ch
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

前往频道在 Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

显示更多
65 864
订阅者
-2424 小时
-667
-28630
帖子存档
ዐይኔ አረዘረዘ ፤ ልቤም ተሰበረ ፤ አንጀቴም ሆድ ባሰው ፤ ገና ሳይወለድ እንዴት ያረጃል ሰው !? By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
显示全部...
51👍 12🔥 12😢 2
ልቡ ግን ምን አለ አዳም ሄዋንን ልክ እንዳያት፣ ተዋት አታግኛት ወይ ደግሞ አፍቅራት፣ ትሂድ ወይ ልቀቃት ወይስ ደግሞ ሳማት፣ ሂድ እቅፍ አድርጋት ወይንስ ትሁንክ ሚስት። እንጃ ምን እንዳለክ፣ አንተ ግን ተናገርክ። እቺ አጥንት ከአጥንቴ፣ ስጋሽ ከስጋዬ፣ የአካሌ ክፋይ የህይወት አጋሬ። አለ፣ ሴት፣ የማያውቀው አዳም ሚስቱን ሄዋንን አወቃት፣ የዘመኑ አዋቂ፣ እናውቃለን ብለን ከስንቱ ስንዘሙት፣ ያቺን ሄዋን፣ እናግኛት ብለን ስንማማል ከስንት። ግን፣ ያኔ አዳም እያለ ሌላ ሴት ያልኖረው፣ የወንድ ልጅ አመል እግዜሩ ገብቶት ነው። እንጃ፣ ብቻ አዳም ያውቃል፣ በአንድ ሚስት መደሰት በአንድ ሚስት መቃጠል፣ ብቻ አዳም ያውቃል አንድ አሀዝ ወይ ፊደል፣ ሺ አመት እንዲፀኑ ከእግዜር ነው መታደል። @abela_black @getem @getem @getem
显示全部...
50👍 3😁 3
‎ደስ እንዲለኝ ‎ሀሴት ልቤን እንዲሞላ ‎ሀዘንሽን አርቀሽ ጣይ ‎ከፊት የለም ያንቺ ኋላ። ‎ ‎በህይወት መስመር ‎ምን ቢኖርም ብዙ ስንኩል ‎ፈገግ ልበል በፈገግታሽ በኩል ‎ ‎ ሳቂሊኝ! ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
20😁 4👎 1
‎አንድዬ ተዘርታ ከተገኘች በቅላ፣ ‎አቅምሳኝ ከሄደች ፍሬዋን አብስላ፣ ‎ ‎ወደ ባቲ ሳትመለስ ታውሳ በትዝታ፣ ‎በድባቴ ታስራ በእምባ ብትፈታ፣ ‎ ‎ህይወት ህይወት እንጂ ፀሀይ አትባልም፣ ‎ደክሟት ከጠለቀች ዳግም አትገኝም። By Behailu Firde @getem @getem @paappii
显示全部...
36👍 7
እባክህ -------------------------------------- እባክህ አምላኬ?. . . የመጣ የሄደው፣ ከሚበጠብጠኝ እኔ የምገዛት፣ ሐገር ሰርተህ ስጠኝ። By Behaylu Mulgeta @getem @getem @paappii
显示全部...
64👍 15🔥 6😁 4😢 1
ልምጣ ይሆን እደርሳለሁ ባላገኝሽ አይሻለው፣ ካለሽበት ልሳለምሽ ባታይኝም አይሻለው፣ የበደልኩሽ የሳትኩት ግን በእጄ እያለሽ ስተውሽ ነው፣ ክንፋም መልአክ የነገረው ትንቢት ይኖር ልቤ ያወቀው። ስታመልጪኝ ከእጄ ሳጣሽ ያኔ ሰጋሁ እንዳላጣሽ፣ ልራመድ ወይ ወደትላንት እንዳገኝሽ በትዝታሽ። የጠፋ አለም የከደንኩት በጨለማ ያዳፈንኩት፣ እንደ እንጀራ በስሎስ ቢሆን ለማ ይሆን እኔ የተውኩት። ባለሽበት አይሻለሁ ልምጣ ልይሽ ጓጉቻለው፣ የጥፋት ጣር የአርፋጅ እግር እየገፋኝ ደርሻለው፣ ይቅር በይኝ ተምሬአለሁ ባንቺ ብቻ እፀናለሁ፣ ልምጣ ይሆን እደርሳለው? @abela_black @getem @getem @getem
显示全部...
29🔥 10😢 5😁 2
ቅንድቧን እንደ ሴት ፥ ኩል አልተኳለችው ፀጉሯ ቢንጨባረር ፥ ጉዳዬ አላለችው ከንፈሯን በቀለም ፥ አልለቀለቀችው እንደነገሩ ነው ፥ ልቤን የረታችው ። እንደ ነገሩ ናት ካፈር የተሰራች ፥ አመለ ውሃ ናት እንደ ነገሩ ናት ባያምር ባይደምቅ ፥ ልብሷና ቀሚሷ እግረመንገዷን ነው ፥ የምታምረው እሷ እንደ ነገሩ ናት በደበዘዘ መልክ ግልገል ፀሐይ አዳይ ያለ ጋሻና ጦር በዝምታ ገዳይ እንደ ነገሩ ናት በጭብጨባ ብዛት የማትደናበር በተቺ ዘለፋ የማትሰባበር እንደ ነገሩ ናት የገዛ ክንፎቿን አጣጥፋ የምትበር ። By Habtamu Hadera @getem @getem @paappii
显示全部...
107🤩 16🔥 11🎉 3
ምን ቢርበው ላሙን ምን ቢርበው ዘሩን አይበላም ገበሬ ፤ እኔስ ጨከንኩና ቆርጥሜያት አደርኩኝ ነፍሴን እንደ ጥሬ ። By Tedros kassa @getem @getem @paappii
显示全部...
73😢 29👍 5🔥 4😁 2
ልብሱ ጫማው ጌጡ ቀርቶ እህል እንኳን ሳልገዛልሽ ፤ ስለ ዐይኖችሽ ስለ እጆችሽ ስለ እግሮችሽ ሳልፅፍልሽ ፤ ሳልጎበኝሽ ሳልሰልልሽ የኾንሽውን ሳልጠይቅሽ ፤ እንዲሁ . . . እንዲያው . . . እንደማንም ፤ እንደ ተራ . . . እንደ ምንም ፤ ድምፄን ውጬ ዝም ስልሽ ፤ ረስቼሽ እንዳይመስልሽ ። ፡ ባይልልኝ ነው አበባዬ ፤ ባይሆንልኝ ባይሞላልኝ ፤ ከዕንባ በቀር በልቤ ላይ ሌላ ገንዘብ ባይቆይልኝ ፤ እንጅማ አንቺን ፤ እመቤቴን ፤ እንዴት ብዬ እረሳለሁ !? ቀን በውኔ ሌት በሕልሜ ትዝ እያልሽኝ አለቅሳለሁ ፤ ብቻ አንድ ቀን ሞት ካልለየኝ ፤ ያ ጨለማ ካልቀደመኝ ፤ ዕምባ አርግዤ ብቅ እላለሁ፤ እጆችሽን እግሮችሽን ዐይኖችሽን እስማለሁ ፤ ከአንቺ ርቄ የሆንኩትን አንድ በአንድ ነግርሻለሁ ፤ ወድሻለሁ ወድሻለሁ ወድሻለሁ ። ። ። ። ። By Tedros kassa @getem @getem @paappii
显示全部...
72🔥 13😢 8👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ና ገነትን እንኑራት………….. ከርምጃህና እርምጃዬ ከትከሻህና ትከሻዬ ከሸባበተዉ ፀጉርህና ጠጉሬ መሀል የመላዕክት ዝማርያቸዉ ይሰማሀል? ምርኩዝህን አይተሀዋል እንደሙሴ………… ድካምህን ወንድነትህን ማጣትና ማግኘትህን አሉባልታ ስሜትህን ከፈልክበት ተሸለምከዉ ተደገፍከዉ። ማርያምን ስወደው ሽብሽብ ገፅህን የፈዘዘዉ ቅንድብህን የጐደጐደዉ አይንህን እኔልሙት…….. ስትስቅ እኮ ምድር ቀዉጢነዉ ምትሆነዉ ደመና ሳቋን - መቆጣጠር አቅቷት ዝናቧንም የምትለቀዉ። ና ገነትን እየኖርናት ነፋሴና ነፍስህ ይሙቃት ትዝታ ወልዴ✍️ @Tizita21 @getem
显示全部...
73🔥 10👍 3🤩 1
አዲስ ቃላት አይደል ወይም አዲስ ግኝት እኔ አንቺን ማፍቀሬ ከቶ አይደለ ጥፋት ንገሪኝ ከሆድሽ ያለሽን አውጥተሽ ላግኝበት ሰላም ከሴት ሁሉ ልሽሽ አትስጊ ንገሪኝ ልቤ ይችለዋል ስምሽን በመቅበር ዘግቶ ያኖረዋል የለመደሽ ጎኔ ሁል ጊዜ የሚያቅፍሽ ሳያገኝሽ ሲቀር ቢልብኝም ኩምሽሽ እጠነክራለሁ ምን አማራጭ አለኝ ከአዳምነት አልሸሽ። by ዳግማዊ@Dagimawisisay @getem @getem @getem
显示全部...
28🔥 4
‎እኔ አፍቅሬያት ሌላ አፍቅራ ‎እሱም ቀርቶ ወልዳ አግብታ ‎          እያየሁ ‎          እቀናለሁ  ‎ባለፈው ትላንቷ በዛሬው እኔነቴ ‎       እቀናለሁ ጅልነቴ ‎አወየው ጉዳቴ አወዬው ፈተና ‎አትታደል ፍቅር ተብያለሁ ቅና ‎ካንድ አምላክ ቸርነት ብማፀን ብጠና ‎እኔው ባወራኋት በኔው እቀናለው ‎          ወዳታለሁና ‎ ‎እኔ አፍቅሬያት ሌላ አፍቅራ ‎አወየው ጉዳቴ አወየው መከራ ‎ ‎ ‎ዮኒ ‎     ኣትን @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
22😢 19🔥 7😁 2
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣ ተጨነቀች ወዲያው ደሞ ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣ ትፈጥናለች ለማግኜት ልቤን አርጋው የቀበሌ  ፣ ታምር አርጋ ቆጠረችው በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣ መቸኮልን አስለምዳኝ ተጣድፎ ዝግታየን አቻኩላ አገባችኝ እይ ስትል እድሜየን ፣ ተቻኩላ አስለምዳኝ ረጋ ያለ አረማመድ  ፣ ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ ፣ @geez_mulat ግዕዝ ሙላት 🦘 @getem @getem @paappii
显示全部...
37😁 6🔥 5👎 4😢 3🎉 1
አበባዬ ብዬ አላሸታት ነገር ወይ ውሃ አላጠጣት አላስታቅፍ አፈር ወይ አትመጣ ከኔ ፍቅሬን አልናገር ... ጠረኗ አልደረሰኝ ሆና ከሩቅ ሀገር ግና ቆም ብዬ ሳስበው እሷ ንግሥት ሆና ሀገሬን ብታየው እኔ ንጉሥ ሆኜ ጠረኗን ብምገው አበባዋን ቀጥፋ ተፈጥሮውን ለየው ብላ ብጠይቀኝ አሳያት ነበረ ያ ጠቢብነቴን መስኮት ዳር ወስጄ በጠረኑ ብቻ ንብ መንጋ መጥራቴን by ዳግማዊ@Dagimawisisay @getem @getem @paappii
显示全部...
25🔥 2
‎ስወድሽ ተረታሁ ‎በደቂቅ ደቃቁ ‎ግርማነቴን ጣሉት ‎ወረድኩ ከሰንደቁ ‎ ‎ስወድሽ ወደኩኝ ‎ኮኮቤ ነሽ ብዬ ኮኮብ አሰቀልኩኝ ‎ ‎ኮከብነትሽም አልፈየደም አንድም ‎አንቺም ታደያለሽ ወደራስሽ ግድም ‎ ‎ስወድሽ ተደፋሁ ‎ይሁን ባልኩኝ ባለም... ተከፋሁ ‎አይቼ እንዳልገባኝ ስንት ነገር ገፋሁ ‎ ‎ልብሽ ላይፈልገኝ ሁሌ እየነገርሽኝ ‎በፈገግታሽ ብቻ የግልሽ አረግሽኝ ‎ ‎ስወድሽ አስመሰልኩ ‎መልስሽን ወሬሽን እንዳላወኩ መሰልኩ ‎ፍቅር ይሻል ብዬ እያየሁኝ ታዘብኩ ‎ፈገግ እንዳልገባኝ ‎ፈገግ እንዳላወኩ ‎በማስመሰል ንዳድ ‎በድርጊትሽ ታወኩ ‎ ‎ስወድሽ ተረታሁ ‎አንቺን ማጣት ፈራሁ ‎ ‎አብዝቼ ፈለኩሽ ‎አብዝተሽ ገፋሺኝ ‎አታውቂውም እንጂ እንዲህ ነው ያደረግሽኝ ‎  ‎መለስ ወደኋላ ‎መለስ ወደፊቴ ‎የጠቀመሽኝ መስለሽ ገለሺኛል ስንቴ ‎ ‎በበፊት ነገርሽ ዛሬን አግኝተሻል ‎ዙፋን ላይ ወርጄ ዙፋን ላይ ወተሻል ‎ጊዜ አይመጣም ብለሽ ጊዜሽን ወስደሻል ‎ ‎ጊዜ ተገልብጦ ጊዜ ይገፋልና ‎ጠንቀቅ በይ አለሜ ወድሻለሁና ‎ ‎ስወድሽ ተከፋሁ ‎አይቼ እንዳለየሁ ስንት ነገር ገፋሁ ‎ ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
28😢 7🔥 3👍 1😱 1
እርግማን ነው //////////////// አፈር ይብላው፣ ያ ገላሽን መቼስ እንደው አይቀርለት፣ እርጅና ይብላው፣ ያ መልክሽን እሱም እንደው አይቀርለት። መርገም አላውቅ መንገድ ጠፋኝ፣ አንችን ብዬ ሳላገኝሽ በጣም ከፋኝ፣ ልራገም ነው በይ ተቀበይ፣ ልብሽ እንደው እኔን አንዴ ባፈቀረኝ። እርግማን ነው አትሳቂ፣ ሳያገኙ ማፍቀር ህመሙን እወቂ። እርግማን ነው ብሸዬሽ የለ፣ ቂም እንደሆን በፍቅር የለ። ያኔ ድሮ ገፍተሽኛል አዎ አውቃለሁ፣ ይህ እርግማን ሲደርስብሽ ቂሙን ትቼ እወድሻለሁ። ሞኝ አደለው። @abela_black @getem @getem @getem
显示全部...
40🔥 6🤩 5
ምን ሊወስድ ይመጣል (በእውቀቱ ስዩም) አንቺ ጻድቅ መሳይ፥ ጭምት ለማያውቅሽ እኔን አርጎ ፈጥሮኝ፥ ስጋ -ለበስ ጥንቅሽ እንኳንስ መረቄ፥ ቅርፊቴ ማይጣል ሞት በቀጠሮው ቀን፥ ምን ሊወስድ ይመጣል:: @getem @getem @paappii
显示全部...
38👍 6👎 1🔥 1
     🤲አሜን በይ ልመርቅሽ ቆሻሻው ተቃጥሎ ሀገር ምድሩ ፀድቶ ታፍኖ የቆየ ፍቅር አገርሽቶ በጦቢያ ምድር ህዳሩ ሲታጠን በለተ ሚካኤል አሜን ሰላም ይስጠን::                አሜን! ሰላም ውሎ ይደር ቀዬው አድባሩ ከመስጊዱ አዛን ቅዳሴው ከደብሩ አይስተጓጎሉ ኬር ሆኖ መንደሩ::            አሜን! አቦል ጀባ ጀባ ቶና እና በረካ አቦ ሀጃ ይውጣ ጠጥተን እንርካ ኑሯችን ይስመር እንደ ፅጌ ይፍካ::               አሜን! አሜን በይ ይሁን ከአሜን ይቀራል የከረመ በቀል በፍቅር ይሻራል! ቤትሽ ፍቅር ይሙላው ካምናው እጥፍ አርጎ ውልቅ ይበል ችግር ማጣት ተጠራርጎ::           አሜን! ልጆችሽ ይደጉ በእውቀት በምግባር ሰውሮ ያቆያቸው ከጦርነት ግንባር አሜን ልብ ይስጣቸው የሚታይ በተግባር:: አንደበትሽ ይጣፍጥ የነካሽው ይብዛ ያንቺን ስራ አይቶ ሰውዘር አደብ ይግዛ::             አሜን! By @Abuugida @getem @getem @paappii
显示全部...
105👍 6🤩 4🔥 1
ቀሚስሽ ደግ ነው መሰሰት አያውቅም ደጅ ለጠናበት ለጋሽ ነው አይነፍግም አርሂቡ አርሂቡ ሁሉን ተቀባይ ነሽ ቀጭን አትይ ወፍራም ጥቁር አትይ ቀይ መቼ ትመርጫለሽ! አርሂቡ! አርሂቡ ግቡ ተቋደሱ አንተም ያዝ አንተም ያዝ እስኪ ተቃመሱ . እንኩ ነው ልሳንሽ ላንኳኳ በሙሉ ለስሜት አበጋዝ የሚገልብሽ ሁሉ እንኩ ነው በነጋ እንኩ ነው በመሸ ያ ነጩ ቀሚስሽ በመስጠት ጠለሸ እንካ ያልሽው ተቀባይ አጣጥሞ ጣለሽ ልክ እንደ ማስቲካ ወትሮም ቅሉ አያምር በሁሉ የተነካ [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @getem @getem @getem
显示全部...
😁 43 32🤩 15👎 10👍 7😢 6🔥 2
እንደ ፍያታዊ መስቀል ተቀብሮ እንደተረሳ ወይ እንደ መበለት ቀሚስ ተሰጥትቶ እንዳልተነሳ ኖርኩ ለማለት ያህል የ-የዕለት ሌት እያነጋሁ እንዲሁ በዝምታ እንደረጋሁ ! ያው የ ሰማንያ እድሌን ከህይወት ሳልጠጋ ብቻዬን የምቀር ይመስለኛል By Bo Hamian @getem @getem @paappii
显示全部...
18😁 7🔥 1