ar
Feedback
መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿

መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿

الذهاب إلى القناة على Telegram

☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ። ☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ አየር ጤና እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን 📞#0918834904 📞#0915310455 መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan

إظهار المزيد
119 968
المشتركون
-17824 ساعات
-1 0237 أيام
-4 79730 أيام
أرشيف المشاركات
#ከህይወት_ውጣ_ውረድ_ልፋት_እና_እንግልት_ለመዳን_የእግዚአብሔር_ጥበብ_ተጠቀሙ !!! #የህይወት_መሰናክል_ገጥሞዎታል?? #የትዳር   መሰናክል #የስራ    መሰናክል #የእቅድ መሰናክል #የኑሮ   መሰናክል #የሀብት መሰናክል #የጤና   መሰናክል ✅ለዚሁሉ ችግር ክፉው የዓይነጥላ መንፈስ ነው እያንዳንዱን በዝርዝር እናያለን፦ ✅የትዳር መሰናክል ፦መልክ አቋም ቁንጅና ፀባይ ሳይጎልብን  ወንዱ እየጠየቀ መመለስ ጎደኝነት ጀምሮ ማቋረጥ  አንድቀን አግኝቶ መጥፋት ✅የስራ መሰናክል፦ ማንኛውንም ስራ አቅደን እንሰራለን ብለን ወሰነን አለመሳካት ስራው ተጀምሮ መቆም ፍፃሜው አለማማር። ✅የእቅድ መሰናክል፦ የአቀድ ነው እቅድ መፍረስ የጀመርነው አለመሳካት ወይም ተጀምሮ መበላሸት  መቋረጥ  ነው። ✅የኑሮ መሰናክል ፦እንደሰው እየለፉ እየደከሙ ከሰው በታች ሁኖ መኖር እንደልፋት አለመኖር (የድካምን) አለማግኘት  የኑሮ ማሽቆልቆል  ወደታች መወረድ ድህነት የዓይነ ጥላመንፈስ በተፈጥሮው ምቀኛና ቅናተኛ ስለሆነ የማይዘጋው እድል የለም ⏩የዓይነጥላ ምልክቶች ፦ ??#ትዳር ማስጠላት 💚#ጓደኝነት ጀምሮ  መለያየት 💚#እራስን ዝቅ አድርጎ ማሰብ (የበታችነት ስሜት ) 💚#ተስፋ መቁረጥ ??#ፀባይ መቀያየር 💚#ወንድ ልጅን ማፈር 💚#ባል እየመጣ መመለስ 💚#ግለ ወሲብ ተጠቃሚ መሆን 💚#ህልመ ሌሊት 💚#እራስን መደበቅ ??#ሱሰኛ መሆን 💚#የእድል መዘጋጋት 💛#የወር አበባ መዛባት 💛#የፅንስ አለመርጋት 💛#ማስወረድ (አቦርሽን ) 💛#ማስለቀስ፣መጨናነቅ ??#ቤተሰብ ማስጠላት 💛#ስራ ማስጠላት 💛#ከፍቅር አጋር ጋር ፆታዊ ግንኙነት ማስጠላት ??#ከፍተኛ የራስ ህመም 💛#ተኝቶ መቃዠት 💛#ፍርሐት 💛#ከፍተኛ ላብ ❤#የጠረን መቀየር ❤#መጥፎ የአፍ ጠረን ❤#በሰው መሐል ሐሳብን አለመግለፅ ❤#በስራ ቦታ የስራ እድገት ማጣት ❤#ከስራ መባረር ❤#ከስራ ባልደረባ ጋር አለመስማማት የዓይነጥላ ምልክቶች ናቸው። #የገርግር_መንፈስ_ተፅኖና_አላማው 🔺የሚመጣልንን ትዳር መመለስ 🔺የሚመጣልንን ገንዘብ መመለስ 🔺የውጭ እድል መመለስ 🔺ከሰው ጋር እንዳንግባባ መገርገር 🔺ልጅ እንዳንወል  መገርገር 🔺ፈተናላይ ልባችን ማሸበር 🔺ፈተና ላይ የምናውቀውን ማስረሳት 🔺ገብያ ስንሰራ መዝጋት መገርገር...     #መፍትሔ_ዓይነ_ጥላ ይህንን መፍትሔ የማቀርብላችሁ በያላችሁበት እንድትጠቀሙበት እንጂ መፍትሄው ይሄ ብቻ ሆኖ አደለም እፅዋቶችን በምትጠቀሙበት ስአት ከቻላችሁ #መዝሙረ_ዳዊት - መዝ፦ 7፣12፣22፣23፣34፣56፣72 ...... አብራችሁ ለመፀለይ ሞክሩ እጅግ በጣም ይረዳችኋል ። #የጊዜዋ ስርና ቅጠል ከ፯ ላይ ቀጥፎ አድርቆ የአጋም ስሩን ከ፯ ላይ ነቅሎ አድርቆ ወቅጦ ሁለቱን በአንድ ለ፯ ቀን ማታ ማታ እየታጠኑ ቢተኙ አይነ ጥላ  ይለቃል። እድሉ አልቃና ላለሰው ስራ ለገረገረው #የጉፋ ተቀፅላ #የዋርካ ተቀፅላ #የፍየለፈጅ ፍሬ ፯ #የምሳና ተቀፅላ #በቅባቅዱስ አንግሶ ከትቦ በኪስ መያዝ ❎ትዳሩን ለገረገረው ሰው የጎበዝ ጠቀስ አበባ ለቅሞ በቅባቅዱስ በሜሮን ፍታዘወልድን ፯ ጊዜ ደግሞ እየተቀቡ ቢወጡት ትዳር ይከፍታል ❎ገንዘብ አልበረክትለት ላለሰው 👉የከርመድ ተቀፅላ ካልተገኘ እንጨቱን በኪስ መያዝ በቤት ማስቀመጥ ወሳኝ መፍትሔ ነው ትጠቀማላችህ። #አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ... #አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት  እንገኛለን 👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት  ለበለጠ መረጃ (ሐሳብ አስተያየትዎን) 📞0918834904 📞0915310455 ይደውሉልን ‼️ማስጠንቀቂያ የምፅፈውን ኮፒ በማድረግና አስመስለው ፔጅ በመክፈት በአካውንት ብር አስገቡ እያሉ የሚያጭበረብሩ ሌቦች አሉ የሽማግሌ ድምፅ በማስመሰል ያጭበረብራሉ ብዙዎች ዘመናዊ ተማሪዎች ናቸው እባካችሁ ተጠንቀቁ በጣም ብዙሰው ተዘርፏል ‼️ ።።።።።። ጥበብን መጠቀም ብልህነት ነው ።።።።።
إظهار الكل...
9👍 1
ጸሎት ፡ በእንተ ፡ መፍትሔ ፡ ሃብት ። በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ ፡ አምላክ ፡ ጸሎት ፡ በእንተ ፡ መፍትሔ ፡ ሃብት ፡ ወግርማ ፡ ወጸሎተ ፡ ድንጋፄ ፡ አአትብ ፡ ገጽየ ፡ ወኲለንታየ ፡ በትእምርተ ፡ መስቀል ፡ በስመ ፡ ሥላሴ ፡ በእንተ ፡ ማዕሠረ ፡ አጋንንት ፡ ወሰይጣናት ፡ ወግርማ ፡ ሞገስ ፡ ከመ ፡ አቡነ ፡ ዳዊት ፡ ወሰሎሞን ፡ በርሃ ፡ በርሃ ፡ በርሃ ፡ በርሃ ፡ በርሃ ፡ በርሃ ፡ በርሃ ፡ ጨ ፡ ጨ ፡ ጨ ፡ ጨ ፡ ጨ ፡ ጨ ፡ ጨ ፡ ሟ ፡ ሟ ፡ ሟ ፡ ሟ ፡ ሟ ፡ ሟ ፡ ሟ ፡ ዮ ፡ ዮ ፡ ዮ ፡ ዮ ፡ ዮ ፡ ዮ ፡ ዮ ፡ ገይሙት ፡ ገይሙት ፡ ያጥብሐል ፡ ፯ ፡ ፌ ፡ ፯ ፡ ዮፍታሔ ፡ በዝንቱ ፡ ግብርከ ፡ ወበኃይለ ፡ ዝንቱ ፡ አስማቲከ ፡ ፍታሕ ፡ ማዕሰረ ፡ እደዊሆሙ ፡ ወአራኀርኀ ፡ ሕሊና ፡ ልቦሙ ፡ ወአደነግጽ ፡ ልቡናሆሙ ፡ ለሰብአ ፡ ሀገር ፡ ወየሀቡኒ ፡ ሃብተ ፡ ወፈኑ ፡ ዘየዓቅቡኒ ፡ መላእክት ፡ መፍቅደ ፡ ልብየ ፡ ሊተ ፡ ለገብርከ ፡ ..................... ፩ ፡ ቅዱስ ፡ ሰንተው ፡ ቀንተው ፡ ቀርነው ፡ ቀርነለው ፡ ሙራኤል ፡ ኃይለ ፡ ግርማሁ ፡ እሳት ፡ ወሞገስ ፡ ፍቅሩ ፡ ጽኑዕ ፡ ወጣዕመ ፡ ነገሩ ፡ ምሉእ ፡ ወሣዕሣዐ ፡ አፉሁ ፡ ጥጡሕ ፡ በእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ንጉሠ ፡ ሰማያት ፡ ወምድር ፡ ዘይሁብ ፡ ሲሣየ ፡ ለኲሉ ፡ ዘሥጋ ። ኃይለ ፡ መስቀሉ ፡ ክቡር ፡ ወፍቅረ ፡ ጸጋሁ ፡ ዓቢይ ፡ ለእግዚእነ ፡ እየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አድናኤል ፡ አድናኤል ፡ አድናኤል ። ኢያኤል ፡ ኢያኤል ፡ ኢያኤል ፡ አስብኤል ፡ አስብኤል ፡ አስብኤል ፡ በእሉ ፡ አስማተ ፡ ቃልከ ፡ ተማኀፀንኩ ፡ መልአከ ፡ ሜምሮስ ፡ ደቡባዊ ፡ ነፋስ ፡ ኃይለ ፡ ድብ ፡ ንጉሥ ፡ ወቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሀበኒ ፡ እግዚኦ ፡ ኃይለ ፡ ወሥልጣነ ፡ ፍቅረ ፡ ወሞገስ ፡ ወሰላመ ፡ በእግዚኦ ፡ ኃይለ ፡ ወሥልጣነ ፡ ፍቅረ ፡ ወሞገሰ ፡ ወሰላመ ፡ በቅድመ ፡ ፀርየ ፡ ወጸላእትየ ። ወበቅድመ ፡ ነገሥት ፡ ወመኳንንት ፡ ከመ ፡ የሀቡኒ ፡ ንዋየ ፡ ዬ ፡ ዬ ፡ ዬ ፡ ፍታሕ ፡ ማዕሠረ ፡ እደዊሆሙ ፡ ወአራኀርኀ ፡ ሕሊና ፡ ልቦሙ ፡ ሊተ ፡ ለገብርከ ..................... መልአከ ፡ ሜምሮስ ፡ ደቡባዊ ፡ ንጉሥ ፡ ደቡባዊ ፡ ነፋስ ፡ ኃይለ ፡ ድብ ፡ ንጉሥ ፡ ፩ ፡ ወልድ ፡ ቅዱስ ፡ ሰንተው ፡ ቀንተው ፡ ቀርነው ፡ ምናቴር ፡ ኃይለ ፡ ግርማሁ ፡ መርዕድ ፡ ወሞገሰ ፡ ስሙ ፡ ዘያስተፌሥሕ ፡ ለትውልደ ፡ ትውልድ ። ወጣዕመ ፡ ከናፍሪሁ ፡ ሐሊብ ፡ ዘያጸግብ ፡ ለኲሉ ፡ ዓለም ፡ ወስብሐተ ፡ ስሙ ፡ ለአምላከ ፡ ሰማይ ፡ ወምድር ፡ ዘይነግሥ ፡ ለቤተ ፡ ያዕቆብ ፡ ለዓለም ፡ ትእምርተ ፡ መስቀሉ ፡ ወነገረ ፡ ጥበቡ ፡ ወፍቅረ ፡ ሰላሙ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ታዖስ ፡ ታዖስ ፡ ታዖስ ፡ አዝዮስ ፡ ፫ ፡ ማስያስ ፡ ፫ ፡ ሔጥ ፡ ፫  ሱሐል ፡ ፫ ፡ ግርማኤል ፡ ፫ ፡ አማሩኤል ፡ ፫ ፡ ዐማኑኤል ፡ ፫ ፡ አምላኪየ፡ሀበኒ፡እግዚኦ፡ኃይለ፡ወሥልጣነ፡ግርማ፡ወሞገሰ፡በቅድመ፡ፀርየ፡ወጸላእትየ፡ወበቅድመ፡ኲሎሙ፡እድ፡ወአንሰ፡ወበኃይለ፡ወቅባዕ፡መልዕልተ፡ርእስየ፡ወኲለንታየ፡ቅብዐ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ጰራቅሊጦስ፡አስተሳልመኒ፡ወአስተፋቅረኒ፡ምስለ፡ኲሎሙ፡ሰብአ፡ሃገር፡ከመ፡የሀቡኒ፡ሀብተ፡ወፈኑ፡ዘየዓቅቡኒ፡መላእክት፡ፍታሕ፡ማእሠረ፡እደዊሆሙ፡ወአራኀርኀ፡ልቦሙ፡ሊተ፡ለገብርከ፡............................. መልአከ ፡ ሜምሮስ ፡ ደቡባዊ ፡ ነፋስ ፡ ኃይለ ፡ ድብ ፡ ንጉሥ ፡ ፩ ፡ ውእቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሰንተው ፡ ቀንተው ፡ ቀርነው ፡ ቀርነለው ፡ አብያቴር ፡ ሰይፈ ፡ መለኮት ፡ ክቡድ ፡ ግርማ ፡ መለኮት ፡ ነድ ፡ ይርእድ ፡ ሞገሰ ፡ ዚአሁ ፡ ወጣዕመ ፡ ልሳኑ ፡ ወሣዕሣዐ ፡ አፉሁ ፡ ፍሡሕ ፡ በቀሐሹን ፡ ፫ ፡ ጊዜ ። አቅመሐሹን ፡ ፫ "፡ ኲሎ ፡ አስማተ ፡ ዘይኴንን ፡ ሞገሰ ፡ መስቀሉ ፡ ምሉእ ፡ ወፍቅረ ፡ መንግሥቱ ፡ ጽኑዕ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ድማሄል ፡ ፫ ፡ አቅማሄል ፡ ፫ ፡ ብርሱ ፡ ባሄል ፡፫ ፡ ባኤል ፡ ፫ ፡ ዘትሁብ ፡ አንተ ፡ ኵሎ ፡ ሠናያተ ፡ ለውሉደ ፡ ሰብእ ፡ በብዝኃ ፡ ጥበብከ ፡ በዝንቱ ፡ ስምከ ፡ ተማኀፀንኩ ፡ ወበዝንቱ ፡ ቃለ ፡ መለኮትከ ፡ ተወከልኩ ፡ ከመ ፡ ተሀበኒ ፡ ዮም ፡ ጥበበ ፡ ወሥልጣነ ፡ ኃይለ ፡ ወመዊአ ፡ አኀድር ፡ በላዕሌየ ፡ ሀብተ ፡ ጸጋ ፡ ወኃይል ፡ ወክብር ፡ ወምላዐሰ ፡ ውስተ ፡ ገጽየ ፡ መንፈሰ ፡ ሰላም ፡ ወከዓው ፡ ሞገሰ ፡ ዘመላእክቲከ ፡ ሥዩማን ፡ ወበዝንቱ ፡ ቃለ ፡ መለኮትከ ፡ ፍታሕ ፡ ማእሠረ ፡ እደዊሆሙ ፡ ወእገሪሆሙ ። ሚጥ ፡ ወአደንግፅ ፡ ልቡናሆሙ ፡ ወአራኀርኀ ፡ ሕሊና ፡ ሥጋሆሙ ፡ አስተፋቅረኒ ፡ ወአስተሳልመኒ ፡ ለእድመለአስት ፡ ወምስለ ፡ ኵሎሙ ፡ ነገሥት ፡ ወመኳንንት ፡ ወሰብአ ፡ ሀገር ፡ ከመ ፡ የሀቡኒ ፡ ንዋየ ፡ እስመ ፡ አንተ ፡ እግዚእየ ፡ ወተስፋየ ፡ ወሞገስየ ፡ የዓለመ ፡ ዓለም አሜን ።
إظهار الكل...
17🥰 5
ከበፊ የቀጠለ ... -        ሸ                 -              Sha ሸ  -  እሼ ፡ ኮሞል ለእውቀት ፍሬውን አዘወትሮ መብላት ነው ። ደሙን ለትምህርት ከሚሆን መድሀኒት ጋር አብረህ ስጥ ወተት ወደ ደም ይቀይራል ። #ሸውሻዊት ባለ ሐረግግዋ አዝዋሪት ናት ለመፍዝዝ የመቃብር አፈር ነስንሰህ ቆርጠህ በአደንግዝ ሐሞት ለውሰህ በቆዳው ሰፍተህ ያዝ ። ሸተሬ ፡ ተ/ ሻል ከሰኮሰ የመለችው ፡ ተ/ #ሸንኮር_አገዳ በግእዝ ሰኮረነቢያት ለሣል አገዳውን ቀቅሎ ማጠጣት ነው ። ሽንጉግ / ጨጎጎት የካህን ቂም / የሞኝ ፍቅር ፩. ለእባጭ ለቁርባ ቀጥቅጠህ ደፍድፈህ እሰር ፪. ለራስ ፍልጠት ቅጠሉን ከወሊትና ከዳማ ከሴ ጋር ደቁሰህ ሲያመው በአፍንጫው ይሳብ ። ፫. ለመስተፋቅር  ደቁሰህ በዘይት ለውሰህ እጅህን ቀብተህ ሰላም በል እንዲሁም ፊትህን በጣዝማ ማር ለውሰህ ቀብተህ ተገናኝ ። ስሙን የሞኝ ፍቅር ወይም የካህን ቂም ይሉታል ። የፍሬው መያዣ ከልብስ ላይ ወይም አልፈው ሲሄዱ ልብሱን ከነካው አይለቀው ። #ሽንጉግ ከጭንጫ ቦታ የሚበቅለው ቅጠሉ ነጭ የመሰለው አጭር ሺንጉግ የሚሉ አሉ ። የውሻ ነጫም የሚሉ አሉ ፡ ቅጠሉ ለቁርባ ለእባጭ ቀጥቅጠህ እሰርለት ይሰበስበዋል ። #ሺብ ዓይኑ ደርሶ ለሚያለቅስ ቅጠሉን ከእንቁላል ጋር ቀላቅሎ መቀባትና በሻሽ አስሮ መተኛት ነው ። #ሺንብሩት የአይጥ ሽንብራም ትባላለች ስሩዋን ቢያላምጡ ፍሬዋን ለቅመው ቢበሉ ብልት ታበረታለች ደም ታጠራለች ፡ እንደሽንብራ በቅላ ትታያለች ከእህል ዘር አይነት ወይም እንደ እህል ዘር ቢዘሩዋት ጥሩ ምርት ይወጣታል ። ሺንብሩት የሚሉት ዛፍ አለ ። ሺንሺና ኻያ ሹንሺና በወንዝ ዳር የሚበቅል ዛፍ ቅጠሉ በክረምት የሚረግፍ ። #ሹሺ  -  ሺሻ በግእዝ እፀከርመድ ፩. ለመስቀል ለመቁጠሪያ ብታስረው ከመናፍቅ ጠብ ይጠብቃል ። ፪. ለመፍትሔ ሐብትና ለሥራይ ቅጠሉን ቅርፍቱን ወቅጠህ በውኃ ዘፍዝፈህ አጥምቅበት ። ፫. ለሆድ ሥራይ ከአቱች ጋር እንደሻይ እያፈላህ አጠጣ ። #ሺነት ፩. ለአስም የገተም የሺነት ቅርፍት ወቅጠህ በማር አቡክተህ በባዶ ሆድ እንደሻይ አጠጣ ። ፪. ለራስ ምታት ቅርፍቱን ከእፀመናሂ ጋር ወቅጠህ በቅቤ አንጥረህ በአፍንጫው ይውሰድ ። ፫. ለፅንስ በማር ቀቅለህ አጠጣ ። ፬. ለፍቅር ቅርፍቱን በሽንት ውሃ ዘፍዝፈህ አቅምስ ። #ሽንኩርት   ፡   ቢጸልቁማ ቀይ ሽንኩርት ፡ ነጭ ሽንኩርት ፡ የጅብ ሽንኩርት የሚባሉ ብዙ ናቸው ። ፩. ነጭ ሽንኩርት የውስጥ አንጀት ህመምን ያስወግዳል ፡ በማር ለውሶ በባዶ ሆድ ይዋጥ ። ፪. የውስጥ የውጭ የእከክ ደዌን በማር ለውሶ አስቀምጦ በባዶ ሆድ አንዳንድ ማንካ ቢወስዱ ይፈውሳል ። ቢያጥወለውለውና ቢያቃጥልም መቻል ነው ። ፫. መንጋጋውን ለሚያመው ጨቅጭቀህ ውኃውን በሚያመው በኩል ያድርግ ወይም ይደፍድፍበት ። ፬. ለሣል በወተት አፈሰልቶ ከሰባት ቀን በላይ ይጠጣ ይፈውሣል ። ፭. ትኩስም ደረቅም እርጥብም ነው ። ሰውነቱ ለበረደ በየጊዜው ከወተት ጋር እያፈላ ወይም ከሽንብራ ጋር ቀቅሎ ይጠጣ ንፍሮውንም ይብላ ደሙን ያጠራለታል ። የደም ግፊትን ያስተካክላል ለብዙ ህመሞች መከላከያና መፈወሻ ነው ። #ቀይ_ሽንኩርት ፩. ለኩላሊት በሽታ በብዙው ቀቅለህ ውኃውን ጧትና ማታ አጠጣው ከአመድማዶ ስር ጋር ቀቅለህ አውዛውን አጠጣው ኩላሊቱ ያስተካክላል ፡ ቆሻሻ ወይም ጠጠር ከአለው ከአልቴት ጋር ቀቅለህ አጥርተህ ስጠው ። ፪. እርጥቡን ቢበሉት የደም ግፊት ይቀንሳል ለጉንፋንም ይበጃል ፡ ጨጓራል ያጠራል ። #የጅብ_ሽንኩርት  ተ/ ? ሺመል የበርሃው ድፍን ቀርክሃ ? #ሺንብራ ፡ ዚፋል ጴርካ አዘውትረው ቢበሉት ደም ያጠራል ። ከወተት ጋር አንፍረው ቢጠጡት ብልት ያበረታህ ። ለሆድ እርጥብ ደረቅ ነው ብቻውን አዘውትረው ቢበሉት ሆድ ያማል ። ሽንብራ ትኩስም ነው በሆድ ያለን ትል / ጀርም ወይም ባክቴሪያ / ያጠፋል ። የንፍሮውን ውኃከአልቴት ጋር ቢጠጡት በኩላሊት ያለን ጠጠር ያወጣል ። ሻሜት ፡ ተ/ ? ሻሚ ፡ ተ/  ? ሻሽ ነጭዛፍ ፡  ? ሾላ ፡ ጰላጢኖስ ፍሬውን ከወተት ጋር ቀቅሎ ቢጠጡት የሆድ ድርቀት ይቀንሳል ። #ሾርባ ቅጠል ለደም ሥሩን ቢጠጡት የወር አበባን ያስተካክላል  ። የሆድ እቃን ሥራ ያቀላጥፋል ፡ እንደልብ ያሸናል ቅጠሉን ከምግብ ጋር ጨምረው ቢበሉት የፊት ቆዳን ያሳምራል ። -         ቀ                 -                   Q ይቀጥላል....
إظهار الكل...
12👍 1👏 1
ከመጽሓ ፡ ዕፀ ፡ ደብዳቤ የተገኙ ፡ መድኃኒቶች ። ፩፣ ለትልቁ ፡ የደዌ ፡ በሽታ ፡ መጀመሪያ ፡ የቊልቋል አበባ ፡ በማር ለውሶ መቅባት ፡ ፪ኛ ያባሎ ፡ ፍሬ ፡ ከእነቅጠሉ ፡ በአንድነት ፡ ወቅጦ መደምደም ፡ ነው ። የሰባውንም የዘንዶ ፡ ስጋ ማብላት ፡ ነው ። ወይም ፡ የጥንቸል ፡ ራስ ፡ ቀቅሎ ፡ በውስጡ ፡ መንከር ፡ ነው ። ፪፤ እግሩ ፡ ለአበጠ ፡ ሰው ፡ ( ከማን ፡ አንሼ) ፡ የዘንዶ ፡ ሞራ ፡ ወይም የዝንጀሮ ፡ ሙርጥ ፡ የአጋዘን ፡ ስብና ፡ የሰጎን ፡ ዕንቊላል ፡ ማሰር ፡ ነው ። ፫ ፡ሽንቱን ፡ ለከለከለው ፡ ሰው ፡ ዝባድ ፡ በቡና ፡ ጨምሮ ፡ ማጠጣት ፡ ወይም ፡ ከሙቅ ፡ ውኃ ፡ ላይ ፡ ማስቀመጥ ነው ። ወይም ፡ እንስላልና ፡ የቲማትም ፡ ቅጠል ፡ አብስሎ ፡ ውኃውን ፡ ማጠጣት ፡ ነው ። ፬ ፡ ጆሮው ፡ የደነቈረ ፡ ሰው ፡ የሰሊጥ ፡ ቅባት ፡ ኑግ ፡ ቅብዐ ፡ ቅዱስ ፡ የፍየል ፡ ቅቤ ፡ የአቱች ፡ ቅጠል ፡ ደቁሶ ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ውኃውን ፡ አዋሕዶ ፡ በቀትር ፡ ፀሓይ ፡ አስተኝቶ ፡ በጆሮው ፡ መጨመር ፡ ነው ። ፭ ፤  የጨብጥ ፡ መድኃኒት ፡ ዋዢብጥ ፡ ክንፋን ፡ እግርዋን ፡ ራሷን ፡ ቁርጦ ፡ ጥሎ ፡ የቀረው ፡ አከላቷና ፡ የምድር ፡ እምቧይ ፡ የአሰርኩሽ ፡ ተበተብሽ ፡ ሥር ፡ ፩ ፡ ላይ ፡ አልሞ ፡ ሰልቆ ፡ በማር ፡ መዋጥ ፡ ነው ፡ ። ጥላ ፡ ተከልከል ፡ የገብስ ጠላ ፡ ጠጣ ፡ ሲያደክመው ፡ ወተት ፡ እና ፡ የደሮ ፡ ጉበት ፡ መስጠት ፡ ነው ፡ ። ፪ኛ  የበልድ በልዶ ፡ ቅጠል ፡ አልሞ ፡ ደቁሶ ፡ በወተት ፡ በጥብጦ ፡ ማጠጣት ፡ ነው ። ፮ ፤ ፅንስ ፡ አጥንት ፡ ለሆነባት ፡ ሴት ፡ የኮክ ፡ ተቀጽላ፡ ባሏ ፡ ቆርጦ ፡ ደቁሶ ፡ በውኃ ፡ አጠጥቶ ፡ ዕለቱን ፡ በሩካቤ ፡ ቢገናኛት ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ ይወለዳል ። ፯ ፤ ለኪንታሮት ፡ የዕፀ ፡ ሳቤቅ ፡ አረግና ፡ የሞይደር ፡ አረግ ፡ የሮቢያው ፡ ሰው ፡ ዕንጨት ፡ ከ፫ቱ ፡ በተገኘው ፡ በአንዱ ፡ አጥብቆ ፡ ቢተኰስ ፡ ቅጽበት ፡ ይድናል ። ፰ ፤ ለእብጠት ፡ አብሽ ፡ ባቄላ ፡ የፍየል ፡ በጠጥ ፡ አልሞ ፡ ፈጭቶ ፡ እንደ ፡ ተልባ ፡ መትቶ ፡ ማሰር ፡ ነው ፡ ጥሬ ፡ ተልባም ፡ አገንፍቶ ፡ ጥሩ ፡ ነው ። ፱ ፤ ለመካን ፡ ሴት ፡ የፈረስ ፡ ወተት ፡ የበቅሎ ፡ ኰቲና ፡ የዝሆን ፡ ጥርስ ፡ ፍቀት ፡ በርግመቷ ፡ ጨምረው ፡ ቢአጠጧት ፡ ትወልዳለች ።
إظهار الكل...
7
በ እ ን ተ ፡ ዓ ይ ነ ፡ ጥ ላ  ። በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ ፡ አምላክ ፡ ጸሎት ፡ በእንተ ፡ ዓይነ ፡ ጥላ ፡ ወዓይነ ፡ ወርቅ  ለመግረሬ ፡ ፀር ፡ ወሾተላይ ፡ እግዚኦ ፡ ሚበዝኁ ፡ እለ ይሣቅዩኒ ፡ ብዙኃን ፡ ዓረብ ፡ ሰፍተህ ፡ ክታቡን ፡ ያዝ ።
إظهار الكل...
1
ከበፊቱየቀጠለ ... - ረ                                 -                               R ሩት ? #ሩዝ - እሩዝ ትኩስ ደረቅ ነው ለሆድ ይቀላል !  ከወተት ጋር ቀቅሎ ቢጠጡት ተቅማጥ ያቆማል ። #ሬት - እሬት  በግዕዝ እፀመሐሪ ወይም እፀማራ - እጉስታር የሬት ዓይነት ብዙም ቢሆን የታወቁት ሴቴው ለስላሣ እሾህ የሌለው ወንዴው እሚወጋ የአለው ናቸው ። ከሴቴው ወንዴው ይመራል ነገር ግን የላዩን ቆዳውን አንስቶ የውስጡን ልቡን መጠቀም ነው ። ፩, የሬት /ልቡ/ ውስጡ ለተለያዩ ለአካላት ደዌዎች ህመሞች ወይም ለቆዳ ድርቀቶች ለአይን መድከም ጧት ጧት ከአብሽ ጋር መጠጣት ወይም ከሰውነት ቅባት ጋር ቀላቅሎ መቀባት ነው ። ፪, ለሚሰነጣጠቅ ለሚደማ ለተጫረ ለቆሰለ ለጭርት ለቋቁቻ ለኩፍኝ ለጠባሳ ጠጉር ለሚረግፍበት ብጫ ልጋጉን አጠራቅመህ ከአደስና ከቅቤ ጋር አቡክተህ ቀባው ። እንዲሁ የውስጡን ልቡን ብላው / አብላው ። ፫, ለስኳር ለአንጀት ድርቀት ለልብ ህመም ለወገብ ህመም ለስብራት ለሐሞት ጠጠር ለኩላሊት ጠጠር ለሆድ ህመም ለጥርስ ለጆሮ ህመም ለቃር ለትውኪያ ህመም ለአእምሮ ጭንቀት ለራስ ህመም ለደም ብዛት ለምች አደር እነዚህን ለመሰሉ ሁሉ የውስጡን ልቡን አውጥተህ ከተቀቀለ ተልባ ውሀ ጋር በማር አዋህደህ ለብዙ ቀን አጠጣው ወይም ከአብሽ ጋር በማር አጠጣው ይፈወሣል ። ፬, ከጆሮ ውስጥ እንደ ትል ለሚላወስበት የሬት ልጋግ የኮክ ፍሬ የላም ሃሞት ከሰሊጥ ዘይት ጋር ለውሰህ አንጥረህ በሻሽ አድርግለት ። ፭, ለኪንታሮት የሬትና የምድር እንቧይ ፍሬ አቃጥለህ ከህመሙ ላይ ደምድመው ። ራማን ራስ አበራ /አበራ/ አፈማህፀንዋ ለቀየረባት ሥሩን ቅጠሉን ወቅጦ በቀዝቃዛ ውኃ ዘፍዝፎ ደጋግማ ትታጠብበት ። #ራስክምር ለምች ቀቅለህ እጠነው ለወስፋት ሳይበዛ ቅጠሉን አጠጣው ሬንጭ ፡ ተ/? ሬንዝ ፡ ተ/? #ርምሣ ለለምጥ ደዌ ከዝግባ ቅጠል ጋር ወቅጠህ ቀባ ። #ሮዝሜሪ ለራስ ህመም ከሎሚ ጋር አፍልቶ መጠጣት ለሥጋ መጥበሻ የሚሆን ቅመም ነው ። #ሮማን ፩, ደም ለሚያስተፋው ፍሬውን ሳይበስል ወቅጠህ አጠጣ ። ለአስም እንዲሁ ስጠው ። ፪, የሮማን ቅርፍትና ጅንጅብል በአንድ ላይ ደቁሰህ በሆድ ነቀርሣ ላለው ደጋግመህ ስጠው ። ፫, አንገቱን ላመመው የሮማን ቅርፍት አብሽ ነጭ ሽንኩርት ነጭ እጣን ከእንኮይ ፍሬ ጋር ወቅጠህ እሰርለት ። ፬, ጥርሱ ለተነቃነቀ የሮማን አበባ ደቁሰህ ከድዱ ላይ ይደምደምበት ወይም አበባውንና የወይራ ቀንበጥ በአንድ ላይ ደቁሶ ይጠቆርበት ። ፭, ሆዱን እያመመ ደም ለሚያስቀምጠው የሮማን ቅርፍት የተምርና የቀረጥ ፍሬ ሂናና ጦስኝ በአንድ ላይ ቀምመህ በቅቤ አንጥረህ አጠጣ ። ፮, ተቅማጥ ላመመው ቅርፍቱንና ፍሬውን እያስፈላ እንደሻይ ይጠጣ ። ፯, ለሚያስተፋው ፍሬውን ወቅጦ በማር ወይም ከዘቢብ ጋር / መብላት ነው / ስጠው ። -  ሸ                            -                          Sha ይቀጥላል ...
إظهار الكل...
9
በተፈጥሮ የሚበቅሉ እፅዋቶችን በምስል መመልከት ለምትሹ 👇👇👇👇👇 http://t.me/merigeta_amedeberha
إظهار الكل...
3
ስቃ፡ ተ/ ? ስቡት፡ ተ/ ? ስንን፡ ተ/ ? ስንደዶ ? #ሰረት በሆዱ ውስጥ ሥራይ ላለበት ቅጠሉን የሮማን የምሳና ቅርፍት የእንቧይ ፍሬ አጥበህ ወቅጠህ በቀይ ጤፍ ቂጣ ግማሽ ማንካ ያህል ጨምረህ አስጋግረህ አብላ ። -        ረ              -              R ይቀጥላል...
إظهار الكل...
7
ከበፊቱ የቀጠለ... S-----------------------         ------------------- ሠሰ   - #ሰሌን   -   ፀመርት ጆሮው ለደነቆረ ፍሬውን ከሰሊጥ ጋር ዘይት አውጥቶ በጆሮው ቢጨምሩበት ደጋግሞ ይከፈትለታል ይሰማል ። #ሰሊጥ  -  አፍላጢስ ፩, ትኩስ ደረቅ እርጥበት አለው፡ ቆልቶ ቢበሉት ጨጓራ ያለሰልሣል ከነጭ ሐሞት የመን እበጥ ይጠፋል ። ፪, ለሣል ለጉሮሮ በሽታ ከወተት ጋር ቅባቱን አፍልቶ መጠጣት ነው ። ፫, ለጆሮ ህመም ዘይቱን በጆሮ ማድረግ ወይም ከአደስ ቅጠል ጋር ለውሶ በራስ ላይ ደፍድፎ ማሰር ጠጉርንም ያሳምራል ። #ሰላቢላ የቆላ የደጋ አለው ! መልኩ ይነስ እንጂ ሴቴውን ቃጫ ይመስላል፡ ትንሹን የዝንጀሮ እመጫት የሚሉትም አሉ። ፩, ጉልበቱን ለሚያመው በቀይ ጤፍ ወይም በጥቁር ገብስ ቂጣ ጋግሮ በወተት እያማጉ ብዙ ቀን መብላት ነው ! ያጠነክራል ቢሄድ አይደክምም ። ፪, ለወገብ በሽታ እንዲሁ በቀይ ጤፍ ወይም በሰመሬታ ገብስ ዱቄት ጋር ገንፎ አድርጎ መብላት ነው ። ፫, የሰላቢላ ስር አዘወትሮ ቢበሉት ፍትወት ይቀንሳል ለነፍሰ ጡር ሴት እንዳትበላው ያስወርዳል ትጠንቀቅ ። ፬, ለሐብት ለፍቅር የሰላቢላን ስር ስትቆርጥ ማርና ወተት አፍሰህ ለዚህ ሁነኝ ብለህ ንቀልና ከማር ጋር አላምጥ በኪስህም ያዝ ፭, ለሐብት ለንግድ ስሩን በሽኮኮ ራስ ውስጥ ከተህ የሽኮኮ ጉመን ቅጠል በአዲስ ሸክላ ራሱን ከተህ ወትፍና በቤትህ ውስጥ ቅበር ። ፮, ለመካን ሴት ወይም ለሚያስወርዳት ከቀጠጥና አበባና ሺል ከተያዘች ከሴት ፍየል ማህፀን ጋር ደቁሰህ በባዶ ሆድዋ ለሰባት ቀን በነጭ ማር አብላት ትወልዳለች ። ፯, ለንብ መሣቢያ ንቡ እንዲበረታ ስሩን ከቁልቋል ተቀጽላ ጋር በቀፎው ሸጉጠው ወይም የቁልቋል ልብ የሰው አጽም የሰላቢላ ስር ንቡን እጠነው የጃርት እሾህና የንብጥራ ቅጠል አብረህ ጨምረህ እጠነው ንቡ ይበረታል ! ማር ያደርጋል ። ፰, ለከሣ ሰው ችምግ ብላ እንደሰላቢላ የምትበቅል የምድር ቁልቋል ጋር ከዶሮ ወይም ከሽኮኮ መረቅ ጋር አብላ ። ፱, ቁመኛ ለያዘው ሰው ስሩን የስረብዙ የሽኮኮ ጉመን የምድር ቅንጭብ ስር ጋር እንደሻይ አጠጣው ወይም በፍየል ሥጋ መረቅ ጋር አጠጣው ። #ስመ_አንፋር ለአኸያ ኪንታሮት ለነቀርሣ ለብሽሮ ከሥር ኩል ጋር በአንድላይ ደቁሰህ በቁስሉ ላይ ብጫ ሌላ ንጹሕ ገላውን ሣታስነካ ደምድመህ የስንዴ ሊጥ በበላዩ አሽገህ በጥጥና በሻሽ ለሶስት ቀን እሰርለት ሲፈነዳ የባቄላ ገለፈትና የዋንዛ ልጥ ደቁሰህ ደምድምበት ወይም ፌጦ ከሬት ልጋግ ጋር ለውሰህ ደምድምበት ። #ሰመቶ_ሰምቾ ቆሽት ያበረታል ! የበሉትን ቶሎ ያጠፋል ! ገላው ለተለወጠና ለፋቀ አዘወትረው ቢወስዱት ይበጃል ። #ሰመግ፦ ሰባት ፍሬ በደምዋ ጊዜ ብትበላ ትመክንአለች ለውጋት ለስብራት ለእባብ ለመርዝ ነገር ሁሉ የሰመግ ስር ቅጠል የእሬት የቀበርቾ ስር የበቀለ ቀንድ እጣን ከርቤ ሁሉንም አክስሎ በቅቤ ለውሶ ተቀብቶ እሳት ይሙቅ ። #ሰረቲ ፩, ለነቀርሣ ስሩን እንጨቱን ከቅንጭ ተቀጽላ ጋር በአንድ ላይ ደቁሶ በቁልቋልና በቅንጭብ ደም ለውሶ ከቁስሉ ላይ ማሰር ነው በእየሶስት ቀን መቀየር ነው ። ፪, ለስኳር በሽታ ስሩን ቅጠሉን ደቁሰህ ከሚበላው ከሚጠጣው ጋር ጨምረህ ስጠው ወይም ከአርማጉሣ / አቆራራጭ/ ጋር ደቁሰህ በማር እየለወስክ አብላውና የተልባ ፍሬ በባዶ ሆዱ ይውሰድበት ፡ ፫, ለመፍትሔ ሐብት ፦ ጸሎተ በእንተ መፍትሔ ሐብት ያረኡፍ ያረፈኡፍ አልመኢዙ አለሐሊሙ አልመናን በኃይለ እሉ አስማቲከ ወበእሉ ቃላቲከ ፈጽሞ ፈቃደ ልብየ ወክስት ሐብትየ በስመ እግዚእነ እየሱስ ክርስቶስ ሊተ ለገብርከ እ/ በሰረቲ ሰርከ መንፈቀ ሌሊት 49 ጊዜ ደግመህ በኪስህ ያዝ ፬, እንቅልፍ ለከለከለው ለደረት ህማም ለሽንት ወተት በሻይ አፍልተህ አጠጣ ለሆድ እርጥብም ደረቅም ነው ። ሰርኪን - ተ? #ሰርዶ - ተ አርባ ቅልጥም ሰርዶ ከሌት ወፍ ሥጋ ጋር ደቁሶ በሽንት ውኃ ለውሶ ቀብቶ ቢገናኝ መስተፍቅር ይሆናል ወይም የተቀመመውን ከሽንቱ ወይም ከሽንትዋ ጋር ቀላቅሎ ቢያስቀምጡት ያፋቅራል በጭሬ ወፍም እንደዚሁ ይሆናል ። #ሰንበታ የጂልዋት ዘር ነው ቢበሉት ኩላሊት ያጠራል ስሩ እንደስኳር ድንች ሆኖ አረጉ እንደ አደንጓሬ አረግ ነው በክረምት ይገኛል ። ስንገላ ብርብራ የመሰለ ለትርፍ አንጀት ቅጠሉን ከሁመር ፍሬ ጋር ዘፍዝፎ መጠጣት ነው ። ሰቃ - ተ/? #ሰናፍጭ ፩, ጆሮው የሆነ ድምፅ ለሚሰማ ከማርና ከቅቤ ጋር አንጥረህ በጆሮው አግባና ወትፈው ፪, ደም ለሚያስቀምጠው ሰናፍጭና አብሽ የሬትና የሎሚ ውኃ በቀይ ጤፍ ገንፎ አድርጎ ከተልባ ጋር መብላት ነው ። ፫, እጁን ለሚቆረጥመው ከቁንዶ በርበሬ ጋር ወቅጠህ በማር አብላው ። ፬, ሰናፍጭ ትኩስ እርጥብ ነው ለሣል ይበጃል ጉሮሮ ያጠራል የዓይን ጠጉርና የቅንድብ ፀጉር ለረገፈ ይኳለው ለአእምሮ ንቃት ጥሩ ነው ። ሰውራ ? ሱማያ ሶማ ሰፋ ሲሃ አንድ ዛፍ ነው ለዘንግ ለብትር ይሆናል ። #ሱፍ ለልብ ደዌ የሱፍ ጭልቃ ለብዙ ግዜ መጠጣት ነው ወይም ከማር ጋር አፍልቆ ጧትና ማታ መጠጣት ነው ። ሢሣ - ተ? #ስንዴ - ሥርናይ ስንዴ እህል ድርቀትና እርጥበት አለው የቦካው ለሆድ ሲቀል ያልቦካው ይከብዳል ። ከአብሽና ከወተት ጋር ቢበሉት ጥሩ ነው ። ቁስል ደዌ ላለው አይሆንም ያበረታበታል ፡ ተቅማጥ ላለው ቂጣውን በቅቤ ለውሶ ይብላ ። #ስረብዙ - ብዙኃሥርው ፩, የስረብዙ የምስርች የፍየለ ፈጂ የአቱች የዶግ የምድር እንቧይ የሥራቸውን የድብርቅ ፍሬና ቅጠል ወቅጠህ በባዶ ሆድ በማር አብላ፡ ለሥራይ ለሣል ላልታወቀ ህመም ሁሉ ይሆናል፡ ይፈታል ። ፪, ለደም ብዛት በማር ለውሰህ ሰባት ቀን አብላ ፫, ለሣል ከጦስኝና ከአቱች ከኮርሺም ቅጠል ጋር እንዘረዘይ ምስንጭር ነጭ ሽንኩርት ጋር በጣዝማ ማር አቡክተህ በቅቤ አንጥረህ አንድ ማንካ ስጥና አቀበት እንዲወጣ አድርግ ያስተፋዋል ። ፬, ለሆድ ደዌ የሥረብዙ የዘንኪላ ስር የድብርቅ ፍሬ በአንድ ላይ ደቁሶ በጣዝማ ማር የኖረ ቅቤ ጨምሮ ጧት ጧት ማብላት ። #ሰረቲ - አርቲ ያሰብከውን ለማግኘት ‛‛ ያረኡፍ  ያረፈኡፍ አልመኢዙ አለሐሊሙ አልመናን በኃይለ እሉ አስማቲከ ፈጽም ፈቃደ ልብየ በስመ እግዚእነ እየሱስ ክርስቶስ ሊተ ለገ/እ/’’ በሰረቲ ስር 49 በመንፈቀ ሌሊት ደግመህ ያዝ #ሣማ  በግእዝ እፀ ኤላም ፩, ለመጽንኤ ስሩን ወቅጠህ በማር ዘፍዝፈህ እንደ ብርዝ አድርገህ ጠጣ፡ ፪, ለመስተፋቅር ስሩን በጧት ሺ/ ውኃ ሰባት ጠብ እያደረጉ ዘፍዝፎ በስቴ አው በመብል ስጥ ፫, ደም ለሚያስተፋው ቅጠሉን በባዶ ሆዱ እየጨመክ አጠጣ #ስልብያ ከዘንጋዳ ከማሽላ መሐል የሚበቅል አረም ነው ፩, ለማንኛውም እብጠት ቅጠሉን ወቅጠህ በሻሽ እሰርለት ፪, ዓይኑ ለቀላና ለታመመ ቅጠሉን በሻሽ ሸፍነህ እሰርለት ፫, ዓይኑ ለፈዘዘ የስልብያ ቅጠል አልቴት የበርበሬ ፍሬ ሁሉን ደቁሰህ በፍየል ሐሞት ለውሰህ ቀባው ፬, ጠጉር ለማብቀል የስልብያ የዋጊኖስ ቅጠል ወቅጠህ በኑግ ዘይት ደፍድፈህ በራሱ እሰርለት ቢቆስልም አይደንግጥ ቁስሉ ሲደርቅ አዲስ ጠጉር ያበቅላል ። #ስሚዛ ወይም ሰልሰል - ሰንሰል ፩, ለአስም ለወፍ በሽታ ቅጠሉን ከሽንቱ ጋር ጨቅጭቆ ግማሽ ማንኪያ ይውሰድ፡ በበነጋታው አንድ ሙሉ ማንኪያ ይጠጣ ። ፪, የስሚዛውን ስር ከትክቶ ከጠላ ጋር ዘፍዝፎ ሲጠራ ቢጠጡት ቁርጥማት ያጠፋል ።
إظهار الكل...
6👍 1🥰 1
🙏🙏ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት አመሻችሁ🙏🙏 ዛሬ ቀኑ አርብ 13/ 10/ 2017 ዓም ከምሽቱ 5:20 ነው ! ሕዝበ መስተፋቅር መስሕበ ንዋይ አቃቤ ዕርስ ሁሉንም በአንድ ያካተተ ጥበብ በንቅሳት ብቻ እየሰጠን እንገኛለን የምንገኘው አማራ ክልል ነው ! ግልፅ የሆነ አድራሻ ለመጥቀስ ከግዜው ጋር ስለማይሄድ በ 0918834904 ይደውሉልን ✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት           @merigetaamedeberhan      ጥበብን መጠቀም ብልህነት ነው !
إظهار الكل...
5🔥 1🤔 1
።።።።።።።   በእንተ ዐቃቤ ርእስ    ።።።።።። በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፩ዱ ፡ አምላክ ፡ ጸሎት ፡ በእንተ ፡ ዐቃቤ ፡ ርእስ ፡ ቄጅ ፡ መጅ ፡ መጅናን ፡ እረቀመጅ ፡ መከመጅ ፡ መማሽ ፡ ሹጅ ፡ አዑር ፡ አዕይንቲሆሙ ፡ ወአጽንዕ ፡ ልቡናሆሙ ፡ ከመ ፡ በድን ፡ ርኵስ ፡ ወከመ ፡ ዕብን ፡ ፍዙዝ ፡ ይኩኑ ፡ ነጌ ፡ ኩምቢያማ ፡ አውራሪስ ፡ ቀንዳማ ፡ ሰብእ ፡ ሰይፋማ ፡ ስልብ ፡ ልቦሙ ፡ ለሰብአ ፡ ኲሉ ፡ ዓለም ፡ ፀርየ ፡ ወጸላእትየ ፡ እገሌ ፡ ፫ ፡ ጊዜ ፡ ድገም ። ።።።።።።።።    ጠላት የሚያፈዝ    ።።።።።።።። መምትፊአል ፡ ፲፱ ፡ ጻፍ ፡ ኤውኮአል ፡ ለውርታ  ፡አህድ ፡ ፯ ፡ ጻፍ ፡ መላም ፡ ተአጀም ፡ ኤውሩ ፡ አላ ፡ የለውርታንአክድህ ፡ የእገሌን ፡ ልጅ እገሌን ፡ ነገሩን ፡ አፍዝዝ ፡ የኔን ፡ ነገር  ፡አንግሥ ፡ ብለህ ፡ በጥቁር ፡ ቀለም ፡ ጻፍ ፡ በጥቁር ፡ አህያ ፡ ጋማ ፡ ነጭተህ ፡ በተጻፈው ፡ ወረቀት ፡ ጠቅልለህ ፡ ታጥነህ ፡ ሒድ ፡ ነገር እንዲቀር ፡ እንዲቀናህ ። ።።።።።።።።።።።   ሹመት የማያሽር ።።።።።።።።።።። ሐማያኤል ፡ ሐንያኤል ፡ ሐቅያኤል ፡ ሐስያኤል ፡ እንዘይብል ፡ ያማዕቆር ፡ ረጡሐርያ ፡ ሩሐንያ ፡ አልኪራም ፡ አጠይቢን ፡ አላአሰማ ፡ ኢኩም ፡ አልሐናን ፡ ግበሩ ፡ በፍቅረ ፡ ዚአየ ፡ አግብአሰማ ፡ ኀበ ፡ እገሌ ፡ ሀቦ ፡ በሎ ፡ ገብርኤል ፡ የኔን ፡ የእገሌን ፡ ነገር ፡ ለእገሌ ፡ ገቢሩ ፡ ነጭ ፡ እጣን ፡ ሉባንጃ ፡ እያጤስክ ፡ በመንፈቀ ፡ ሌሊት ፡ ከመዳመጫ ፡ ደንገይ ፡ ላይ ፡ ቆመህ ፡ ፵፱ ፡ ጊዜ ፡ ድገም ፡ ። ሹመት ፡ የማያሽር ፡ የማያስከስስ ፡ ሕዝቡን ፡ የሚያፈዝ ፡ ደግሞ ፡ የመቃብር ፡ አፈር ፡ አምጥተህ ፡ በመንፈቀ ፡ ሌሊት ፡ ፵፱ ፡ ጊዜ ይስማዕከን ፡ ደግመህ ፡ ፫ ጊዜ ፡ ወደግራ ፡ አዙረህ ፡ በምትሰራበት ፡ ላይ ፡ በትን ።
إظهار الكل...
4🔥 2🫡 1
ከላይ የተጠቀሱ እፅዋቶችን በምስል እስከነ ስማቸው መመልከት ለምትፈልጉ 👇👇👇 http://t.me/merigeta_amedeberha
إظهار الكل...
👍 3
፱, #ለፍጥነት ስሩን ከጭላት ልብ ጋር ሰፍተህ አሲዝ ወይም ... ከድመትና ከጭላት ጥፍር ጋር አሲዝ፡ ፲, #ለእግረ_መልስ ወይምለተጣሉ ባልና ሚስት ለማገናኘት የሁለቱን ወዝ ከሞይደር ስር ጋር በጥፍሬና አበባና ደም ለውሰህ ከጥፍሬናው ልጥ ጠምጥመህ ከሁለት ከፍለህ አንዱን መታጠን ሌላውን ከአልጋው አጠገብ መስቀል ነው ። ፲፩,  ለማንኛውም ነገር ሞይደርን ዘፍዝፎ መታጠን ወይም ሲተኛ መታጠን አይነጥላን ገርጋሪን ያስለቅቃል ። ፲፪, ሞይደር ሲቆረጥ  የሚጸለየው ጸሎት ፦ጸሎት መስተሣልም ወመስተዋድድ በፍቅር ወበሰላም ምሳለ ሕዝብ ወአህዛብ ወምስለ ብእሲ ወብእሲት ሹርፍዝ  ፫  ፓርታሎና አጅጁ ቆመጀጁ አስተፋቅር ወአስተጻምር በዛቲ እፀ ቡሩክ ወዕፀ ፍቅር በአፈ ካህን እገሌ ለገብርከ /ለዓመትከ/ እ፡ ፲፫, ለጥበብ እንዲሰምር ‛‛ ያሽጣኤል ’’ ፯ ያሸርጣኤል ፯ እጅ ከማሁ አስምሮ ጥበብ በእዴየ ለገ/እ ’’ የሞይደርን ሥር ከቀይ ቀለም ጋር ጨምሮ ጽፎ በብርዝ ላይ ዘፍዝፎ 49 ጊዜ ደግሞ መጠጣት ነው ። ፲፬, ሥሩን ከበርሃ እንቁራሪት ጋር አክስሎ በጣዝማ ማር ለውሶ እጅን ወይም ብልትን ቀብቶ ማስነካት ነው ። #ሞናሄ_በግእዙ_እፀ_መናሂ ፩, #ጆሮው_ለመገለ አፍንጫው ለሚገማ ጆሮው ለተዘጋ ከወርቅ በሜዳ ጋር ወቅጦ በሰሊጥ ዘይት ለውሶ መቀቀልና ማጥለል ከሚያመው ላይ ማድረግ ነው ። በቅቤም እንዲሁ አንጥሮ ማድረግ ነው ። ፪, #ለብብት_ቅርናት  የእፀመናሂን ስር በቅቤ አንጥሮ መቀባት ወይም ብቻውን መቀባት ነው ። ፫, ለልብ ደዌ ከአሚራ ጋር በመጠጫ መሳብ ነው ። ፬, #ለቁርጥማት ለውጋት ለራስ ህመም ለሆድ  ደዌ ከቅቤ ጋር አንጥሮ መጠጣት ነው ። ፭, ለማንኛውም ደዌ ከወርቅ በሜዳ ጋር ወቅጦ በቅቤ አንጥሮ መጠጣት ነው ። ፮, ለራስ ፍልጠት ከሺነት ቅርፍት ጋር ሲያመው በአፍንጫው  ይሳብ ። ፯, #ለመካን ሴት ከወተት ጋር እያፈላህ አጠጣ ፰, #ለፎረፎር ከደም መረጭ ጋር በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ። ፱, #ለሥር ደዌ እከክ ለመሰለው የእፀመናሂ የጠንበለል ቅጠላቸውን በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ። ፲, እንደ እከክ ሰውነቱን ለሚያሳክከው የጠንበለል የዋጊኖስ ስራቸውን ከእፀመናሂ ጋር ደቁሶ መቀባት ነው ። ፲፩, ጉሮሮው ለአበጠ ከወርቅ በሜዳ ጋር በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ። #ሟጠሺ ፩#ለገበያ ቅጠሉን ከሞይደር ስር ጋር መታጠን ተቀጽላውን ከከሴ ከጉፋ ተቀጽላ ጋር ከአለት ላይ ወቅጦ በነጭ ቄብ ዶሮ ደም ለውሶ ከገንዘብ ጋር መያዝ ነው ። S                           -                         ሠሰ ይቀጥላል...
إظهار الكل...
5👍 2
ከበፊቱ የቀጠለ... መ ---------_ --------- M #መሎክያ ለወጥ እንደጎመን ቅጠሉን ቀቅለህ በመንታ እንጨት ስበቀው እርሱን ከገንፎ ጋር ለውሰህ ቢበሉት ሆድ ያለሰልሳል ለሽንት ጥሩ ነው ። መረቃ  ? እፀጳጦስ  ? መርቆ     ? #መናሂ - እፀመናሂ ፩, #ጆሮው_ለመገለ አፍንጫው ለሚገማ ጉሮሮው ለተዘጋ የስሩን ቅርፍትና ከወርቅና በሜዳ ጋር በቅቤ አንጥሮ በአፍንጫው ማድረግ ነው ። ፪, #ለብብት_ቅርናት በቅባት ለውሶ መቀባት ነው ። ፫, #ለልብ_ደዌ ከአሚራ ጋር በመጠጫ እንደሲጃራ ይጠጣው ። ፬, #ለቁርጥማት ለውጋት ለራስ ህመም ለሆድ ደዌ ከቅቤ ጋር አንጥሮ በባዶ ሆድ መጠጣት ነው ። ፭, #ለማንኛውም_ደዌ ሥራይ ከወርቅ በሜዳ ጋር ወቅጦ በቅቤ አንጥሮ በባዶ ሆድ መጠጣት ነው ። ፮, #ለራስ_ፍልጠት ከሺነት ቅርፍት ጋር ወቅጦ ሲያመው ዱቄቱን በአፍንጫው ይሳብ ። ፯, _ለመካን_ሴት ከወተት ጋር እያፈላች ደጋግማ ትጠጣ ። ፰, #ለፎረፎር ከደረጭ መረጭ ጋር በቅቤ ለውሶ በፀሐይ ማቅለጥና የቀለጠውን ንጥር ቅቤ መቀባት ነው ። ፱, #ለሥጋ_ደዌ እከክ ለመሰለው የእፀመናሂና የጠንበለል ቅጠላቸውን በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ። ፲, እንደ እከክ ሰውነቱን ለሚያሳክከው የጠንበለል የዋጊኖስ የእፀመናሂ ሥራቸውን ወቅጦ በቅቤ ለውሶ መቀባትና ፀሐይ መመታት ታጥቦ እንደገና ተቀብቶ እሳት መሞቅ አለበት ። ፲፩, #ጉሮሮው_ለአበጠ ከወርቅ በሜዳ ጋር ደቁሶ በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ። ፲፪, #ለመፍትሔ_ለሥራይ ለቁመኛ ለቡዳ ሥሩን ከግሜ አረግ /ግምአረግ/ ሥር ጋር ወቅጦ ዘፍዝፎ መታጠብ ። ለሰባት ቀን ያህል መጠመቅ አለበት ። #መሬንዝ - ምሬንዝ ፩, #መሬዝ -  ምሬንዝ ፦ አጥንት ለሆነባት ተቀጽላውን ቅጠሉን ቅርፍቱን በአንድ ላይ ደቁሶ በነጭ ማር ሰባት ቀን ማብላት ነው ። በሰባተኛው ቀን የዋጊኖስ ቅጠል ከወተት ጋር ቀቅሎ ሣያበዙ ለብ ሲል ማጠጣት ነው ይወጣል ። ፪, #ለቆዳ_በሽታ ሥሩን ቅጠሉን ቀቅለህ በውኃው ሰውነቱን እየተቀባ ፀሐይ ይሙቅ በበነጋው የምድር እንቧይ የግዜዋ የቀረጥ ፍሬ በአንድ ላይ ቀቅለህ አጠጣው ። ፫, ለማንኛውም የቁስል ደዌ ሥሩን ከፍየል ቅቤ ጋር አንጥረህ ቅባው ይፈውሣል ። #መዝረንጁስ ትኩስ ደረቅ ነው ! አፉ ለተጣመመ አፍንጫው ለተዘጋ ቁርጥማት ላመመው አሽተው ይፈወሣል በአፍንጫ ማሸተትና መሣብ ነው ። #መቅመቆ_ለፅንስ ፩, #ከሰሊጥና ከኑግ ቅባት ዘይት ጋር በቅለህ በባዶ ሆድ አጠጣ ይወጣል ። ፪, #ሰገራ_ለከለከለውና ለሚያስቀምጠው ከወተት ጋር አፍልተህ አጠጣው ። ፫, #ለእከክ በቅቤ ለውሰህ ቅባው እንደሻይም ይጠጣ ። ፬, #ለሣል ከጦስኝና ከእንጭብር ጋር በቅቤ አንጥረህ ቅባው ይፈወሳል ። ሙሬ  ? #ሙዝ  #ለችፌ አጥበህ ቀባው #ሚዳቁያ #ሙታንሣ የሙታንሣ ቤተሰቦች አደንድን አደንዶ የሰይጣን ሙቀጫ ጂልዋት ዛብና እነዚህን የመሰሉና የሚመሣሰሉ ብዙ ናቸው ሌሎችን በፊደል ቤታቸው የምገልፅ ይሆናል የሙታንሣ ስሩን በወተት ቀቅለህ ብትጠጣው ከራስ እስከ እግርህ ያለው ጅማት ይፍታታል አዘወትረህ በሰመሬታ ገብስ ብትጠጣው ብልትህ ይበረታል ወይም በብርዝ ብትጠጣውና ከመረቅ ጋር ብትወስደው የሰውነትህ ድካም ይጠፋል የሶሪ ቆቅ ሐሞትና ጉበትዋን ወስደህ ሥጋዋን ከአደንድን ስር ጋር አሰርተህ መረቁን ብትጠጣ ንቁ የማትረሣ ትሆናለህ ። ተሐድሶነት አለውና ለማንኛውም ብርታት ይሆናል ። #ማቱሣላ ለእድሜ ለሰባት ወር ግልገል በግ አብልተህ በ3 ቀን አርዶ መብላት #ማሽላ  -  ቃቤላ፡ በረድ ደረቅ እርጥብም ነው ለሆድ ቀላል ነው ውስጡንም ያለሰልሣል ። #ሚጥሚጣ ፦ ለሰውነት ብርታት ማነቃቂያ ይሆናል ። ስብን ካልስትሮን ስለሚያስወግድ ከተልባ ጋር መጠጣት ነው ። #ምሳና #ለሣል ለወስፋት ለቂጥኝ ፍሬውን ሰልቀህ በወተት አፍልተህ ግማሽ ኩባያ አጠጣ ። ! ማርከሻው ቡና ነው ! ! ፍሬው ከአሥር እንዳይበልጥ ! ! ለደካማ ሰው ከአንድ እስከ አምስት እንዳይበልጥ ! ፪, #ለጭብጦ #ለኪንታሮት ወገቡን ለሚይዘው ቀንበጡን ቅርፊቱን የበቶ ስር ጋር ወቅጦ ግማሹን ማንኪያ በቀይ ጤፍ ቂጣ አብልቶ አጓት ማጠጣት ነው ። ፫, #ለቂጥኝ #ለወስፋት #ለሣል ለቆዳ ደዌ ፍሬውን ደቁሶ ግማሽ ማንኪያ በወተት አፍልቶ መጠጣት ነው ።   ! በሶ ቡና ማርከሻ ! ፬, #ለነስር ቅጠሉን በአፍንጫ ለሴት ደም በብልትዋ ማድረግ ነው ለማንኛውም ህመም ፍሬውን ከዋጊኖስ ፍሬ ጋር መውሰድ ። #ምስር ለሆድ ቀላል ደረቅ ነው ! አዘውትረው ቢበሉት ዓይን ያደክማል ከወተት ጋር ቀቅለው ቢበሉት አፍረተ ሥጋ ያበረታል ። #ምስርች ፩, ዓይኑ ለሚቀላና ብጫ ለሚሆን ለወፍ ቅጠሉን ቀቅለህ አጠጣ ፪, እጁን ለሚቆረጥመው የምስርች የሰመግ የአንደሁላ ሥራቸውን ደቁሰህ በቅቤ አንጥረህ ቀባ ወይም አጠጣ ። ፫, #ለመፍትሔ_ሐብት ቅጠሉን ከፍየለፈጅና ከቀጠጥና ፍሬ ጋር በዶሮ እንቁላል ለውሰህ በጅብ አር ደምድመህ ያዝ ። #ምጫምጮ #የወርቅ በሜዳ ዘር ለወስፋት ለኮሶ ከወገራት ጋር በኑግ መብላት ነው  ። #ምስንጭሮ ለትምህርት የዋርካ ተቀጽላ የእንጆሪ የቀጠጥና የአቱች ሥራቸውን ቅጠላቸውን ጋር የምስንጭሮን ቅጠል ወቅጠህ በምስር ንፍሮ አብላ ወይም በነጭ ማር ለውሰህ አውጥ ። #ምንጭርር #ለሣል የአሚራ የመቅመቆ የቀጠጥና የሥረ ብዙ የምድር እንቧይ ሥራቸውን ከምንጭር ስር ጋር በቅቤ አንጥሮ ማጠጣት ነው ወይም ስሩን ከነጭ ሽንኩርትና ከጤና አዳም ጋር በወተት እያፈላህ ጧትና ማታ አጠጣ ። አንድም ለኖረ ሣል ስሩን ከጦስኝና ከአቱች ከኮርሺም ከእንዘረዘይ ስር ጋር በነጭ ሽንኩርት ጤና አዳም ጋር ቀቅለህ ውኃውን ከጣዝማ ማር ጋር በትንሹ አጠጣ ። ምድር እንቧይ ‛‛‛የ’’’ የምድር እንቡዋይ ከሚል ተመ/ #ሞይደር_በግእዝ #እጽ_ኦይደር ፩, #ለመፍትሔ_ሐብትና_ ለማንኛውም ነገር የሞይደር የወገርት የጉሽርጥ የአጋም ሥራቸውን ከሴቴ ብርጉድ ጋር ደጋግሞ መታጠን ነው ። ፪, #ለሴት_ባል_ላጣች_ወይም_ባልዋ_ለጠላት_ ሥሩን ከሴት ዶሮ ሥጋ ጋር አሰርታ ትብላ፡ ወደባልዋ ስትሄድ ወይም ስትተኛ ከከርቤ ጋር ትታጠን ወይም ከጎዝ ጠቀስና ከሴቴ ብርጉድ ጋር ወቅጣ ማታ ማታ ትታጠነው ጉኛዋን የጠላት የናቃት ያፈቅራታል ። ፫, ከሰባት ቦታ የሞይደር ስር ቆፍሮ ከአደስ ቅጠል ጋር ወቅጣ በቅቤ ለውሳ ትቀባና ማታ ትታጠን ወንድም ለጠላች ሴት እንደዚሁ ታድርግ ከመኝታዋ ላይ የተወቀጠውን የሞይደር ስር ነስንሣ ትተኛበት ፬, ከወንድ ጋር አልስማማ ላለችም ከሎሚ ጋር ቀቅላ ትታጠን በውኃው ሰውነትዋን ትታጠብበት ። ፭, ለማንኛውም ነገር ሴቶች ወንዶች እንዲወዷቸው ከሰባት ከሰባት ቦታ የሞይደር የቆንጥር የቀንጣፋ የጎበዝ ጠቀስ የቀጠጥና የወገርት ከሴቴ ብርጉድ ጋር ይታጠኑት ከቅባት ጋርም ለውሰው ይቀቡት ። ፮, ለወንድ ስሩን ደቁሶ ቀቅሎ ይታጠን ወይም ብልቱን ቀብቶ በተቀቀለው ድፍድፍ ይሸው ወይም ከቅቤ ጋር ለውሶ ቀብቶ ይገናኝ ። ለማንኛውም ከሜሮን ጋር ለውሶ ይቀባ ሰው ሁሉ ያፈቅረዋል ። ሥሩን ማላመጥ ለብዙ ነገር ይሆናል ። ፯,#ለትምህርት ለመክስት ከጥቁር ገብስ ጋር ወይም ከዘቢብ ጋር ወቅጠህ በነጭ ማር እየለወስክ ሰባት ቀን ይብላና ትምህርቱን ያጥና ይገለጽለታል ብልህ ይሆናል ። ፰, #ለጥበብ ስሩን ከቀንጣፋ ተቀጽላ ጋር በምስር ንፍሮ ቀቅለህ ለአርባ ቀን አብላው አጠጣውም ።
إظهار الكل...
4😱 1
ከበፊቱ የቀጠለ.... ለ                       -                         L ለሀ  ? ላንቁሶ   ? #ለንቁጣ ሆዱ ለደረቀ ሰገራ ለከለከለው ! የለንቁጣ ልጥ የላንቁስ ቅጠል ከእንስላል ጋር አጠጣ ወይም ለንቁጣውን ከተልባ ጋር በማር / አውጥ / አብላ #ለውዝ እርጥብ ነው ቅባት አለው አዘወትሮ ለሚበላው ለንቃት ይሆናል አእምሮውን ያጠራዋል ከገብስ ጋር ቢበሉት ሀዘንን ያስቀራል ዓይንን ያጠራል ብልትን ያጠነክራል ለራስ ምታት ከሎሚ ጋር ቢጠጡት ያስታግሣል ደጋግመው ከወሰዱት ህመሙን ያስተዋል ። ሊንደን  (Linden) ለራስ ህመም ቅጠሉን አበባውን ቅርፍቱን እንደሻይ መጠጣት ነው ። #ላንቁሶ ላንቁሶ አንድ ነው ! ተቀጽላውን ከቀጠጥና ቅጠል ጋር ደቁሶ የታሰሩበትን ሰንሰለት ቢቀቡት ይፈታል ። ላሎ  ? #ልት ፩, #ዓይኑ_ለአበጠበት የእንቁላል ቢጫውን ጥሎ ከልት ቅጠል ውኃ ጋር አድርጎ ማጠብና ማሰር ነው ። ወይም የልቱን ቅጠል ቀቅሎ በውኃው የገብስ ዱቄት ለውሶ ከማር ወይም ከእንቁላል ውኃ ጋር በአንድ ላይ ከአይኑ ደፍድፎ ማሰር ነው ። የእንቁላል ብጫው አንዳይጨመር  ። ፪, #ጠጉር_ለማጥቆርና ለማሳመር የኑግ የአባሎ የልት የአደስ ቅጠላቸውን የቁራ አረግ ቅጠል ፍሬ ሁሉንም ወቅጠህ በኑግ ዘይት አዘውትረህ ቀባው ። ፫, #ለአንጀት_በሽታ ቅጠሉን ቀቅለህ አጠጣው ። ፬, #አፍረተ_ሥጋው_ለሚመግልበት የልት ቅጠሉን እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላት ወይም በኑግ ዘይት ጠብሶ መብላት ነው ። ወይም በትኩስ ከአፍረተ ሥጋው ላይ ደፍድፎ ማሰር ነው ። #ልምጭ ? ሎል ? #ሎሚ_ለመፍትሔ_ሁሉ_የሚገባ_እፀ_ነው ! ከርካዕ   ጸሎተ መፍትሔ ሐብት ወመፍትሔ ሥራይ በሐበርጂን  ፯  መርደን  ፯  በጂር  ፯  አክሎግ   ፯  በስፍዛዜዎር  ፯  በኃይለ  እሉ አስማቲከ ፍታሕ ወሰአሮ ሥራየ ወክስት ሐብትየ ሊተ ፩, በሉሚ ተቀፅላ ደግመህ በማር አውጥ ወይም በሎሚ ውኃ ደግመህ አጠጣ ። ፪, ለሣል ቅጠሉን ከነጭ ሽንኩርትና ከነጭ እጣን ጋር በወተት አፍልተህ ጧትና ማታ አጠጣ ። ፫, ለትኩሣት ለጉንፋን ለራስ ህመም ፍሬውን አበባውን ቅርፍቱን ቅጠሉን ወቅጠህ አድርቀህ አጠጣ ለሌላውም እንደዚሁ አጠጣ ። ፬, ለሆድ እከክ ለራስ መቆሸሽ የሎሚ ውሀ ከማርና ከነጭ ሽንኩርት ጋር ለውሰህ በባዶ ሆድ አብላ ። ፭, እራሱን ሁልጊዜ ለሚያመው የሎሚ ውኃ ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር ከደባልቆ ከቡና ጋር ከጠጣው ደጋግሞ ይውሰድ ይፈውሣል ። #ሎሚሸት ፩, ሎሚሸት ደም ለሚበዛበት ከጠንበለል ስር ጋር ሰፍተህ አሲዝ ፪, #ለገበያ ከሰባት ቦታ ቅጠሉን ስሩን ነቅሎ ከሞይደር ጋር በነጭ ዶሮ ደም ለውሶ ከሚሸጥበት ቦታ መቅበር ነው ! በበላዩ ነጭ እጣን ማጤስ ነው ። መ                       -                       M ይቀጥላል...
إظهار الكل...
9
በተፈጥሮ የሚበቅሉ እፅዋቶችን በምስል መመልከት ለምትሹ 👇👇👇👇👇 http://t.me/merigeta_amedeberha
إظهار الكل...
🌿🌿🌿🌿 በግእዝ በአማረኛ 🌿🌿🌿 ከ ‛‛ ሀ ’’  እስከ ‛‛ ፈ ’’ የእፅዋት ስም ዝርዝር እስከ ገቢር ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ #ሃሉ_ሁለገብ ሌላው ስሙ ተሶላት ለምች ቀባው ፩, #ለኪንታሮት ቅጠሉን ወቅጠህ ከጎርጠብ ጋር በእሳት አሙቀህ  ተኩሰው ይፈወሣል ። ፪,#ለልብ_ድካም ሥሩን ከአቹች ስር ከእንጭብር ስር ጋር ሀምል ገላ አንገቱን ለአመመው ቅጠሉን ከአሚራ ቅጠል ጋር ውስጡን መቀባት ነው ። #ሀመር  ሁመር  - ፍሬውን ለትርፍ አንጀት ከስንገላ ቅጠል ጋር አጠጣ ። ሃምቦ ? ሃረገ ወይን ? #ሐረግ_ሬሣ  በግእዝ እፀ ሣቤቅ ፩, #ለሚረሣ ቅጠሉን የሎሚሸት የዮዲት የጦስኝ አበባቸውን የእንጎችት ስር ሁሉንም በአንድ ላይ ወቅጠህ በነጭ ማር ሰባት ቀን መብላት ነው ። ፪, #ለቅኔ ለድርሰት ለግጥም ‛‛ ናዝ ላቢሉ በርሃ መጅቸች ክስት ሊተ/ሎቱ/ ነገራተ ወልሣናተ አብርህ ልብየ ለድርሰት ወለተርጎሞ ቃላተ ለገብርከ እ/’’ ከአረግሬሣ ተቀጽላ ጋር የሞይደርና የእንሰላል ስር ደቁሰህ በሚዳቋ  ሐሞት ወይም በአረቄ መዋጥና መጻሕፍት ሲያነቡ መሰንበት ነው ። ፫, ደም ለቀረባት ቅጠሉን ወቅጦ ከአዋዜ ጋር መብላት ወይም መጠጣት ነው ። #ሐበዛንጣ_ወይም_የሽኮኮ_ጎመን ቁራኛ ለያዘው ህፃን የሰመግ የምስርች ቅጠላቸውን ሥራቸውን ወቅጠህ በውሀ ዘፍዝፈህ ለሰባት ቀን እጠበው ሐበዛንጣ ማለት ቦዝ መሰል ትንሽዋ ናት እንጂ ትልቁንም አበዛንጣ የሚሉት አሉ ሁለቱም ለመፍትሔ ሐብት ይሆናሉ ። ሐበዝ አምጣ የሚባሉ እፀዋት አበዛንጣ የአየኸውን ለእኔ አምጣ ቀረጥ ቆርጠህ አምጣ ሟጠሽ ሟጠህ አምጣ ከሴ ከሰህ አምጣ ጎፋ ገፈህ አምጣ ዋሽንት ዋሸተህ አምጣ ከሸሽላ ከሻሽተህ አምጣ ፍየለፈጅ አፋጅተህ አምጣ ግራምጣ ግራ አጋብተህ አምጣ እየተባሉ የሚቆረጡና ለመፍትሔ ሐብት ለገበያ የሚሆኑ ሁሉ ሐበዝ አምጣ የቆላ ሐበዛንጣ ኃበዝ አምጣ የቆላ በርገሌ: ሀበዝ ዘበርገሌ የደጋ ሐበዛንጣ ኀበዝአምጣ የደጋ በርገሌ ሀበዝ ዘበርገሌ ኀበዝ አምጣ ገበያን ክፈት እየተባለ የሁሉንም ተቀጽላ በዶሮ ደም አንግሰው ይቆርጣሉ ። ሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑሑ #ሑለገብ_ሃሉ_ወይም_ተሰላት_ይባላል ፩, ለድንገተኛ ህመም ሥሩን ማላመጥ ቅጠሉን ወቅጦ በእሳት እያሞቁ ቁስልን መተኮስ ያደርቃል ። #ሑመር_ወይም_ሐመር_ይባላል ፩, ለሆድ ፍሬውን ዘፍዝፎ መጠጣት ጤነኛ ያደርጋል ። #ሑስጱ አሽክት ይባላል ፡ አንህስት ለቁስል ቅጠሉን አድርቆ መደምደም ነው ። ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ #ሂና በረዶ ደረቅ ነው በሐሞት ለመጣ ደዌ ከጉበት ጋር ቢወስዱት ይበጃል ። ሂናውን አሙቀው ብልትን ቢያሹበት ይበረታል ያሳድጋል ። ሂስጶ ? ሂጶ   ? ሃያ /ኻያ/ የወንዝ ዛፍ ? ሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆ ሆማ  ? ሆሜ  ጥቁር ዛፍ    ? ሆጭ   ? ሆበኔ ሐበኔ በግእዝ እፀ ባሮክ ወይም እፀ ኤልያስ ትባላለች ። በትረ ሙሴ መስላ ከበትረሙሴ ዛፍ አጠገብ የምትበቅል ባለማእዘን የሆነች ናት ። ፩, ፍሬዋን ለቅሞ አርባ ቀን በሱባኤ የበላ አያረጅም ቢያረጅም ይታደሳል ። ፪, ውኃ ለማፍለቅ በለበቅዋ ሰረገላ ኤልያስን ደግመህ ነቅአ ማይ የተባለውን ድንጋይ ምታው ይፈልቃል ። ለደረቀ ምንጭም በበላዩ ቅበርበት አይነጥፍም አይደርቅም ። ፫, ቅጠሉን ከቀረጥና ከጉፋ ቅጠል ጋር ወቅጠህ ነስንስበት አይፈርስም ። ፬, የእንጨቱን ውስጡ አውጥተህ ከሰባት ቀለማት አክፀሣቤቅ ቅጠል ከሎሚ ውኃ ጋር አድርገህ የተመኘኸውን እያስገባህ ጻፍበትና በእብነበረድ ውስጥ አስገብተህ በስውር ቦታ ቅበረው ትከብራለህ ። ፭, ለራእይ እንጨቱን እንደ መስቀል እንደ መቁጠሪያ አድርገህ ጸልይ ሁሉ ይሰምርልሃል ። ፮, እሄን አስማት ከቅጠሉ ጋር ጽፈህ ለሁሉ አጠጣ ይፈውሣል ለውጥ ያያል ከአፈ ያሬድ ደም ጋር ጻፈው ብትሄድ አትደክምም ‛‛ ሰረገላ ኤልያስ አስማተ እግዚአብሔር ያሸመሰት ያሸስተጸምያሁ መጠጢታ ያመሊጠ ያጠልብህ ያጠውብሔር ነያንፒፐ ያእዠትዠ ሸጌታ ያሸሊጥዕ ያጊሙት ያፍቶሕ ያሸሰረረ ያርፍዕ ያምን ሁስብትጥያ ያሸልኩፋ ክምጡሺ የሐዝ ሕንብያ ያታፍአይታ መጠሽ ያሸዕሸፅ ያሟማዕ ሊከ ያጥኢና ይአትዠ ያመጠሸ ያፍአይታ ያፍፍያ ያሐዪ ያቀዩም ያሸልክፋ ያጠዊጢ ያረስከብት ያህዱይይ ያአሸብርት መቅደሰ ዘየም ሻልቁኩየ አፍዝብል ሕርኬና ወተመናጽልም ለጽለል ራብኤል አቀት ትዱቅ ’’ ለ                  -                   L ይቀጥላል ...
إظهار الكل...
1
00:23
Video unavailableShow in Telegram
ሉባን ዘከር እጣነ ዘካሪያስ ሲጨስ ይህን ይመስላል ቀጥ ብሎ ወደ ሰማይ ይወጣል
إظهار الكل...
2.83 KB
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ሉባን ዘከር እጣነ ዘካርያስ ይህ እጣን በጣም እጅግ ብዙ ጥቅሞች ሲኖሩት ከጥቅሞቹ ውስጥ በጥቂቱ አስማተ ሠለሞንን ለመዋረስ ሙራድ ገንዘብ ለማውረድ ለመሠውር ሌሎችም ጥቅሞች አሉት ገንዘብ ያስወረዱ ትልልቅ ባለሀብቶች አሉ በጣም ረቂቅ ሚስጥሮች አሉት ዋነኛ ጥቅሙ ብር ለማውረድ ነው ። ገንዘብ ለማውረዱ ሊቃውንት አባቶች ይመሰክራሉ ። ።።።።። መርጌታ አምደ ብርሃን ።።። ማንኛውንም ጥያቄ ለምትሹ በሙሉ 0918834904 ብለው ይ�ደውሉ። ✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት           @merigetaamedeberhan ።።።።።። ጥበብን መጠቀም ብልህነት ነው !!! ።።።።
إظهار الكل...