TIKVAH-ETHIOPIA
Open in Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
Show more1 574 957
Subscribers
+7524 hours
+6507 days
+76130 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
www.desktutorial.com
በኢትዮጲያ የመጀመሪያ የሆነዉ በኦንላየን አስተማሪዎችና ተማሪዎችን (ከ 1ኛ - 12ኛ ክፍል) የሚያገናኝ የጥናት ፕላትፎርምን ይቀላቀሉ፡፡
መምህራን እና ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ጥናት የሚያካሄዱብት፤ ከ 1200+ መምህራን የሚገኙብት፡፡
Desktutorial.com ይጎብኙ በቀላሉ አስጠኝ ይቅጠሩ፡፡ ለ6ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሃገር አቀፍ ፈተናዎች ማዘጋጃ ጥናት ጀምረናል፡፡
How it works:
Sign up → choose a tutor → join your virtual class (whiteboard, video, audio, quizzes, and more) → recording is saved automatically.
Sign up now: www.desktutorial.com
Email: info@desktutorialsolutions.com
❤ 136😢 7🕊 7🙏 5👏 3😱 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቴሌ ብር ሱፐርአፕ
ስጦታው ጨምሯል!
ቴሌብር ሱፐርአፕ አውርደን ስንጠቀም 100 ሜ.ባ የነበረው ስጦታ ወደ 500 ሜ.ባ ከፍ ብሏል!
default pin ስንቀይር የ15 ብር ስጦታ፤ ከ100 ብር በታች አየር ሰዓት ስንሞላ 15% ስጦታ፤ 100 ብር እና ከዚያ በላይ አየር ሰዓት ስንሞላ 25% ምርቃት፤ በቴሌብር ጥቅል ስንሞላ 10% ተጨማሪ ወደ ስልካችን በቀጥታ ይገባል!
በቴሌብር ስንመረቅ እንዲህ ነን!
*127# ደውለን ወይም ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
❤ 220😡 16🙏 8🥰 3😱 1
#SocialMedia🚫
በአውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ተደረገ።
ሀገሪቱ እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ሬዲት ባሉ መድረኮች ላይ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዳይኖራቸው የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አድርጋለች።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ይህንን አዲስ ህግ ካላከበሩ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡
የሃገሪቱ መንግስት እገዳው ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው ብሏል።
ህጉ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች በቀጥታ እንዲወጡ/እንዲወገዱ ተደርገዋል።
አውስትራሊያ ውስጥ የትኞቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሕጉን እንዲተገብሩ ይገደዳሉ ?
እንደ:-
- ቲክቶክ፣
- ዩትዩብ፣
- ኢንስታግራም፣
- ፌስቡክ፣
- ስናፕቻት፣
- ሬዲት፣
- ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር)፣
- ትዊች፣
- ኪክ፣
- ትሬድስ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች አገልግሎት እንዳያገኙ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡
ዋትስአፕ ፣ ሜሴንጀር፣ የኢሜል አገልግሎቶች ፣ የኦንላይን ላይ ጨዋታዎች እና የተለያዩ ትምህርታዊ መሳሪያዎች ከእገዳው ነፃ ሆነዋል፡፡
የእገዳው ግቡ ምንድነው?
- ልጆችን ከሳይበር ጥቃት ፣ ማዋረድ ፣ ከክፉ ሃሳቦች ፣ ስድብ መከላከል፡፡
- የልጆችን የአእምሮ ጤና መጠበቅ፡፡
እገዳው እንዴት ይሰራል?
መተግበሪያዎቹ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ለምሳሌ ፡- የፊት ዕድሜ ግምት ፣ የዶክመንት ማጣራት ፣ ሌሎች ምክንያታዊ የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ (ከ16 ዓመት በታች ልጆች አካውንት እንዳይከፍቱ ያላቸውንም እንዳይጠቀሙ)።
በእርግጥም ኩባንያዎቹ ህጉን ተግባራዊ ያደርጋሉ?
ትልልቆቹ ኩባንያዎች ህጉን ለመተግበር ተስማምተዋል። እንደ ሜታ (ፌስቡክ ፣ ኢንስታግረም እና ትሬድስ ) እንዲሁም ቲክቶክ ተጠቃሚዎችን ማሳወቅ ፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን አካውንት ማስወገድ ጀምረዋል፡፡
ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር ) በይፋ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አልገለፀም ፤ ነገር ግን ኩባንያው ህጉን የግድ ተግባራዊ እንዲያደርግ በመንግስት በዝርዝር ከተቀመጡት የማህበራዊ ሚዲካ ኩባንያዎች መካከል ነው።
ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ እና ማሌዥያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት መንግስታት የአውስትራሊያን አካሄድ ለመተግበር እያጤኑ ነው።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በህግ የከለከለች ቀዳሚ ሀገራ ሆናለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው ያሰባሰበው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#SocialMedia🚫
በአውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ተደረገ።
ሀገሪቱ እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ሬዲት ባሉ መድረኮች ላይ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዳይኖራቸው የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አድርጋለች።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ይህንን አዲስ ህግ ካላከበሩ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡
የሃገሪቱ መንግስት እገዳው ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው ብሏል።
ህጉ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች በቀጥታ እንዲወጡ/እንዲወገዱ ተደርገዋል።
አውስትራሊያ ውስጥ የትኞቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሕጉን እንዲተገብሩ ይገደዳሉ ?
እንደ:-
- ቲክቶክ፣
- ዩትዩብ፣
- ኢንስታግራም፣
- ፌስቡክ፣
- ስናፕቻት፣
- ሬዲት፣
- ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር)፣
- ትዊች፣
- ኪክ፣
- ትሬድስ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች አገልግሎት እንዳያገኙ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡
ዋትስአፕ ፣ ሜሴንጀር፣ የኢሜል አገልግሎቶች ፣ የኦንላይን ላይ ጨዋታዎች እና የተለያዩ ትምህርታዊ መሳሪያዎች ከእገዳው ነፃ ሆነዋል፡፡
የእገዳው ግቡ ምንድነው?
- ልጆችን ከሳይበር ጥቃት ፣ ማዋረድ ፣ ከክፉ ሃሳቦች ፣ ስድብ መከላከል፡፡
- የልጆችን የአእምሮ ጤና መጠበቅ፡፡
እገዳው እንዴት ይሰራል?
መተግበሪያዎቹ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ለምሳሌ ፡- የፊት ዕድሜ ግምት ፣ የዶክመንት ማጣራት ፣ ሌሎች ምክንያታዊ የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ (ከ16 ዓመት በታች ልጆች አካውንት እንዳይከፍቱ ያላቸውንም እንዳይጠቀሙ)።
በእርግጥም ኩባንያዎቹ ህጉን ተግባራዊ ያደርጋሉ?
ትልልቆቹ ኩባንያዎች ህጉን ለመተግበር ተስማምተዋል። እንደ ሜታ (ፌስቡክ ፣ ኢንስታግረም እና ትሬድስ ) እንዲሁም ቲክቶክ ተጠቃሚዎችን ማሳወቅ ፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን አካውንት ማስወገድ ጀምረዋል፡፡
ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር ) በይፋ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አልገለፀም ፤ ነገር ግን ኩባንያው ህጉን የግድ ተግባራዊ እንዲያደርግ በመንግስት በዝርዝር ከተቀመጡት የማህበራዊ ሚዲካ ኩባንያዎች መካከል ነው።
ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ እና ማሌዥያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት መንግስታት የአውስትራሊያን አካሄድ ለመተግበር እያጤኑ ነው።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በህግ የከለከለች ቀዳሚ ሀገራ ሆናለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው ያሰባሰበው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
" ተማሪው ከዋናዉ ቤተ መጽሐፍ ሰገነት ላይ ወድቆ ወደ አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ነው ህይወቱ ያለፈው " - የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
➡️ " አስክሬኑ ዛሬ ወደ ቤተሰቦቹ ተሸኝቷል፤ የሻማ ማብራት መርሃግብር ይደረጋል " - የተማሪዎች ሕብረት
በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የኢኮኖሚክስና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረው ጥላሁን ባዘዘዉ ትላንት ምሽት በጫሞ ካምፓስ ከዋናዉ ቤተ መጽሐፍ ጣሪያ ሰገነት ላይ ወድቆ ወደ አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ጉዳዩን በቅርበት እናዉቃለን ያሉ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጫሞ ካምፓስ ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ተማሪው ባሳለፍነዉ ዐርብ ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እሁድ መመለሱን አረጋግጠናል " ያለን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አንድ የተማሪዎች ሕብረት አመራር ትላንት ማምሻውን በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጫሞ ካምፓስ ከሚገኘዉ ዋናው የተማሪዎች ቤተመጽሐፍ ጣሪያ ላይ ወድቆ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ በዚያው ሕይወቱ ማለፉን አብራርቷል።
ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በመስከረም ወር የኢኮኖሚክስና ፋይናስ የትምህርት መስክ በመምረጥ ወደ ጫሞ ካምፓስ መምጣቱን የገለፁት ተማሪውን በቅርበት የሚያዉቀው አንድ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ " የተለየ ሕመምና ባህሪ አይቸበት አላዉቅም " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
'' አስክሬኑ ማድረቂያ እንዳይወጋ የተማሪዉ ቤተሰብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና 'አስክሬን እናስመረምራለን' በማለታቸው ወደ አዲስ አበባ በፖሊስ እና የተማሪዉ አብሮአደግ ጓደኛ ተልኳል " ያሉት የተማሪ ሕብረት አመራሮች በሚቀጥሉት ቀናት የሻማ ማብራት ስነስርዓት በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ ዉስጥ እንደሚከናወን ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪው አሟሟት ጋር በተያያዘ ከጋሞ ዞን ፖሊስ እና ከዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ አድርጓል።
የዞኑ ፖሊስ አዛዥ " በአካል ካልተገኛችሁ መረጃ አልሰጠም " በማለታቸው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ስብሰባ ውስጥ መሆናቸውን በመግለፃቸዉ በዚህ መረጃ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
😭 1 553❤ 897🕊 77💔 66😢 50🙏 19🤔 5😱 4👏 3😡 2🥰 1
ካፈነገጡ አለባበሶች ጋር በተያያዘ የሀገራችን ሕግ የሚለው ነገር አለ ? ተጠያቂነቱስ ምን ያህል ነው ? ሕጉ ምን ይላል ?
" ጥሩ ነገር ለህዝብ ሳያስተምሩ ወይም ምንም ባልሰሩበት ሁኔታ የወረደ ድርጊት እየፈጸሙ በቲክቶክ የህዝቡን ትኩረት መያዝ መቆም አለበት ! " - የሕግ ባለሙያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " በG-Power TikTok Creative Award " በተሰኘ ዝግጅት ላይ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ ታይተዋል የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎችን እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተገናኘ ሌላ አንድ ሰው በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ መጀመሩ መግለጹ ይታወቃል።
ፖሊስ ግለሰቦቹ ፈጸሙት ያለድ አስነዋሪ እና አፀያፊ ድርጊት በኢትዮጵያ ሕግ እንዴት ይታያል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ጠይቋል።
የህግ አማካሪና ጠበቃ ሳሙኤል ግርማ ግለሰቦቹ የፈጸሙት ድርጊት " በኢፌዴሪ የወንጀል መቅጫ ህግ አዋጅ 4/14/1996 አንቀፅ 639 መሰረት እያንዳንዳቸው ከ3 ወር እስከ 3 አመት ፅኑ እስራት " ሊያስቀጣቸው እንደሚችል ተናግረዋል።
የሕግ ባለሙያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱ አለባበስ እና ባህል ያለው ነው፣ ህፃናትና ትልልቅ ሰዎች በሚያዩበት ሁኔታ ወጣ ባለ አለባበስ ጡት እያሳዩ መታየት፤ ወንዶችም የሴት ልጆችን አይነት አለባበስ ለብሰው አደባባይ የወጡበት እና ለህዝብ ያሳዩበት መንገድ መንግስት ወይም ህግ የለም እንዴ ? የሚያስብል ነው። በአዋርዱ ላይ ግለሰቦቹ ያደረጉት ነገር እጅግ አስነዋሪ እና የወረደ ተግባር ነው።
በመሆኑም ከሀገራችን ባህልና እሴት ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሶ አደባባይ መውጣትን የኢፌዴሪ የወንጀል መቅጫ ህግ አዋጅ 4/14/1996 አንቀፅ 639 ይከለክላል፣ ቅጣቶችንም አስቀምጧል።
ይህን አስነዋሪ እና አጸያፊ ድርጊት የፈጸሙ ግለሰቦች በወንጀል መቅጫ ህጋችን መሰረት እያንዳንዳቸው ከ3 ወር እስከ 3 አመት ፅኑ እስራት ይጠብቃቸዋል።
ቲክቶክ እየተጠቀመ ያለው በተለይ አዲሱ ትውልድ ነው፣ ትውልዱን የሚመርዝ ነገሮችን የመቆጣጠር ሃላፊነት ደግሞ የመንግስት ነው። ሰዎች እውቅና ለማግኘት ከባህል እና ከእሴቶቻችን ያፈነገጡ ተግባሮችን ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም። መንግስትም እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይበል የሚያስብል ነው።
በተለይም በዝግጅቱ ላይ ወጣ ያለ አለባበስ ከለበሱት ግለሰቦች ውስጥ የአንዷ በተለየ መልኩ የሚገለጥ አስነዋሪ እና አፀያፊ ድርጊት ነው።
ጥሩ ነገር ለህዝብ ሳያስተምሩ ወይም ምንም ባልሰሩበት ሁኔታ የወረደ ድርጊት እየፈጸሙ በቲክቶክ የህዝቡን ትኩረት መያዝ መቆም አለበት።
ፕሮግራሙን ያዘጋጀው እና መድረኩን ያመቻቸው ' G-Power TikTok Creative Award ' እራሱ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ይገባል። ተቋም ስለሆነ ልብስ ስላለበሰ እንጂ ይህ አስነዋሪ ድርጊት የተንጸባረቀው በሱ አማካኝነት ነው።
የራሱን ብራንድ የሚያስተዋውቀው የህዝብን Morality በሚነካ እና ባፈነገጡ ሰዎች መሆን የለበትም። እሱ ራሱ ተጠቃሚ ነው፣ ድርጊት ፈጻሚዎችም ሆኑ ድርጊቱ እንዲፈጸም ያመቻቹት አካላቶች ለወንጀሉ እንደተባባሪ ታይተው የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።
መድረኩን ያዘጋጀውን አካል G-Powerን በቀጥታ የሚያስጠይቀው ነገር ባይኖርም እሱ ራሱ ባዘጋጀው መድረክ ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲመለከት በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት እንዳይተላለፍ መከላከል ይችል ነበር። ነገር ግን ይህን አላደረገም፣ በመሆኑም በቸልተኝነትም ሆነ በተዘዋዋሪ ለዚህ ድርጊት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ስላለው ተጠያቂ ነው።
መጀመሪያውኑም ቲክቶክ Informal ሚዲያ ነው፣ ጋዜጠኛ ነን የሚሉትም የጋዜጠኝነት ሞያ የሌላቸው፣ አርቲስት ነን የሚሉትም አርቲስት ያልሆኑ ናቸው፣ ሁሉም ሰው እንደፈለገ የሚሆንበት በስነምግባር የማይመራ ነው። በአዋርዱ ዝግጅት ላይም የሐይማኖት ነገሮች ተነስተዋል፣ ይህም ልክ ያልሆነ ተግባር ነው።
ሀገራችን የሚዲያ ህግ አላት፣ አዋጆችም አሉ፣ የብሮድካስት ባለስልጣንም አለ። በቲክቶክ እየሆነ ያለው ግን ይህን ሁሉ በሚጣረስ መልኩ ነው።
ሰው በሞያው ሰርቶ ሳይሆን በጫዎታ፣ በአስነዋሪ ድርጊት፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት እያጫረሱ ህይወቱን የሚቀይር ከሆነ ለምንድን ነው የሚማረው ? ቲክቶክ ላይ እየሆነ ያለው የማይሆን ነገር ነው።
ወንጀሎች ሲፈጸሙ እየጠበቁ ከመቅጣት ይልቅ ወደፊት እንደዚህ አይነት ነገሮች እንዳይደገሙ በጥናትና ምርምር የተደገፈ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ተገቢ ነው።
የሀገራችንን መሰረታዊ እሴት መጣስ ከባድ መዘዝ አለው፣ ከዚህ በፊት በቲክቶክ ታውቀው ችግር ውስጥ ከገቡ ሰዎች መማር ያስፈልጋል፣ ለእውቅና እና ለዝና ተብሎ የሀገራችን ባህል፣ እሴት እና ህግ የሚጥስ ነገር እንዳይፈጸም ቲክቶከሮችን የሚያማክር አካል እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" በቁጥጥር ስር ውለዋል ! "
ከሀገራችን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አንዱ የሆነውን ቲክቶክ በመጠቀም ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችና ምስሎችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ግለሠቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።
በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ስነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስ " ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባራትና ትውልድን ለማነጽ መጠቀም ሲገባ ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል " ብሏል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
" የሃይል ስርቆት ሲፈጸም የተገኘ ደንበኛ በትንሹ ከ 20 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ብር ሊደርስ የሚችል ቅጣት ይቀጣል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 4 ወራት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በደረሰ ስርቆትና ውድመት እንዲሁም በተፈፀመ የኃይል ስርቆት 143 ሚሊዮን 299 ሺህ 114 ብር ጉዳት እንዳጋጠመው ገልጿል።
አገልግሎቱ ይህንን ያሳወቀው የ2018 ዓም በጀት አመት የአራት ወራት በጀት አፈጻጸሙን አስመልክቶ ለሚዲያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ባለፉት አራት ወራት ብቻ በ17 የትራንስፎርመር ስርቆት ከ23 ሚሊየን 85 ሺህ 847 ብር በላይ ጉዳት አጋጥሞኛል ብሏል።
በተጨማሪም፣ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ስርቆት 88 ሚሊዮን 849 ሺህ 858 ብር፣ 15 መኪናዎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ባደረሱት ግጭት 18 ሚሊዮን 178 ሺህ 731 ብር፣ እንዲሁም በኃይል ስርቆት13 ሚሊዮን 184 ሺህ 677 ብር ጉዳት ያጋጠመው መሆኑን ገልጿል።
የሃይል ስርቆት ሲፈጽም የተገኘ ደንበኛ በተቋሙ የቆጣሪና ተያያዥ ዕቃዎች ምርመራ መመሪያ መሰረት ሃይሉ እንዲቋረጥ ከማድረግ በተጨማሪ የሰረቀውን ሃይልም በባለሞያዎች ስሌት ተደርጎ እንዲከፍል እንደሚደረግ አገልግሎቱ አሳውቋል።
በመመሪያው መሰረት ከሚጣልበት ቅጣት በተጨማሪም የሃይል ስርቆትን በመፈጸሙ የወንጀል ተጠያቂነትን ይኖረዋል የተባለ ሲሆን ፣ የሃይል ስርቆት ሲፈጽም ቅጣቱ በትንሹ ከ 20 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ብር ሊደርስ የሚችል ቅጣትም የሚጣል ይሆናል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማርኬቲንግ የሽያጭ እና የደንበኞች አገልግሎት ኤክስኪቲቭ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ስርቆቱን የፈጸሙ የተለያየ አይነት የታሪፍ መደብ ያላቸው ደንበኞች እንዳሉ አስረድተዋል።
አቶ ብርሃኑ "በመመሪያው መሰረት ስርቆት የፈጸሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ከሆኑ እስከ 20 ሺ ብር ይቀጣሉ፣ የንግድ ቤት ደንበኞች ሲሆኑ እስከ 500 ሺ ብር ይቀጣሉ" ብለዋል።
ዳይሬክተሩ "ዝቅተኛ ኢንዱስትሪዎች ወይም ከዋናው መስመር ሃይል በቀጥታ የማያገኙ ነገር ግን የኢንዱስትሪ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችን የሃይል ስርቆት መፈጸማቸው በተቆጣጣሪ አካላት ሲረጋገጥ እስከ 1 ሚሊየን ብር የሚቀጡ ይሆናል" ነው ያሉት።
የከፍተኛ አንዱስትሪ ተጠቃሚዎችም በተመሳሳይ 1 ሚለየን ብር ይቀጣሉ ያሉ ሲሆን ተጨማሪ ጥፋት እና ስርቆት ከተገኘባቸው ደግሞ ቅጣቱ እጥፍ እየሆነ የሚሄድ መሆኑን መመሪያውን በመጥቀስ አስረድተዋል።
የቆጣሪ እና ተያያዥ እቃዎች ምርመራ መሰረት የኢነርጂ ስርቆት ሲፈጸም የሚጣለውን አስተዳደራዊ ቅጣት ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 567😡 64👏 26🕊 16💔 11😭 9🥰 8🤔 8😱 5😢 5
" በክልሉ ሩቅ በሚባሉ ገጠራማ አካባቢዎች የቫይረሱ ስርጭት መኖሩ አሳሳቢ ነው " - ምክትል የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጉሻ በላኮ
➡️ " በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤችአይቭ ኤድስ ምርመራ ተረስቷል " - የጤና ባለሙያ
በኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት መኖሩ የማይታወቅባቸው ራቅ ያሉ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ የቫይረሱ ስርጭት መመዝገብ መጀመሩ አሳሳቢ ነው ሲል የኦሮምያ ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የጤና ቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የኤችአይቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር ጉሻ ባላኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት በፀጥታ ችግር፤ በድርቅ እንዲሁም ኑሮ ለማሻሻል ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ራቅ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች ሳይቀር ሪፖርት እየተደረገ ለመሆኑ መንስኤ ነው ብለዋል።
ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እነማን ናቸው ?
✓ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች
✓ በማዕድን ቁፋሮ ስራ የተሰማሩ ዜጎች
✓ ተፈናቃዮች
✓ የቡና ቤት ሴቶች
✓ የሎጅስቲክ አገልግሎት መዳረሻ ከተሞች ፤ የቱሪስት መስዕቦች ባሉባቸው ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች
✓ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ዜጎች እና ለቫይረሱ ስርጭት አመቺ በሆነ አካባቢ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል ዶክተር ጉሻ በላኮ።
" የእነዚህን ዜጎች ተጋላጭነትን ለመቀነስ የክልሉ ጤና ቢሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው " ያሉት ዶክተር ጉሻ " ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው ተብለው የተለዩ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች ናሙና እንዲሰጡ፤ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ለቫይረሱ ከተጋለጡ ደግሞ መድሃኒት እንዲጀምሩ ተከታታይ ትምህርት ባሉበት ቦታ እየተሰጣቸው ይገኛል " ብለዋል።
በኦሮምያ ክልል አሁን ባለው መረጃ የኤችአይቭ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት 0.6 በመቶ ነው ያሉት ዶ/ር ጉሻ 157,000 ሽህ የሚሆኑ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 134,000 ለሚሆኑ ዜጎች የፀረ ኤችአይቪ ኤድስ መድሃኒት ማስጀመር መቻሉን ገልፀዋል።
በጤና ተቋማት ያሉት የህክምና ባለሙያዎች ቫይረሱን በተመለከተ የህረተሰቡን ግንዛቤ እንዴት ይገልፁታል ?
የህክምና ባለሙያዋ ሲስተር ሃይማኖት ይገረም ምልከታዋን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳጋራችው አሁን አሁን ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤችአይቭ ኤድስ ምርመራ እያደረጉ አይደለም ከዚህ ቀደም ግን እራሳቸውን ለማወቅ የሚመጡ ሰዎች ብዙ ነበሩ።
ከተወሰኑ አመታት ወዲህ እናቶች ለወሊድ ክትትል ወደ ጤና ተቋማት ሲመጡ በዚያውም ነው ደማቸውን ለናሙና የሚሰጡት ስትል ገልፃለች።
ከዚያ ውጭ አልፎ አልፎ ሊጋቡ ያሰቡ ጥንዶችም ራሳቸውን ለማውቅ ይመጣሉ ስትል አክላለች።
" የኤችአይቪ ስርጭት ውስጥ ለውስጥ ስርጭቱ መቀጠሉን አብዛኛዎቹ ሰዎች ዘንግተዋል ገዳይ መሆኑንም ሰዎች ረስተዋል " የምትለው ሲስተር ሃይማኖት ህብረተሰቡ አሁንም መንቃት አለበት ስትል ትመክራለች።
ህብረተሰቡስ ስለቫይረሱ ስርጭቱ ምን ይላል ?
አቶ ብርሃኑ ዋቅዋያ የሸገር ከተማ ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ስለ ኤችአይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ህብረተሰቡ እየተዘናጋ ነው በማለት የራሳቸውን ተሞክሮ አጋርተውናል።
አቶ ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ባለቤታቸው ነፍሰጡር ናት እናም የወሊድ ክትትል እያደረገች ትገኛለች እሷ እግረ መንገዷን ስትመረመር እኔም ተመረመርኩ ይላሉ።
ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤቶች፤ በእምነት ተቋማት ፤ በገቢያ ቦታዎች ፤ የተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ስለ ቫይረሱ ስርጭት እና የሚያስከትለውን ጉዳት በተመለከተ ትምህርት ይሰጥ ነበር አሁን ግን የለም ብለዋን።
ስለቫይረሱ የሚሰማው በአመት ቀኑ ስከበር ብቻ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ህብረተሰቡ ቫይረሱን ችላ ብሏል አሁንም በተለያዩ አጋጣሚዎች የማስታወሻ ትምህርት ቢሰጥ " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የኦሮምያ ጤና ቢሮ በበኩሉ ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው ባላቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
#TikvahEthiopiaFamilyNekemte
@tikvahethiopia
❤ 637😭 84🤔 18🙏 16😡 12😱 10🥰 8🕊 7😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
#MPESASafaricom
በብር ማነስ ምክንያት የግብይት እቅዳችን አይስተጓጎልም! እርፍ በM-PESAን በመጠቀም የጎደለውን እንሙላ።
አገልግሎቱን በ *733# ወይም በ M-PESA መተግበሪያ ያግኙ።
ለማስጀመር ይህን ይጫኑ፥ https://mpesaconsumerappet.page.link/etTA
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ
https://onelink.to/ewsb22
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
https://t.me/MPesaETCustomerCare
#MPESASafaricom #MPESAEthiopia
❤ 153🙏 6🥰 1😢 1
ሜሮን መብራህቱ የተባለች ወጣትን የገደለው ወንጀለኛ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ።
የፍርድ ውሳኔው ከሦስት ዓመት በላይ ጊዜ ፈጅቷል።
የ23 ዓመቷ ሜሮን መብራህቱ የካቲት 18 /2015 ዓ.ም በመቐለ የአውቶቡስ መናሃሪያ አከባቢ ነው በባጃጅ ተገድላ ተጥላ የተገኘችው።
በግድያው ተጠርጥሮ ክስ የተመሰረተበት በላይ ፀጋይ የተባለ ግለሰብ ነው።
ጉዳዩን የያዘው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ በወጣት ሜሮን መብራህቱ ግድያ የተከሰሰውን ግለሰብ ወንጀለኛነቱን አረጋግጦ ዛሬ ሀሙስ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል።
ወንጀለኛው ግለሰብ ግድያውን ጨለማን ተገን በማድረግ መፈፀሙ የተገለጸ ሲሆን ይህ የጭካኔ ድርጊቱ አልበቃ ብሎት የፈጸመውን እኩይ ተግባሩን ለመደበቅ ጥረት ማድረጉ የፍርድ ቅጣቱን ከባድ አድርጎታል።
ፍርድ ቤቱ ግለሰቡ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ይህ የፍርድ ውሳኔ የተላለፈው ከሶስት አመት በኃላ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
❤ 1 312👏 373😭 145😡 65💔 56🙏 41🕊 29😢 21😱 11🥰 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Reminder 🔔
የባንክ ደንበኞች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የባንክ ሒሳባቸውን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማጣመር እንዳለባቸው ብሄራዊ ባንክ አሳስቧል።
የባንክ ሒሳብ ከፋይዳ ጋር ማጣመሪያ የጊዜ ሰሌዳውን ከላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopia
😡 368❤ 175😭 32😢 15👏 3🙏 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Reminder 🔔
የባንክ ደንበኞች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የባንክ ሒሳባቸውን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማጣመር እንዳለባቸው ብሄራዊ ባንክ አሳስቧል።
@tikvahethiopia
❤ 9🙏 1😡 1
" በቫይረሱ ስርጭት ስጋት ምክንያት በዓሉ በአደባባይ አይከበርም " - የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ
የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ዲሽታ ጊና" በዓል በማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት ዘንድሮ እንደማይከበር የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በብሔረሰቡ ዘንድ የአብሮነት ፣ የዕርቅና የሠላም፣ የመረዳዳትና የአዲስ ዘመን ብስራት ወቅት ተደርጎ የሚወሰደዉ ይህ በዓል በየዓመቱ በታህሳስ ወር መግቢያ በታላቅ ድምቀት ይከበር እንደነበር አስታውሰዋል።
ዘንድሮ ግን በአከባቢዉ ተከስቶ ለሰዎች ሞት ምክንያት በሆነዉ የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት በዓሉ ታስቦ ብቻ እንዲዉል ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከባህል አባቶች ጋር ከመግባባት መደረሱን ገልፀዋል።
በዓሉን በዓለም አቀፉ የትምህርት ሳይንስና ባህል ጥበቃ ድርጅት ዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረቶች መጀመራቻቸዉን ያነሱት አቶ አብረሃም ሕዝቡ ዘንድሮ በዓሉን እሴቱን በወል እያሰበ በዓሉን በታሳቢነት እንዲያከብረዉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
❤ 370😢 55👏 31🙏 15😡 12🤔 9🕊 7💔 5😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
⚡️አግሪላንሰር
ወደ ከብት እርባታ እና ዶሮ እርባታ ስራ ዘርፍ ለመግባት አስበዋል??
የሆላንድ የወተት ጊደሮች | የተመረጡ ምርታማ የዕንቁላል እና የስጋ የዶሮ ዝርያዎችን | ዘመናዊ የዶሮ ኬጆችን | የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖችን | አውቶማቲክ የወተት ማለቢያ ማሽኖች እና ሌሎችም የእርባታ ቁሳቁስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የመኖ ዘሮችን ለአርብቶ አደሩ እና በከተማ ግብርና ላይ ለተሰማራው ማህበረሰብ በሽያጭ ከማቅረብ ባሻገር ለዘርፉ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችንም በቴሌግራም በቀጣይነት እየሰጠን እንገኛለን።
The AgriLancer, Official partner of Brazmart International General Trading
ቴሌግራም👉 https://t.me/agrilancer
❤ 242👏 31🙏 27🕊 11🥰 6
Photo unavailableShow in Telegram
አቢሲንያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ
ብርቱዎች ነገአቸውን ዛሬ ላይ ከሁነኛ አጋር ጋር ይገነባሉ!
በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮቻችን አዲስ ሂሳብ በመክፈትና ተቀማጭ በማድረግ ምርጫዎ ሲያደርጉን - እኛ ደግሞ ለቤተሰባዊነትዎ እና ለትጋትዎ እንሸልምዎታለን!
ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ - ያድሱ - ይደጉ!
#StartRenewGrow #BOARewards #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
❤ 143😡 15🙏 12🥰 7👏 6😢 6🤔 4🕊 1
" አምስቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነው በቁጥጥር ስር ያዋልኩት " - ፖሊስ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።
" አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነው " ሲል ፖሊስ አስታውቋል።
" ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህል ለመጫን የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የጀመርኩትን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ " ሲል ፖሊስ አስታውቋል።
#EthiopianFederalPolice
@tikvahethiopia
#ጊፋታ
' #ጊፋታ ' በዓለም አቀፉ የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) በሰዉ ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ ዛሬ በወላይታ ዞን ሁሉም አከባቢዎች ህዝቡ አደባባይ በመውጣት ደስታውን ሲገልጽ እንደዋለ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ጊፋታ ለወላይታ ብሔረሰብ ከዘመን ዘመን የመሸጋገሪያ ብቻ ሳይሆን የማንነት መገለጫ ወደ መሆን ደርሷል ፤ አሁን ላይ ከብሔረሰቡ ባሻገር የመላዉ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ሀብትና የወላይታ ሕዝብ ለመላዉ ዓለም ያበረከተዉ የደስታ ስጦታ ነዉ " ሲሉ ገልፀዋል።
"ደስታው የመላዉ ኢትዮጵያውያን እንደሆነ አመልክተው " ጊፋታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ቱባ ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቀው ላቆዩ አባቶቻችን እንዲሁም በቅርስነት እንዲመዘገብ ለደከሙ ሁሉ ምስጋና ይገባል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
ፋይዳ ዲጂታል የማንነት መረጃ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር ስራ መጀመሩን ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ዘርፍ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ምዕራፍ ነው ያለውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከባንክ ስርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረ መሆኑን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል።
ባንኩ ፋይዳን መሰረት አድርጎ የሚሰጡ የፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎቶችን የማቀናጀት ሀገራዊ ግብን ለማሳካት በትግበራው ላይ በሰፊው እየተሰራ እንደሆነ ይታወቃል ያለ ሲሆን በዛሬው እለትም ለፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ የተባለውን ፋይዳ ዲጂታል የማንነት መረጃ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር (Harmonization) ስራ በይፋ ተጀምሯል ብሏል።
ይህ የመረጃ ሥርዓቶችን የማጣመር ስራ አላማው:-
• ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣
• በሀሰተኛ ሰነድ የእራሳቸውን ሂሳብ ሌሎች ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ፤
• በቀላሉ የብድር አገልግሎትን ማግኘት እንዲችሉ፣
• በአንድ ፋይዳ መታወቂያ የሁሉንም ባንክሂሳብ ለመጠቀም እንዲያስችላቸው ማድረግ
• ባንኮች በዚህ መረጃ ጥምረት የደንበኞቻቸውን ትክክለኛ እና ወቅታዊ የሆነ መረጃን እንዲያገኙ፣
• በሀሰተኛ ማንነት የሚከሰት የገንዘብ መጭበርበርን ለመከላከል እንዲሁም
• ለፋይናንስ ሴክተር ዲጂታል ትግበራ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት ሆኖ ያገለግላል ተብሏል፡፡
የባንክ ሂሳብ ቁጥር ክፋይዳ መረጃ ጋር ለማጣመር ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፎቻቸው በአካል በመሔድ ወይም ኦንላይን (ባንኩ በሚያስቀምጠው አሰራር መሰረት) የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሃዝ-FAN Number) በማቅረብ ማከናወን እንደሚችሉ ባንኩ ገልጿል።
ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ለማጣመር የተፈቀደው ጊዜ ገደብ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።
ለፋይዳ ያልተመዘገበ ማንኛውም የባንክ ደንበኛ በቅድሚያ በአቅራቢያው በሚያገኘው የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያ በመሔድ መመዝገብ እንደሚኖርበት ያሳሰበው ባንኩ በዚህ ሒደት ደንበኞች መጉላላት እንዳያጋጥማቸው አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በመፈፀም ላይ ናቸው ብሏል፡፡
ሙሉ መግለጫውን ከተያያዘው ፋይል ያንብቡ።
@tikvahethiopia
❤ 857😡 361😭 56👏 40🤔 21😢 17🥰 14🙏 10🕊 10
Photo unavailableShow in Telegram
#SafaricomEthiopia
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
ሰኞ ህዳር 29/2018 15ኛው ዙር ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና ፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረዉ መሰረት የ1,000,000 ብር ዕድለኛ ከጭሮ ሆኑዋል።
ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
ሌሎች የ100ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጽያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን።
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 196🙏 7😭 6👏 4😡 3🕊 2🥰 1
