272 337
订阅者
-1924 小时
+3617 天
+1 50830 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
ታኬሂሮ ቶሚያሱ አያክስን ተቀላቀለ !
የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመስመር ተሰላፊ ታኬሂሮ ቶሚያሱ የኔዘርላንዱን ክለብ አያክስ ተቀላቅሏል።
ከአርሰናል ጋር ከተለያየ ወዲህ ያለ ክለብ የነበረው ቶሚያሱ በነፃ ዝውውር አያክስን መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።
ታኬሂሮ ቶሚያሱ አያክስን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ለስድስት ወራት መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
🔥 150❤ 61👍 28👌 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሊቨርፑል ደጋፊዎችን የገጨው ግለሰብ እስራት ተፈረደበት !
ባለፈው ግንቦት ወር የዋንጫ ድላቸውን በማክበር ላይ የነበሩ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ላይ ተሽከርካሪ የነዳው ግለሰብ የፍርድ ውሳኔ አግኝቷል።
ግለሰቡ በርካታ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን በተሽከርካሪ ገጭቶ ጉዳት አድርሶባቸው እንደነበር የሚታወስ ነው።
ይህንንም ተከትሎ ግለሰቡ ጥፋተኛ በተባለበት ወንጀል 21 አመት እና ስድስት ወር እስር እንደተፈረደበት ይፋ ሆኗል።
ግለሰቡ በቅርቡ የቀረበበትን በርካታ ክስ በመቀበል ጥፋተኝነቱን አምኖ ነበር።
❤ 198👍 63🙏 11😢 8🥰 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ኪሊያን ምባፔ የፒኤስጂን ክርክር አሸነፈ !
ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተሰላፊ ኪሊያን ምባፔ ከፒኤስጂ ጋር ሲከራከሩበት የነበረውን የፍርድ ክስ ማሸነፉ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ ፒኤስጂ ለኪሊያን ምባፔ 61 ሚልዮን ዩሮ ቀሪ ክፍያውን እንዲከፍል እንደተፈረደበት ተነግሯል።
በተጨማሪም ፒኤስጂ ክሱን በኪሊያን ምባፔ እንደተሸነፈ በይፋ ድህረገፁ እንዲያሳውቅ ታዟል።
ፒኤሴጂ በይፋዊ ድህረገጹ የሚያሳውቀውን የፍርድቤት ውሳኔ ለአንድ ወር ያህል በፊት ገፁ እንዲያደርግ መመሪያ እንደተሰጠው ተገልጿል።
😁 513❤ 167👍 62👏 27🔥 7😱 6🤬 3😢 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ ልታዘጋጅ ነው !
ሀገራችን ኢትዮጵያ 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ እንድታዘጋጅ መመረጧን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን ለማዘጋጀት ያቀረቡት ጥያቄ በአኖካ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሙሉ ድምፅ በማግኘት ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሁለት አመታት በኋላ የሚደረገውን 5ኛውን የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ታስተናግዳለች።
4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ ውድድር በዚህ ሰዓት በአንጎላ እየተካሄደ ይገኛል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
😁 111❤ 78👏 15🤔 2
Repost from TgId: 1571225671
ለወሳኙ 90 ደቂቃ ጠንካራ ሆኖ የተገነባ።
ለረጅም ጊዜ ከባድ ጨዋታዎችን ለመቋቋም በሚያስችል የውድድር ደረጃ ስፌት እንዲያገለግል የተሰራ።
ማልያ ብቻ፦ 499 ብር
ሙሉ ትጥቅ፦ 999 ብር
📞ደውለው ለማዘዝ!
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣ | +251901138283
🛫በቴሌግራም ለማዘዝ
https://t.me/m/RbKNbQGCNjI0
❤ 43
照片不可用在 Telegram 中显示
“ ዩናይትድ እንድለቅ ፈልጎ ነበር “ ብሩኖ ፈርናንዴዝ
“ ያንን ማወቄ በጣም ጎድቶኝ ነበር “
የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ክለቡ ባለፈው ክረምት ለአል ሂላል ሊሸጠው ፈልጎ እንደነበር ተናግሯል።
“ ዩናይትድ ሊሸጠኝ ፈልጎ ነበር “ ያለው ፈርናንዴዝ “ ነገርግን እኔ ውድቅ አድርጌዋለሁ በቤተሰብ ምክንያት እና ለክለቡ ባለኝ ፍቅር ለመቆየት ወስኛለሁ “ብሏል።
“ ክለቡ ብትለቅም ለእኛ መጥፎ አይደለም አይነት ሀሳብ እንደነበረው ተሰምቶኛል “ ሲል ፈርናንዴዝ ተናግሯል።
“ ይሄ በጣም ጎድቶኛ በጣም አዝኛለሁ “ ያለው ተጨዋቹ አሳዝኖኛል ምክንያቱም የሚተቹበት ነገር አልነበራቸውም ሁልጊዜ ዝግጁ ነኝ ያለኝን ሁሉ እሰጣለሁ ሲል ገልጿል።
“ ቀጥሎም በዙሪያህ ለክለቡ ዋጋ የማይሰጡ እና ለክለቡ በተመሳሳይ መንገድ የማይከላከሉ ተጨዋቾችን ስታይ ሀዘን ይሰማሀል “ ፈርናንዴዝ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ጠንካራ ሀሳብ ያነሳበትን አስተያየት የሰጠው በብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት ሰዓት በፖርቹጋል ነበር።
ይሁን እንጂ ቃለ ምልልሱ ከትላንቱ የበርንማውዝ ጨዋታ በኋላ ለህዝብ እይታ መቅረቡ ተገልጿል።
❤ 402😁 107😢 62👍 23👎 6
照片不可用在 Telegram 中显示
ዳን በርን ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !
የኒውካስል ዩናይትዱ ተከላካይ ዳን በርን በሳምንቱ መጨረሻ በጎን አጥንቱ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ነበር።
ተጨዋቹ ከጉዳቱ በኋላ ለመተንፈስ በመቸገሩ ምክንያትም ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር ይታወቃል።
ዳን በርን በጨዋታው የጎድን አጥንት ጉዳት እና የሳንባ ችግር እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ኤዲ ሀው አረጋግጠዋል።
ይህንንም ተከትሎ ዳን በርን እስከ ስድስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኙ አሳውቀዋል።
“ እሱ ባለፉት ሳምንታት ምርጥ ሆኖ ነበር ለእኛ ትልቅ ማጣት ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ተናግረዋል።
❤ 79😢 35👎 5👍 2👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ቶተንሀም የሲቲን ሀላፊ ሊቀጥር ነው !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የማንችስተር ሲቲውን ስራ አስፈፃሚ ራፊ ሞርሰን ለመቀጠር ንግግር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ቶተንሀም ሀላፊውን የክለቡ እግርኳስ ኦፕሬሽን የበላይ ሀላፊ አድርጎ እንደሚሾም ተነግሯል።
አሁን ላይ ስምምነቱ ባይጠናቀቅም በቀጣይ ሙሉ ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ሀላፊው ኦማር ቤራዳ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ካመሩ በኋላ በዝውውር ድርድር ላይ የማንችስተር ሲቲውከስፖርቲንግ ዳይሬክተር ቲኪ ቤግርስቴን ሲያግዙ ነበር።
❤ 137😁 25👍 8👎 5🤔 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ሴስክ ፋብሪጋስ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው !
የጣልያኑ ክለብ ኮሞ ዋና አሰልጣኝ ሴስክ ፋብሪጋስ በማህበራዊ ሚዲያው ከሴኔጋላዊያን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
ሴኔጋላዊው የኮሞ ተጨዋች አሳኔ ዲያኦ መጎዳቱን ተከትሎ ሴኔጋላዊያን አሰልጣኝ ሴስክ ፋብሪጋስን ተጠያቂ አድርገዋል።
ተጨዋቹ ኮሞ ትላንት ምሽት በሮማ በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት የገጠመው ሲሆን ከአፍሪካ ዋንጫው ውጪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ተጨዋቹ ከጉዳት የተመለሰ ሲሆን ለሮማ ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ እንደሆነም ተነግሮ ነበር።
አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ ተጨዋቹ ለስምንት ወራት ብዙም እንዳልተጫወተ እና ጉዳት እያስቸገረው ስለሆነ እንዳይጠራ ጠይቀው እንደነበር ገልጸዋል።
ከሴኔጋል አሰልጣኝ ጋር የነበራቸው ንግግር “ ጥሩ አልነበረም “ ያሉት ፋብሪጋስ አሁን ካልመጣ ለአለም ዋንጫ አንጠራውም ብለውኛል “ ሲሉ ገልጸዋል።
አክለው “ ዛሬ መጫወት አልነበረበትም ይሆናል ነገርግን ለሳምንታት ስለማይኖር ነው ያሰለፍኩት ደሞዝ እንከፍለዋለን ትንሽ ይጫወት ብለን ነው “ብለዋል።
አሁን ላይ አሰልጣኙ በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በርካታ የተቃውሞ መልክት በማስተናገድ ላይ ናቸው።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 183🤬 40😁 28👎 26👍 12👏 5🤔 2🤩 1
照片不可用在 Telegram 中显示
በአፍሪካ ዋንጫው ደጋፊዎች ምን ተከተለከሉ ?
ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ሲያመሩ ይዘው መግባት የማይችሏቸው ነገሮች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሰረት :-
- ተንቀሳቃሽ መብራቶች ( laser pointers )
- ተሰባሪ ጠርሙሶች
- የጦር መሳሪያዎች እና ተቀጣጣይ ርችቶች ( Fireworks ) ስታዲየም ይዞ መግባት የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም የአልኮል መጠጥ ፤ ሲጋራ እንዲሁም አፀያፊ እና ተገቢ ያልሆኑ የፅሁፍ መልዕክቶችን ማሳየት በጥብቅ ተከልክለዋል።
እንዲሁም እንሰሳት ፤ ትልቅ አርማዎች ፤ ፕሮፌሽናል ካሜራዎች እና ኳስ ከተከለከሉት ውስጥ ይጠቀሳሉ።
የአፍሪካ ዋንጫው በሞሮኮ ዘጠኝ ከተሞች የፊታችን እሁድ መካሄድ ይጀመራል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 303👍 53😁 11👎 4
照片不可用在 Telegram 中显示
የትኞቹ ክለቦች ብዙ ተጨዋቾች ያጣሉ ?
የ 2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከቀናት በኋላ ሲካሄድ ተጨዋቾች ብሔራዊ ቡድናቸውን በመቀላቀል ላይ ናቸው።
ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 3️⃣4️⃣ ተጨዋቾች ክለባቸውን በመልቀቅ ለአህጉሪቱ ትልቅ ድግስ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሰንደርላንድ 6️⃣ ተጨዋቾች በመልቀቅ በርካታ ተጨዋቾቹ ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያመሩበት ቀዳሚው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ነው።
አርሰናል ፣ ቼልሲ ፣ ኒውካስል ፣ በርንማውዝ እና ሊድስ በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ምንም ተጨዋች የማያጡ ክለቦች ናቸው።
እነማን ብዙ ተጨዋች ያጣሉ ?
- ሰንደርላንድ :- 6️⃣ ተጨዋቾች
- ማንችስተር ዩናይትድ :- 3️⃣ ተጨዋቾች
- ፉልሀም :- 3️⃣ ተጨዋቾች
- በርንሌይ :- 3️⃣ ተጨዋቾች
- ማንችስተር ሲቲ ፣ ቶተንሀም ፣ ዌስትሀም ፣ ኖቲንግሃም ፣ ብሬንትፎርድ ፣ዎልቭስ ፣ ክሪስታል ፓላስ ፣ ኤቨርተን :- 2️⃣ ተጨዋቾች
- ሊቨርፑል ፣ አስቶን ቪላ ፣ ብራይተን :- 1️⃣ ተጨዋች
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 208👍 93😁 21👏 3😢 3🥰 2
照片不可用在 Telegram 中显示
“ በጣም ተበሳጭተናል “ ሩበን አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከጨዋታው በኋላ መበሳጨታቸውን ተናግረዋል።
“ ተበሳጭቻለሁ ሁላችንንም ይሄ ነው የሚሰማን “ ያሉት አሰልጣኙ ጨዋታውን የተሸነፍነው በመጀመሪያው አጋማሽ ነው በሁለተኛው አይደለም ብለዋል።
አክለውም “ ነጥቦች እያጣን የምንገኘው በአጨዋወታችን ምክንያት አይደለም በጥቃቅን ነገሮች ምክንያት ነው “ ሲሉ አስረድተዋል።
“ በሜዳችን ካደረግናቸው ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች የዛሬው እንቅስቃሴ የተለየ ነው ፤ ድል ሳይሆን ንዴት ነው ያለው ነገርግን እንቅስቃሴው የተለየ ነው።"ሩበን አሞሪም
❤ 474😁 324👍 29👎 21🤩 11👏 8🤬 2
照片不可用在 Telegram 中显示
“ የአመቱ ምርጥ ጨዋታ ነው “ ጄሚ ካራጋር
የቀድሞ እንግሊዛዊ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራጋር የምሽቱን ጨዋታ የአመቱ ምርጥ ጨዋታ ሲል ገልፆታል።
“ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመቱን ምርጥ ጨዋታ ነው ያየነው “ ሲል ጄሚ ካራጋር ተናግሯል።
አክሎም “ አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድ የተለየ ነበር፤ የመጀመሪያ ደቂቃ የድሮውን ጊዜ ያስታወሱ ናቸው “ ሲል ተደምጧል።
🥰 244❤ 126😁 92👍 23👎 19💯 14🔥 6👏 5
ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቷል !
በፕሪሚየር ሊግ መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ4 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
የማንችስተር ዩናይትድን ግቦች አማድ ዲያሎ ፣ ካሴሚሮ ፤ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ማቲውስ ኩንያ አስቆጥረዋል።
የበርንማዝን ግቦች ሴሜኒዮ ፣ ኢቫኒልሰን ፣ ታቬርኔር እና ክሩፒ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
6️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 26 ነጥብ
1️⃣3️⃣ በርንማውዝ :- 21 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዳሜ - በርንማውዝ ከ በርንሌይ
እሁድ - አስቶንቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
😁 345❤ 188👎 45👍 28🔥 10😱 5😢 5
照片不可用在 Telegram 中显示
90+1
ማንችስተር ዩናይትድ 4 - 4 በርንማውዝ
⚽ አማድ ዲያሎ ⚽ ሴሜኒዮ
⚽ ካሴሚሮ ⚽ ኢቫኒልሰን
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ታቬርኔር
⚽ ኩንያ ⚽ ክሩፒ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
😁 146❤ 34👎 24👍 20😢 11👏 5🔥 3🥰 1
照片不可用在 Telegram 中显示
53'
ማንችስተር ዩናይትድ 4 - 4 በርንማውዝ
⚽ አማድ ዲያሎ ⚽ ሴሜኒዮ
⚽ ካሴሚሮ ⚽ ኢቫኒልሰን
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ታቬርኔር
⚽ ኩንያ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
😁 208❤ 41👎 23🤬 9😢 7🤩 4👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
78'
ማንችስተር ዩናይትድ 4 - 3 በርንማውዝ
⚽ አማድ ዲያሎ ⚽ ሴሜኒዮ
⚽ ካሴሚሮ ⚽ ኢቫኒልሰን
⚽ ፈርናንዴዝ ⚽ ታቬርኔር
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 115🔥 22🤔 14👎 7👍 6👏 5😁 5😱 5
照片不可用在 Telegram 中显示
'
ማንችስተር ዩናይትድ 3 - 3 በርንማውዝ
⚽ አማድ ዲያሎ ⚽ ሴሜኒዮ
⚽ ካሴሚሮ ⚽ ኢቫኒልሰን
⚽ ታቬርኔር
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 91🔥 19👍 7👎 6🤔 1
照片不可用在 Telegram 中显示
70 '
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 3 በርንማውዝ
⚽ አማድ ዲያሎ ⚽ ሴሜኒዮ
⚽ ካሴሚሮ ⚽ ኢቫኒልሰን
⚽ ታቬርኔር
@tikvahethsport @kidusyoftahe
😁 62❤ 14👎 5👍 4
照片不可用在 Telegram 中显示
64 '
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 3 በርንማውዝ
⚽ አማድ ዲያሎ ⚽ ሴሜኒዮ
⚽ ካሴሚሮ ⚽ ኢቫኒልሰን
⚽ ታቬርኔር
@tikvahethsport @kidusyoftahe
😁 61❤ 12👎 9👏 8😱 3😢 3
