134 016
Подписчики
-1424 часа
-1207 дней
-28530 день
Архив постов
ሰራተኞቹ ላይ ድብደባ በመፈፀም፣ በማሰር፣ በማሳሰር እና ሰብዓዊ ጥሰት በመፈፀም በራሱ ሰራተኞች ውንጀላ የቀረበበት ሱፐር ደብል ቲ ጄነራል ትሬዲንግ ነገ ቅዳሜ በርካታ ጋዜጠኞችን ይዞ ወደ ፋብሪካው ሊሄድ ቀጠሮ ይዟል።
የፋብሪካው አመራሮች በዕለቱ ጋዜጠኞችን አዲስ አበባ ከሚገኘው ማሪዮት ኢንተርናሽናል ሆቴል ሰብስበው ወደ ቅጥር ግቢው ይወስዳሉ ተብሏል።
የፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆኖ ደፍሮ እውነታውን ለሚድያ የሚናገር ሰራተኛ እንደማይኖር ቢታወቅም በዚህ ፕሮግራም ላይ ማስተባበያ የሚሰጡ ሰራተኞች ተዘጋጅተዋል ተብሏል፣ ለታዳሚ ጋዜጠኞች ደግሞ ሞቅ ያለ አበል እንደተዘጋጀም ታውቋል።
የመሠረት ሚድያ የምርመራ ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ ድርጅቱ ለሰራተኞቹ የደሞዝ እና ቦነስ ጭማሪ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ እንደሚጨምር ቃል መግባቱ ተሰምቷል፣ የስራ ቦታ ሁኔታውም መሻሻሉን ሰራተኞቹ ይናገራሉ።
የፋብሪካው ባለቤት ደግሞ በድብደባ ጉዳት የደረሰባቸውን እና ታስረው የነበሩ የቀድሞ ሰራተኞችን ጉዳቱን እና እስሩን እንዲያስተባብሉ በማረግ በገንዘብ አስማምቶ ቪድዮ ለመቅረፅ ሙከራ እያረጉ መሆኑ ታውቋል። በዚህ መልኩ ተጎጂዎች "ዜናውን አስተባብሉ፣ ገንዘብ እንሰጣለን" እየተባሉ መሆኑም ማስረጃዎች ያሳያሉ፣ ክስ እንደሚመሰርቱም ዝተዋል።
የምርመራ ዘገባ ይለምልም!
#መሠረትሚድያ
@EliasMeseret
❤ 449😢 143👍 71😁 16🤔 5🕊 4😱 3🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
A must read!
https://www.facebook.com/share/p/1BZ6c6KVNr/
❤ 89👍 48😢 12😁 9🤔 6😱 3🕊 1
በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ታጣቂዎች እንዳሻቸው እየተመላለሱ ሶስት ጥቃቶችን ፈፅመው የ22 ምዕመናንን ህይወት ቀጥፈዋል፣ ታግቶ የተወሰደው ይበዛል። እንዲህ ተደጋጋሚ ጥቃት ንፁሀን ዜጎች ላይ ሲፈፀም የመንግስት የፀጥታ አካላት የስራ ድርሻቸው ምንድነው?
#ዜናመሠረት አርሲ ውስጥ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በደረሱ ሶስት ተከታታይ ጥቃቶች 22 ምዕመናን መገደላቸው ተሰማ
ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ ሲሆን 27 ምዕመናን ደግሞ አሁንም ድረስ ታግተው ያሉበት እንደማይታወቅ ታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://tinyurl.com/zcb292pc
😢 747❤ 78😱 28👍 12🤔 9🙏 9😁 4🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለሸገር ከተማ ፖሊስ፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለፍትህ ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም ሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ለምትሰሩ ድርጅቶች ሁሉ!
በትናንትናው ዕለት ሸገር ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሱፐር ደብል ቲ ኃ/የ/የ/ማ (የሮዳስ ቀለም እና ሱፐር ፋይበር ውሀ ማጠራቀሚያ አምራች) ዙርያ መሠረት ሚድያ የምርመራ ዘገባ ሰርቷል (https://tinyurl.com/48rbrfwr)
በዘገባው ላይ ድርጅቱ ሰራተኞቹ ላይ ከድብደባ ጀምሮ በርካታ ወንጀሎችን እየፈፀመ መሆኑ ተጠቅሷል። ማህበራዊ ሚድያ ላይ በዜናው ስር ከሚሰጡ አስተያየቶች ማየት እንደሚቻለው በርካታ ህዝብ ወንጀሉን እና በደሉን በደንብ ያውቀዋል፣ ነገር ግን ማንም ጉዳዩን ሊያወጣ አልፈለገም።
ዜናው መውጣቱን ተከትሎ በርካቶች ወደ መሠረት ሚድያ በመምጣት የደረሰባቸውን ዘግናኝ ግፍ፣ ድብደባ እና ወንጀል እየተናገሩ ይገኛሉ። እነዚህ ዜጎች "የኢትዮጵያ ልጆች ነን አድኑን፣ ያናግሩን ማስረጃ አለን" እያሉ ነው።
ለማሳያ እንዲሆን በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ የድርጅቱ ሰራተኛ የነበረ ነው። ከድርጅቱ መውጣት ፈልጎ ሲወጣ 2 ሚልዮን ብር ሰርቋል ተብሎ ሲወነጀል ከዚህ በፊት ሰዎች ላይ የደረሰውን ስለሚያውቅ ጠፋ፣ የድርጅቱ ባለቤት ግን ከተደበቀበት ካስያዘው በኋላ የወሰደው ወደ ህግ ሳይሆን ፓራላይዝድ እስኪሆን ድብደባ አስፈፅሞበታል። ከዚህ በኋላ በእግሩ ለመሄድ 10 ዓመት ይፈጅበታል እንደተባለ ሰምቻለሁ (ጉዳቱ ከጀርባው ላይ ሲሆን ሚድያ ላይ ለማቅረብ የሚከብድ ከባድ ጉዳት ስላለበት ይህ ከፊት የተነሳ ፎቶ ቀርቧል)።
ከዚህ ውጪ የአካል፣ የአዕምሮ፣ እና ፆታዊ ጥቃት ደረሰብን ያሉ ብዙ ናቸው፣ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች እንዳሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ደጋግመው ተናግረዋል። በቅጥር ግቢ ውስጥ በግልፅ የሰራተኞች ማሰሪያ እና መደብደቢያ ቤት እንዳለ የአደባባይ ሀቅ ነው።
እነዚህ ዜጎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው የዕለት ጉርስ ለራሳቸው እና ለቤተሰባቸው ለማግኘት ሲሉ ነው፣ የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ አጣርቶ ወንጀሉን ወደ ህግ እንዲመራ እንዲሁም ተጎጂዎች የሞራል እና የአካል ጉዳት ካሳ እንዲሰጣቸው መደረግ አለበት ብዬ አምናለሁ።
የሚድያ ስራም እንዲህ የተሸሸገን ጉዳይ አውጥቶ ለህዝብ ማቅረብ ነው።
#መሠረትሚድያ
@EliasMeseret
❤ 872😢 791👍 228🙏 93😱 43🤔 27🕊 8
በመጀመርያ ስሰማው ለማመን የከበደኝ፣ ግን እውነታው አሳዛኝ እና አሳሳቢ የሆነ መረጃ። መሠረት ሚድያ ለሁሉም አንባቢ ክፍት ደርጎ ያቀረበውን ይህን የምርመራ ዘገባ ያንብቡ ⤵️
#የምርመራዘገባ ሰራተኞች 'ሲኦል' ሆነብን ያሉት የግል ድርጅት በቅጥር ግቢ ውስጥ አካላዊ ድብደባን ጨምሮ እየፈፀማቸው ያሉት አነጋጋሪ ድርጊቶች
"ከስራ አንድ ደቂቃ ያረፈደ 700 ብር፣ ማስቲካ ያኘከ 1 ሺህ ብር ይቀጣል። ልምድ ያለው ሰራተኛ ሆኖ ስራ መልቀቅ እፈልጋለሁ ካለ ድብደባ እና እስር ይጠብቀዋል፣ ብር ሰርቋል የሚል ክስም ይመሰረትበታል"
ለሁሉም ክፍት ሆኖ የቀረባውን ይህን መረጃ ያንብቡ:
https://tinyurl.com/48rbrfwr
😢 447😱 102❤ 78🤔 45🙏 25👍 22😁 14🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጋዜጠኝነት በአሜሪካ...
በሐዋርድ ካውንቲ፣ ሜሪላንድ ግዛት ታዋቂ እና ተወዳጅ ከሆነው ማይክል ኦበርማን ጋር በአለም ዙርያ በሙዚየሞች ውስጥ ተሰቅለው በሚጎበኙት ፎቶግራፎቹ ዙርያ ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ አርጌለታለሁ።
በሌላ በኩል በኮርያ፣ ቪየትናም፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተ ሀገራቸውን ላገለገሉ ቀደምት የአሜሪካዊ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በህብረተሰቡ የሚደረግላቸውን ድጋፍ በተመለከተም ሰፋ ያለ ፅሁፍ አቅርቤያለሁ።
በዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቪርጂኒያ አካባቢ ያላችሁ አዲሱን የ Beacon ጋዜጣ እትም በበርካታ ቦታዎች ታገኙታላችሁ።
መልካም ንባብ!
@EliasMeseret
❤ 202👍 97🙏 5😁 1😱 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ነፍስ ይማር አባታችን!
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የእርቅ፣ የፍቅር እና የሰላም አባት ነበሩ።
😢 2 266❤ 456🕊 118🙏 91👍 79😱 33😁 8🤔 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጎንደር ላይ እገታ ሲፈፅሙ ስለነበሩ የፀጥታ አካላት ዛሬ የፃፍኩትን ተከትሎ ፋና የሰራውን ዜናውን በዚህ መልኩ አክሮባት አሰርቶታል!
እንደ አንድ የሚድያ ሰው ይህን የሚያክል ተቋም እንዲህ ሲሆን ከማየት በላይ የሚያሳዝን ነገር የለም። በፋና የውስጥ አሰራር ዙርያ በቅርብ እመለስበታለሁ።
@EliasMeseret
😁 707👍 130❤ 81😢 57🤔 21🙏 15😱 14
Фото недоступноПоказать в Telegram
ታዬ ቦጋለ ምን እየሆኑ ነው?
ከሰሞኑ 'እኔ ልውደዳቸው እንጂ ብልፅግናዎች አይወዱኝም' እያሉ መንግስትን ክፉኛ እየተማፀኑ የሚገኙት ታዬ ዛሬ አንድ አፀያፊ ፅሁፍ ማህበራዊ ሚድያ አጋርተዋል፣ ይህም በአማራ ክልል ባለው ጦርነት በአሰቃቂ ሁኔታ አካሏ ተቆራርጦ የተገደለችን አንዲት ወጣት ተዋጊ ላይ ሲሳለቁ ይታያል።
ታዬ ወደ ሀገር ቤት መመለስ ፈልገዋል። ቀድመው መንግስትን የተናገሯቸው ተራ ስድቦች እና ዘለፋዎች ግን ስጋት ላይ ጥለዋቸዋል። ታድያ ለእነዚህ የመንግስት የተቃውሞ ንግግሮች ማርከሻ መላ እያፈላለጉ ነው፣ መንግስትም ይህን ረስቶላቸው ወይም ይቅር ብሏቸው እንደሆነ ለመመዘን ድጋፍ ላይ ናቸው። ማንንም መደገፍ መብታቸው ነው፣ መንግስትም አፉ እንዲላቸው እመኛለሁ።
ነገር ግን በአንዲት ወጣት ሴት እጅግ አሰቃቂ ግድያ ተሳልቆ መንግስትን የደገፉ መምሰል አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን አረመኔነትም ጭምር ነው።
@EliasMeseret
❤ 737👍 357😢 121😁 52🤔 48😱 17🙏 10🕊 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጎንደር ከተማ ውስጥ እገታ እና ሌሎች ወንጀሎችን ከሚፈፅሙት አካላት ውስጥ በዋነኝነት ከተማው ውስጥ ያሉ አንዳንድ አድማ በታኝ እና የሚሊሺያ አባላት እንደሚገኙበት #መሠረትሚድያ ከጥቂት ወራት በፊት ተከታታይ መረጃዎችን አቅርቦ ነበር:
የሚታገቱብንን ልጆቻችንን መልሰን በገንዘብ እየገዛን ነው:
https://t.me/meseretmedia/259
ጎንደርን እያመሰ ከሚገኘው ሀይል ውስጥ የእኛው ሚሊሺያ እና አድማ በታኝ አለበት፣
https://t.me/meseretmedia/277
ዘገባው ውሸት እንደሆነ፣ የከተማውን ስም ለማጥፋት የተቀናበረ ሴራ እንደሆነ በወቅቱ ካድሬዎች ሲነግሩን ነበር።
ግዜ ደጉ መጣና በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ በወንጀል ድርጊቶች የተሳተፉ 52 የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮች በህግ ተጠያቂ መሆናቸውን የመንግስት ሚድያዎች አስነብበውናል። በእገታና በሌሎች የወንጀል ድርጊቶች የተሳተፉ 52 የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጋቸው ተሰምቷል (ፋና: https://www.facebook.com/share/p/1Fng1Rpf9P/)
@EliasMeseret
❤ 296👍 118🙏 25😁 11😢 7🕊 4🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዲ/ን ዳንኤል ክብረት የዛሬ ንግግር ሲፈተሽ!
ዲ/ን ዳንኤል ዛሬ በነበረ አንድ ፕሮግራም ላይ "የትኛውም የአሜሪካ ሚዲያ የአሜሪካ የኒውክሊየር እና የአቶሚክ ቦምብ የት ቦታ እንዳለ ሲዘረዝር አታዩትም። የኢትዮጵያ ሚድያ ግን የኢትዮጵያ strategic ማዕድናት እዚህ ይገኛሉ፣ እንዲህ እየሆኑ ነው እያለ በየቀኑ ሲያወጣ ግን ታቁታላችሁ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ለጥቂት ደቂቃዎች ማንም የኢንተርኔት ዳሰሳ ቢያደርግ ይህ እውነታ እንዳልሆነ ይረዳል።
የአሜሪካ ወይም የምዕራባውያን ሚድያዎች በዚህ በኒውክሊየር ዙርያ ቦታ እየጠቀሱ ከዘገቡት ለቁጥር ከሚታክት ማስረጃ ውስጥ እጅግ ጥቂቶቹ እነዚህ ከታች የተቀመጡት ሊንኮች ናቸው።
ማንም እንደ National Geography እና History Channel ያሉ የቲቪ ጣብያዎችን የተመለከተ የአሜሪካ ኒውክሊየር የት ቦታ እንደሚገኝ ብቻ ሳይሆን ካርታ እያስደገፉ እንዴት እንደተገነባ ሲያስረዱ ማየት ይችላል፣ ጋዜጠኞችም እየተጋበዙ ሄደው ይዘግባሉ። ከራሳቸው አልፈው የሩስያን፣ የቻይናን፣ የሰሜን ኮርያን ወዘተ የኒውክሊየር ማብላያዎች ስፍራዎች በየቀኑ ያቀርባሉ።
ይህ ማለት ግን የድብቅ የጦር መሳርያ መገንቢያ፣ ማጠራቀሚያ ወይም ማብላያ ቦታ የላቸውም ማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ራሱ እዚህ ቦታ ማዕድን አለ ብሎ ሚድያ ላይ የሚያውለውን መረጃ ጠቅሰው የሚዘግቡ እንጂ በራሳቸው ተመራምረው ወይም የማዕድን ፍተሻ አርገው 'ኢትዮጵያ ይሄ ማዕድን አላት' የሚል የኢትዮጵያ ሚድያ አይቼ አላውቅም... ይህን ለማድረግ አቅሙም፣ እውቀቱም፣ ገንዘቡም፣ ድፍረቱም ያለውን ሚድያ ለማወቅ ይቸግራል።
ምናልባት የዲ/ን ዳንኤል ንግግር ኢትዮጵያ ኒውክሊየር ልገነባ ነው ስላለች የግንባታ ስፍራውን ማንም ሚድያ ቀድሞ እንዳያወጣ አስበው ከሆነ በቀጥታ ማሳሰቡ ወይም መጠየቁ ይሻል ነበር እንጂ ለማሳያ ብለው ያቀረቡት መረጃ ፍፁም የተሳሳተ ነው።
እድሜ ለ ChatGPT ማስረጃዎቹ እነሆ:
https://www.washingtonpost.com/archive/politics/1993/01/14/reporters-granted-first-look-at-texas-nuclear-weapons-facility/c6d8186c-1ab7-48f0-934b-20c6a73f7bab/?utm_source=chatgpt.com
https://apnews.com/article/missile-bases-cancer-air-force-malmstrom-military-1999fad70393f0d141676b7faa587eda?utm_source=chatgpt.com
https://apnews.com/article/missile-cancer-nuclear-air-force-f17d9f56e01e2750990d294d4b51a25c
https://apnews.com/article/missile-nuclear-cancer-pcbs-air-force-military-b8787f2f849476af3a24268f80c6603b
https://www.latimes.com/archives/la-xpm-2009-nov-13-na-radiation-nevada13-story.html?utm_source=chatgpt.com
https://www.washingtonpost.com/history/2023/11/13/project-iceworm-greenland-nuclear/?utm_source=chatgpt.com
https://www.washingtonpost.com/world/2019/07/16/location-us-nuclear-weapons-europe-accidentally-revealed-report-nato-body/?utm_source=chatgpt.com
https://thebulletin.org/premium/2025-01/united-states-nuclear-weapons-2025/?utm_source=chatgpt.com
https://www.theguardian.com/us-news/article/2024/aug/26/los-alamos-new-mexico-plutonium-contamination?utm_source=chatgpt.com
https://nypost.com/2025/08/03/us-news/radioactive-wasp-nests-at-sc-nuclear-site-raise-worries-about-possible-contamination-leaks/?utm_source=chatgpt.com
😁 519❤ 351👍 133🙏 25🤔 7🕊 4😱 1😢 1
ይቅርታ!
በጋዜጠኝነት ሙያ መስራት ከጀመርኩባቸው ካለፉት 16 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ በግሌም ይሁን በሰራሁባቸው የሚድያ ተቋማት መረጃ ሳቀርብ ቆይቻለሁ። እነዚህ መረጃዎች ጠቃሚም፣ ጎጂም፣ አስደሳችም፣ አስጨናቂም፣ አናዳጅም ተብለው ሊወሰዱ ይችላሉ።
የማይካደው ሀቅ ግን በርካታ ዜናዎች በተፈጥሯቸው አሉታዊ ስለሆኑ ወደፊት ገፍተው ይመጣሉ።
ታድያ እነዚህ አሉታዊ ይዘት ያላቸው ዜናዎች ያለማቋረጥ ወደ አንባቢ እና አድማጭ ሲደርሱ እንደ ሀገር እና እንደ ማህበረሰብ ድብርትን፣ ጭንቀትን እና ድባቴን ማምጣታቸው እውን ነው።
በማያቋርጥ የግድያ፣ መፈናቀል፣ እገታ፣ የኑሮ ችግር፣ ርሀብ፣ ስደት የታጨቁት የሚድያዎች ዘገባዎች አንዳንድ የማህበረሰብ ክፍል አሁን ላይ ለሚስተዋልበት ጭንቀት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው ግልፅ ነው።
ግን ደግሞ ተጎጂው የማህበረሰብ ክፍል 'ድምፃችንን አሰሙልን፣ ህመማችንን ህዝብ ይወቅልን' ሲል የሚድያ ድርሻ መረጃዎቹን አጣርቶ አየር ላይ ማዋል ነው። በዚህ እሳቤ እነዚህ አሉታዊ (negative) የሆኑ ዜናዎች በዝተዋል።
አይ ህዝብ ሊጨንቀው ይችላል፣ ስለዚህ ተጎጂዎች ህመማችሁን ይዛችሁ ቻሉት ተብሎ ዝም እንደማይባለው ሁሉ ጥሩ ይዘት ያላቸውን፣ ህዝብን የሚያነቃቀቁ መረጃዎችንም ማውጣት ከእኛ ከሚድያዎች ይጠበቃል።
በሚያሳዝን መልኩ ትልልቆቹ የመንግስት/የህዝብ ሚድያዎች ለእንዲህ አይነት የህዝብ ጩኸት ድምፅ ስለማይሆኑ ህዝቡ ወደ ግል ሚድያዎች እና ግለሰቦች መሄድ ብቸኛው አማራጩ ሆኗል።
በግሌም ይሁን በመሠረት ሚድያ ህዝብን ድምፅ ወደፊት በማምጣቴ ቅር የሚለኝ የለም፣ ወደፊትም ባላንስ ባረገ መልኩ ይቀጥላል። አሉታዊ ይዘት ባላቸው ዜናዎች ብዛት ህብረተሰባችን ላይ ለተፈጠረው፣ ወደፊትም ለሚፈጠረው ነገር ሁሉ ግን በግሌ ይቅርታ!
መልካም ምሽት።
@EliasMeseret
❤ 1 127🙏 417👍 167😁 47🕊 26🤔 12😢 11😱 7
ዛሬ በቪርጂኒያ የተካሄደው Grand African Run ድንቅ ነበር፣ እኔም ተካፍዬ ስለነበር የተወሰኑ ፎቶዎችን አያይዣለሁ። ነገ ደግሞ ሰይፉ ፋንታሁን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ጋሽ መሀሙድ አህመድ እና አቶ ጆ ማሞ የሚሸለሙበት የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ፕሮግራም በሜሪላንድ ግዛት ይካሄዳል። ፕሮግራሙ ላይ መገኘት ይፈልጋሉ?
👉 ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ በዚህ ሊንክ አሁኑኑ ይመዝገቡ: https://www.eventbrite.com/e/1744356420009?aff=oddtdtcreator
📍 ቦታ: Civic Building, 1 Veteran Plaza, Silver Spring, Maryland
🗓️ ቀን እና ሰዓት: ኦክቶበር 12, 5:30 PM
🍽️ የእራት ግብዣም ይኖረናል
🎤 የአሜሪካ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎች እና የልዑክ ቡድኖች ይገኛሉ
ነገ በሽልማት ፕሮግራሙ ላይ እንገናኝ!
❤ 231👍 72😁 18😢 4🤔 1🙏 1🕊 1
00:48
Видео недоступноПоказать в Telegram
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ በአሜሪካ ስለሚካሄደው ግራንድ አፍሪካን ረን ያስተላለፈው መልዕክት በቪድዮው ተያይዟል።
በየዓመቱ በአሜሪካ የሚከናወነው እና በርካታ ወገኖቻችንን የሚያሳትፈው ግራንድ አፍሪካን ረን በቪርጂኒያ እና ዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ቦታ ላይ ኦክቶበር 11 (ጥቅምት 1) ጠዋት ይካሄዳል።
በቦታው ላይ ተገኝተው መጨረሻም ሆነ መጀመሪያ ርቀቱን ሲያጠናቅቁ የ2026 ቶዮታ ኮሮላ ለማግኘት ዕጣ ውስጥ ይካተታሉ። በዝግጅቱ ላይ የኦሎምፒክ ጀግኖቻችንም በእንግድነት ይገኛሉ፣ አብረዋቸው እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።
ለመመዝገብ www.africanrun.com ድረ-ገፅን ይጠቀሙ። ከአስሩ የበጎ አድራጎት አጋር ድርጅቶቻችን መካከል ለአንዱ ሲሮጡ ደግሞ በመመዝገቢያ ክፍያዎ ላይ ቅናሽ ያገኛሉ። ለዚህም www.africanrun.com/charity-partners ይጎብኙ።
የግራንድ አፍሪካን ረን አዘጋጅ ኖቫ ኮኔክሽን
7.29 MB
❤ 283👍 50😢 7😁 2🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለደማቁ የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!
ኢሬቻ የዝናብ ወቅት አልፎ ፀሀይ ሲገለጥ ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረቢያ ታላቅ በዓል ነው፣ መልካም ግዜ!
@EliasMeseret
😁 624❤ 189👍 35🤔 25🕊 25🙏 13😱 11😢 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለዘመናት በመንግስት ነዳጅ ላይ ሲደረግ የነበረው ድጎማ ተነስቶ አልቋል፣ ከዚህ በኋላ በአለም አቀፍ ገበያ ሂሳብ ይመራል ተባለ።
አሁን ደግሞ አዲስ የ30 በመቶ ግብር ነዳጅ ሊጣል ነው እየተባለ ነው። የዛሬ አመት ደግሞ ሌላ አዲስ ግብር ይመጣል፣ ከዛም ሌላ... ህዝብን የሚራቁት አዙሪት!
@EliasMeseret
😢 1 063👍 130❤ 102😱 65🙏 25🤔 22😁 21🕊 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከሶስት ሳምንት በላይ እስር ላይ የቆዩት የሸገር ኤፍኤም ጋዜጠኞች በዋስ ተለቀዋል
እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ!
https://tinyurl.com/3m2zd7ch
@EliasMeseret
👍 394❤ 118🙏 42🤔 12🕊 12😁 5😱 3
መሠረት ሚድያ ላይ ከሚሰጡ በርካታ አስተያየቶች አንዱ መረጃዎች በፕሪሚየም አባልነት በመሆናቸው ማንበብ አልቻልን፣ አማራጭ ይፈለግ የሚል ነው።
ይህ የፕሪሚየም አገልግሎት ባይጀምር ኖሮ ሚድያው በአንድ ሰው ጫና ላይ ወድቆ እስካሁን መቀጠል መቻሉን እጠራጠራለሁ። ለዚህ ግዜያዊ መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደው አንዳንድ ዜናዎችን ለሁሉም ክፍት ማድረግ፣ በሳምንት አንድ ቀን (አርብ) ጠርቀም ያሉትን የሳምንቱን ዜናዎች በዩትዩብ ለህዝብ ማቅረብ እና የ30% የፕሪሚየም አባልነት ቅናሽ ማድረግ ነው።
ሌላ መፍትሄ እስኪበጅ በዚህ ሊንክ አማካኝነት በ30% የፕሪሚየም አባል ይሁኑ፣ በስምንት ሪፖርተሮቻቸን ከመላው ኢትዮጵያ የሚሰናዱትን እና የትም ቦታ የማያነቧቸውን ሀገራዊ መረጃዎች ይከታተሉ ⤵️
https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
👍 223❤ 114😁 79🙏 33😢 18🤔 10
Фото недоступноПоказать в Telegram
መሠረት ሚድያ ከመፍረስ የታደገው ትምህርት ቤት!
መሠረት ሚድያ ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም በሰራው አንድ ዘገባው አራት ኪሎ የሚገኘው የምኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በአሁን አጠራሩ ደግሞ የኮተቤ ዩኒቪርሲቲ የሳይንስ ካምፓስ (STEM Academy) ሊፈርስ መሆኑን መረጃ ለህዝብ አቅርቦ ነበር። ዜናው ከቀረበ ብዙ ቀናት ቢያልፉትም ዛሬ መንግስታዊው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) መረጃው 'ሀሰት ነው' ብሎ ብቅ ብሏል።
የሚገርመው ግን እዛው የኢፕድ መረጃ ላይ የመሠረት ሚድያ መረጃ ትክክል እንደነበር ይጠቁማል።
ቦታው በመንግስት ስለተፈለገ ትምህርት ቤቱ ሌላ ቦታ እንዲፈልግ በደብዳቤ ተጠይቆ እንደነበር፣ አሁን ላይ ጥያቄው በመቅረቱ ትምህርት ቤቱ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን በዚሁ ግቢ መጀመሩን ያስነብባል (በምስሉ ላይ በቀይ ይታያል)።
ባለፉት ጥቂት ቀናት የደረሰኝ መረጃ እንደሚያሳየው ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ታሪካዊው ትምህርት ቤት ሊፈርስ መሆኑን የሚድያ ዘገባውን አይተው ጣልቃ በመግባት ትምህርት ቤቱን እንደታደጉት ነው።
ስለዚህ መሠረት ሚድያ ትምህርት ቤቱን ከመፍረስ ታድጎታል፣ መረጃውም ትክክል እንደነበር ራሱ የመንግስት ሚድያው አረጋግጧል። ታድያ የሌባ አይነ ደረቅ ነገር ካልሆነ ውሸቱ የቱ ነው?
#መሠረትሚድያ
👍 599❤ 257🙏 69😁 60😱 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንደ ሸገር ኤፍኤም የጋዜጠኞቹን እስር ችላ ያለ ሚድያ እስካሁን አላየሁም!
ሁለት ጋዜጠኞቹ ከታሰሩ 17 ቀን የሞላቸው ቢሆንም ሚድያው አንድ ነገር ሳይተነፍስ ቆይቷል። ትናንት መሠረት ሚድያ ሸገር ኤፍኤም ለራሱ ጋዜጠኞች እንኳን ድምፅ ሊሆን አልቻለም የሚል ዜና ማውጣቱን ተከትሎ ዛሬ "በቁጥጥር ስር ከዋሉ 17 ቀን ሆናቸው" የሚል ዜና ይዘው ብቅ ብለዋል።
ለራስህ ጋዜጠኛ ድምፅ ካልሆንክ እንዴት ለሌላው ህዝብ ድምፅ ልትሆን ትችላለህ?
ሁለቱ ታታሪ ጋዜጠኞች ትግስት ዘሪሁን እና ምንተአምር ፀጋው የታሰሩት በጤና ባለሙያዎች ዙርያ በሰሩት ዘገባ ነው፣ ጥፋት ካለባቸው እንኳን በሚድያ ህጉ መጠየቅ እየተቻለ አሁንም ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ማቆያ ተይዘው ይገኛሉ።
@EliasMeseret
❤ 436😢 248👍 75😁 15🤔 13
