TIKVAH-MAGAZINE
Відкрити в Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
Показати більше194 690
Підписники
-7124 години
-977 днів
-64730 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሩዋንዳ በምስራቃዊ ኮንጎ እየፈፀመች ያለችው ተግባር የሰላም ስምምነቱን የጣሰ እንደሆነ አሜሪካ አስታወቀች።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ በምስራቃዊ ኮንጎ ሩዋንዳ የምትፈፅመው ተግባር ከሳምንት በፊት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱን ሃገራት ያፈራረሙትን የሰላም ስምምነት የጣሰ ነው ብለዋል።
ሩቢዮ" የሩዋንዳ የምስራቃዊ ኮንጎ ተግባር በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተፈረመውን የዋሽንግተን ስምምነት የጣሰ ነው፤ አሜሪካ ለፕሬዚዳንቱ የተገቡ ቃሎች መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ እርምጃ ትወስዳለች" ብለዋል።
በተመሳሳይ አሜሪካ አርብ በነበረ የተመድ ስብሰባ ላይ ሩዋንዳ በምስራቃዊ ኮንጎ ያለውን ግጭት እያባባሰች ነው ሰትል ከሳታለች።
ስምምነቱ ተፈርሞ ብዙም ሳይቆይ የኮንጎው ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሼስኪዲ ሩዋንዴ የኤም 23 ታጣቂዎችን ከባድ ጥቃት በመደገፍና እራሷም ጥቃት መፈፀሟን መናገራቸው ይታወሳል።
ሩዋንዳ በበኩሏ ቡሩንዲና ኮንጎ ቀጣናውን እየረበሹ ነው ብላ ስትወነጅል፣ በእሷ የሚደገፉት የኤም 23 ታጣቂዎችም ኮንጎን ከቡሩንዲ የሚያገናኝ ቁልፍ ከተማ መያዛቸውና በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተዘግቧል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 54😢 10👍 6👎 2🤔 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሩዋንዳ በምስራቃዊ ኮንጎ እየፈፀመች ያለችው ተግባር የሰላም ስምምነቱን የጣሰ እንደሆነ አሜሪካ አስታወቀች።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ በምስራቃዊ ኮንጎ ሩዋንዳ የምትፈፅመው ተግባር ከሳምንት በፊት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱን ሃገራት ያፈራረሙትን የሰላም ስምምነት የጣሰ ነው ብለዋል።
ሩቢዮ" የሩዋንዳ የምስራቃዊ ኮንጎ ተግባር በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተፈረመውን የዋሽንግተን ስምምነት የጣሰ ነው፤ አሜሪካ ለፕሬዚዳንቱ የተገቡ ቃሎች መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ እርምጃ ትወስዳለች" ብለዋል።
በተመሳሳይ አሜሪካ አርብ በነበረ የተመድ ስብሰባ ላይ ሩዋንዳ በምስራቃዊ ኮንጎ ያለውን ግጭት እያባባሰች ነው ሰትል ከሳታለች።
ስምምነቱ ተፈርሞ ብዙም ሳይቆይ የኮንጎው ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሼስኪዲ ሩዋንዴ የኤም 23 ታጣቂዎችን ከባድ ጥቃት በመደገፍና እራሷም ጥቃት መፈፀሟን መናገራቸው ይታወሳል።
ሩዋንዳ በበኩሏ ቡሩንዲና ኮንጎ ቀጣናውን እየረበሹ ነው ብላ ስትወነጅል፣ በእሷ የሚደገፉት የኤም 23 ታጣቂዎችም ኮንጎን ከቡሩንዲ የሚያገናኝ ቁልፍ ከተማ መያዛቸውና በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተዘግቧል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
#WeeklyNewsQuiz #Leaderboard
😀 | @tikvahethmagazine
#Update
የሳምንቱን መረጃዎች በጥያቄ መልክ አቅርበን ከመቶ በላይ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል።
በዚህ ሳምንት ጥያቄ መልስ (10/10) 🎉 ያመጡ ቤተሰቦቻችን ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፤ ስለተሳትፏችሁ ሁላችሁንም እናመሰግናለን 👏
#WeeklyNewsQuiz #Leaderboard
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 29👍 1👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ናሚቢያ በሃገሯ ከተሰጣቸው ጊዜ በላይ የቆዩ የውጪ ሃገር ዜጎች ለቀው እንዲወጡ የአንድ ወር ጊዜ ሰጠች።
ናሚቢያ በሰጠችው ጊዜ ለቀው የማይወጡ የውጪ ሃገር ዜጎች እስር እና ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብላለች።
ውሳኔው በሃብት ላይ እየደረሰ ያለውን መጨናነቅ ተከትሎ የመጣ ነው ያለችው ናሚቢያ በሚቀጥሉት 30 ቀናት በፈቃዳቸው ለቀው የሚወጡ ሰዎች ያለ ምንም የህግ ቅጣት በ120 ሰዓታት ናሚቢያን ለቀው ይወጣሉ ብላለች።
ከተፈቀደላቸው ጊዜ በተጨማሪ 30 ቀን የቆዩ የውጪ ዜጎች ለአንድ አመት ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ አግዳለሁ ያለቸው ናሚቢያ ከ30 ቀን በታች የቆዩ ለ6 ወራት ወደ ናሚቢያ ተመልሰው እንዳይገቡ ይታገዳሉ ብላለች።
ዘገባው የXinhua ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 33🤣 8👍 7👎 6
ጊነስ የአለም ሪከርዶች የኬንያዊቷን ለ48 ሰዓታት ዛፍ አቅፎ የመቆየት ተግባር በሪከርድነት መዝግቧል።
ትሩፊና ሙቶኒ የተባለች ኬንያዊት ከፈረንጆቹ ጥር 31 እስከ የካቲት 2 ድረስ ለሁለት ቀናት ያህል ዛፍ አቅፋ መቆየት የቻለች ሲሆን ጊነስ ይህንን በሪከርድነት መዝግቧል።
ምንም እንኳን ጊነስ ለየካቲቱ ሪከርድ አሁን ገና እውቅና ቢሰጣትም ሙቶኒ ከቀናት በፊት ለሶስት ቀን ወይም 72 ሰዓታት ዛፍ በማቀፍ ይህንኑ ሪከርድ አሻሽላለች።
ሙቶኒ የ48 ሰዓቱን ዛፍ የማቀፍ ሪከርድ ለመያዝ 5 ወር ዝግጅት ነበራት ሲባል ሙቶኒ ዛፍ የማቀፉን ተግባር የፈፀመችው ዛፍ ማቀፍ የሚሰጠውን የአዕምሮ ሰላም ላይ ያለውን ንቃት ለመጨመር እንደሆነ ገልፃለች።
ጊነስ የአለም ሪከርድ ሙቶኒ 72 ሰዓት ማቀፏን በሪከርድነት ለመመዝገብ ያሏትን ማስረጃዎች እንድታቀርብ ጠይቋል።
ጊነስ የቀረበውን ሪከርድ ከተመለከተ በኋላ የሙቶኒን የ48 ሰዓታት ሪከርድ ከቀናት በፊት ወዳሻሻለችው የ72 ሰዓት ሪከርድ ከፍ ያደርገዋል።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
🤣 170❤ 63🤔 15🤷♂ 6👍 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!!
🌟አያት ግራንድ ሞል
✨ 3000 የንግድ ሱቆች
✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ
✨ከ 24 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው
✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል
🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ
🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!!
💥ለበለጠ መረጃ በ 251944856735 በቀጥታ @tegegne123 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
❤ 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሳምንቱን መረጃዎች በጥያቄ ይሞክሩ
❓ https://forms.gle/iu4w7mQLYG68rdj2A
#WeeklyNewsQuiz #001
😀 | @tikvahethmagazine
👍 15❤ 9👏 2
የታይም መጽሔት የዓመቱ ሰው በሚል ለሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰዎችን ሰይሟል።
የ2025 የታይም መፅሔቱ የአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ አንድ ግለሰብ ሳይሆን መፅሔቱ "Architects of AI" ብሎ የሰየማቸው ሰዎች መሆናቸውን ገልጿል።
በመፅሔቱ የአመቱ ሰው ሽፋን ላይም የኒቪዲያ አለቃ የንሰን ሁዋንግ፣ የሜታው ማርክ ዙከርበርግ፣ የኤክሱ ኢሎን መስክ፣ የኦፕን ኤአዩ ሳም ኦልትማን፣ የጎግል ኤአይ ላብሱ ዴሚስ ሃሳቢስ፣ የአንትሮፒኩ ዳሪዮ አሞዴይና ፕሮፌሰር ፌይ ሊን ጨምሮ በዘርፉ የሰሩ ሰዎች ተካተዋል።
መፅሔቱ እነዚህን ሰዎች የአመቱ ሰዎች ማለቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና ከጀርባው ያሉ ተቋማት ማህበረሰብን በፍጥነት እየቀየሩ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት በአሁኑ ጊዜ 800 ሚሊየን ሳምንታዊ ተጠቃሚዎች ያሉት የቻትጂፒትን በ2022 ይፋ መሆን ተከትሎ ዝነኛ የሆነ ሲሆን ባለፉት 3 አመታትም አስደናቂ ለውጥን አሳይቷል።
ትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ተቋማት በዘርፉ ረብጣ ቢሊየን ዶላሮችን እያፈሰሱ ሲሆን በዘርፉ ቀዳሚ ለመሆንም አዳዲስ ፈጠራዎችን በማስተዋወቅ ተጠምደዋል።
የታይም መፅሔት ዋና አርታኢ ሳም ጄኮብስ "በ2025 የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ካሰቡ፣ ዲዛይን ካደረጉና ከገነቡ ግለሰቦች በላይ ትልቅ ተፅዕኖ የነበረው የለም" ሲሉ ሁላችንም በዚህ ቴክኖሎጂ ላይ አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን ብለዋል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት በአስደማሚ ሁኔታ ማደጉን ሲቀጥል ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሃገራት የዳታ ፖሊሲ በማውጣትና ተቋም በመመስረት ከዘርፉ ለመጠቀም እየሞከሩ ነው።
አንዳንዶች ቴክኖሎጂውን በስጋትነት ቢመለከቱትም የደረስንበት ጊዜ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መቀበልና በኃላፊነት መጠቀም የሚገባበት ጊዜ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለፅ ይሰማል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 37🤬 5🔥 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አሜሪካ መነሻቸው ናይጄሪያ በሆኑ የኦንላይን ማጭበርበሮች በየአመቱ 1.8 ቢሊየን ዶላር እንደሚጠፋ ገለፀች።
ናይጄሪያ በኦንላይን ማጭበርበር መነሻ በመሆን ከአለም አምስተኛ መሆኗ ሲነገር በነዚህ ማጭበርበሮች አብዛኞቹ ተጋላጮች አሜሪካውያን መሆናቸውና በአመት 1.8 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደሚደርስ ተነግሯል።
በ2022 ብቻ ናይጄሪያ 500 ሚሊየን ዶላር ከሳይበር ወንጀሎች ጋር በተያያዘ አጥታለች ሲባል የሳይበር ወንጀሎች መነሻ መሆኗ ያላትን ተቀባይነትም እየቀነሰው ነው።
ከባለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ አሜሪከ በዘርፉ ለናይጄሪያ ድጋፍ ማድረግ መጀመሯና ከ700,000 ዶላር በላይ የተጭበረበረ ገንዘብ እንዲመለስ መደረጉ ተነግሯል።
አሜሪካ በተጨማሪ ህፃናቷ በዚህ የሳይበር ወንጀል ለወሲባዊ ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆኗን ስትገልፅ ይህንን ለማስቆም በጋራ መስራት አለብን ብላለች።
እያንዳንዱ በሳይበር ደህንነት ላይ የሚወጣ ዶላር በርካታ ሚሊየን ዶላሮችን ያድናል ያለችው አሜሪካ፣ ናይጄሪያ የደህንነት ሁኔታዋን ማሻሻል እና የሳይበር ወንጀል የሚፈፅሙትን ተጠያቂ ማድረግ እንዳለባት ገልፃለች።
ዘገባው የቫንጋርድ ኒውስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 38🤣 16👍 4😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
📱ብድር ለመውሰድ ቀላል መንገድ ይፈልጋሉ?
Digaf MFI ብለው ከፕላይ ስቶር /playstore/ በማውረድ ብድር ማመልከት ይችላሉ፡፡
በስልክዎ ብቻ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ እና የብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
👉 አሁን ይዉሰዱ | ቀላል | ፈጣን | ተደራሽ
📥 መተግበሪያውን አሁን ይጫኑ እና ብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.digaf.digafselfapp
ለበለጠ መረጃ ደሞ 6575 ላይ ይደውሉ!
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ
❤ 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር
- በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
https://t.me/addisapartmentforu
❤ 18
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ኦፕንኤአይ የግድያና የራስ ማጥፋትን በመደገፍ ተከሷል።
ኦፕንኤአይ እና የፋይናንስ ሰጪው ማይክሮሶፍት ቻትጂፒቲ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ሰው እናቱን እንዲገድልና እራሱንም እንዲያጠፋ አበረታቷል በሚል በካሊፎርኒያ ፍርድ ቤት ተከሰዋል።
በክሱ ቻትጂፒቲ የ56 ዓመቱ ግለሰብ በዙሪያው ያሉ ሰዎች በተለይ የ83 አመት እናቱን በስጋትነት እንዲመለከት አድርጓል ሲባል እናቱን እንዲገድልም ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
ቻትጂፒቲ የግለሰቡን ህይወት "The Matrix" ከተሰኘው ፊልም ጋር በማነፃፀር ሰዎች ሊገድሉት እየሞከሩ እንደሆነ ያሰበውን ሃሳብ አበረታቷል።
ቻትጂፒቲ ግለሰቡ እናቱን ከመግደሉ በፊት እናቱና የግለሰቡ ጓደኛ መርዘው ሊገድሉት እንዳሰቡ ያሰበውን ሃሳብም ደግፎታል።
ኦፕንኤአይ ሁኔታውን ልብ ሰባሪ ብሎ ሲገልፀው ቻትጂፒቲ የአዕምሮ ጭንቀትን እንዲለይ እና በዛ አኳኋን እንዲመልስ እንደሚያሰለጥነው ገልጿል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 71😢 54🤣 19💔 5🤔 4🤬 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በውሸተኛ ፍቅር በማታለል ከ8 ሚሊየን ዶላር በላይ ያጭበረበረው ጋናዊ ታሰረ።
አቡ ትሪካ በሚል የማህበራዊ ሚዲያ ስሙ የሚታወቀው የ31 ዓመቱ ወጣቱ ግለሰብ በእድሜ የገፉ አሜሪካውያንን በፍቅር በማውራትና በማጭበርበር( Romance scam) በማድረግ 8 ሚሊየን ዶላር አጭበርብሯል ተብሏል።
ጋናዊው "የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ" በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ሃሰተኛ ማንነቶችን በመጠቀም ማህበራዊ ሚዲያን እና የፍቅር አገናኝ መተግበሪያዎችን በመጠቀም እድሜያቸው የገፉ አሜሪካውያንን በፍቅር በማጥመድ ከ8 ሚሊየን ዶላር በላይ አጭበርብሯል ተብሏል።
ግለሰቡ በአሜሪካ እና ጋና በተሰራ የጋራ ኦፕሬሽን በጋና ውስጥ ሲያዝ አሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጣት እየጠየቀች ትገኛለች።
አቡ ትሪካ አሜሪካ እድሜያቸው የገፉ ዜጎችን ኢላማ ያደረጉ የምዕራብ አፍሪካ አጭበርባሪዎች ላይ ሰፊ ምርመራ በጀመረችበት ጊዜ የተያዘ ሲሆን እስከ 20 አመት እስር ሊጠብቀው እንደሚችልም ተዘግቧል።
ዘገባው የ DW ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
🤣 92❤ 35👍 9👏 9🤔 4🔥 2💔 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!!
🌟አያት ግራንድ ሞል
✨ 3000 የንግድ ሱቆች
✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ
✨ከ 24 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው
✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል
🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ
🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!!
💥ለበለጠ መረጃ በ 251944856735 በቀጥታ @tegegne123 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
❤ 7🤣 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኔፓል አመጽ ምን ያህል ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ አስከተለ ?
ኔፓል ከወራት በፊት በሃገሪቱ በወጣቶች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ 586 ሚሊየን ዶላር ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንዳደረሰባት አስታወቀች።
በኔፓል ባለፈው መስከረም ወር በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የሃገሪቱ መሪ ከስልጣን ለመልቀቅ የተገደዱ ሲሆን ከዛ በኋላ የመጣው መንግስት ተቃውሞው 586 ሚሊየን ዶላር ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንዳደረሰ ገልጿል።
በተቃውሞው የመንግስትና የግል ተቋማት እና የአንዳንድ ፖለቲከኞች ቤት ላይ ውድመት ሲደርስ መልሶ ግንባታው 252 ሚሊየን ዶላር እንደሚፈጅ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለመልሶ ግንባታው የሃብት ማሰባሰብ የጀመረ ሲሆን ከህዝቡና ከተለያዩ ተቋማት እስካሁን ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ መሰብሰቡን ገልጿል።
አሁን ያለው ጊዜያዊ መንግስት በተቃውሞው የወደሙት የፕሬዚዳንቱ ቤትን ጨምሮ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የቁልፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ግንባታ ዳግም ተጀምሯል ብሏል።
በወጣቶች ተቃውሞ የሃገሪቱ መሪ ከስልጣን ለቀው ከተሰደዱ በኋላ ስልጣን የያዘው ጊዜያዊ መንግስት በመጪው መጋቢት ወር ምርጫ ለማድረግ አቅዷል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 48🤔 13
አንድ መጽሐፍ ለማሳተም መጽሐፉን ከማዘጋጀት ባሻገር ምን ፈተናዎች አሉት?
ከሰሞኑ በአንድ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያ ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የታየበት ምስል ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሙሉ ጊዜ ደራሲ መሆን ያሉትን ፈተናዎች በተለያየ አቅጣጫ ሲጠቀሱ ተስውሏል።
ለመሆኑ አንድ ደራሲ ድርሰቱን እውቀቱንና ጊዜውን ተጠቅሞ ለማሳተም ምን ፈተናዎች አሉበት?
- ለመጀመሪያ ጊዜ የሚታተም አዲስ መጽሐፍ “ብዙ” ከተባለ እስከ 3ሺ ቅጂ ቢታተም ነው፡፡
- አንድ ደራሲ አንዱን መጻሕፍ በ400 ብር ዋጋ እንዲሸጥ ዋጋ ካወጣለት፤ ከዋጋው ላይ 40 በመቶውን የሚወስደው አከፋፋዩ ነው፡፡
- መጽሐፍት አከፋፋዮች ድርሻቸውን የሚያሰሉት ከትርፍ ላይ ስለሆነ የማሳተሚያ ወጪ ተቀንሶ ደራሲው የሚገኘው ትርፍ በአንድ መጽሐፍ ከ60 እና 70 ብር አይበልጥም።
- ለዘመናት የደራስያን አበሳ ሆኖ የቀጠለው አሳታሚ የማጣት ችግር ነው፡፡
- ደራሲያን ሥራዎቻቸውን ለአድማጮች በትረካ መልክ ለማቅረብ ፍላጎት የላቸውም
በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥንና ከአንድ ዓመት በፊት የተዘጋጀውን ጹሑፍ በድጋሜ እንዲያነቡት ጋበዝን 📖https://concepthub.net/article/5
#FYI: ይህ ጹሑፍ በጋዜጠኛ አልታየህ ኪዳኔ ተዘጋጅቶ በ Concepthub.net ላይ የታተመ ሲሆን ደራሲ ሌሊሳ ግርማ፤ ጠበቃና የህግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ፤ ደራሲ ህይወት እምሻው፤ ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ (ዶ/ር)፤ የደራሲያን ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አበረ አዳሙ፤ የተራኪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ናሆም ፀጋዬ እና ሌሎችም ሐሳባቸውን ሰጥተውበታል።
Via @ConceptHubeth
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 83👍 11
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በዝናብ መብዛት የምትፈተነው ማላዊ በ2 ሳምንት ብቻ 14 ዜጎቿ በመብረቅ ህይወታቸው አልፏል።
በማላዊ ባለፉት ሳምንታት መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ እየዘነበ ሲሆን በመብረቅ የተነሳ 14 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና በዝናቡ ከ8000 በላይ ቤቶች መውደማቸው ተገልጿል።
የሀገሪቱ የአደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ አሁንም የሚጥለው ከባድ ዝናብ ቀጥሏል ያለ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል አስጠንቅቋል።
በማላዊ ባለፈው አመት በዚሁ ወቅት በዘነበው ዝናብ ከ10,000 በላይ ሰዎች ቤት አልባ ሲሆኑ 8 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተው ነበር።
በ2023 በነበረው የሳይክሎን አደጋም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሞተው በሚሊየኖች ሲፈናቀሉ፤ በአደጋው ከደረሰባት ውድመትም ገና አላገገመችም።
በተመሳሳይ በዝናብ መብዛት ዜጎቿን የምታጣው ማላዊ ባለፉት ሁለት አመታት ከባድ የሚባል የምግብ እጥረት ውስጥ ትገኛለች።
ባለፈው ወርም ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግላት መጠየቋ ይታወሳል።
ዘገባው የአናዶሉ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 39💔 33😢 12🙏 2🤔 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እስራኤል በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶቿ ስልክ መጠቀምን ልታግድ ነው።
የእስራኤል የትምህርት ሚኒስቴር ከመጪው የካቲት ወር ጀምሮ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስልክ መጠቀምን አግዷል።
በእስራኤል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚባለው ከ1-6 ክፍል ያለው ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ትኩረት ለመጨመር እንደዚሁም የማህበራዊ እና የስሜት ክህሎት እንዲያዳብሩ ለማድረግ ሲባል በትምህርት ቤቶች ስልክ መጠቀምን ማገዱን አስታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዮኣቭ ኪሽ ተማሪዎቻችን ያለ ስክሪን እውነተኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን ውሳኔው ሰፊ ጥናት ከተሰራ በኋላ የመጣ ነው ብለዋል።
ዩኔስኮ በ2024 መጨረሻ 40 በመቶ በሚሆነው የአለማችን የትምህርት ስርዓት ውስጥ ስልክ መጠቀም መታገዱን አስታውቋል።
ብራዚል፣ ቺሊ፣ ፈረንሳይ፣ ሃንጋሪ፣ ኔዘርላንድስ፣ ቻይና እና የተወሰኑ የአሜሪካ ግዛቶች በተለያየ ደረጃ በትምህርት ቤቶች ስልክ መጠቀምን ከልክለዋል።
በኢትዮጵያም፥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ዓመቱ መጀመሪያ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ስልክ ፣ ታብሌት እና የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በፍጹም ይዘው መገኘት እንደማይችሉ እና ይህን ቢያደርጉ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል።
ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ በትምህርት ቤትና አካባቢ ሞባይል፣ ታብሌት እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ በመገኘት ከትምህርትና ትምህርት አዘል ፕሮግራሞች ውጭ መጠቀም መከልከሉን ይጠቅሳል።
ዘገባው የታይምስ ኦፍ እስራኤል ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 64🤣 11👏 8👎 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
📱ብድር ለመውሰድ ቀላል መንገድ ይፈልጋሉ?
Digaf MFI ብለው ከፕላይ ስቶር /playstore/ በማውረድ ብድር ማመልከት ይችላሉ፡፡
በስልክዎ ብቻ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ እና የብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
👉 አሁን ይዉሰዱ | ቀላል | ፈጣን | ተደራሽ
📥 መተግበሪያውን አሁን ይጫኑ እና ብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.digaf.digafselfapp
ለበለጠ መረጃ ደሞ 6575 ላይ ይደውሉ!
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ
❤ 6👎 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር
- በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
https://t.me/addisapartmentforu
❤ 19
