ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
Відкрити в Telegram
| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና | የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል! የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ "የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው " https://www.youtube.com/user/TheNahusenai Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc
Показати більше10 829
Підписники
-824 години
-237 днів
-14230 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም ዜና!
👉ኖቫ ማሰልጠኛ ተቋም 100% በተግባር የተደገፈ የዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) ስልጠና ተመርቃችሁ ስራ እየፈለጋችሁ ላላችሁ ወጣቶች፣ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም ለቢዝነስ ባለቤቶች የሚሆን ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡
ስልጠናው መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕውቀት፣ ዲጂታል አይደንቲቲ፣ ኮንተንት ክርኤሽን፣ በማህበራዊ ሚዲያ አልጎሪዝም (TikTok, facebook, YouTube…) ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች እንዲሁም፣ መሰረታዊ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ላይ ያተኩራል፡፡
🖼ስልጠናውን⏰በጠዋት (3-5)፣ በከሰአት(8-10) ወይም በማታ(12-2) ፈረቃ መከታተል ይችላሉ፡፡
📌ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡ #ለሰልጣኞች በሙሉ ሰርተፍኬት እንሰጣለን እንዲሁም #የስራና #ኢንተርንሺፕ እድል እናመቻቻለን።
ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ ☎️ 0991311111/ 0912664084 ይደውሉ፡፡
🏠አድራሻ ፦ ቦሌ ብራስ ከቦራ ፖርክ ፊት ለፊት (ብሪቲሽ ስኩል አጠገብ)
❤ 7👏 2
የትብብር ጥያቄ!
ይህንን መልዕክትና ጥያቄ ቢያንስ ባላችሁበት አንድ የቴሌግራም ግሩፕና ለአምስት ጓደኞቻችሁ አድርሱልኝ?
😔🙏😔
=======================
፩. በዚህ ምድር ላይ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ቢሆን ኑሮ አሁን ምን ታደርጉ ነበር?
፪. በጣም የምትወዱት/ የምታፈቅሩት ሰው ዛሬ የመጨረሻው ቀን ቢሆን ምን ታረጋላችሁ?
=======================
ይህንን ጥያቄ ሳትመልሱ እንዳትተኙ
መልካም አዳር!
@Psychoet
❤ 13👏 7
በጣም ጠቃሚ ምክር ስለሆነ ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው፣ ፔጁንም ፎሎ ያድርጉ
1. ተስፋ አድራጊ መሆን ረጅም ርቀት ይዞህ ይሄዳል፡፡
በጣም አስከፊ በሆኑ ጊዜያት እንኳ ተስፋ ባለመቁረጥ ችግሮችን መጋፈጥና ለመቀየር መቁረጥ የመፍትሄ መላ እንዲመጣልን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጨለምተኛ አትሁን፡፡ከፈተና ባሻገር የሚገኘውን ድል አስብ።
2. መርህ፣ አቋም፣ ያመንክበት ጉዳይ ይኑርህ ነገር ግን ለመስተካከል ቦታ ይኑርህ፡፡
በደረስክበት እውቀት መሰረት በነገሮች ላይ አቋም ሊኖርህ ይገባል፡፡ ነገር ግን የህይወት ዘመን ሁሉ ተማሪ ከሆንክ በአንድ ወቅት የያዝከው አቋም ትክክል እንዳልሆነ ስትረዳ ያመንክበትን ጉዳይ ማስተካከል ይኖርብሃል፡፡
3. አዋዋልህን እና ጓደኞችህን ምረጥ፡፡
አስተሳሰብህን እና ድርጊትህን በገንቢ ጎን ከሚተቹና ከሚገነቡ ሰዎች ጋር የምታደርግ ከሆነ በየጊዜው እየተሻሻልክ የምትሄድ ሰው ትሆናለህ፡፡ ባህሪህ እና ህይወትህ እያደር የሚመስለው የጓደኞችህን ነው፡፡
4. መሆን የምትፈልገውንና መስራት የምትፈልገውን በጊዜ አውቀህ ጀምር፡፡
በወጣትነት ጀምረህ መርጠህ የምትሄበት መንገድ እያደር አንተንም እየቀረፀህ ስለሚሄድ በዛው የመቀጠል እድል ይጨምርልሃል፣ አይቻልም ለሚሉህ በቀላሉ ላትሸነፍ ትችላለህ፣ በእድሜህ ብዙ ሳትገፋ ስኬታማ እና ብዙ ተፅእኖ አምጪ ትሆናለህ፡፡ የራስህን ራእይ የማትገነባ ከሆነ ሌሎች ቀጥረውህ ራእያቸውን እንድትገነባላቸው ያደርጉሃል፡፡
5. ከሌሎች ጎበዞች ጋር በጥምረት ስራ፡፡
ከጎበዞች ጋር በጥምረት ስትሰራ አንተ የማታውቃቸውን ነገሮች ያሳውቁሃል፣ አንተ ልታገኛቸው የማትችላቸውን ሰዎች እንድታገኝ እድል ይከፍቱልሃል፣ ይበልጥ ወደፊት ያራምዱሃል፡፡
6. በቅፅበት ከፍተኛ ደረጃ እደርሳለሁ አትበል፡፡
ከትምህርት ቤት አንደወጣህ ወዲያው ሃብታም፣ ባለስልጣን፣ ወይም ስኬታማ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ቢኖርህ እንኳ ስኬታማ ለመሆን ብዙ ልምድ ያስፈልግሃል፡፡
7. ስለ ስህተቶችህ ሌሎችን ሳይሆን ራስህን ውቀስ ተማርባቸው፡፡
ስህተቶች እንድንቆጭባቸው ሳይሆን እንድንማርባቸው ካደረግን ደግመን አንሰራቸውም፡፡
8. ምርጡ ትምህርት ቤት ኮሌጅ ሳይሆን ህይወት ነው፡፡
ምንም ያህል መፅሀፎች ብታነብ፣ ፈተናዎችን ብትወስድና ብታልፍ፣ በህይወት ሂደት የምትማረውን ያህል ብቁ አያደርጉህም፡፡ ስራዎች እና የስራ ሃላፊዎች ያስተምሩሃል፣ ያበቁሃል፡፡
9. ህይወት ሁሌም የቀና አይደለም፡፡
በህይወት ጉዞህ ትገጫለህ ትወድቃለህ፡፡ ኑሮ ፈተና ነው፣ ጌም መሳይ ነው፣ ተነስተህ እስኪሳካልህ ጉዞህን ቀጥል፡፡
10. ለስኬታማነት ትእግስት እና ጠንክሮ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ዘላቂ ስኬት የለም፡፡
11. ለራስህ ክብር ይኑርህ፣ በማንነትህ ኩራ፡፡
እያንዳንዳችን የተለያየን ስለሆንን ራስህን ከሌላው ጋር እያወዳደርክ ዝቅተኝነት አይሰማህ፡፡ በሌላው ውስጥ የሌለ አንተ ውስጥ ያለ ችሎታ ስላለ ፈልገህ አግኘው፣ ተቀበለው፣ እዛ ላይ አተኩር፣ አዳብረው፣ በራስህ ተማመን፡፡ ስኬታማ የምትሆነው በዚህ መንገድ ነው፡፡
12. ራስህን አታሳብጥ፡፡
ስኬታማና ታላቅ የመሆን ራእይ መሰነቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ ብትወጣ ነገ ደግሞ ታች መውረድ ሊገጥምህ ይችላል፡፡ ላይ መውጣትህ የብዙ ነገሮች ጥምር ውጤት ስለሆነ ራስህን አይነኬና ልዩ ፍጡር አድርገህ አታስብ፡፡
13. "ደሃ ሆነህ ተወልደህ ከሆነ ጥፋቱ የአንተ አይደለም፤ደሃ ሆነህ ልትሞት ከሆነ ግን ጥፋቱ የአንተ ነው"።
#ኢትዮጵያዊነት#
ፔጁን Follow ማድረግ እንዳትረሱ
ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው
@psychoet
❤ 26👍 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🙏🙏የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ
➵ በ3ኛ ቀን ጥፍሩ መነቃቀል ይጀምራል
➵ በ4ኛ ቀን ጸጉሩ ይራገፍና ጭንቅላቱ ባዶ ይቀራል
➵ በ5ኛ ቀን አእምሮው እንደ ቅቤ መቅለጥ ይጀምራል
➵ በ6ኛ ቀን ቆዳው ጠቁሮ መላላጥ ይጀምራል
➵ በ7ኛ ቀን የውስጥ አካሉ ሁሉ ይበሰብስና #እጅግ በጣም መሽተት ይጀምራል!
➵ በ60ኛ ቀን ሥጋ ሁሉ ሸሽቶት ብዙ አጥንቶች ብቻቸውን ይቀራሉ 🙏🙏🙏
እና ታዲያ ይህን እያወቅን
👉ከኩራት
👉 ከስግብግብነት
👉 ከክፋት
👉 ከጥላቻ
👉 ከራስ ወዳድነት
👉 ከተንኮል ... ምን እናተርፋለን? ለምን?
#በነገሮች_ሁሉ _ትሁት_እንሁን
ይህቺ የምናያት ህይወት እኮ ከንቱ ናት። ከዚህ ዓለም ስንለይ ወደ ዘላለም ህይወት ወይም ወደ ዘላለም ሞት መሄድ ምርጫችን ነው! ደግሞም ይህ #እውነታ አይካድም።
❣️ ፈጣሪአችንን እንውደድ፥ እንፍራም
❣️ እርስ በርሳችን እንዋደድ
❣️ ለሌሎች መልካም እንሁን
❣️ አንቅና
❣️ ሁሌም ደግነትን እናድርግ፤ ጉዳት የለውምና
❣️ ያንተ ያልሆነውን ነገር ከሌሎች አትቀማ!
#ሼር እንዳይረሳ ❣️❣️❣️❣️
ሳሙኤል ጥሩነህ
❤ 45👍 3👏 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የማያዛልቃችሁን ሰው ለዩ!
በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ሼር አድርጉት
ከሚከተሉት ባህሪያት ቢያንስ አንዱን የምታዩባቸው ሰዎች ምናልባት ብዙም የማያዛልቋችሁና አንድ ቀን ለስሜት ጉዳት አጋልጠው የሚሰጧችሁ አይነት ሰዎች እንደሆኑ ጠርጥሩ፡፡
• ራሳችሁንም ሆነ ያላችሁን ነገር በነፃ ስላቀረባችሁላቸው፣ ልክ እንደ ርካሽ የሚቆጥሩና የማያመሰግኑ ሰዎች፡፡
• በዓላማችሁና ለማደግ በምታደርጉት የየእለት ጥረት የሚያላግጡና የሚያሾፉ ሰዎች፡፡
• እየጠፉና እየቆዩ ለአንድ ነገር አማራጭ ሲያጡና ያንን ነገር ከእናንተ ብቻ እንደሚያገኙ ሲያውቁ ብቻ የሚፈልጓችሁ ሰዎች፡፡
• እናንተንና ወዳጅነታችሁን ሳይሆን የእናንተንና ያላችሁን ነገር ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች፡፡
• በፍጹም የማያምኗችሁ ሰዎች፡፡
• ስህተታችሁን እየቆጠሩ የሚወቅሷችሁና በፍጹም ይቅር የማይሏችሁ ሰዎች፡፡
• ስህተታቸው እንዳይገኝባቸው እናንተን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች፡፡
• ሰዎችን ለእናንተ የሚያሙና ስለሰው ክፉን የሚያወሩላችሁ ሰዎች፡፡
• እናንተ የጀመራችሁትን ነገር እነሱ እንደጀመሩት አድርገው ለማሳየት የሚጣጣሩ ሰዎች፡፡
• ለእነሱ መኖር፣ መስጠትና መልካም ነገር ማድረግ፣ ልክ እንደ ግዴታችሁ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች፡፡
(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
👍 27❤ 16
Repost from TgId: 3082977446
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም የጥቅምት ወር ይኹንላችሁ!
🧭 Compass Properties🧭
🔗የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
TikTok:https://www.tiktok.com/@compass_properties
Facebook:https://www.facebook.com/Compasspropertieset
Telegram: t.me/Compass_properties
#realestateinAddisAbaba #Apartment #Houseforsale
❤ 3
Repost from TgId: 3082977446
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም የስራ ሳምንት
🧭 Compass Properties🧭
🔗የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
TikTok:https://www.tiktok.com/@compass_properties
Instagram & Thread:https://www.instagram.com/compassproperties.et
Facebook:https://www.facebook.com/Compasspropertieset
Telegram: t.me/Compass_properties
❤ 10
Repost from TgId: 3082977446
Фото недоступнеДивитись в Telegram
✨🎁 መልካም ሰኞ!
🔗 ገጻችንን ይቀላቀሉ
Tlegram: t.me/Compass_properties
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram t.me/psychoet
‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!
1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡
2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::
3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡
4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡
5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::
6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡
7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::
8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡
9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡
10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::
በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!
(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist
Telegram t.me/psychoet
❤ 19👏 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ባልተለወጠ አስተሳሰብ የተለወጠ ዓመት ለውጥ የለውም!
@psychoet
❤ 22👏 4👍 3
ለፔጃችን ቤተሰቦች በሙሉ፣
እንኳን ለኢትዮጵያውያን 2018 ዐዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ፣
ከፊታችን ባለው 2018 አመት እንደ ሀገር 🌘ብዙ እድሎችና እጅግ ብዙ ተግዳሮቶች የሚገጥሙን አመት እንደሆነ ይጠበቃል። ስለሆነም፥ እድሎችን በአግባቡ በመጠቀም የሚገጥሙንንም ተግዳሮቶች በብልሀት በማለፍ አመቱን በስኬት እንድናጠናቅቀው ፈጣሪ ይርዳን።
ለኹላችሁም የቻናሉ ቤተሰቦች መልካም ዐዲስ አመት እንዲኾንላችሁ እመኛለሁ 🌼🌼🌼
@psychoet
❤ 14👍 9
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ሳይኮሎጂ | ብዙ ያስተማረኝ የቤት ውስጥ ገጠመኝ🏠
አንብባችሁ #ሼር አድርጉት
ባለፈው ሳምንት እቤት ውስጥ ተቀምጬ ስራዬን በመስራት ላይ ሳለሁ አንዲት ቢራቢሮ መጋረጃ ላይ ስታርፍ ተመለከትኩ ፡፡ ከዛ ተመልሳ ሳትበር በፊት ቀስ ብዬ ተጠጋሁና ይሄን ምስል በስልኬ አስቀረሁ ፡፡
ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ፎቶውን ሳየው ብዙ ቁም ነገር አገኘሁበት ፡፡ ለካ ሲያስተውሉ ብዙ ትምህርት ይገኛል ፡፡ ስዕሉ ሁለት ቢራቢሮዎች መጋረጃ ላይ አርፈው ያሳያል ፡፡ አንዱ እውነተኛ ( Real ) ፣ አንዱ ሀሰተኛና ተመሳስሎ የተሰራ ( Fake ) ነው ፡፡ በዙሪያችን ያለው ነገርም ከዚህ ይለያል ብዬ አላስብም ፡፡ በእውነተኞች መካከል ውሸተኛና አስመሳዮች፣ በውሸተኞች መካከል እውነተኞች ይኖራሉ ፡፡ የተደበላለቀ ዘመን ፣ የተደበላለቀች አለም፡፡
ይህን ፎቶ ለሚመለከት ሰው ጎልታ የምትታየው ቢራቢሮ ቀድማ ቀልቡን እንደምትገዛ ጥርጣሬ የለም ፤ ግን አንድ ነገር ስለተለቀ ፣ ስላማረ ፣ ስላንፀባረቀ ፣ አይን ውስጥ ስለገባ ወይንም ብዙ ቦታ ስለያዘ እውነተኛ ነው ማለት አይደለም ፡፡ ምክኒያቱም 'እውነት' እውነት የምትሆነው በአብላጫ ድምፅ ሳይሆን በማንነቷ ምክኒያት ነው ፡፡ እውነት ግዑዝ አይደለችም ፣ ሕይወት አላት ፤ የደከመች ፣ ያረፈች ፣ የተዋጠች ብትመስልም መነሳቷ ፣ መብረሯ አይቀርም፡፡
👏 22❤ 9👍 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ችግሮችን መጋፈጥ ወይስ መሸሽ ?
የግልም ሆነ የጋራ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በሚያጋጥሙ ጊዜ፤ በተለያየ መንገድ ለችግሩ ምላሽ እንሰጣልን፡፡ አንዳንዴም ስለተፈጠረው ችግር ማሰብ ከሚያስከትልብን መጥፎ ስሜት ለመገላገል ስንል መፍትሄ ከማፈላለግ ይልቅ ሽሽትን የምንመርጥ ብዙዎች ነን፡፡ በቀላሉ መፍታት የምንችለውን ችግር ስንሸሸው ደግሞ ችግሩ ተልቆ ለህይወታችን አስጊ ሁኖ ይመጣል ፡፡ መፍትሄ ሳናገኝ ሆነ ብለን ወደ ጎን የምንተው ከሆነ፤ ከጊዜያዊ መጥፎ ስሜት እራሳቸንን እየተከላከልን እንጅ ችግሩን እያባባስነው እንደሆነ መገንዘብ ይገባል፡፡
እንደ ምሳሌ :- በሕይወታችን ብዙ የፍላጎት ግጭት ማለትም ሁለት ነገር ወደን ግን አንዱን ብቻ የመምረጥ ግዴታ (Conflict of interest ) በሳይኮሎጂ (Approach -Approach )የምንለው ይገጥመናል ፡፡ በዚህ ጊዜ በስልት ነገሩን ከመፍታት ይልቅ ከሁለቱም ሳንሆን በድብርትና በአለመቻል ስሜት እንጠቃለን ፡፡
_____
ነገ ቅዳሜ በሚጀምረው ስልጠና በተጨማሪ ብዙ የተለያዩ ስልታዊ የሕይወት ችግር መፍቻ መንገዶችን እንዴት በተግባራዊ መንገድ እንደምናዳብር ከአንድ ሳምንት ልምምድ ጋር እንመለከታለን
ለመመዝገብ +251912664084 አሁኑኑ ይደውሉ
__
@psychoet
❤ 13👍 2
ጥቂት ቦታዎች ቀርተውናል፡፡
👉ለስድስት ሳምንት የሚቆይ ተግባራዊ የህይወት መምሪያና የስነልቦና ስልጠና 14ኛ ዙር
-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ስራ ፈጠራ
-ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም
-ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች
-ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።
በ#2500 ብር !
★ልምድ ባላቸው ሳይኮሎጂስቶችና የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች ይምጡ ይሰልጥኑ።
★ሁሉንም ለሚካፈል በነፃ የግል የማማከር ጊዜ ፣ የንግግርና የተግባቦት ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።
#ሀምሌ 19 ይጀምራል ። ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድሞ ለተመዘገበ በፈለጉት ፈረቃ የመሰልጠን ቅድሚያ እንሰጣለን ፡፡
በአካል መመዝገብ ያልቻላችሁ በስራ ሰአት ( ሰኞ - አርብ ) በስልክ በመደወልና መረጃዎችን በመላክ መመዝገብ ይቻላል ፡፡0912664084 ይደውሉ።
ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ ጠዋት 3-5 / ቅዳሜ ከሰአት 9 - 11
አድራሻ: ቦሌ ብራስ፣ ቦራ ፖርክ ፊትለፊት (British School) አጠገብ- ዛሙ ፈርኒቸር ህንፃ ቁጥር 206
ስልጠናውን መካፈል ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው @Psychoet
❤ 3👍 3
ማኅበራዊ ፍርሃት
Join My Telegram Channel t.me/Psychoet
ይህን ጠቃሚ ትምህርት #Share እናድርገው
✍ማኅበራዊ ፍርሃት #ብዙ_ሰው_በተሰበሰበበት ቦታ ለመናገር ወይም አንድን ድርጊት ለመፈጸም በተዳጋጋሚ የሚፈጠር በብዙ ግለሰቦች ላይ የሚስተዋል #ምክኒያታዊ_ያልሆነ_ፍርሃት ነው፡፡ ይህ #የጭንቀት ዓይነት ያለባቸው ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ንግግር ያለበት ተግባር አጥብቀው #ይሸሻሉ ምክኒያቱም አይደለም ንግግር አድርገው ገና ለማድረግ ሲያስቡ የሚሰማቸው #የፍርሃት ወይም #የጭንቀት_ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ፡፡ ከህጻናት በስተቀር ማኅበራዊ ፍርሃት ያለባቸው ሰዎች ፍርሃታቸው ምክኒያታዊ እንዳልሆነ ይረዳሉ ምንም እንኳን ይህ ከፈርሃታቸው ባይታደጋቸውም፡፡
★እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች ናቸው፡-
1.ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ አጥብቆ መፍራትና በትምህርት ገበታም ሆነ በስራ ቦታ የተዘጋጁትን በአግባቡ ማቅረብ አለመቻል
2.እንደ ካፌ፣ ሬስቶራንት፣ ቤተ-መጻሕፍትና ሌሌች ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሰዎች እኔን እየተመለከቱኝ ነው ብሎ መሳቀቅ ፣ ከልክ በላይ አንገት አቀርቅሮ መጓዝ
3.ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ በሚያስቡበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ይተቹኛል ብሎ ማሰብ
4.ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ሲያደርጉ በላብ በጠመቅ ወይም ልዋረድ እችላለሁ ብሎ በፍርሃት ማሰብ
5.ብዙ ሰው ባለበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ የሆነ ያልሆነ ምክኒያት በመደርደር እራስን ማቀብ
6.አዲስ ሰው ጋር ለመገናኘት ተደጋጋሞ የሚከሰት ፍርሃት
7.ብዙ ሰው ባለበት ቦታ ምግብ በሚመገቡት ጊዜ ትንታ ወይም መታነቅ እንዲሁም ምግቡ ሊዝረከርክብኝ ይችላል ብሎ መፍራት
8.ከእነዚህ ጋር ተዛምዶ የሚከሰት እንደ የልብ ምት መጨመር፣ ላብ ላብ ማለት፣ የሰውነት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት ፍርሃት ወለድ አካላዊ ለውጦች ናቸው፡፡
፠፠፠ መፍትሄ ፠፠፠
1.የአስተሳሰብ ለውጥ፡- ብዙ ጊዜ ማኅበራዊ ፍርሃት እንዲከሰት የሚያደርጉ ከበስተጀርባ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ፍርሃት መከሰት አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ ምክኒያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ አስተሳሰቦችን ነቅሶ በመለየትና በአዎንታዊ አመለካከት መተካት፡፡
2.መለማመድ፡- ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ መናገር ስለሚያስፈራን ንግግር የምንሸሽ ከሆነ የፍርሃቱ መጠን እንዲጨምር መፍቀድ ነው፡፡ ከሸሻችሁት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው መቼም ቢሆን ከዚህ ችግር እንደማትገላገሉ ነው፡፡ ስለዚህ እራስን ቀስ በቀስ ማለማመድ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡ ለምሳሌ ለተማሪዎች የምታቀርቡት ንግግር/Presentation ካለ፣ መጀመሪያ ብቻችሁን ማንም በሌለበት ነገር ግን ብዙ ሰው ክፍሉ ውስጥ እንዳለ በምናብ በማሰብ ማቅረብ፡፡ ከዚያም የተወሰነ ሰው በተለይም የምናውቃቸው ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባላት ፊት ለፊት ማቅረብ፡፡ በመጨረሻም ዋናውን ንግግር ማቅረብ ነው፡፡ ይህ የስራ ቅጥር ቃለ መጠይቅና ሌሌች ሁኔታዎች ላይም ያገለግላል፡፡
✍ለምሳሌ ቲያትር ሰሪዎችን ብንመለከት የተሰጣቸውን ገፀባህሪ በአንዴው መድረክ ላይ መተው በብዙ ሺ ለሚቆጠር ህዝብ አያሳዩም ይልቁንስ በመጀመሪያ ለብቻቸው የሚናገሩትን አጥብቀዉ ለብዙ ጊዜ ይለማመዱና በመድረክ ደግሞ አስቀድመው ካላገኙት ሌላ ገፀባህሪ ጋር ደግመው ደጋግመው ይለማመዱታል ፡፡ በመጨረሻም ከብዙ ውጣ ውረድና ከሙያ አጋሮች አስተያየት በኀላ የተሰጣቸውን አሪፍ አርገው ያቀርቡታል ፡፡ ለዚህ ሁሉ መነሻ ግን እቤታቸው ለብቻቸው ሁነው የተለማመዱት ነው ፡፡
3.ስራ ላይ ማተኮር፡- ብዙ ጊዜ የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ከሚሰሩት ስራ ይልቅ ሌሎች ሰዎች ስለሚሰጧቸው አስተያየትና ምላሽ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ እዚህ ላይ መታሰብ ያለበት ከስራው ይልቅ አድማጭ ተመልካች ላይ የምናተኩር ከሆነ መጀመሪያ በተገቢው ስራን መስራት እንችልም ምክኒያቱም ቀልባችን ሌሌች ሰዎች ላይ ነውና፡፡ ሲቀጥ ልሌሎች ሰዎች ላይ ስናተኩር የበለጠ ስለፍርሃት ስሜታችን ላይ እንድናተኩርና የበለጠ አሉታዊ ሃሳቦች እንዲፈጠሩ ይገፋፋል፡፡
4.ጡንቻን ማዝናናት መለማመድ፡- ከውስጥ ከሆድ መተንፈስ በመለማመድ ጭንቀቱ የሚፈጥረውን የረብሻ ስሜት መቀነስ፡፡ ይህ በጣም ቀላልና የትም ቦታ ሊለማመዱት የሚችሉት ዘዴ ነው፡፡ ለተወሰነ ደቂቃ (እስከ 10 ሴኮንድ) ወደ ውስጥ በመተንፈስ ትንፋሽህን መያዝ ከዚያም መልቀቅ፡፡ እንደገና ወደ ውስጥ ትንፋሽን በመያዝ አሁንም ወደ ውጪ መተንፈስ፡፡በተደጋጋሚ ይህን በማድረግ የጭንቀት ስሜቱን ማቅለል ይቻላል፡፡ ይህን ዘዴ ጭንቀቱ ቀለል እሰከሚልድረስ መከወን ይቻላል፡፡
5.የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና መውስድ፡- እንደ ዓይንን እየተመለከቱ ማውራት፣ ፈገግታ፣ የንግግር ፍሰትን መጠበቅና የመሰሳሰሉት ልምምዶች በንግግርና በሌሎች ማህበራዊ ተግባቦት ላይ ውጤታማነታችንን ሲለሚጨምሩ ለወደፊት የበለጠ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ መናገርና ሌሌች ተግባሮችን ለመፈጸም አወንታዊ ማበረታቻዎች ናቸው፡፡
★★★ከዚህ ጋር በተያያዘ ሥነልቡና ፔጅ የተዘጋጀውን የአንድ ወር ተግባራዊ ልምምድ ስልጠና ብትካፈሉ ብዙ የአመለካከትና የባሕሪ ለውጥ እንደምታመጡ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ 2 ቀን በቀረው ስልጠና ባሉት ጥቂት ቦታዎች አሁኑኑ ደውለው/ በአካል ቢሮ በመምጣት ይመዝገቡ +251946333951
# ★★★
6.ሌላው presentation ሲኖርብን ከመስታወት ፊት በመቆም በደንብ መለማመድ ፣ ስናወራ ምን እንደምንመስል ማየትና ራሳችንን እያረምን ደጋግሞ መለማመድ ፡፡ በተጨማሪ ደፋር ሰዎች ራሱ ብንሆን አንዳንድ ያልተዘጋጀናቸውን ነገሮች ስናቀርብ / ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ ስንገኝ ፍርሀት ሊከሰት ስለሚችል ሁልጊዜ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅብናል ደግሞም ከልክ ያለፈ በራስ መተማመንም ማስወገድ መልካም ነው ፡፡
የፍርሃት ስሜት ወይም ጭንቀት የዕለት ተዕለት ህይዎታችን በደስታ እንዳንመራ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማኅበራዊ ፍርሃትም እንደዚሁ በህይወታችን ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽኖ ይኖራል፡፡ ለችግሩ መፍትሄ ማፈላለግ እንጂ ለምን ይህ ተከሰተብኝ ብሎ እራስን መኮነንና ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ምክኒያቱም ምንጩ እኛ ሳንሆን አስተዳደጋችን ፣ አካባቢያችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ሊሆኑ ይችላሉና ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፍረሀት ያላችሁ ሰዎች የጠቀስኳቸውን ነገሮች በደንብ ተግባራዊ አድርጉ ፡፡ ጥያቄ ካላችሁ ጻፉልኝ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ ።
(በአሸናፊ ካሳሁን እና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
በቴሌግራም በዚህ አግኙኝ t.me/Psychoet
በተለያዩ ማህበራዊ ፍርሀት ያለባችሁ በተለይም ወጣቶች 2 ቀን በቀረው ስልጠና ባሉት ጥቂት ቦታዎች አሁኑኑ በመደወል / በአካል ቢሮ በመምጣት ይመዝገቡ +251912664084
ስልጠናው ያሁኑ ቅዳሜ ጠዋት እንዲሁም አሑድ በመረጡት ፈረቃ ይጀምራል ።
❤ 11👍 1👏 1
#ሳይኮሎጂ| ለለውጥ መነሳሳት
በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡
1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”
3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡
4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡
5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡
6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡
7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡
8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡
9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡
10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡
t.me/psychoet
❤ 12👍 6
