en
Feedback
TIKVAH-ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA

Open in Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Show more
1 575 056
Subscribers
-4224 hours
+8177 days
+1 01030 days

Data loading in progress...

Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
December '25
December '25
+2 907
in 3 channels
November '25
+5 434
in 0 channels
Get PRO
October '25
+10 710
in 3 channels
Get PRO
September '25
+38 343
in 6 channels
Get PRO
August '25
+6 716
in 4 channels
Get PRO
July '25
+5 885
in 3 channels
Get PRO
June '25
+7 838
in 3 channels
Get PRO
May '25
+7 220
in 2 channels
Get PRO
April '25
+3 976
in 6 channels
Get PRO
March '25
+7 591
in 3 channels
Get PRO
February '25
+3 610
in 1 channels
Get PRO
January '25
+9 170
in 5 channels
Get PRO
December '24
+7 005
in 2 channels
Get PRO
November '24
+14 459
in 4 channels
Get PRO
October '24
+36 805
in 7 channels
Get PRO
September '24
+45 041
in 4 channels
Get PRO
August '24
+32 002
in 3 channels
Get PRO
July '24
+29 509
in 4 channels
Get PRO
June '24
+17 573
in 4 channels
Get PRO
May '24
+18 474
in 7 channels
Get PRO
April '24
+28 612
in 9 channels
Get PRO
March '24
+27 551
in 6 channels
Get PRO
February '24
+10 054
in 3 channels
Get PRO
January '24
+7 267
in 9 channels
Get PRO
December '23
+6 565
in 6 channels
Get PRO
November '23
+4 990
in 9 channels
Get PRO
October '23
+55 726
in 12 channels
Get PRO
September '23
+5 304
in 7 channels
Get PRO
August '23
+5 798
in 6 channels
Get PRO
July '23
+10 924
in 5 channels
Get PRO
June '23
+192
in 4 channels
Get PRO
May '23
+6 079
in 6 channels
Get PRO
April '23
+3 717
in 0 channels
Get PRO
March '23
+2 517
in 0 channels
Get PRO
February '23
+51 346
in 0 channels
Get PRO
January '230
in 0 channels
Get PRO
December '220
in 0 channels
Get PRO
November '220
in 0 channels
Get PRO
October '22
+1 165
in 0 channels
Get PRO
September '22
+9 922
in 0 channels
Get PRO
August '22
+11 915
in 0 channels
Get PRO
July '22
+13 795
in 0 channels
Get PRO
June '22
+3 382
in 0 channels
Get PRO
May '22
+3 363
in 0 channels
Get PRO
April '22
+6 885
in 0 channels
Get PRO
March '22
+7 552
in 0 channels
Get PRO
February '22
+19 245
in 0 channels
Get PRO
January '22
+1 219 483
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
16 December+330
15 December+44
14 December+79
13 December+93
12 December+57
11 December+319
10 December+754
09 December+314
08 December+110
07 December+78
06 December+48
05 December+188
04 December+300
03 December+66
02 December+64
01 December+63
Channel Posts
#Update #Gambella " የፓሊስ አባላትም ወደ አንድ ብሔር በማተኮር የግድያ ጥቃት ጥቃት ይፈጽማሉ " - ነዋሪዎች " ሁሉም ፓሊሶች ሳይሆን የተወሱት ወንጀል (ጥቃት) የሚፈጽሙበት ሁኔታዎች አ
#Update #Gambella " የፓሊስ አባላትም ወደ አንድ ብሔር በማተኮር የግድያ ጥቃት ጥቃት ይፈጽማሉ " - ነዋሪዎች " ሁሉም ፓሊሶች ሳይሆን የተወሱት  ወንጀል (ጥቃት) የሚፈጽሙበት ሁኔታዎች አሉ፤ እንደተባለው ትክክል ነው " - የጋምቤላ ክልል ጸጥታ ቢሮ "ዛሬ የተገደለው የጋምቤላ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ነው። ከቢሮው ወጥቶ ስራ እየሰራ ነበር፤ ወደቢሮ ሊመለስ ሲል ነው ጥቃቱ የተፈጸመው! " በጋምቤላ ክልል፣ ጋምቤላ ከተማ ዛሬ ረፋድ አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር፣ የከተማው ፓሊስ አባል እንደተገደሉ ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን፣ ክልሉም ድርጊቱ መፈጸሙን ዛሬ ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ሰሞኑን ባገረሸው የጸጥታ ችግር ንጹሐንና የፓሊስ አባላት ሲገደሉ፣ የቆሰሉም አሉ። ችግሩ ከዓመት በፊት ይስተዋል እንደነበር በማስታወስ፣ ከሳምንታት ጀምሮ ማገርሸቱን ገልጸው፣ " የፓሊስ አባላትም ወደ አንድ ብሔር በማተኮር የግድያ ጥቃት ይፈጽማሉ " ሲሉ ወቅሰዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ የክልሉን ባለስጣናት ቢጠይቅም ባለመሳካቱ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተደድር ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድን ጠይቋል። እሳቸውም ፥ " አሁን ስራ ላይ ናቸው ማታ ደውልላቸው። ከደወሉላችሁ አንሱ ብዬ እነግራቸዋለሁ። በተለያየ ሰው መልስ ሊሰጥ አይገባም፤ የጸጥታ አካሉ ስላለ እነርሱ ናቸው መስጠት ያለባቸው " ብለዋል። በኋላም፣ በተለያዩ ወረዳዎች ሰሞኑን በተስተዋለ የጸጥታ ችግር ንጹሐን ጭምር መገደላቸውን ፤ ዛሬም ከተማዋ ላይ ተኩስ እንደነበርና ፓሊስ እንደተገደለ ነዋሪዎች ገልጸዋል፤ ፓሊስ ተገድሏል መባሉ እውነት ነው ? በአጠቃላይ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ስንል የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጠይቀናል። የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማበር ኮር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ ? " ዛሬ የሞተው የፓሊስ አባል ብቻ ነው እንጅ ሌላ የሞተ ሰው የለም። ድርጊቱ ሲፈጸም በቦታው አልነበርንም፤ የተገደለው የጋምቤላ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ነው። ከቢሮው ወጥቶ ስራ እየሰራ ነበር፤ ወደቢሮ ሊመለስ ሲል ነው ጥቃቱ የተፈጸመው። ህዝቡም እንዲረጋጋ በየቀበሌው የማረጋጋት ስራ እየሰራን ነው። ዛሬ የተፈጠረው ችግር የማይጠበቅና ነው። ግን ወደ ከፋ ችግር እንዳይሄድ በስጋት ቀጠናዎች የጸጥታ ኃይሎች በመመደብ ህዝቡ ወደ ከፍተኛ ግጭት እንዳይገባ ተደርጓል። ሰሞኑን በክልሉ የተከሰተው አለመረጋጋት እንደ ክልል ብዙ ስራዎች ሰርተናል። በየወረዳ የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል። ከጉዳዩ ጋር የተጠረጠሩ ወንጀሎች ተይዘዋል፤ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው በህግ ቁጥጥር እንዲውሉ አድርገናል " ብለዋል። ነዋሪዎቹ፣ " አንዳንድ የፓሊስ አካላት በንጹሐን ግድያ ተሳታፊ የሚሆኑበት፣ ወደአንዱ ብሔር የሚያደሉበት ሁኔታ እንዳለ " ይገልጻሉ፤ በጥቃቱ ጠርጥራችሁ ከያዛችኋቸው መካከል የጸጥታ ወይም የፓሊስ አባላት አሉ ? ለሚነሳው ቅሬታ ምላሻችሁ ምንድን ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቢሮ ኃላፊውን ጠይቋል። ኃላፊው አቶ ማበር፣ " ሰው ሲፈጠር ሙሉ ስላልሆነ፣ የሚጎድል ነገር ስላለ፣ ይህንን ነገር (ጥቃቱን) አያደርግም ማለት ሊከብድ ይችላል። ሁሉም ፓሊሶች ሳይሆን የተወሱት ወንጀል (ጥቃት) የሚፈጽሙበት ሁኔታዎች አሉ፤ እንደተባለው ትክክል ነው። ግን አጠቃላይ ፓሊስ አይደለም። አንዳንዶቹ በራሳቸው ችግር ምክንያት በእነዚህ የወንጀል ድርጊቶች የሚሳተፊበት ሁኔታዎች አሉ " ሲሉ መልሰዋል። በሰሞንኛው ጥቃት ንጹሐን መገደላቸው ተነግሯል፤ በትክክል ምን ያክል ናቸው የተገደሉት ? ተጠርጣሪዎችን መያዛችሁንም ገልጻችኋል፣ ስንት ናቸው ? የተጠረጠሩት በግድያ ወይስ በምንድን ነው? ግልጽ ብታደርጉት ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም ለኃላፊው አቅርበናል። ኃላፊው፣ " በእርግጥ ብዙ ሰው ሞቷል። ሁለት መኪናዎች በመንገድ ላይ ጥቃት ደርሶባቸው። በኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢም ሁለት ሴቶች የተገደሉበት ሁኔታ ነበረ። ሲጠቃለል ግን 10 አይደርስም። ግን አንድ ሰው ቢሆንም ሞት ነውና እንደ ትልቅ ነገር መቆጠር አለበት፤ እየሰራንበት ነው " ብለዋል። " 18 ተጠርጠሪዎች በፓሊስ ተይዘዋል፤ ግን ከዚያ በላይ ናቸው። ያልተያዙ አሉ። በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ አሉ በዚያ ውስጥ፤ በተጨማሪም ግድያ እንዲፈጸም ሰዎችን ያደራጁ ሰዎች አሉ። መኪና መንገድ ላይ ጠብቆ ጥቃት የማድረስ፤ ከተማ ላይ ሰው በመግደል ወንጀሎች ነው ተጠርጥረው የተያዙት። ሌሎችንም ገና በማፈላለግ ላይ ነን" ነው ያሉት። የጸጥታ ችግሩ ምንጭ ምንድን ነው ? ከአንድ አመት በፊትም ተከስቶ ነበር፤ አሁን ያገረሸበት ምክንያት ምንድን ነው ? ችግር እንዳይቀጥል ቀድሞ መፍትሄ መስጠት ያልተቻለው ለምንድን ነው ? አሁን ችግሩ እንዳይቀጥልስ ምን እየተሰራ ነው? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም የቢሮው ኃላፊ ምላሽ ሰጥተዋል። የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊው አቶ ማበር ምን መለሱ ? " ሁለት ብሔረሰቦች በሚገናኙባቸው ቦታዎች ይጋጫሉ ምንጊዜም፤ ግን እርቅ ተፈጥሮ፣ ህዝቡ ወደ አንድነት የመጣበት ሁኔታ ነበር። ከዚህ በፊት ስልጣን ላይ የነበሩት፣ ስልጣናቸው ዝቅ ተደርጎ የወረዱ አካላት ደስተኛ ስላልሆኑ እንደገና ከዚህ በፊት ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮችን ለመፍጠር አልተኙም። ዋና ምንጩ እንደ ክልላችን ባገኘነው አንጻራዊ ሰላም ደስተኞች ያልሆኑ፤ ክልሉ ወደብጥብጥ እንዲገባ ወጣቶችን የሚገፋፉ አሉ። ሌላው ህገወጥ የሆኑ ሚዲያዎች ህዝቡ ተቻችሎ እንዲኖር የማይፈልጉ ስላሉ ክልሉ እንዳይረጋጋ እያደረጉ ነው። በኛ በኩል በውይይት የሚያምን ህዝብ ለመፍጠር በየደረጃው የማወያየት ስራ እየሰራን ነው። ህዝቡም ወንጀል ፈጻሚዎችን አጋልጦ ለህግ መስጠት አለበት " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia

63 470580

2
" ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ናት " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ+5
" ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ናት " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት መደረጉን ገልጸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረጉ በኃሏ ከልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በመሆን የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን አመልክተዋል። " በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል " ብለዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረገው  ፦ - በጉምሩክ የጋራ አስተዳደር ድጋፍ፣ - በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ምስረታ፣ - በአለምአቀፍ የሰላም ማስከበር ላይ ኢትዮጵያና ህንድ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እና የሚያጠናክረውን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ሥራ የመግባቢያ ሥምምነት የፊርማ ሥነሥርዓት ላይም መገኘታቸውን አሳውቀዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) " ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ስትሆን የዛሬዎቹ ውይይቶች እና ሥምምነቶችም ለጋራ ጥቅም በተለያዩ ዘርፎች ያሉንን ትብብሮች ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኛ አቋም ያሳያሉ " ብለዋል። የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ነገ ደግሞ በህዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋሉ። #Ethiopia 🇪🇹 #India 🇮🇳 @tikvahethiopia
118 013
3
" ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ነዳጅ የሚከማችበት የአለት አይነት በቅልጥ አለት ተሸፍኗል። ያ ደግሞ የተፈጥሮ ነዳጁን ሙሉ በሙሉ ወደላይ እንዳይወጣ ያደርገዋል "- ደረጀ አያሌው (ፕ/ር) "በትንሹ ከ1 ኪ+1
" ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ነዳጅ የሚከማችበት የአለት አይነት በቅልጥ አለት ተሸፍኗል። ያ ደግሞ የተፈጥሮ ነዳጁን ሙሉ በሙሉ ወደላይ እንዳይወጣ ያደርገዋል "- ደረጀ አያሌው (ፕ/ር) "በትንሹ ከ1 ኪሎሜትር የማያንስ ቅልጥ አለት ነው የሸፈነው! " በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ሰሞኑን የተፈጥሮ ነዳጅ በራሱ ኃይል ወደ መሬት ገንፌሎ መፍሰሱን የዞኑ ማዕድን መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል። ነዳጁ በወረኢሉ፣ ለገሂዳና ከለላ ወረዳዎች እንደሚገኝ የገለጹት የመምሪያው ኃላፊ አቶ አሕመድ አበባው፣ ነዳጁን ለማውጣት ከፍተኛ ቲክኖሎጅና የጂኦሎጂ ባለሙያ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ነዳጁን አውጥቶ ለመጠቀም ምን አይነት ቴክኖሎጂ ነው የሚያስፈልገው ? በቀጣይ ምንስ መደረግ አለበት ? ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምድር ትምህርት የእሳተ ገሞራ መምህርና ተመራማሪ ደረጀ አያሌው (ፕ/ር)ን ጠይቋል። ተመራማሪ እና መምህሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? " ነዳጁ ወጥቷል። በእርግጥ ከዚህ በፊትም ነበር። ግን አንዳንዴ ጎላ ብሎ ይፈሳል፤ አንዳንዴም ይጠፋል። የወጣው የተፈጥሮ ነዳጅ ፍሳሽ የሚያሳየው በአካባቢው ድፍድፍ ዘይት እንዳለ ነው። ነገር ግን ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ነዳጅ የሚከማችበት የአለት አይነት በቅልጥ አለት ተሸፍኗል። ያ ደግሞ የተፈጥሮ ነዳጁን ሙሉ በሙሉ ወደላይ እንዳይወጣ ያደርገዋል። ምክንያቱም በውስጡ ሰፊ ቀዳዳዎች ስለሌሉ ነው። እናም ትልቁ ነዳጅ በቅልጥ አለት ስለተሸፈነ ያን የግድ ቆፎሮ ማግኘት ያስፈልጋል፤ ትልቁ ችግር እሱን ቆፍሮ የተፈጥሮ ነዳጅ የተከማቸበትን አካባቢ የአለት አይነት የማግኘት ነው፤ እንጅ ሌላም ሀገር እንደተለመደው ቆፎሮ ማውጣት ይቻላል። እኛ ጋ ልዩነቱ ነዳጅ የሚፈጥረውና የሚያከማቸው የአለት አይነት በቅልጥ አለት የተሸፈነ ስለሆነ ነው፣ ግን ደግሞ በተፈጥሮ አነስተኛ እፍግታ ስላለው ወደላይ በመጠኑ ይወጣል። በአካባቢው ብዙ ጊዜ ሲወጣ የሚታየው ነዳጅ በቀለጠው አለት ውስጥ ነው የሚፈሰው፤ ያ የሆነው የተሰነጣጠቀ አለት ስላለ ነዳጁ የተወሰነ በዚያ ውስጥ ስለሚፈስ ነው" ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በጉዳይ ጥናት ሰርቶ እንደነበር ተነግሯል፤ የጥናቱ ውጤት ምንድን ነው ? የተፈጥሮ ነዳጁ ምን ያክል ቦታ ይሸፍናል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ በተለያየ ጊዜ መጠናቱን አስረድተዋል። " ምን ያህል ርቀት ላይ ይገኛል? መጠኑ ምን ያህል ነው? የሚለው በእርግጥ ብዙ ዝርዝር ጥናቶች አሉ። ትልቁና ዋናው ቁልፍ ችግር የተፈጥሮ ነዳጁ አከማችቶ የሚይዘው አለት በቅልጥ አለት መሸፈኑ ነው ብዙ ነገሮችን በትክክል እናዳናውቅ ያደረገው። በትንሹ ከ1 ኪሎሜትር የማያንስ ቅልጥ አለት ነው የሸፈነው " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
52 349
4
“በግጭት የተጠረጠሩ 6 ሰዎች እስር ቤት ገብተዋል። ኢታንግ ልዩ ወረዳ ወደ 4 ሰዎች በተፈጠረው ጉዳይ ታስረዋል። ጋምቤላ ወረዳም የታሰሩ ሰዎች አሉ” - አሽኔ አስቲን በጋምቤላ ክልል ጋምቤላና አቦል+1
“በግጭት የተጠረጠሩ 6 ሰዎች እስር ቤት ገብተዋል። ኢታንግ ልዩ ወረዳ ወደ 4 ሰዎች በተፈጠረው ጉዳይ ታስረዋል። ጋምቤላ ወረዳም የታሰሩ ሰዎች አሉ” - አሽኔ አስቲን በጋምቤላ ክልል ጋምቤላና አቦል ወረዳዎች፣ ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢዎች ሰሞኑን በተስተዋለው ጥቃት በርካቶች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን፣ ከዚህ ሳይከፋ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ነዋሪዎቹ እየጠየቁ ነው። "የስልጣን ክፍፍል ኢፍትሃዊ" መሆን፣ "አንድን ብሔረሰብ መጨቆን"፣ "የጸጥታ አካላትም ወደአንድ ብሔር የማድላት ዝንባሌ" ለሰሞንኛው አለመረጋጋት እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሱም ይናገራሉ። የክልሉ ባልጣናት ደግሞ፣ በ“ግጭቱ” የተጠረጠሩ አካላትን “እያነጠርን እርምጃ እየወሰድን” ነው፤ "ግጭቱ የልሂቃን ነው" እያሉ ናቸው። ይህን ካሉት መካከል አንዱ የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ አስቲን ሲሆኑ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ብዙ ጊዜ "እርምጃ እየተወሰደ ነው" ይባላል፣ እርምጃው ምን እንደሆነ ግን በግልጽ አይነገርም፣ ለመሆኑ በምን ያህል አካላት፣ ምን አይነት እርምጃ ተወሰደ? ሲል ጠይቋቸዋል። አቶ አሽኔ አስቲን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ ? “ምን ያህል ሰዎች እርምጃ ተወሰዶባቸው የሚለውን ከፖሊስ መረጃ መውሰድ አለብኝ። ቁጥሩ ይሄ ነው ለማለት ለመግለጽ ይከብዳል። ለምሳሌ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የተጠረጠሩ ተይዘው እስርቤት ገብተዋል። በተፈጠረው ግጭት የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች እስርቤት ገብተዋል። ኢታንግ ልዩ ወረዳ ወደ አራት ሰዎች በተፈጠረው ጉዳይ ታስረዋል። ጋምቤላ ወረዳም የታሰሩ ሰዎች አሉ። ስለዚህ በእያንዳንዱ ክስተት በሀሳብ የደገፉ የተሳተፉ በምርመራ ተጣርቶ መያዛቸው አይቀርም። የተያዙትን ብዛት ሰዎች ፖሊስ ነው የሚያውቀው፣ የእኛ ድርሻ  ሁኔታውን መከታተል ማህበረሰቡ እንዲያወግዝ፣ ወንጀለኞች እንዲያዙ እንዲያግዝ፣ አንድነት መፍጠር፣ በእንደዚህ አይነት ክስተት እንዳይሳተፍ ማድረግ ነው። ፖሊስ ደግሞ ስራው ወንጀለኞችን ማደን፣ ተጠርጣሪዎችን ከያሉበት ማደንና ማስገባት ነው” ብለዋል። የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን በበኩሉ፣ በጋምቤላና ላሬ ወረዳ ህዳር 30 እና ታህሳስ 3/2018 ዓ/ም በነበረው ጥቃት የተጠረጠሩ 18 ሰዎች መያዙን አስታውቋል። እርስዎ የግጭቱ መንስኤ "የአመለካከት ችግር" እንደሆነ ገልጸዋል፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ በብሔረሰቦች መካከል ያለው “የስልጣን ክፍፍል” ፍትሃዊ አለመሆን፣ "የጸጥታ አካላት ወደ አንድ ብሔር የማድላት ዝንባሌ”፤ "በተወሰኑ ብሄረሰቦች የሚያሳድሩት አላስፈላጊ ተፅዕኖ' እንዳለ ነው፤ ጉዳዩን በዚህ ረገድ ገምግማችሁት ነበር? ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው? የሚል ተጨማሪ ጥያቄ ለአቶ አሽኔ አቅርቧል። አቶ አሽኔ በምላሻቸው ፦ " በውይይቱ ላይ የተነሱ ጉዳዮች አሉ፤ ነገር ግን 'የስልጣን ክፍፍል ነው ወደግጭት የወሰደን' በሚል የተነሳ ጉዳይ የለም። ምክንያቱም የክልሉ ስልጣን ከ40 በመቶ በላይ የኑዌር ብሔረሰብ የክልሉ ወንበር አለው። አኙዋ ብሔረሰብ 39 በመቶ ናቸው። ፕሬዚዳንት ከአኙዋ ነው፤ ምክትሉ ከኑዌር ነው። ትልቁ ችግር የአኙዋ ልሂቃን 'የክልሉ ባለቤቶች፣ ነባሮቹ እኛ ነን፣ ኑዋር ደግሞ ከኋላ የመጣ ነው፣ ስለዚህ ሁሉም ነገር የሚገባን እኛ ነን' የሚል ነው። ይሄን የሚያነሱት ጥቂት የፓለቲካ ልሂቃን ናቸው። ማህበረሰቡ ይህን አያነሳም። ከፋፋይ ፖለቲካ አይከተልም፤ ‘እኔ ብቻ ነኝ’ አይልም። በክልሉ ደግሞ አምስት ነባር ብሄረሰቦች አሉ፤ ሌሎችም አሉ። ከአኙዋ ብሄረሰብም ‘ክልሉ የእኔ ብቻ ነው፤ ለኔ ነው የሚገባኝ’ የሚል አስተሳሰብ የለም። ይሄን የሚያራምዱት ተምረናል፣ ሰልጥነናል የሚሉ ዲያስፖራ ናቸው የሚያራግቡት። ግንዛቤ የሌላቸው የተወሰኑ ወጣቶችም ይሄን ይተገብራሉ። ጥቃት የሚፈጽሙት አብዛኞቹ የተማሩ አይደሉም፣ የሰሙትን ቀጥታ የሚወስዱ፣ አንዳንዱ ከእስር የተፈታ፣ አንዳንዱ ከፖሊስ የተመለሰ፣ አንዳንዱ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ሱሰኞች፤ አንዳንዶቹ ከልሂቃኑ ባለፈ ከስልጣን የወረዱ የከሰሩ እና ያኮረፉ ናቸው።  ሌላው የመሬት ጉዳይ ነው የሚያነሱት፣ 'የእከሌ ብሄር መሬት ወስዷል፣ የአባቶቻችን መሬት ተወስዷል' የሚሉ አሉ። እነዚህ የራሳቸውን ጥቅም ፍለጋ ነው። ክልሉ ወደ ግጭት ገብቶ ሰዎች ተገዳድለው አይደለም። የተወሰኑ ግለሰቦች ናቸው፣ እነዚህም መንግስት እየተከታተለ እስርቤት እያስገባ ተጠያቂ እያደረገ ነው” ብለዋል። ግጭቱ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፤ መቼ ነው የሚቆመው? ለምን ማስቆም አልተቻለም? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ኃላፊው ምን መለሱ? “መቼ ነው የሚቆመው? ለምን አልቆመም? የሚለው ትክክል ነው። በኛ እይታ ቀንሰናል፣ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረው ነው እንጂ፣ ከ2016 መጨረሻ ጀምሮ የአመራር ለውጥ ካደረግን በኋላ ክልሉ ሰላም ነው።  እንደሌላው አካባቢ ትንኮሳ የሚፈጥሩ የተወሰኑ ግለሰቦች አሉ። ስራዎች ሰርተናል፣ ስብሰባዎች አድርገናል ግንዛቤ ፈጥረናል፣ ብዙ እርምጃ ተወስዷል፣ ዋናው ትልቁ ጉዳይ የሚቆሙ ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ያስፈልጋሉ። አንደኛው የህግ የበላይነት ማስከበር ነው፣ ሁለተኛው ማስተማር ነው፣ ሶስተኛው ልማት ነው” ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
145 893
5
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
118 002
6
በተራዘመ ክፍያ ሳምሰንግ ጋላክሲ A16 5G ስማርት ስልክ የግልዎ ያድርጉ! 🗓🤝 በወር 2,930 ብር (ለ12 ወራት) ወይም 5,426 ብር (ለ6 ወራት) ክፍያ ዘመናዊ ስማርት ስልክ የግልዎ ያድርጉ
በተራዘመ ክፍያ ሳምሰንግ ጋላክሲ A16 5G ስማርት ስልክ የግልዎ ያድርጉ! 🗓🤝 በወር 2,930 ብር (ለ12 ወራት) ወይም 5,426 ብር (ለ6 ወራት) ክፍያ ዘመናዊ ስማርት ስልክ  የግልዎ ያድርጉ። 💁‍♂️ በ *127# ወይም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp “ቴሌ ዲቫይስ ፋይናንሲንግ” ሚኒ አፕ ተመዝግበው ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ጎራ ይበሉ! 👉ማሳሰቢያ: የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ብድር ካለብዎ መክፈልዎን አይዘንጉ! ኢትዮ ቴሌኮም ከአዋሽ ባንክ ጋር በአጋርነት #Ethiotelecom  #AwashBank #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
121 595
7
ፎቶ፦ የህንድ 🇮🇳 ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል። ሞዲ 105 ሚሊ+4
ፎቶ፦ የህንድ 🇮🇳 ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል። ሞዲ 105 ሚሊዮን ተከታይ ባላቸው የX ገፃቸውን ላይ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስመልክቶ በአማርኛ ባሰራጩት ፅሁፍ " ኢትዮጵያ ታላቅ ታሪክ እና የደመቀ ባህል ያላት ሀገር ነች። ህንድ እና ኢትዮጵያ ጥልቅ የሆነ የስልጣኔ ትስስርም አላቸው። በተለያየ ዘርፍ ያለንን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ከኢትዮጵያ አመራር ጋር ለመወያየት ተዘጋጅቻለሁ " ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቦሌ ኤርፖርት ከተቀበሏቸው በኋላ፤ ወደ የሳይንስ ሙዚየም በመኪና እንደወሰዷቸው ገልጸዋል። " ይህ ሙዚየም የተለያዩ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎችን እና ለኢትዮጵያ እድገት እንዴት ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ያሳያል " ብለዋል። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ይፋዊ የስራ ጉብኝት የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን የሚያደርጉ ሲሆን ነገ ህዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ፎቶ፦ የጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ የX ገጽ @tikvahethiopia
194 763
8
#MoE #ExitExam ትምህርት ሚኒስቴር በጥር ወር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ይሰጣል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆ+1
#MoE #ExitExam ትምህርት ሚኒስቴር በጥር ወር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ይሰጣል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል። እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈሉበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማቸው ለየትምህርት ክፍላቸው መላክ ይጠበቅባቸዋል። የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት ደግሞ በራሳቸው እንደሆነ ተገልጿል። ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ምዝገባቸውን https://exam.ethernet.edu.et ላይ ማከናወን ይችላሉ። የምዝገባ ሒደቱን የሚያሳይ ቪዲዮ👇 https://youtu.be/C9KkQ9AHd2o Via @tikvahuniversity
253 644
9
አቢሲንያ - የሁሉም ምርጫ! ዕድል እና አጋጣሚዎች ፈጣን ተጠቃሚን ይመርጣሉ! እርስዎም ፈጠን ብለው ተሸላሚ እንዲሆኑ፣ አቢሲንያ ባንክ - ከ ኅዳር 22 እስከ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ “ከአ
አቢሲንያ - የሁሉም ምርጫ! ዕድል እና አጋጣሚዎች ፈጣን ተጠቃሚን ይመርጣሉ! እርስዎም ፈጠን ብለው ተሸላሚ እንዲሆኑ፣ አቢሲንያ ባንክ - ከ ኅዳር 22 እስከ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ - ያድሱ እና ይደጉ” የተሰኘ የሽልማት መርሀ-ግብር ለደንበኞቹ አዘጋጅቷል! ከእርስዎ የሚጠበቀው የባንካችን ቤተሰብ በመሆን፣ በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮቻችን አዲስ ሂሳብ መክፈትና ተቀማጭ ማድረግ ፣ ነባር ሂሳብዎ ላይ ተጨማሪ ገቢ ማድረግ ፣ በፊት ገፅታዎ እና በጣት አሻራዎ የደንበኝነት ምዝገባ ማካሄድ፣ በባንካችን የውጭ ምንዛሬ መመንዘር ወይም ገቢ ማድረግ እንዲሁም ከባንካችን ጋር በአጋርነት ከሚሠሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአቢሲንያ ባንክ በኩል ክፍያ መፈጸም ብቻ ነው! ያን ጊዜ የሚያስሸልሙ ኩፖኖችን ወዲያውኑ ያገኛሉ! እነዚያ ኩፖኖች ደግሞ፦ አዲስ ሀዩንዳይ ኤሰንት መኪና፣ ቲቪና ላፕቶፕ፣ ጨምሮ ሌሎች በየ15 ቀኑ ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና ሌሎችም አጓጊ ሽልማቶችን አሸናፊ ያደርግዎታል፡፡ ያስታውሱ—የብዙ ኩፖኖች መኖር  የሽልማት ዕድልን ይጨምራል ይበሉ ከአቢሲንያ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ! ለበለጠ መረጃ 8397 ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል   አቢሲንያ - የሁሉም ምርጫ!
229 495
10
#USA🇺🇸 ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአዲሱ የአሜሪካ ውሳኔ ተጠቂ ይሆናሉ። አሜሪካ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጧ ይታወሳል። በዚህ ከለላ ስር+1
#USA🇺🇸 ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአዲሱ የአሜሪካ ውሳኔ ተጠቂ ይሆናሉ። አሜሪካ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጧ ይታወሳል። በዚህ ከለላ ስርም 5001 ኢትዮጵያውያን የህግ ከለላ ተሰጥቷቸው እንደነበርና 263 የሚሆኑ ተጨማሪ ዜጎች አመልክተው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል። ጊዜያዊ የህግ ከለላው መቼ ተሰጠ ? አሜሪካ በፈረንጆቹ ታህሳስ 12,2022 በኢትዮጵያ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ለኢትዮጵያ ዜጎች ጊዜያዊ የህግ ከለላ መስጠት የጀመረች ሲሆን በሚያዚያ 2024 ዳግም ተራዝሞ ነበር። የጊዜያዊ የህግ ከለላው ለምን ተነሳ ? አሜሪካ ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ከሚመለከታቸው የራሷ የመንግስት ተቋማት ጋር ንግግር በማድረግ የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ መገምገሙን አንስታለች። በግምገማው የተዳሰሱ ነገሮች፦ - በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለ ግጭት ስለመኖሩ - ይህ ግጭት በመኖሩ ግለሰቦች ቢመለሱ የሚያጋጥማቸው የደህንነት ስጋት ስለመኖሩ - የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዳይመለሱ የሚያደርግ ከአቅም በላይ የሆነና ጊዜያዊ ችግር ስለመኖሩ - የኢትዮጵያ ዜጎች በጊዜያዊነት በአሜሪካ ቢቆዩ የአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም ስለመፃረሩ ከግምገማው በኋላ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እየተካሄደ ያለ ግጭት የተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ስጋት ውስጥ ይከታል የሚለውን መመዘኛ እንደማያሟላ ተቀምጧል። አሜሪካ በ2022 በትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የነበሩ ግጭቶች ይህ የጊዜያዊ ከለላ እንዲሰጥ ምክንያት ነበሩ ስትል የትግራዩ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቋጨቱንና በኦሮሚያም ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አካል ጋር ክልሉ የሰላም ስምምነት መፈራረሙን፣ ታጣቂዎች መግባታቸውንና ከስምምነቱ በኋላ ግጭት መቀነሱንም አንስታለች። አሜሪካ የትግራዩ ጦርነት ሲገባደድ በአማራ ክልል ግጭት መቀስቀሱን ጠቅሳ በመንግስት እና ፋኖ መካከል ያለው ግጭት መቀነሱን ንፁሃን ግን ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩ አንስታለች። አሜሪካ ኢትዮጵያ ትኩረቱን መሰረተ ልማት እና የሰብዓዊ ልማት ግንባታ ላይ ያደረገ የ33.7 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ በጀት ማፅደቋን አንስታ እነዚህ ማሻሻያዎች የተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከት ነገር እንደሌለ ያሳያሉ ብላለች። የውስጥ መፈናቀሎች ቀንሰዋል ያለችው አሜሪካ የምግብ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች መሻሻላቸውን ለዚህም ማሳያው አሜሪካ ራሷ በሰሜን ኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ለጣምራ ኮሚቴ ማስተላለፏን አንስታለች። ከ2022-2025 ድረስ 2147 የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የጉዞ ሰነድ መጠየቃቸውንም በጥሩ ጎን ተመልክቼዋለሁ ብላለች። ከቪዛ ጊዜ በላይ መቆየትን በተመለከተ አሜሪካ ምን አለች ? አሜሪካ በ2024 የኢትዮጵያ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ከቪዛ ጊዜ በላይ የመቆየት ምጣኔ ነበራቸው ብላለች። በዚህም፦ - ለB-1/B-2 ቪዛ የ8.27 በመቶ ከቪዛ ጊዜ በላይ የመቆየት ይህም ከአማካዩ በ250% እንደሚበልጥ - ለF,M እና J ቪዛ የ13.95% የመቆየት ምጣኔና ይህም ከአማካዩ በ330% እንደሚበልጥ እና የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ እንደሆነባትም ጨምራ ገልፃለች። ምን ያህል ሰዎች ከለላው ነበራቸው ? የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ 5001 የኢትዮጵያ ዜጎች ይህ ከለላ ፀድቆላቸው ተጠቃሚ እንደነበሩ ሲገልፅ እንደ ባለፈው ህዳር መረጃ ተጨማሪ 263 ሰዎች ይህንን ከለላ ለማግኘት ጥያቄ አቅርበዋል። #TikvahEthiopiaMagazine Via @tikvahethmagazine
268 142
11
" ወንድማችን ከቤት እንደወጣ እስካሁን አልተመለሰም ! " - ቤተሰቦች አቶ አደራጀው የሺዋስ (ኤዲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዜግነታቸው አሜሪካዊ ናቸው። አዲስ አበባ ከመኖሪያ ቤታቸው እንደወጡ እስካሁን+1
" ወንድማችን ከቤት እንደወጣ እስካሁን አልተመለሰም ! " - ቤተሰቦች አቶ አደራጀው የሺዋስ (ኤዲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዜግነታቸው አሜሪካዊ ናቸው። አዲስ አበባ ከመኖሪያ ቤታቸው እንደወጡ እስካሁን እንዳልተመለሱ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል። " እኛ ቤተሰቦቹ በራሳችን መንገድ ከመፈለግ ባሻገር፤ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማለትም ለአዲስ አበባ ፖሊስ እና ለፌዴራል ፖሊስ አሳውቀናል " ብለዋል። " በፌዴራል ፖሊስ የጠፉ ሰዎች ማፈላለጊያ መተግበሪያ (App) ላይ እንዲመዘገብና እንዲለጠፍ አድርገናል። ከዚህ በተጨማሪም ጉዳዩን ለሚመለከተው የአሜሪካን ኢምባሲ በአካል እና በስልክ አመልክተናል " ሲሉ ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ ግን ምንም አይነት ፍንጭ ሊገኝ እንዳልተቻለ ጠቁመዋል። " ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኖብናል ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የጸጥታ አካላት ወንድማችንን እንድታፋልጉን በትህትና እንጠይቃለን። ከህዝብና ከመንግስት የሚደበቅ የለምና፤ እባካችሁ ያለበትን የምታውቁ ወይም የት እንደታየ ትንሽም ቢሆን ጥቆማ ወይም ፍንጭ ያላችሁ ከታች በተቀመጠው ስልክ በአስቸኳይ አሳውቁን። ለምታደርጉልን ትብብር ሁሉ በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን " ብለዋል። ስልክ ፡ +251920256451 (ቤተሰቦቹ) @tikvahethiopia
245 880
12
" አባታችንን አፋልጉን " 🙏 አባታችን ሹሚ ኢዳ ትላንት እሁድ ታህሳስ 05-2018 ዓ/ም ቀን 9:30 አከባቢ ከወንድማቸው ቤት ወለቴ ማርያም መውጫ ኮንዶሚኒየም በድንገት እንደወጡ አልተመለሱም። ከ
" አባታችንን አፋልጉን " 🙏 አባታችን ሹሚ ኢዳ ትላንት እሁድ ታህሳስ 05-2018 ዓ/ም ቀን 9:30 አከባቢ ከወንድማቸው ቤት ወለቴ ማርያም መውጫ ኮንዶሚኒየም በድንገት እንደወጡ አልተመለሱም። ከቤት ሲወጡ ጋቢ ደርበው ፣ Blueblack መለዮ (ኬፕ)፣ ደብዘዝ ያለ ጌሾአማ ኮት፣ ጠቆር ያለ ሱሪ እና ነጭ ጫማ አድርገው ነበረ። ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀዋል። ያያችኋቸው ወይም ያሉበትን የምታውቁ ካላችሁ በሚከተሉት ስልኮች እንድታሳውቋቸው በእግዚአብሔር ርኅራሄ ተማጽነዋል። ዮሱፍ ሹሚ 0912819540 ናታን ሹሚ 0919409727‌‎ ጉታ ኤዴአ 0912089208 ዳዊት አሰፋ 0900574369 @tikvahethiopia
221 070
13
አፋልጉን 🙏 የ7 ዓመቱ ህፃን ሀበን ካሱ ከአዲስ አበባ፣ ሰሚት 30 ሜትር አካባቢ የጠፋ ሲሆን ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ነው። ህፃን ሀበን ካሱ ትናንት እሁድ፣ 5/4/2018 ዓ.ም፣ ከሰዓት በኋላ ከቤት
አፋልጉን 🙏 የ7 ዓመቱ ህፃን ሀበን ካሱ ከአዲስ አበባ፣ ሰሚት 30 ሜትር አካባቢ የጠፋ ሲሆን ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ነው። ህፃን ሀበን ካሱ ትናንት እሁድ፣ 5/4/2018 ዓ.ም፣ ከሰዓት በኋላ ከቤት ከወጣ በኋላ እንዳልተመለሰ ቤተሰቦቹ አሳውቀዋል። የሀበን ወላጆች ልጃቸው በመጥፋቱ ከፍተኛ የልብ ስብራት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸው፣ የህዝቡን እና የመገናኛ ብዙኃንን እርዳታ በአስቸኳይ ጠይቀዋል። ህጻኑ መልኩ ጠይም ሲሆን የለበሰው ልብስ፡ ባለ ኮፊያ ሁዲ (Hoodie) ነው። ወላጅ እናት “እባካችሁ ማንኛውም ፍንጭ ያገኛችሁ ሰዎች በፈጣሪ ስም አፋልጉን!” ብለዋል። ስልክ ፦ ➡️ 0911 684 713 ➡️ 0911 651 991 ➡️ 0901 083 827 @tikvahethiopia
209 279
14
‎" ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ይዘጋሉ፤ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለበሽታዉ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ጥለናል" - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ‎ ‎በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወ+1
‎" ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ይዘጋሉ፤ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለበሽታዉ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ጥለናል" - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ‎ ‎በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በማርበርግ ቫይረስ ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሕዝብ የሚሰበሰብባቸዉ የትራንስፖርት እና የመዝናኛ ቦታዎች ላይ ዕገዳ መጣሉን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡመር ኖኩዌ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎በአከባቢው አንድ ሰዉ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ዉሳኔው መተላለፉን የገለፁት ምክትል አስተዳዳሪዉ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ግብረሃይል ተወያይቶ ዉሳኔ ማስተላለፉን ገልፀዋል። ‎ ‎በዚህም መሠረት በወረዳዉ የሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዕገዳና ክልከላ መጣሉን አቶ ኡመር ገልፀዋል። ‎ ‎በዚህም መሰረት ፦ ‎ ‎➡️ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው ይቆያሉ፤ ‎➡️ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡና የሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችም ከአሽከርካሪው ውጪ ሁለተኛ ሰው ላልተወሰነ ጊዜ መጫን አይችሉም፤ ‎➡️ ሰርግ፣ ምረቃ፣ ድግስና በሀዘንም ህዝብ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ሁኔታዎችም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆሙና ቀብር በጤና ባለሙያዎች ስምሪት ብቻ እንዲከናወን፤ ‎➡️ ዲ ኤስ ቲቭ (Dstv) ጨምሮ ፑል ቤቶች፤ ቤቲንግ ቤቶች እንዲሁም የምሽት ዳንስ ቤቶች፣ ጫት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩ፤ ‎➡️ ሰዎች በቡድንና በብዛት የሚሳተፉባቸዉ ማንኛውም አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች በወረዳዉ እንዳይካሄዱ ዉሳኔ መተላለፉን አብራርተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ @tikvahethiopia
249 810
15
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት ተሹሞለታል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ የባንኩ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን በማበራዊ ትስስር ገጹ በመግለጽ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆ+2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት ተሹሞለታል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ የባንኩ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን በማበራዊ ትስስር ገጹ በመግለጽ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞቱን አስፍሯል። ከአዲስ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ ባንኩ አዲስ የቦርድ ሰብሳቢ የተሾመለት ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ታዬ አዲሱ የልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል። በተጨማሪም ዶ/ር ሶፍያ ካሳ፣ ስዩም መኮንን፣  ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ አቶ ሃቢብ መሀመድ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማርታ በለጠ እና ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል የባንኩ የቦርድ አባላት ሆነው ተሰይመዋል። አዲሱ የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ ከቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር እመቤት መለሰ ጋር የስራ ርክክብ በዛሬው ዕለት አከናውነዋል። የቀድሞ የባንኩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ ባንኩን እንዲመሩ በገንዘብ ሚኒስትር በተፃፈ ደብዳቤ የተሾሙት ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነበር። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
257 346
16
የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ። በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙን አሳውቋል።+1
የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ። በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙን አሳውቋል። በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተሰጡ መመሪያዎች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሕግ በተሰጠው የቁጥጥር ስልጣን መሰረት፣ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የተሰረዙ መሆኑን ገልጿል። አገልግሎቱ የፈቃድ ስረዛው አስመልክቶ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ውሳኔው የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ ነው ያለው ሲሆን "ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል" ብሏል። የፈቃድ ስረዛ ውሳኔው የተወሰደው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ በመመስረት መሆኑንም ተጠቁሟል። የሎተሪ አገልግሎት ያወጣው መግለጫ"ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ህገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል" ነው ያለው። አገልግሎቱ ለሚመለከታቸው አካላት ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች : - • ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ ወዲያውኑ ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል። • ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች (Deposit Gateways) አገልግሎት መስጠት ማቆም አለባቸው። • አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ አይቻልም። • ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችን እና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው የማቆየት ግዴታ አለባቸው። • ማስረጃን ማጥፋት፣ መቀየር ወይም ማሸሽ በወንጀል ሕጉ መሰረት ያስቀጣል። ለፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ፔይመንት ኢንስቱርመንት ኢሹወርስ እና ፔይመንት ሲስተም ኦፕሬተሮች: - • ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ የሁሉም የውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ በመሰረዙ፣ በእናንተ በኩል የውርርድ ድርጅቶቹ የሽያጭ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑ እንድታደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል። • የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደ ተቆጣጣሪና አስፈጻሚ አካል በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት፣ ይህን ውሳኔ ከሁሉም መንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር በጥብቅ ይከታተላል። በውሳኔው መሰረት የተላለፈውን መመሪያ የሚጥስ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አሳውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
301 700
17
የመጨረሻው የበሽ ዕጣ የማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል! እድለኞቹ እነማን ይሆኑ? ዛሬ ነገ ሳይሉ እድልዎን ይሞክሩ! ቀጣይ ዕድለኛ እርስዎ ይሆኑ ይሆናል! 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያ
የመጨረሻው የበሽ ዕጣ የማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል! እድለኞቹ እነማን ይሆኑ? ዛሬ ነገ ሳይሉ እድልዎን ይሞክሩ! ቀጣይ ዕድለኛ እርስዎ ይሆኑ ይሆናል! 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ። https://onelink.to/ewsb22 ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ! #SafaricomEthiopia #MPESAsafaricom #furtheraheadtogether #besh
271 696
18
🙏 "በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከእምብርቷ በላይ አልፈን ነው የሰራነው። በጣም ትልቅ እጢ ሲሆን ይጠማዘዛል ተብሎ ባይታሰብም ግን ሁለት ጊዜ ተጠማዞ ነው ያገኘነው" - 19Kg የማህጸን እጢ ያወጣ+2
🙏 "በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከእምብርቷ በላይ አልፈን ነው የሰራነው። በጣም ትልቅ እጢ ሲሆን ይጠማዘዛል ተብሎ ባይታሰብም ግን ሁለት ጊዜ ተጠማዞ ነው ያገኘነው" - 19Kg የማህጸን እጢ ያወጣው ዶክተር ሙሉ የእርግዝና ክትትል ባለማድረጓ፣ ሳይታወቅ ከጽንስ ጋር ተሸክማው የነበረውን 19 ኪሎግራም የማህጸን እጢ ከአንዲት እናት በቀዶ ህክምና ማውጣቱን ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ቀዶ ህክምናውን የሰሩት የማህጸንና ጽንስ ስፓሻሊት ሀኪም፣ በዩኒቨርሲቲው በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚያስተምሩት ዶክተር ጁሃር መሐመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? " እናታችን የመጣችው ከገጠር አካባቢ ነው። ከአንድ ወር በፊት ልጅ የወለደችው ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ጤና ጣቢያ ነው። ግን ከወለደች በኋላ ሆዷ አልሟሸሸም፣ እርግዝና እንዳለ አይነት ሆኖ ተወጥሮ ነበር የሚታየው። ነገር ግን አንዲት እናት ከወለደች በኋላ ማህጸን ተኮማትሮ ወደቦታው ይመለሳል፤ በእርግዝና ወቅት የተወጠረ ሆዷም እየቀነሰ ነው መሄድ ያለበት። የዚችኛዋ እናት ግን ከወለደች በኋላም 30 ቀናት እንዳለ ነው የነበረው። አዋላጅ ነርሷም ሲያየውም ሆዷ አልቀነሰም። እርሷም ህመም ይሰማታል። የቀረ ነገር እንዳለም ተሰማት። ባለሙያውም ጥሩ ባለሙያ ነው ሳላመሰግነው አላልፍም፤ ማህጸኗ ሳይመለስ የቀረ ነው የመሰለው፣ የሚችለውን አድርጎ ካቅሙ በላይ ሲሆን ለወልዲያ አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ጻፈ። መጥታ ሳያት ነፍሰጡር ነበር የምትመስለው፤ ሆዷ እንደተወጠረ ነበር። ከዚያም አልትራሳውንድ ስካን ሰራሁላት። በአልትራሳውንድ ለመለካት የሚያስቸግር፣ ሙሉ ሆዷን ከማህጸን ማስቀመጫው እስከ ሳምባዋ ድረስ የተወጠረ ሆድ ነው የነበራት። ምክንያቱም ከእርግዝናው ጋር አብሮ ያደገ የማህጸን እጢ ነበረባት። በጣም ትልቅ (19Kg) እጢ ነው። ሲታይ ከማህጸን ዘር ፍሬ ማምረቻ የተነሳ ውሃ የቋጠረ እጢ ነበር የሚመስለው። እንደዚህ አይነት ኦፕሬሽኖች መሰራት ያለባቸው ስድስት ሳምንት ከሞላ በኋላ፤ የእርግዝና ጊዜው ካለፈ በኋላ፣ ማህጸን ወደቦታው ከተመለሰ በኋላ ቢሆን ይሻላል ተብሎ ነው የሚመከረው። ግን ሴትዮዋ ስመለከታት ከፍተኛ ህመም ነበራት፤ ሆዷ በጣም ተወጥሮ ነበር፤ የምትመገበው አይስማማትም፤ እስከ ሳምባዋ ስለያዛት ለመመገብም ትቸገር ነበር። ህመም ካስከተለ እጢው የመጠምዘዝ እድል አለው። ግን ደግሞ እጢው የመጠማዘዝ እድል ይኖረዋል ተብሎ የሚታሰበው መጠኑ ከ5 እስከ 10cm ሲሆን ነው። ከዚያ በላይ ከሆነ ይጠመዘዛል ተብሎ አይጠበቅም። ህመሙ ስላለ ስድስት ሳምንት መጠበቅ አልተቻለም። በወለደች በወሯ ኦፕሬሽን ተሰራላት " ብለዋል። በቀዶ ህክምና ወቅት ስላጋጠማቸው ነገር ዶክተር ጁሃር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? " እጢው በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከእምብርቷ በላይ አልፈን ነው የሰራነው። በጣም ትልቅ እጢ ሲሆን ይጠማዘዛል ተብሎ ባይታሰብም ውስጥ ስንገባ ግን ሁለት ጊዜ ተጠማዞ ነው ያገኘነው። ግን በጣም ጥብቅ ያለ መጠማዘዝ አይደለም። ህመሙን ያስከተለባት መጠማዘዙ ነበር። ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ሴትዮዋ እድለኛ የሆነችው ነገር፦ እጢው ሳይፈነዳ ነጥለን ነው በኦፕሬሽን ያወጣንላት። ከወር በፊት ሦስተኛ ልጇን ነው የወለደችው፤ ገና በመውለድ እድሜ ክልል ውስጥ ነች፣ 28 ዓመቷ ነው። በመውለድ እድሜ ያለን ሰው ማህጸኑ ይተዋል፤ ከ50 ዓመት በላይ ሲሆን ግን እንደዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥም ወደ ካንሰር የመቀየር እድል ስለሚኖረው ማህጸን፣ የዘር ፍሬዎች፣ ቱቦዎችም አብረው ይወጣሉ። የሷን ግን እጢ ያለበትን ጎን የማህጸን ቱቦ ማስተላለፊያውን ጨምረን አወጣላት። ምንም ነገር ሳይፈስና ሳይሰራጭ ነው ያወጣንላት። አብዛኛው ሰው እጢው ከወጣ በኋላ በፌስታል የተቋጠረ ነው የመሰለው። ግን የራሱ የእጢው ከረጢት ነው። በራሱ ከረጢት ነው ቋጥረን ያወጣነው። በጣም ትልቅ ስለሆነ ባንዴ አይወጣም፣ ቀስ እያልን እየገፋን አወጣነው። ስንመዝነው ማመን አልቻልንም፤ ሳፋውን ሞልቶ አልፏል። 19 ኪሎ ግራም ነው። እንደዚህ አይነት ገጠመኝ አጋጥሞን አያውቅም። አሁን ታካሚዋ በሙሉ ጤንነት ላይ ነች። ልጇንም እያጠባች ነው። ታህሳስ 1/2018 ነው ቀዶ ጥገና የተሰራላት። ወደቤቷ ሄዳለች። በሁሉ ነገር ሰላም ነች" ብለዋል። የተሰማቸውን ደስታ ስንጠይቃቸውም፦ " ሀኪም ሲኮን ብዙ ነገሮች ያጋጥማሉ፤ የአሁኑ ግን ከሁሉም እርካታው የተለዬ ነው። ስቃዩዋም ብዙ ነበር።  ደስታዋን፣ ልጀዋን ስታጠባ፣ በጤና ስትንቀሳቀስ ከማየት የበለጠ ደስታ የለም። የሰው የሰውን ህመም ወደራሱ አምጥቶ አስተያየት የሚሰጠው አስተያየት ሲሰጥ ሲታይ ያስደስታል። ለካ ከዚህም በላይ በመስራት፣ በተለይ የገጠሩን ማህበረሰብ መድረስ አለብን ያስብላል። የሰው ማበረታታት ጥሩ እንድንሆን ነው የሚያደርገው፤ ለወደፊት ከዚህ በላይ ለመስራት፣ ማህበረሰቡን ለማገልገል ነው የምዘጋጀው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አባበ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
332 351
19
"የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅና አንድ አብሯቸው የነበረ አገልጋይ ተገድለዋል፤ በትክክል ግድያው እንደተፈጸመ አረጋግጠናል" - ቤተክርስቲያኗ "ምዕመናን የተረጋጋ ኑሮ እየቀጠሉ አይደለም በቦታው፣ አገ+1
"የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅና አንድ አብሯቸው የነበረ አገልጋይ ተገድለዋል፤ በትክክል ግድያው እንደተፈጸመ አረጋግጠናል" - ቤተክርስቲያኗ "ምዕመናን የተረጋጋ ኑሮ እየቀጠሉ አይደለም በቦታው፣ አገልጋዩም ይሄ ይከተለኛል ብሎ ከአገልግሎቱ ተቆጥቦ ነው ያለው!" የሆሮጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ ኤዶም ቀሲስ ድጉማ እና ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ የተባሉ አገልጋይ በታጣቂዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸች። በቤተክርስቲያኗ በኃላፊነት ደረጃ የሚገኙ አካል፣ "ሰሞኑን የህዳር ፅዮን በዓል አክብረው ሲመለሱ የነበሩ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅና ሌላ አገልጋይ፣ ሌሎችም በአጠቃላይ አምስት ሰዎች ታግተው ነበር። ሁለቱ ተገድለዋል" ብለዋል። "በትክክል ግድያው እንደተፈጸመ አረጋግጠናል። ሌሎቹን ግን እንደለቀቋቸው ነው የደረሰን መረጃ የሚመላክተው፤ ገዳዮቹ ህገወጥ ታጣቂዎች ናቸው" ያሉት እኚሁ አካል፣ "በአካባቢው ግን አብረዋቸው የሄዱ በርካታ ወጣቶች ነበሩ ወደ አረቶ ማርያም" ሲሉም ገልጸዋል። "ከአረቶ ማርያም ሲመለሱ ነው ሻምቦ አካባቢ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው በህገወጥ ታጣቂዎች የታገቱት። ከብዙ ጥረት በኋላ ሌሎቹን ሲለቋቸው ሁለቱ ግን እንደተገደሉ ነው መረጃው ያለን" ሲሉም ሟቾቹ መጀመሪያ ታግተው እንደነበር አስረድተዋል። ስጋት እንዳላቸው ገልጸውላችሁ ነበር? አካባቢው ምን የተለየ ነገር አለ? ስንል የጠየቅናቸው የቤተክርስቲያኗን አመራር ምን መለሱ ? "በአካባቢው የክርስቲያኖች መገደል እና ሞት አዲስ አይደለም። ለረጅም ጊዜ በርካታ ምዕመናን እና አገልጋዮች ህይወታቸው አልፏል። ባለፈው አንድ አመታት ከስድስት ወራት ግን ምዕራብም ምስራቅ ወለጋም ላይ ቆም ብሎ ነበር። አሁን ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን፣ ትልልቅ ኃላፊነት የተሰጣቸውን አገልጋዮችን በእንዲህ አይነት መልኩ ማጥቃት በጣም ቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የሚከትና አገልጋዩንም ሆነ አማኙን አንገት ያስደፋ አሳዛኝ ክስተት እየተፈጸመ ነው። የኃላፊ፣ የካህናትም የምዕመናን ነፍስ፣ ነፍስ ነፍስ ነው። በተለየ መልኩ እነዚህን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አገልጋዮች ጠብቆ እንዲህ አይነት እርምጃ መውሰዱ መልኩን ቀየር ያደርገዋል። የአካባቢው ታጣቂዎች ናቸው አጥቂዎቹ፤ ይሄ ነው ለማለት የሚያስችል ሁኔታም አይደለም። ብቻ ህገወጥ ታጣቂዎች ናቸው። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እጅግ አዝነናል፣ ጉዳዩንም ከምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ጋር እየተነጋገርን ነው፣ ከሆሮ ጉድሩ ሻምቦ ወለጋ። ሁለቱ ምስራቅ ወለጋም ሆሮ ጉዱሩ ሻምቦንም የብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ናቸው። ጉዳዩን በሪፓርት መልክ ለቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረግን ነው" ብለዋል። ባለፉት አመታት ምን ያክል ምዕመናን ተገድለዋል ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ጥናት ይጠይቃል፤ ምክንያቱም መረጃ የመለዋወጥ እድሉ በጣም የጠበበ ነው፤ የኔትወርክ መቋረጥ፣ አገልጋዮች በፍርሃት ውስጥ መሆን የዶክመንት ልውውጣችን ምቹ አለመሆን " ሲሉ መልሰዋል። " በጥቅሉ ብዙ ምዕመናን ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ብዙ አገልጋዮችም ከሞት ባሻገር በመሰደድ፣ ላልተረጋጋ ኑሮ ተዳርገዋል፣ የሆነው ሆኖ ግን ይሄን ያህል ቁጥር ነው ብሎ ለመግለጽ የተጨበጠ የተሰነደ መረጃ ማቅረብ ይጠበቃል፣ ግን ምዕመናን የተረጋጋ ኑሮ እየቀጠሉ አይደለም በቦታው፣ አገልጋዩም ይሄ ይከተለኛል ብሎ ከአገልግሎቱ ተቆጥቦ ነው ያለው፣ እና በመንግስትም በኩል ልዩ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ይመስለኛል " ሲሉም አክለዋል። " የምዕመንና አማኞች ግድያ፣ እገታ መፈናቀል ተስፋፍቷል ፤ ቤተክርስቲያኗ ምን ጥረት አደረገች ? ጫና ማድረግ አለባት " የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፤ ቤተክርስያኗ እንዲህ አይነት ጥቃት እንዲቆም ምን እያደረገች ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአመራሩ አቅርቧል። የቤተክርስቲያኗ አመራር ምን መለሱ ? " ችግሩ እንደሀገር ያለነው፤ እንዲህ አይነት ነገሮች የጋራ ምክክር፣ ጥረት ይጠይቃሉ። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞቿን የእግዚአብሔር ቃል ከማስተማር ውጭ ምንም ለማድረግ አትመርጥም። ለዜጎች ዋስትና መስጠት ያለበት መንግስት ነው በየትኛውም መልክ። ቤተክርስቲያን ተልኮዋ ሰውን በእግዚአብሔር ቃል ኮትኩታ አሳድጋ የእግዚአብሔር መንግስት ወራሾች ማድረግ፤ ቤተክርስቲያን እንዲያገለግሉ በበጎ ምግባር ላይ እንዲጸኑ ማድረግ እንጂ ከእግዚአብሔርና ከጸሎች ውጭ ጥቃቱን የምትከላከልበት አቅም የላትም። ያሉትን ችግሮች ለመንግስት አቀረብንም አላቀረብን፣ መንግስት ዓይኑ ትልቅ ነው፤ ጆሮውም በሰፊው ይሰማል። የሆነው ሆኖ ግን በአማኝና አገልጋዮች ላይ የሚደርሰውን  ጥቃት በመዋቅራችን በየጊዜው መረጃዎች ያውም በሚስተግር መንገድ ተቀብለን ለሲኖዶስ እናቀርባለን፣ ሲኖዶሱ ለመንግስት አካል ያቀርባል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
334 181
20
#USA 🇺🇸 ከሰሞኑን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ 1 ሚሊዮን ዶላር (156,000,000 ብር በላይ) የሚከፈልበት፣' ጎልደን ካርድ የተሰኘ የጉዞ ማለፊያ ፈቃድ /ቪዛ/ ይፋ አድርገዋል።+1
#USA 🇺🇸 ከሰሞኑን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ 1 ሚሊዮን ዶላር (156,000,000 ብር በላይ) የሚከፈልበት፣' ጎልደን ካርድ የተሰኘ የጉዞ ማለፊያ ፈቃድ /ቪዛ/ ይፋ አድርገዋል። 'ጎልደን ካርድ' ቪዛ፣ ወደ አሜሪካ ለመሄድ ቢያንስ 1 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ለሚችሉ የውጭ አገር ዜጎች የሚሰጥ ነው።  የዚህ ቪዛ አመልካቾች፣ ማመልከቻቸው ከመታየቱ በፊት፣ ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችል፣15 ሺህ ዶላር (ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ) መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በሌላ በኩል፤ አሜሪካ ወደ ሃገሯ ያለ ቪዛ የሚገቡ የወዳጆቿ ሀገራት ጎብኚዎችን የ5 አመት የማህበራዊ ሚዲያ ታሪካቸውን እንዲያሳዩ ለመጠየቅ ማቀዷ ተነግሯል። ሀገሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተግባራቸውን ፣ የኢሜይል አካውንታቸውንና የቤተሰብ ታሪካቸውን ለመጠየቅ አቅዳለች። ባለፉት 5 አመታት የተጠቀሙትን የስልክ ቁጥርና ባለፉት 10 አመታት የተጠቀሟቸውን የኢሜይል አድራሻዎች እንዲያሳውቁ ይጠበቃል። ያለ ቪዛ ወደ አሜሪካ መግባት የሚችሉ የአሜሪካ ወዳጅ ሃገራት መንገደኞች 42 ሲሆኑ  እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ኳታር፣ እስራኤልና ጃፓን ይገኙበታል። በቪዛ ወደ አሜሪካ በሚመጡ ሰዎች ላይ የማህበራዊ ሚዲያ መረጃቸውን እንዲያቀርቡ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል። @tikvahethiopia
325 094