አዲስ ነገር መረጃ
الذهاب إلى القناة على Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
إظهار المزيد103 410
المشتركون
-6824 ساعات
-937 أيام
+16730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ከ5 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአዲሱ የአሜሪካ ውሳኔ ተጠቂ ይሆናሉ ተባለ
አሜሪካ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጧን ተከትሎ 5ሺ ኢትዮጵያውያን የውሳኔው ተጠቂ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡
ቀደም ሲል 5001 ኢትዮጵያውያን በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዘመን የህግ ከለላ ተሰጥቷቸው እንደነበርና 263 የሚሆኑ ተጨማሪ ዜጎች አመልክተው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
አሜሪካ በፈረንጆቹ ታህሳስ 12ቀን 2022 በኢትዮጵያ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ለኢትዮጵያ ዜጎች ጊዜያዊ የህግ ከለላ መስጠት መጀመሯ የሚታወስ ሲሆን በሚያዚያ 2024 ዳግም ተራዝሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ስደተኛ ጠል ነው የሚባለው የትራምፕ አስተዳደር ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ውሳኔው ለእነዚህ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ከለላ አንስቷል፡፡
@seledadotio
@seledadotio
Photo unavailableShow in Telegram
ሕፃናት በ12 ዓመታቸው የሞባይል ስልክ እንዲጠቀሙ መፍቀድ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ❓
ሕፃናት በ12 ዓመታቸው የሞባይል ስልክ (ስማርት ስልክ) እንዲይዙ እና እንዲጠቀሙ መፍቀድ ልጆቹን ለድባቴ እንዲዳረጉ፣ ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት ታጋላጭ እንዲሆኑ እና ለእንቅልፍ እጦት እንደሚዳርጋቸው አንድ ጥናት አመልክቷል።
አዳጊዎች በረጅም ጊዜ ሂደት የአዕምሮ ዕድገት እና ጤና በተመለከተ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ከ10 ሺህ ሰዎች መረጃ በመሰብሰብ ነበር ጥናቱ በአሜሪካ ብሔራዊ የጤና እንስቲቲዩት ድጋፍ የተከናወነው።
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፊላደልፊያ የሕፃናት ሆስፒታል እና የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ በመሆን ነበር ሕፃናት የሞባይል ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ መፈቀድ የሚያስከትልው ጉዳት ምንድነው የሚለውን ጉዳይ ለመለየት እና የመፍትሔዎችን ለመጠቆም ጥናቱን ሲያከናውኑ የቆዩት።
ዩኒቨርሲቲዎቹ ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሆኑ ሕፃናት ዘመናዊ ስልክ እንዲጠቀሙ መፍቀድ ከአእምሮ በሽታ እና ከመጠን በላይ ውፍረት ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው በዚሁ በሠሩት ጥናት ማረጋገጥ ችለዋል።
❤ 23
Photo unavailableShow in Telegram
.
በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ
✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family
ET Creatives
🔥 1
" ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ይዘጋሉ፤ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለበሽታዉ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ጥለናል" - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በማርበርግ ቫይረስ ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሕዝብ የሚሰበሰብባቸዉ የትራንስፖርት እና የመዝናኛ ቦታዎች ላይ ዕገዳ መጣሉን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡመር ኖኩዌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በአከባቢው አንድ ሰዉ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ዉሳኔው መተላለፉን የገለፁት ምክትል አስተዳዳሪዉ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ግብረሃይል ተወያይቶ ዉሳኔ ማስተላለፉን ገልፀዋል።
በዚህም መሠረት በወረዳዉ የሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዕገዳና ክልከላ መጣሉን አቶ ኡመር ገልፀዋል።
በዚህም መሰረት ፦
➡️ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው ይቆያሉ፤
➡️ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡና የሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችም ከአሽከርካሪው ውጪ ሁለተኛ ሰው ላልተወሰነ ጊዜ መጫን አይችሉም፤
➡️ ሰርግ፣ ምረቃ፣ ድግስና በሀዘንም ህዝብ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ሁኔታዎችም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆሙና ቀብር በጤና ባለሙያዎች ስምሪት ብቻ እንዲከናወን፤
➡️ ዲ ኤስ ቲቭ (Dstv) ጨምሮ ፑል ቤቶች፤ ቤቲንግ ቤቶች እንዲሁም የምሽት ዳንስ ቤቶች፣ ጫት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩ፤
➡️ ሰዎች በቡድንና በብዛት የሚሳተፉባቸዉ ማንኛውም አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች በወረዳዉ እንዳይካሄዱ ዉሳኔ መተላለፉን አብራርተዋል።
Via : tikvah
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 24😢 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዜና፡ ቲክቶከሩ አዶናይ ከፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መፈታቱ ተሰማ!
ለአዶናይ አድናቂዎች መልካም ዜና
አዲስ አበባ – በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት የሚታወቀው ቲክቶከር አዶናይ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ከቆየ በኋላ አሁን ከእስር መፈታቱን የቅርብ ምንጮች አመለከቱ።
መረጃው ይፋ የተደረገው በአዶናይ የቅርብ ሰው አማካኝነት ሲሆን፣ ድምፃዊ መርከብ ቦኒቷ ፋስት መረጃ ጉዳዩን አረጋግጠዋል ተብሏል።
ይህ ዜና ለቲክቶከሩ አድናቂዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታዮች ደስታን የፈጠረ ትልቅ ዜና ሆኗል::
@seledadotio
@seledadotio
❤ 107🤪 11👏 5🥱 5🔥 1💔 1
ባርሴሎናን ለመግዛት 10 ቢሊዮን ዩሮ ያዘጋጁት የሳዑዲው ልዑል
የሳዑዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሰልማን ከአውሮፓ ታላላቅ ቡድኖች አንዱ የሆነውን ባርሴሎናን ለመግዛት 10 ቢሊዮን ዩሮ እንዳዘጋጁ ተነግሯል።
በእንግሊዝ ኒውካስል ዩናይትድን የሚያስተዳድረው የሳዑዲ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አሁን ደግሞ ከፕላኔታችን ሀያል ቡድኖች አንዱ የሆነውን ባርሴሎናን ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቱ ተዘግቧል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በገጠመው የገንዘብ ቀውስ ከተቀናቃኞቹ ሪያል ማድሪድ፣ ፒኤስጂ እና ማንችስተር ሲቲ መፎካከር ያልቻለው የካታላኑ ክለብ በመካከለኛው ምስራቅ ባለሀብቶች እይታ ውስጥ ገብቷል፡፡አሁን ላይ ለተጫዋቾች ዝውውር ያልከፈለው በቢሊየን የሚቆጠር ፓውንድ እዳ ያላበት ክለቡ በልዑሉ እጅ ከገባ የአለማችን ውዱ ክለብ ይሆናል፡፡
ክለቡ የቱንም ያክል የገንዘብ ቀውስ ቢገጥመው ከእግር ኳስ ባለፈ የካታሎንያ የነጻነት ምልክት ሆኖ የተሰራ መሆኑ ምን አልባትም መሀመድ ቢን ሰልማን ባርሴሎናን የመግዛት ፍላጎታቸው ችግር ሊገጥመው ይችላል ተብሏል፡፡
ክለቡ ለውጭ ባለሀብቶች ይሸጣል ወይስ ባርሴሎናን ከገባበት የገንዘብ እዳ ለማላቀቅ የስራ ሃላፊዎቹ ሌላ አማራጭ ይጠቀማሉ የሚለው በቀሪ ቀናቶች መልስ የሚያገኝ ይሆናል፡፡
የመካከለኛው ምስራቅ ባለሀብቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአለም የእግር ኳስ ውስጥ በጥልቀት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን በተለይ እንደ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ አይነት ስም ያላቸው ተጫዋቾች ወደ ሳዑዲ ፕሮ ሊግ ማምራታቸው ሳዑዲ ለእግር ኳስ የሰጠችውን ትኩት በሚገባ የሚያሳይ ነው፡፡
@Addis_News
@Addis_News
❤ 19👍 5🤪 5🤣 3
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ ለማካሄድ ባስቀመጠው ዕቅድ መሠረት 12ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ማክሰኞ ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ባንኩ በዚህ ዙር ለጨረታ ያቀረበው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 50 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፤ ይህም በ11ኛው ዙር ከቀረበው መጠን ጋር ተመሳሳይ ነው።
በቅርቡ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 11ኛዉ ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ላይ፣ የኢትዮጵያ ብር በዶላር ላይ በሁለት ወራት ውስጥ ከ11 በመቶ በላይ ተዳክሞ፣ የምንዛሪ ተመኑ 1መቶ54 ብር መድረሱን ካፒታል ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 11😢 3🤪 3
Photo unavailableShow in Telegram
ዜጎቻችሁን ተቀበሉኝ - ምያንማር
የምያንማር መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ዜጎቻቸውን እንዲቀበሉት ጥያቄ አቅርቧል።
ምያንማርን እያስተዳደረ የሚገኘው ወታደራዊ መንግስት በማጭበርበሪያ ካምፖች የያዛቸውን የውጪ ሃገራት ዜጎች ሃገራቱ እንዲቀበሉት ጠይቋል።
በቅርቡ በታይላንድ ድንበር አካባቢ በተደረጉ ዘመቻዎች በርከት ያሉ የውጪ ሃገራት ዜጎች መያዛቸው ሲታወስ እነዚህን የያዛቸውን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር ስለተቸገረ የዜጎቹ ሃገራት በተቻለ ፍጥነት ቶሎ እንዲቀበሉ ምያንማር ጠይቃለች።
ምያንማር ዘመቻው ባለፈው ጥር ከተጀመረ ወዲህ ከ47 ሃገራት የተውጣጡ 13,272 የውጪ ሃገራት ዜጎችን መያዟን ስትገልፅ አብዛኞቹ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው አሁንም 1655 ያህሉ እዛው እንደሆኑ ገልፃለች።
ከቀሩት መካከል ከ500 የሚበልጡት የቻይና ዜጎች ሲሆኑ ከ100- 300 የሚደርሱ #የኢትዮጵያ ዜጎች እንደዚሁም የቬትናም፣ የኬንያ፣ የኢንዶኔዥያ እና የህንድ ዜጎችም እንዳሉ ምያንማር አስታውቃለች።
ምያንማር አብዛኞቹ ወደ ሃገራቸው ያልተላኩ የአፍሪካ ሃገራት ዜጎች ሃገራቸው በታይላንድም ይሁን በምያንማር ኤምባሲ ስለሌላቸው ነው ብላለች።
ምያንማር በአመት 40 ቢሊየን ዶላር ለወንጀለኛ ቡድኖች የሚያስገኙ የማጭበርበሪያ ካምፖች መፍለቂያ ስትሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ የበርካታ ሃገር ዜጎች ተታለው በካምፖቹ በግዳጅ እንዲሰሩ ይደረጋሉ።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 22👍 6
አሸዋ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባደረሰዉ አደጋ የአንድ ቤተሠብ አባላት የሆኑ አራት ሕፃናት እና የአሽከርካሪው ህይወት አለፈ
የባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ያሬድ ታደሰ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ከአርባ ላይ አሸዋ የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ የአንድ ቤተሠብ አባላት አራት ሕፃናት እና አሽከርካሪው ሕይወታቸው ማለፉን ገለፁ።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ3 52420 ኢቲ የሆነ ዩዲ የጭነት ከባድ ተሽከርካሪ ከአሳሳ ከተማ አሸዋ ጭኖ ወደ ባሌ ዲንሾ ወረዳ ሀዋ ቀበሌ በተባለ ስፍራ መንገዱን ስቶ የሰው ግቢ ውስጥ በመግባት ሶስት ወንድ እና አንድ ሴት ልጅን ጨምሮ በአጠቃላይ አራት የአንድ ቤተሰብ ላይ ባደረሰው አደጋ አሽከርካሪውን ጨምሮ የአምስት ሠው ህይወት ማለፉን ገልፀዋል።dagu
@seledadotio
@seledadotio
😢 45❤ 18💔 4
Photo unavailableShow in Telegram
🚨ውፍረት መጨመር ይፈልጋሉ❓❓
+251964593642
✔ ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ
ክብደት መጨመር የሚረዳ
✔ የምግብ ፍላጎት መጨመር የሚያስችል
✔ የቆዳን ጥራት እና ልስላሴ ለመጨመር
የሚረዳ
✔ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤
ለቀጭን ሰዎች የሚመከር
✔ ለሴቶችም የተስተካከለ አቋም
እንዲጎናፀፉ የሚያግዝ
✔ ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን ፤
🚴♂ያሉበት እናደርሳለን
------------------------------------
ለበለጠ መረጃ ☎️ +251964593642
+251906495051
+251907495051
Telegram: 📥 t.me/AM_CS
t.me/AM_CS1
t.me/AM_CS2
------------------------------------
❤ 7👍 2
በፍቅርም ሆነ በትዳር ግንኙነት ውስጥ ስምምነት እንዲሰፍን የሚጠቅመው የ5 ለ1 ቀመር
ባልና ሚስቶችን ደስተኛ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?
መልሱ በቀላል ቀመር ውስጥ ይገኛል፦ ለእያንዳንዱ አሉታዊ መስተጋብር፣ ቢያንስ አምስት አዎንታዊ መስተጋብሮች ሊኖሩ ይገባል። ትናንሽ ምልክቶችና ዐውቆ በሚወሰዱ ውሳኔዎች ግንኙነታችሁን እንዴት ማጠናከር እና የበለጠ መቀራረብ መፍጠር እንደምትችሉ ይወቁ!
በስነ-ልቦና ባለሙያው ጆን ኤም. ጎትማን አገላለጽ፣ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቁ እና ደስተኛ የሆኑ ግንኙነቶች በቀላል ሕግ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፦ ለእያንዳንዱ አሉታዊ መስተጋብር፣ ቢያንስ አምስት አዎንታዊ መስተጋብሮች መከተል አለባቸው። እኚህ የሥነ ልቦና ባለሙያ ከሮበርት ደብሊው. ሌቨንሰን ጋር በ 1970 ዎቹ ያገኙት ይህ ግንዛቤ፣ ስለ ግንኙነቶች ያለውን ግንዛቤ በመሠረቱ ለውጦታል።
ሁለቱ ተመራማሪዎች ጥንዶች ግጭቶችን የሚፈቱበትን መንገድ በመመልከት ብቻ ጥንዶቹ አብረው ይቆያሉ ወይስ ይለያያሉ የሚለውን ከ 90 በመቶ በላይ ትክክለኛነት መተንበይ ችለዋል።
የ 5:1 ሕግ ለእርስዎ ምን ማለት ነው?
የጸኑ ግንኙነቶች እንኳን የአሉታዊ ጊዜያት ድርሻ አላቸው። ይሁን እንጂ፣ ቁልፉ ያለው በሚሰጡት ምላሽ ላይ ነው። ጎትማን እንደ ቁጣ ያሉ አሉታዊ ስሜቶች የሚጎዱት በትችት፣ በንቀት ወይም በጥላቻ ሲታጀቡ ብቻ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ።
በሌላ በኩል፣ አዎንታዊ ምልክቶች እና መስተጋብሮች ውጥረትን ለመቀነስ፣ ርኅራኄን ለማሳየት እና የአድናቆት መንፈስ ለመፍጠር ይረዳሉ።
በተለይም በቅርቡ ብዙ ትችት ወይም ጥቃቅን ኃጢአት መፈለግ ከነበረ፣ ከሚከተሉት ነጥቦች ውስጥ በተቻለ መጠን ብዙዎቹን በዕለት ተዕለት ግንኙነታችሁ ውስጥ ለማካተት ሞክሩ።
በግንኙነታችሁ ውስጥ ለበለጠ አዎንታዊነት የሚረዱ ስምንት ምክሮች
1. ቀልድ ይጠቀሙ
ሳቅና ጨዋታ ውጥረትን ለመቀነስ ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር ይረዳል።
2. ፍላጎት ያሳዩ
የትዳር ጓደኛችሁን በጥሞና አዳምጡ። በተለይም አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ ስሜቷን/ ስሜቱን በተመለከተ እውነተኛ ፍላጎት አሳዩ።
3.በየቀኑ ቢያንስ ትንሽ ፈገግታ አይለዮት
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ያሉ ትናንሽ ምልክቶች
እንደ አፍቃሪ እይታ፣ ምስጋና ወይም ትንሽ አስገራሚ ነገር ያሉ ትናንሽ ምልክቶች ትልቅ ተጽእኖ አላቸው እንዲሁም ግንኙነታችሁን በረጅም ጊዜ ያጠናክራሉ።
4. ይቅርታ ይጠይቁ ።ሩኅሩኅ ይሁኑ
እውነተኛ ይቅርታ እና ርኅራኄ የትዳር ጓደኛችሁን ስሜት በቁም ነገር እንደምትመለከቱ እና እንደምታደንቁ ያሳያሉ።
5. የጋራ የሆኑትን ነገሮች አጽንኦት ይስጡ
በውይይቶች ላይ፣ በምትስማሙባቸው ነጥቦች ላይ አተኩሩ። ይህ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችል መሠረት ይፈጥራል።
6. ሌሎች አመለካከቶችን ይቀበሉ
ሁልጊዜ ከእርሷ ጋር ባትስማሙም እንኳ፣ የትዳር ጓደኛችሁን አመለካከት ማክበርና መቀበል አስፈላጊ ነው።
7. ዐውቆ ማድነቅ
ትችትን ለማመጣጠን እና ግንኙነቱን ለማጠናከር በትዳር ጓደኛችሁ ጥንካሬዎችና አዎንታዊ ባህሪያት ላይ ትኩረት ያድርጉ።
8. ፍቅርን ይግለጹ
እንደ ማቀፍ፣ ለስለስ ያለ ፈገግታ ወይም የሚያጽናና ቃል የመሳሰሉ የመቀራረብ ምልክቶች ውጥረትን ሊቀንሱና በእናንተ መካከል ያለውን ትስስር ሊያጠናክሩ ይችላሉ።
✨ ምስጋናዎች፦ ለትልቅ ስምምነት ቁልፍ ናቸው
ምስጋና እና እውቅና ለተሟላ ግንኙነት አስፈላጊ ናቸው። በግለሰቦች መካከል ባሉ ግንኙነቶች ላይ ባለሙያ የሆኑት አርተር ሲ. ብሩክስ ሰዎች በአዎንታዊ አስተያየት አማካኝነት እንደሚያድጉና ዋጋ እንዳላቸው እንደሚሰማቸው አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። ስለዚህ፣ የትዳር ጓደኛችሁን አድናቆት በመደበኛነት በማሳየት፣ በፍቅር የተሞላ እና ደጋፊ መንፈስ ትፈጥራላችሁ።
🔑 ማጠቃለያ፦ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ደስታ ቁልፍ
የ 5:1 ሕግ የሚያሳየው ደስተኛ አጋርነት የአጋጣሚ ጉዳይ እንዳልሆነ ነው። እሱ የሚመጣው ከዐውቆ ከሚወሰዱ ውሳኔዎችና የጋራ አድናቆት ነው። በአዎንታዊ መስተጋብሮች ላይ በማተኮር፣ በፍቅር የተሞላና የተሟላ ግንኙነት ለማድረግ መሠረት ትጥላላችሁ።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 26👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
እንግሊዝኛ ቋንቋን ቤትዎ ቁጭ ብለው ይማሩ
Mark Language Academy
የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመናገር ክህሎትዎን ወይም ችሎታዎን የትም ሳይሄዱ ቤትዎ ቁጭ ብለው Face to Face በ Zoom, በቴሌግራም Video Call ወይም Google meet ላይ መማር ይችላሉ
እንዲሁም አስገራሚ ለውጥ ያመጣሉ
✅ Speaking ( ንግግር)
✅ Listening ( ማዳመጥ)
✅ Grammar ( ሰዋሰው )
✅ How to read and Write ( መፃፍ ና ማንበብ )
ሁሉንም በ5 ወር ውስጥ ብቻ ይቻሉና ራስዎን ይለውጡ
ከ ሰርተፍኬት ጋር ......
ለመመዝገብ ያናግሩን 👇
@MarkEngAcademy
☎️ 0908880599
❤ 12🔥 2
ናይጄሪያዊዉ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከነዳጅ ተቆጣጣሪ አካል ጋር ግጭት ዉስጥ ገቡ
የናይጄሪያ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ እሁድ እለት ከነዳጅ ተቆጣጠሪ አካል ጋር ያለውን ውዝግብ ጋር ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በናይጄሪያ የሚገኙ የነዳጅ ማጣሪያዎችን አደጋ ላይ የሚጥል ርካሽ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ አድርገዋል ሲሉ ዳንጎቴ ከተቆጣጣሪዉ አካል ጋር ያላቸዉን ልዩነት ገልጸዋል፡፡ናይጄሪያ በአፍሪካ ትልቁ የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገር ብትሆን ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ ናት፡፡ይህንኑ ችግር ለመቀየት የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።ዳንጎቴ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ቁጥጥር ካልተደረገባቸው ለሥራ፣ ለኢንቨስትመንትና ለኢነርጂ ደህንነት ስጋት ይሆናሉ ብለዋል።
በሌጎስ በሚገኘዉ እና በቀን 650 ሺ በርሜል የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ንግግር ያደረጉት ዳንጎቴ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች “የአገር ውስጥ አቅምን ለመፈተሽ” ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፣ ይህም ናይጄሪያ ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገዉ ሽግግር ፈተና እየሆነ ይገኛል ብለዋል፡፡ዳንጎቴ የናይጄሪያ ሚድ ስትሪም እና ዳውንስትሪም ፔትሮሊየም ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ኃላፊ ፋሩክ አህመድን በተመለከተ በዘርፉ ያላቸውን የአስተዳደር ስጋት እና የግል ወጪዎች ከህጋዊ ገቢ በላይ ናቸው በሚል ክስ ላይ ይፋዊ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
አህመድ በሚመሩት ተቋማት ላይ ለቀረበዉ አስተያየት ወዲያውኑ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም የዳንጎቴ ማጣሪያ በፔትሮሊየም ምርቶች ሽያጭ ላይ በብቸኝነት መያዝ እንደሚፈልግ ተናግረዉ ነበረ፡፡ የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካው ምርት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሊያሟላ አይችልም ሲሉ ተደምጠዋል።
Dagu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 19🤪 4
ሊቃውንት አባቶቻችን ቤተክርስቲያን የሚለው ጥምር ቃል ሦስት ፍቺ እንዳለው ይገልጻሉ፡፡
የሚጀመሪያው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእያንዳንዳችን የክርስቲያኖች አካል እንደሆነ ይነገራል፡፡
ሦስተኛው ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች ሕብረት ነው፡፡
በሕብረት ውስጥ እኛነት እንጂ እኔነት ቦታ የለውም፣ በሕብረት ውስጥ ለእኛ እንጂ ለእኔ የሚለው ሀሳብ ውሃ አያነሳም፡፡ በዚህ ህብረት ውስጥ ክርስቲያኖች አንዱ ስለሌላኛው ድህነት ይጸልያል፤ ሌላኛው ስለሁሉም ደህንነት ይተጋል፡፡ ገንዘብ ያላቸው አቅመ ደካሞቹን ያግዛሉ፤ ጸጋው የበዛላቸው ደግሞ በጸሎትና በስግደት ስለሁሉም በእግዚአብሔር ፊት ይማጸናሉ፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘውን ታላቅ የበረከት ስፍራ ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳምን የልማት ሥራ እያገዝን ያለነው በዚሁ ክርስቲያናዊ አንድነት መነሻነት ነው፡፡
እኛ ቤተክርስቲያን ነን፡፡ አንዳችን ስለሁላችን የምንጸልይ፣ ሁላችን ስለሌሎቻችን ልማት የሚገደን፡፡
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በረከት የተትረፈረፈልን ቤታችንን በእልልታ የሞላልን እኛ በክርስቶስ አንድ አካል ነንና በዚህ የጾም ወቅትም መልካም ስራዎቻችንን እናጠናክር።
ቪዲዮውን ያድምጡት፤ ይመልከቱት🙏
❤ 36
Photo unavailableShow in Telegram
የኢንተርኔት ንግድን ወደ ግብር‼
ገቢዎች ቢሮ የኢንተርኔት ንግድን ወደ ግብር ሥርዓቱ የሚያስገባ አሠራር መዘርጋቱን አስታወቀ
: በአዲስ አበባ ከተማ ግብር የማይሰበሰብበት የኢንተርኔት (ኦንላይን) ንግድ እየተስፋፋ በመሆኑ ዘርፉን ወደ ግብር ሥርዓት ለማስገባት የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ፣ የማኅበራዊ ሚዲያው እየፈጠረ ባለው ተፅዕኖ የተነሳ፣ በአሁኑ ወቅት የኦንላይን ንግድ በከተማ እየተስፋፋ መሆኑን፣ ከፍተኛ የግብይት እንቅስቃሴ የሚከናወንበትና ሰፊ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እየሆነ መምጣቱን፣ ነገር ግን ቁጥሩ ይኼ ነው ብሎ ለመናገርና ምን ያህል ግብር አሳጥቷል የሚለውን ለማወቅ ጥናት ማድረግ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።
@Addis_News
@Addis_News
🤪 22❤ 16🤔 5🤣 3👍 1💯 1😨 1
ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲሾሙ፡፡
መንግስታዊው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር) የባንኩ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር ) ለአንድ ዓመት የባንኩ ፕሬዝዳንት በነበሩት እመቤት መለሰ (ዶ/ር) ምትክ ተሾመዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰራተኞች የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን መሾማቸውን ባንኩ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቦርድ አባልነት ደግሞ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር)፣ ስዩም መኮንን፣ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ አቶ ሃቢብ መሀመድ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማርታ በለጠ እና ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) መመረጣቸውን በመግለጽ ለሁሉም ተሿሚዎች መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል።
ባንኩን ለአራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት ዮሐንስ አያለዉ ( ዶ/ር) በግል ምክንያት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ዶ/ር እመቤት መለሰ ከጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ሆነዉ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 19
እናት እና ልጅ ምሳ ከበሉ በኋላ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት በተከታታይ ሰዓት ሕይወታቸው አለፈ
👉 ፖሊስ የአሟሟታቸውን ሑኔታ በጥልቅ እየመረመረ ይገኛል
እንደ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ገለፃ እናት እና ልጅ ምሳ ከበሉ በኋላ በተከታታይ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡
እናት እና ልጅ ታህሣስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት ተኩል መስጊድ ሰላት ቆይተው ወደቤታቸው ገብተው ምሳቸውን ከበሉ በኋላ እናት ሻወር ለመውሰድ ሻወር ቤት ሲደርሱ አረፋ በመድፈቅ እና በመወራጨት ሲወድቁ የተመለከተች ልጅ በድንጋጤ በመጮህ የአካባቢው ሠው ሲደርስ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጥዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ከሰዓት ቆይታ በኃላም ልጅ እንደ እናቷ ከአፏ አረፋ በመድፈቅ ስትወድቅ ወደ ካራሚሌ ሆስፒታል ለህክምና ብትላክም በህክምና ላይ እያለች ህይወቷ አልፏል።ፖሊስ የሟቾችን አስክሬን ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የላከ ሲሆን በተጨማሪ ለምሳ የተመገቡትን ምግብ እና የጠጡትን ውሀ ናሙና ለኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለ ስልጣን በመላክ ስለ አሟሟታቸው ምክንያት ሰፊና ጥልቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡
@Addis_News
@Addis_News
😢 37❤ 16💔 5👍 2
