uk
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Відкрити в Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Показати більше
65 868
Підписники
-2424 години
-667 днів
-28630 день
Архів дописів
(ምን መሰለሽ? ) ሌላን ሴት ጠይቀው ‘እሺ’ የተባሉ … በርግጥ ለአንዲት ቀን ፈክተው ይስቃሉ። ፡ ሆኖም የገረመን ፡ አንቺን ተለማምጠው ‘እንቢ’ ብለሽ እንኳን ድግስ ደግሰዋል.. ዳስ ጥለዋል ድንኳን። ፡ ‘እርሷን ሞክሪያለሁ’ ብለው ስላወሩ ስንቱን ሰው አየነው ኮርተው ሲከበሩ። (ሚካኤል አ) @getem @getem @paappii
Показати все...
31😁 17🔥 7🎉 1🤩 1
'ደሀ አይደለሽም!' ~~~~~ ተወጣጠርሽ አሉ    ቆዳሽ እስኪጠብሽ ተመፃደቅሽ አሉ    መልክሽ እስኪበልጥሽ፤ ደግሞም ብለሽ ብለሽ    ንቀት ጀመርሽ አሉ ትናንትን ረስተሽ፣ ዛሬን ብትጎብዢ    በሰው 'ሰው' ብትሆኚ ሰውነትን ትተሽ! ~~~~ የሆነውስ ሆኖ ወቃሽ ተቺሽ በዝቶ     ብንጠላሽም እኛ፣ ማድረግሽ አይቀርም   በገንዘብ በሀብትሽ     እኛኑ ዘበኛ፤ እሱ አልበቃ ብሎም   በአሽሙር በሀሜት      ወጋ ቢያደርጉሽም፣ ይፈሩሻልና   ፊትለፊትሽ መጥተው     አይናገሩሽም..... ም ክ ን ያ ቱ ም    ደሀ አይደለሽም!!!!!!!! By @Weyblann    ያቡ @getem @getem @getem
Показати все...
56🔥 14👍 10😢 4😱 1
እኔ ባይተዋር የእፍታ ብናኝ በየሄድኩበት ዕምባ ሚቀናኝ፤ በዬጥላው ስር የምሰባበር ያለ በረሃ የማላውቅ ሀገር፤ ከቁር ከሐሩር የተወዳጀሁ ገና ሽል ሳለሁ ኑሬ ያረጀሁ፤ ድስቴ ምጣዴ ያልተሟሸልኝ ፤ ከማማጥ በቀር ወልዶ መደሰት የማይኾንልኝ፤ - እኔ ባይተዋር የዕጣ ፍርደኛ ለጊዜ በደል የሌለኝ ዳኛ፤ የጊዜ ንጉስ ያለገላጋይ የሚበድለኝ ከማደግ በቀር ጥላት የሌለኝ፤ ልክ እንደ ብናኝ ያነስኩ የሳሳሁ ስበርር የምኖር እየተገፋሁ፤ ድንገት ተነስቶ ሰው የሚርበኝ በየትከሻው ማልቀስ የሚያምረኝ፤ በየትከሻው ጎጆ የሰራሁ ከሰው የምኖር ሰው እየፈራሁ፤ - እኔ ባይተዋር የምርጫ ጌታ፤ ሀገሬ ማዶ ከጉም ኮረብታ፤ ለብሶ የሚኖር የጭጋግ ኩታ፤ ዘሬ መከራ አድባሬ ዋይታ የማይሞላልኝ ሳስር ስፈታ ፤ አባቴ ለቅሶ እናቴ ለቅሶ ሕይወት ያቆመኝ ያለ ምሶሶ፤ ቢገልጡኝ ቁስል ቢነኩኝ ቁስል ቶሎ ሚደክመኝ ገና አረፍኩኝ ስል፤ - እኔ ባይተዋር ፎካሪ ሽፍታ ጫካ የማድር ድቤ ስመታ ፤ ሐዘኔን ትቼ የማልሰደድ ያለ በረሃ ሀገር የማልለምድ ፤ እንጀራዬ ዕውር ወጤ ደንቆሮ ሳለቅስ የምውል ግዋሮ ለግዋሮ፤ እኔ ባይተዋር የድብርት ራት ከወዳጅ በቀር የሌለኝ ጥላት። By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
Показати все...
42😢 13🔥 6
ጥበብ ////////////////////////// የቆሰለች ጉድፍ ነብሴን፣ አውሬ የሆነች ማንነቴን። አንቺ ቀርበሽ አላመድሻት፣ በመዳበስ ዝም አስባልሻት። የኔ ሂሶጵ ከጉድፌ ያነፃሽኝ፣ ዘማዊ ነህ ብለሽ እንክዋን ያልገፋሽኝ፣ አንቺን ላጠምድ ልሰርቅሽ ስል የሰረቅሽኝ፣ ሌባ ስሆን ዘብ ጠባቂሽ ያደረግሽኝ፣ ከሺ እንዳልሄድኩ ካንቺ እንዳልርቅ ያለገመድ የጠለፍሽኝ። ቃልሽ አስማት እጅሽ ደግሞ የአስማት በትር፣ ከነካሽኝ ተቀይሬ ካንቺ ስር ነው እኔ ማድር። ያንቺስ ይገርማል፣ ሰለሞንስ ያውቀው ይሆን ይህን ጥበብ፣ በነካው ሰው መጠበቅን ወይ መከበብ። በታሪክስ ይኖር ይሆን ቁርጥ አንቺን የመሰለ፣ ተቅበዝባዥን በማላመድ ከቤቱ ስር ሰው ያዋለ። እሷ ያጠመደች እኔን አሳ፣ ያለመረብ በዳበሳ። የያዘችኝ እኔን እሳት፣ ያለውሃ በእጅዋ ብልሃት። እኔም ብሄድ ዞሬ ከስዋ፣ ይሄ ልቤ ፍቅር አይረሳ። ማን አስተማራት ይህን ጥበብ፣ በዝምታ ዳብሳ አገኘች የኔን ልብ፣ ማን አስተማራት? ማን አስተማረሽ? ማን? @abela_black @getem @getem @getem
Показати все...
21👍 1
« የት ጠፋህ አንተዬ? » ታምሜ! ታምሜ ስሞት ከማይ ቆሜ ጥበቡን ባላውቅም መድሃኒት ልለቅም ፤ ከሰዎች ርቄ... ከጫካው ዘልቄ ቅጠል ሥራሥሩን ሞራ፥ ሥቡን፥ ማሩን አመዱን አፈሩን አፍሼ ለቅሜ ጨቅጭቄ ቀምሜ ወዙን አንጠፍጥፌ ባፍንጫዬ ባፌ አስርጌ ጠጥቼ ሕሊናዬን ስቼ ሞቼ ሞቼ ሞቼ ሞቼ ተነስቼ ..፤ « ሞት ተፋህ አንተዬ! » እውነትም ሞት ተፍቶኝ በሽታዬም ትቶኝ ሲታደስ ጤናዬ 'የሰው ልጅ ነኝ' ብዬ፤ እንደኔው ያመመው መንደሬን ላክመው መድሃኒት ታቅፌ፡ ብመለስ ከቅዬው ሰዉና ህመሙን ፡ ምን ብዬ ልለየው? « ምን አልከኝ አንተዬ? » ከደዌ በሽታው ማንም ላያፋታው፤ እየተዋሃደ ፡ በስጋ በደሙ ሰው ስለተጋባ፡ ከገዛ ሕመሙ ተወግዞ ጠበቀኝ፡ የመድሃኒት ሥሙ። መች ሰማሁ እኔማ? ህመሜን ልታገል፡ እንዳልራቅኩኝ ከሰው ስሽር በዳንኩበት ፡ ጥበብ ልፈውሰው፤ ደዌ ካጠላበት ፡ ህዝቤ መሃል ስገኝ ሰው አውቆ ሰው አልቆ ፡ ሞት አቅፎ ጠበቀኝ። « ከፋህ ወይ አንተዬ? » ፍፁም አልከፋኝም የልክ የሥህተቱ ፡ ወሰን ቢያለፋኝም የህይወት የጊዜ ፡ ትርጉም ቢጠፋኝም፤ አልከፋኝም ፍፁም ባይሆን ከቃል ልፁም ፤ ብዬ ነው የጠፋሁ... «ውሸት! ሀቅን አትሽሻት የደረሰብህን የሆንከውን ነገር እውነቱን ተናገር የት ጠፋህ አንተዬ? » ግጥም ልቅዳ ብዬ ከሰው ተነጥዬ ከድፍርስ ጽዋዬ በልቅልቅ ዋንጫዬ፤ ያንጠፈጠፍኩትን ለብ ያለ ጠብታ ፉት ብዬው ላፍታ ቃናው እየሸሸኝ ስላንገሸገሸኝ፤ ተፍቼ ብጭብጩን ደፍቼ ጭላጩን ልፈልገው ምንጩን፤ ከሰው ተነጥዬ ግጥም ልቅዳ ብዬ ጥዑም ልፃፍ ብዬ...፤ አልፎ የሚያገድመው ዘግኖ ከሚቅመው ከቆሎው ከዜናው ከንፍሮው ከዝናው ፤ ከወሬ ማንደጃው ከሰደድ መረጃው ከልብልቡ ርቄ ከልቤ ዘልቄ ፤ «ግን ቀናህ አንተዬ? » ተረከዝ ያልዳጠው ሰው ያልተረገጠው ከሀሳብ ለምለሙን ከቃል ቀለማሙን ፤ ከሐረግ እርጥቡን ከስንኝ ቁጥቡን አርቄ አምቄ ለቅሜ ጨምቄ ፤ ጠጥቼ ነቅቼ ሰው ላድን ጓጉቼ ከሻረው ህመሜ ከፀጤ ከዝሜ ህብረቃል ቀምሜ ፤ ስመልስ ከዱሩ በያዝኩት መድሃኒት ተጠለቅልቋል ምድሩ። «ምን ጉድ ነው አንተዬ?» አዬ! አዲስ ልፍጠር ብዬ ከሰው ተገልዬ ፤ ያሰብኩ ያረቀቅኩት የፃፍኩ ያነበብኩት ከፍታ ጣራዬ ብርቁ ፈጠራዬ ውድ ሆኖ የታየኝ ፤ በየሰው በራፍ ተጥለቅልቆ የሚገኝ ርካሽ ተደራሽ እዳ ሆኖ ቆየኝ። « ሞተሃል አንተዬ! » ኧረግ ኧረግ ኧረግ ሞት ቢሉህ የሞት ጥግ! የታመመ ወገን ፡ መድሃኒት ሳይፈልግ ፤ የማቀቀ ሁሉ፡ ሲስማማ ከደዌው መፍትሄ ፍለጋ ፡ ርቆ ከቅዬው የእድሜውን ግማሽ፡ ጫካ ለሚቆየው ለቀማሚው ወየሁ! ላፍታ በመዳኑ ፡ ላይልቅ ከታመሙት ፈውስ ፃፍ እያሉ፡ አንዱንም ላይሰሙት ቃላት በማስቀመም፡እድሜውን ለቀሙት ለገጣሚው ወየሁ ! ቃል ማሰር መፍታቱ ከእድል ጋር ትግሉ፡ ከቀን ጋር ሙግቱ መፍትሔ ፍለጋ ፥ መጣር መቃተቱ ታሞ ራሱ ድኖ ፡ ሰው ሊያድን መሻቱ ይሄ ድካም ኑሮ ፡ ምን ይሰራለታል ? ሞት ያራራለታል? ( እኔስ ይሄ ድካም ፡ ምን ይሰራልኛል? ሞት ይራራልኛል? ) Red-8 @getem
Показати все...
65🔥 10😱 6👍 2🤩 1
ቃል ሁኚልኝ //////////// እኔ ገጣሚ ነኝ አንቺ ባለሽበት ሃሳብ ማይጠፋኝ፤ ባየሁሽ ቁጥር ነው ከሃሳቤ ቀለም ብእር ማገናኝ፤ የሚያምር ቃል ጽፌ ሰው እንዳላስዋብኩኝ፤ የሚያምሩ ቃላትን ላንቺ አድናቆት ብዬ እንዳልደረደርኩኝ፤ የወረቀት ገላን አንቺን ባየሁ ቁጥር ስገርፍ እያደርኩኝ፤ ደግሜ ሳይሽ ግን የገጠምኩትን ቃል በማፍረስ ገደፍኩኝ፤ ስጽፍ የኖርኩትን አንደበት አጥቼ የምልሽ ሲጠፋኝ፤ ወይ እውቀት አልሆነኝ፤ ወይ ካንቺ አላግባባኝ፤ አንቺን ባየሁ ቁጥር አካሌ ሲከዳኝ፤ ሽባ ራሴን መተርተር ነው የተረፈኝ፤ እስኪ ባክሽ ወንድ ከሆንሽ ቃል ሁኚልኝ። በወረቀት ሳሰፍርሽ ነው በብእሬ ስጽፍ ማድር፤ ብዬ እንዳልል ወንድ አትሆኚ እኔም ካንቺ ውዬ አላድር። ከቻልሽ እስኪ አንዴ ባክሽ ቃል ሁኚልኝ፤ በሱ መልኩ አንችን ማግኘት ከቀለለኝ፤ እባክሽን ቃል ሁኚልኝ ። @abela_black @getem @getem @getem
Показати все...
32🤩 6🔥 2🎉 2👍 1
<አድናቂና ቀልቡ> ለግርዶሽ ቢኳሉ ዝለው የሰቀሉት... ይከብድ የለ ቅሉ ሲንከባለል ውሎ ወጪት በአፍ ጢሙ ከመውደቁ በፊት ----------------------- በተመልካች ገመድ ታስሮ ነበር ቢሉ... ለቅሉ የተደፉ.... አንዳቸው ሳይተርፉ ቅሉ ግን የኋሊት... |ሽቅብ መንጠልጠሉ|       ተፃፈ : በኢያሱ ከበደ        ህዳር 30, 2018 ዓ.ም @getem @getem @getem
Показати все...
27🔥 4
(በከሪም) ከመዉደዴ ጀርባ    ከመዉደዴ መሃል ከመውደዴ ዉስጠት  ቅንጣት የምታህል ከኢምንት ያነሰች  ትንሽ ክብር ቢጤ ከግብሬ ስጣረስ   ያልተዋጠች ድምጤ ነፍስ ዘራች መሰል  ትሰማኝ ጀመረ                                  ትቀር ትሆን ሆና ልረሳሽ ነው መሰል  ቢቀር ጊዜ መና                                    ይሄው ሆነ ወና በተስፋ ላይ ተስፋ ቆርጦ                              እስካይሆን ላልሆነው የሆነው እስኪሆን  የወደዴሽ ልቤ                                  ይወድሽ ተሳነው @getem @getem @getem
Показати все...
34🔥 7
አርበኛው አያቴ . . ጋቢዉን ደርቦ ጠሀይዋን ይሞቃል፤ ሲለዉ እያነባ ሲያሻዉ ይስቃል። ትክ ብሎ ሲያየዉ የጋቢዉን ጥለት፤ ፊቱን አረጠበዉ እንባዉ ከመቅፅበት። እጉያዉ ሸጉጦ አይን አይኔን እያየኝ፤ በለስላሳ እጆቹ እየደባበሰኝ፤ የጥለቱን ምስጢር.... ከስር መሰረቱ አመሰጠረልኝ። ይቺ ክቡር ሰንደቅ.......... ከሞት ለመዳኑ፤ የኖህ ቃልኪዳኑ። በሰሜን አስታከን በደቡብ ስንወጣ፤ ምስራቅን ጨርሰን ከምዕራብ ስንመጣ፤ በማርያም መቀነት አየናት ተቀልማ፤ ለምድር ምስክር ለመሐላ ቆማ። ከሳቅ ይልቅ ዉብ እንባ ነች፤ ከልብ ምት ትረቃለች። ይቺን ክቡር ሰንደቅ... በአልባስሽ ተዋቢባት፤ በመኖርሽ ድመቂባት፤ በእንቶፈንቶ አትለዉጫት፤ እስከሞትሽ ታገይላት። ብሎ መከረኝ አያቴ...... [ዔደን ታደሰ ] @topazionnn @getem @getem
Показати все...
32👍 5🔥 4😱 1
ረፍዷል ---------- ያሻኝን አግኝቼ በእጄ እንዳስገባሁት፣ የእኔው እንደሆነ መፈለጌን ተውኩት ። አለምን አየኋት ቀልቤንም ማረከኝ፣ ስህተቱ እንኳን ልክ ሆኖ እየታየኝ፣ አታለለኝ ። ፍላጎቴን አላውቅ ተቅበዝባዥ ሆኛለሁ፣ አላፊ አግዳሚውን ልሆን እመኛለሁ። አሁን ወስኛለሁ እንዳልኩኝ በቅፅበት፣ መልአከ ሞት ያዘኝ ወሰደኝ ሰማይ ቤት። @abela_black @getem @getem @getem
Показати все...
22🔥 13😢 12👍 1
ወይን ሙዚቃ ዳንስ'ና ቡና የማያክመው ፤ የጋለ ገላ የጋለ ፍቅር የማያድነው፤ የነፍስ ኮርኒስ የልብ ጥላ የማይሸፍነው፤ እንቅልፍና ሞት መንገድና ዕድሜ የማይበግረው፤ አለ አንድ ድብርት ድንገት ብቅ የሚል ሄደ ስንለው። By Tewodros Kassa @getem @getem @paappii
Показати все...
40🔥 12😢 6👍 1
እልፍ አዕላፍ ሰዎች..... ይኖሩ ይመስል በምድር ዘላለም፤ ዳግም ላይፋቱ ተጋብተው ከአለም፤ የጊዜን ምንነት ወርቅነት ሳያዉቁ፤ ከእድሜያቸዉ ላይ ዘመናት ሰረቁ። ............................................ ✍ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Показати все...
32🔥 14😢 2
ቀን የለም ------------ የጨረቃ ግማሽ ሰማይ ላይ ተስላ፣ ግማሹ መጥፋቱን ከዜና ስሰማ። ድንገት አንቺን አየሁ፣ አገኘኋት ብዬ መናገርን ፈራሁ። ከየት ልደብቅሽ እንዴትስ ልውሰድሽ፣ በምን ውስጥ ቆልፌ ደግሞ ልከልልሽ። አለሙን ታውቂያለሽ ጨለማ ካልሆነ ወዳንቺ አያይም፣ ከደመኖች እኩል ቀን አንቺን ቢያደርግም፣ አይገርምም፣ ለምን ያልሽ እንደሆን ዋጋሽን አያውቅም። እሺ ካልሽኝ ይኸው አገኘሁኝ ቦታ፣ ትንሽ የጨለመ ማይገኝ ስጦታ። ገብተሽ ተደበቂ ልቤ ይሁን መኖሪያሽ፣ እኔ እየጨለምኩ አንቺ እያበራሽ። @abela_black @getem @getem @getem
Показати все...
32👍 1🔥 1😁 1
[ነጋ እንዴ እላታለሁ] ₁ ብዙ ነገር አይቻለሁ ከኖርኩም ያለሁት ለሷ ነው ለራሴማ ሞቻለሁ። ለራሴ? ሳቅም ለቅሶም ቀምሻለሁ ይመሰክራል ትራሴ። አንድ ጎኔ በእንባ አንደኛው በፈገግታ ባንዱ ብርሃን ስትገባ ባንዱ ስትበራ ነግታ እንደዚህ ነው ስሪቴ እንደዛ ነው ህይወት ያዋቀረኝ ያላየሁት የሷ ደስታ ብቻ ቀረኝ። ₂ ብዙ ነገር አይቻለሁ! በቅቶኛል አቅቶኛል የዚህ ዐለም ሸክም ጉዝጓዝ ምን ይደክማል እራስን ተሸክሞ እንደመጓዝ? ይከብደኛል እከብዳለሁ ምን ትመስላለች ፀሐይ? ምን ይቆላታል ጨረቃዋ? ቻለችኝ ዐለም እንደምን? ያዘችኝ በምን ጫንቃዋ? ₃ እከብዳለሁ ለምድሩም ለሰማዩም ይከብደኛል ሰማዩና ምድሩ የምስማው የማየውም በቅቶኛል የምነካው የማልነካው የኔ መኖር አንዱን ማጣት ባንደኛው ነው የሚተካው! በቅቶኛል! ባበቃ ነገር ላይ እንዳላበቃ መወስለት አልመለስም ወደዚህ መቀስቀስ ያቆመች እለት። ₄ ዐለም ግን አላወቀችኝም እሷን እስከጥግ አውቃታለሁ እና መኖር እንደሚመኝ ስትቀሰቅሰኝ እነቃላታለሁ። ነጋ እንዴ? እላታለሁ የፊቷ ብርሃን ደብዝዟል የኔስ ጉዳይ አከተመ፣ መኖር ለሷ ምን ይዟል? ነጋ እንዴ? ፊቷ ታዲያ ምነው ጨለመ አላደረም መዋል እያለመ? ለምን ቀሰቀሰችኝ ታዲያ? እንጃ! ነጋ እንዴ እላታለሁ ቢነጋም ለርሷ ነው የሚነጋው "ተነስ ተነስ" ትለኛለች እሺ አንዴ መቃብሬን ልዝጋው! By Yadel Tizazu @getem @getem @paappii
Показати все...
45😢 4🔥 2
የፈራሁ የኮራሁ ያጨድኩኝ የዘራሁ በልቼ ጠጥቼ አግኝቼ ነጥቼ ቅር ያልኩ የተመቸኝ እሰይ ያልኩ የቆጨኝ የሳቅኩኝ ያነባሁ የጨከንኩ የባባሁ የወጣሁ የገባሁ ለማፍሰስ ለማፈስ በእቅድ በደመነፍስ የጀገንኩ የሰነፍኩ እንዳቅሜ የሞከርኩ አንድ ሰው፡ የሰው ልጅ እዚች ቦታ ነበርኩ። በዚህ ነፋስ ህይወት ህያው ይሉኝ ወረት ማለፍ መሄድ እንጂ ስለማልችል መቅረት ስለማልችል መቆም ባለኝ ብቸኛ አቅም እስኪ ግጥም ልፃፍ ማለፌን ልጠቁም። ( red-8 ) @getem @getem @paappii
Показати все...
38🔥 6👍 5
በረደኝ.. ወትሮስ መቼ ሞቆኝ    አንቺን ተመርኩዤ ያሁኑ ግን ባሰ    በተስፋሽ ደንዝዤ፥ ተስፋ..ባዶ እውነታ፣            የቀን ማታ፣            ብልጭታ፣            ከምኞት ጨዋታ!     ነገን እያሰብኩኝ ጓደኛ ሁሉ ሸሸው፣     መከረኛው ልቤ     በተስፈኛው ፍቅርሽ ሰው አንገሸገሸው፤ ብቻ ግን አደራ! በቀቢፀ ተስፋ ስታኖሪኝ ከርመሽ ልብሽ ወደሌላ አድልታ ብትሸሽ፣ ማ   ር   ያ   ም   ን         እ    ን    ዳ   ት   መ   ለ    ሽ! By @weyblann  ያቡ @getem @getem @getem
Показати все...
53👍 5😢 3
ምንድን ነው እውነት!? ምንድን ነው እውቀት!? ምንድን ነው እምነት!? በምን ይሻላል ካንቺ ሰውነት !? ምንድን ነው ቦታ !? ምንድን ነው ጊዜ !? ምንድን ነው ሕይወት!? በምን ይለያል ከገላሽ ሙቀት!? ምንድን ነው አምላክ!? ምንድን ነው ጥበብ !? ምንድን ነው ኪነት !? በምን ይበልጣል ከዐይኖችሽ ውበት!? ምንድን ነው ሎጂክ !? ምንድን ነው ሳይንስ !? ምንድን ነው ፍልስፍና !? በምን ይሻላል ከአንገትሽ ቃና !? ልልሽ እልና . . . አንቺ ለራሱ ምድንነሽና !? By Tewodros Kassa @getem @getem @paappii
Показати все...
😁 81 39👎 10😱 4😢 1🤩 1
አንዳንዴ በዕጣ ፤ አንዳንዴ በዕድል እያታለለኝ ፤ ሲሻው ሲያነሳ ፤ ሲሻው ሲጥለኝ ፤ ከጊዜ በቀር ጥላትም የለኝ ። By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
Показати все...
71👍 7👎 2🔥 2🤩 1
ገጣሚ፦ ቴዎድሮስ ካሳ አንባቢ፦ ሲራክ ወንድሙ @sirakoo @getem @getem @getem
Показати все...
የህይወት ጣዕም.mp31.61 MB
23🔥 8👎 2
ዐይኔ አረዘረዘ ፤ ልቤም ተሰበረ ፤ አንጀቴም ሆድ ባሰው ፤ ገና ሳይወለድ እንዴት ያረጃል ሰው !? By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
Показати все...
51👍 12🔥 12😢 2