አንተ ግን ተናገርክ።
እቺ አጥንት ከአጥንቴ፣
ስጋሽ ከስጋዬ፣
የአካሌ ክፋይ
የህይወት አጋሬ። አለ፣
ሴት፣ የማያውቀው አዳም
ሚስቱን ሄዋንን አወቃት፣
የዘመኑ አዋቂ፣
እናውቃለን ብለን ከስንቱ ስንዘሙት፣
ያቺን ሄዋን፣
እናግኛት ብለን ስንማማል ከስንት።
ግን፣
ያኔ አዳም እያለ
ሌላ ሴት ያልኖረው፣
የወንድ ልጅ አመል
እግዜሩ ገብቶት ነው።
እንጃ፣
ብቻ አዳም ያውቃል፣
በአንድ ሚስት መደሰት
በአንድ ሚስት መቃጠል፣
ብቻ አዳም ያውቃል
አንድ አሀዝ ወይ ፊደል፣
ሺ አመት እንዲፀኑ
ከእግዜር ነው መታደል።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤ 50👍 3😁 3
ልምጣ ይሆን እደርሳለሁ
ባላገኝሽ አይሻለው፣
ካለሽበት ልሳለምሽ
ባታይኝም አይሻለው፣
የበደልኩሽ የሳትኩት ግን
በእጄ እያለሽ ስተውሽ ነው፣
ክንፋም መልአክ የነገረው
ትንቢት ይኖር ልቤ ያወቀው።
ስታመልጪኝ ከእጄ ሳጣሽ
ያኔ ሰጋሁ እንዳላጣሽ፣
ልራመድ ወይ ወደትላንት
እንዳገኝሽ በትዝታሽ።
የጠፋ አለም የከደንኩት
በጨለማ ያዳፈንኩት፣
እንደ እንጀራ በስሎስ ቢሆን
ለማ ይሆን እኔ የተውኩት።
ባለሽበት አይሻለሁ
ልምጣ ልይሽ ጓጉቻለው፣
የጥፋት ጣር የአርፋጅ እግር
እየገፋኝ ደርሻለው፣
ይቅር በይኝ ተምሬአለሁ
ባንቺ ብቻ እፀናለሁ፣
ልምጣ ይሆን እደርሳለው?
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤ 29🔥 10😢 5😁 2
ቅንድቧን እንደ ሴት ፥ ኩል አልተኳለችው
ፀጉሯ ቢንጨባረር ፥ ጉዳዬ አላለችው
ከንፈሯን በቀለም ፥ አልለቀለቀችው
እንደነገሩ ነው ፥ ልቤን የረታችው ።
እንደ ነገሩ ናት
ካፈር የተሰራች ፥ አመለ ውሃ ናት
እንደ ነገሩ ናት
ባያምር ባይደምቅ ፥ ልብሷና ቀሚሷ
እግረመንገዷን ነው ፥ የምታምረው እሷ
እንደ ነገሩ ናት
በደበዘዘ መልክ ግልገል ፀሐይ አዳይ
ያለ ጋሻና ጦር በዝምታ ገዳይ
እንደ ነገሩ ናት
በጭብጨባ ብዛት የማትደናበር
በተቺ ዘለፋ የማትሰባበር
እንደ ነገሩ ናት
የገዛ ክንፎቿን አጣጥፋ የምትበር ።
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
❤ 107🤩 16🔥 11🎉 3
ልብሱ
ጫማው
ጌጡ ቀርቶ
እህል እንኳን ሳልገዛልሽ ፤
ስለ ዐይኖችሽ
ስለ እጆችሽ
ስለ እግሮችሽ ሳልፅፍልሽ ፤
ሳልጎበኝሽ
ሳልሰልልሽ
የኾንሽውን ሳልጠይቅሽ ፤
እንዲሁ . . . እንዲያው . . . እንደማንም ፤
እንደ ተራ . . . እንደ ምንም ፤
ድምፄን ውጬ ዝም ስልሽ ፤
ረስቼሽ እንዳይመስልሽ ።
፡
ባይልልኝ ነው አበባዬ ፤
ባይሆንልኝ
ባይሞላልኝ ፤
ከዕንባ በቀር በልቤ ላይ
ሌላ ገንዘብ ባይቆይልኝ ፤
እንጅማ አንቺን ፤
እመቤቴን ፤
እንዴት ብዬ እረሳለሁ !?
ቀን በውኔ
ሌት በሕልሜ
ትዝ እያልሽኝ አለቅሳለሁ ፤
ብቻ አንድ ቀን
ሞት ካልለየኝ ፤
ያ ጨለማ ካልቀደመኝ ፤
ዕምባ አርግዤ ብቅ እላለሁ፤
እጆችሽን
እግሮችሽን
ዐይኖችሽን እስማለሁ ፤
ከአንቺ ርቄ የሆንኩትን
አንድ በአንድ ነግርሻለሁ ፤
ወድሻለሁ
ወድሻለሁ
ወድሻለሁ
። ። ። ። ።
By Tedros kassa
@getem
@getem
@paappii
❤ 72🔥 13😢 8👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ና ገነትን እንኑራት…………..
ከርምጃህና እርምጃዬ
ከትከሻህና ትከሻዬ
ከሸባበተዉ ፀጉርህና ጠጉሬ መሀል
የመላዕክት ዝማርያቸዉ ይሰማሀል?
ምርኩዝህን አይተሀዋል እንደሙሴ…………
ድካምህን
ወንድነትህን
ማጣትና ማግኘትህን
አሉባልታ ስሜትህን
ከፈልክበት
ተሸለምከዉ ተደገፍከዉ።
ማርያምን ስወደው ሽብሽብ ገፅህን
የፈዘዘዉ ቅንድብህን
የጐደጐደዉ አይንህን
እኔልሙት……..
ስትስቅ እኮ ምድር ቀዉጢነዉ ምትሆነዉ
ደመና ሳቋን - መቆጣጠር አቅቷት
ዝናቧንም የምትለቀዉ።
ና ገነትን እየኖርናት
ነፋሴና ነፍስህ ይሙቃት
ትዝታ ወልዴ✍️
@Tizita21
@getem
❤ 73🔥 10👍 3🤩 1
Show all...
❤ 22😢 19🔥 7😁 2
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ
ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣
ተጨነቀች ወዲያው ደሞ
ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣
ትፈጥናለች ለማግኜት
ልቤን አርጋው የቀበሌ ፣
ታምር አርጋ ቆጠረችው
በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣
መቸኮልን አስለምዳኝ
ተጣድፎ ዝግታየን
አቻኩላ አገባችኝ
እይ ስትል እድሜየን ፣
ተቻኩላ አስለምዳኝ
ረጋ ያለ አረማመድ ፣
ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ
ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ ፣
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት 🦘
@getem
@getem
@paappii
❤ 37😁 6🔥 5👎 4😢 3🎉 1
Show all...
❤ 25🔥 2
ስወድሽ ተረታሁ
በደቂቅ ደቃቁ
ግርማነቴን ጣሉት
ወረድኩ ከሰንደቁ
ስወድሽ ወደኩኝ
ኮኮቤ ነሽ ብዬ ኮኮብ አሰቀልኩኝ
ኮከብነትሽም አልፈየደም አንድም
አንቺም ታደያለሽ ወደራስሽ ግድም
ስወድሽ ተደፋሁ
ይሁን ባልኩኝ ባለም... ተከፋሁ
አይቼ እንዳልገባኝ ስንት ነገር ገፋሁ
ልብሽ ላይፈልገኝ ሁሌ እየነገርሽኝ
በፈገግታሽ ብቻ የግልሽ አረግሽኝ
ስወድሽ አስመሰልኩ
መልስሽን ወሬሽን እንዳላወኩ መሰልኩ
ፍቅር ይሻል ብዬ እያየሁኝ ታዘብኩ
ፈገግ እንዳልገባኝ
ፈገግ እንዳላወኩ
በማስመሰል ንዳድ
በድርጊትሽ ታወኩ
ስወድሽ ተረታሁ
አንቺን ማጣት ፈራሁ
አብዝቼ ፈለኩሽ
አብዝተሽ ገፋሺኝ
አታውቂውም እንጂ እንዲህ ነው ያደረግሽኝ
መለስ ወደኋላ
መለስ ወደፊቴ
የጠቀመሽኝ መስለሽ ገለሺኛል ስንቴ
በበፊት ነገርሽ ዛሬን አግኝተሻል
ዙፋን ላይ ወርጄ ዙፋን ላይ ወተሻል
ጊዜ አይመጣም ብለሽ ጊዜሽን ወስደሻል
ጊዜ ተገልብጦ ጊዜ ይገፋልና
ጠንቀቅ በይ አለሜ ወድሻለሁና
ስወድሽ ተከፋሁ
አይቼ እንዳለየሁ ስንት ነገር ገፋሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 28😢 7🔥 3👍 1😱 1
እርግማን ነው
////////////////
አፈር ይብላው፣
ያ ገላሽን
መቼስ እንደው አይቀርለት፣
እርጅና ይብላው፣
ያ መልክሽን
እሱም እንደው አይቀርለት።
መርገም አላውቅ
መንገድ ጠፋኝ፣
አንችን ብዬ
ሳላገኝሽ በጣም ከፋኝ፣
ልራገም ነው በይ ተቀበይ፣
ልብሽ እንደው
እኔን አንዴ ባፈቀረኝ።
እርግማን ነው አትሳቂ፣
ሳያገኙ ማፍቀር
ህመሙን እወቂ።
እርግማን ነው
ብሸዬሽ የለ፣
ቂም እንደሆን በፍቅር የለ።
ያኔ ድሮ
ገፍተሽኛል አዎ አውቃለሁ፣
ይህ እርግማን ሲደርስብሽ
ቂሙን ትቼ እወድሻለሁ።
ሞኝ አደለው።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤ 40🔥 6🤩 5
🤲አሜን በይ ልመርቅሽ
ቆሻሻው ተቃጥሎ ሀገር ምድሩ ፀድቶ
ታፍኖ የቆየ ፍቅር አገርሽቶ
በጦቢያ ምድር ህዳሩ ሲታጠን
በለተ ሚካኤል አሜን ሰላም ይስጠን::
አሜን!
ሰላም ውሎ ይደር ቀዬው አድባሩ
ከመስጊዱ አዛን ቅዳሴው ከደብሩ
አይስተጓጎሉ ኬር ሆኖ መንደሩ::
አሜን!
አቦል ጀባ ጀባ ቶና እና በረካ
አቦ ሀጃ ይውጣ ጠጥተን እንርካ
ኑሯችን ይስመር እንደ ፅጌ ይፍካ::
አሜን!
አሜን በይ ይሁን ከአሜን ይቀራል
የከረመ በቀል በፍቅር ይሻራል!
ቤትሽ ፍቅር ይሙላው ካምናው እጥፍ አርጎ
ውልቅ ይበል ችግር ማጣት ተጠራርጎ::
አሜን!
ልጆችሽ ይደጉ በእውቀት በምግባር
ሰውሮ ያቆያቸው ከጦርነት ግንባር
አሜን ልብ ይስጣቸው የሚታይ በተግባር::
አንደበትሽ ይጣፍጥ የነካሽው ይብዛ
ያንቺን ስራ አይቶ ሰውዘር አደብ ይግዛ::
አሜን!
By @Abuugida
@getem
@getem
@paappii
❤ 105👍 6🤩 4🔥 1
ቀሚስሽ ደግ ነው መሰሰት አያውቅም
ደጅ ለጠናበት ለጋሽ ነው አይነፍግም
አርሂቡ አርሂቡ ሁሉን ተቀባይ ነሽ
ቀጭን አትይ ወፍራም
ጥቁር አትይ ቀይ መቼ ትመርጫለሽ!
አርሂቡ!
አርሂቡ ግቡ ተቋደሱ
አንተም ያዝ አንተም ያዝ እስኪ ተቃመሱ
.
እንኩ ነው ልሳንሽ ላንኳኳ በሙሉ
ለስሜት አበጋዝ የሚገልብሽ ሁሉ
እንኩ ነው በነጋ
እንኩ ነው በመሸ
ያ ነጩ ቀሚስሽ በመስጠት ጠለሸ
እንካ ያልሽው ተቀባይ
አጣጥሞ ጣለሽ ልክ እንደ ማስቲካ
ወትሮም ቅሉ አያምር በሁሉ የተነካ
[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr
@getem
@getem
@getem
😁 43❤ 32🤩 15👎 10👍 7😢 6🔥 2
