134 016
Подписчики
-1424 часа
-1207 дней
-28530 день
Архив постов
#YouTube ከሰሞኑ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር በኢሚግሬሽን ዙርያ አዳዲስ ለውጦችን ማድረጉን ወይም ሊያደርግ ማሰቡን እያስታወቀ ይገኛል። ታድያ ይህ ለውጥ ለኢትዮጵያውያን እና ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?
በዚህ ዙርያ የመሠረት ሚድያ በርካታ ተከታታዮች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በአሜሪካን ሀገር የኢሚግሬሽን የህግ ባለሙያ ከሆነው ጠበቃ ሙሉአለም ጌታቸው ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርገን ነበር፣ ይከታተሉት።
https://youtu.be/Iowexmd_OtQ?si=G2NWB0EzdGfCWKBy
❤ 127👍 39🙏 15😁 2
ከሰሞኑ መንግስት ቆፍጠን ያሉ እርምጃዎችን ሲወስድ እየተመለከትን ነው። በተለይ አንድ ሰሞን አይነኬ የሚመስሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ጥብቅ የምርመራ ፋይል እየተከፈተ ነው። ጥሩ ሲሰራ ማመስገንም ይገባልና በርቱ ልንል እንወዳለን 🙏🏽
@EliasMeseret
👍 1 514❤ 321🙏 127😁 23🕊 22🤔 16😱 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
አንድ አጭር ክትትል አረግን። መሠረት ሚድያ ላይ ከሚቀርቡ የመልካም አስተዳደር፣ የሙስና እና ህዝብ ላይ የሚደርሱ በደሎች ዘገባዎች መሀል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 65 ፐርሰንት ገደማው በሚመለከተው አካል ምላሽ ተሰጥቶበታል፣ ወይም ምላሽ ለመስጠት ሙከራ ተደርጓል (ለማሳያ አንድ የዛሬ ዘገባን ይመልከቱ: https://www.meseretmedia.org/p/2aa)
አንድ የመንግስት ሀላፊ በቅርቡ "አንዳንዴ ታበዙታላችሁ እንጂ ሚድያችሁ ስራዎችን ለማስተካከል እየጠቀመን ነው" በሚል የተናገሩት ለዚህ ይመስላል። 'ታበዙታላችሁ' የሚለው ያው subjective ነው 🙃
ታድያ በእንዲህ አይነት የሁሉንም በር ቀስ በቀስ በሚያንኳኳ የመልካም አስተዳደር ችግር ዙርያ ትኩረት ተደርጎ ዜና ሲሰራ ካድሬው "ተቃዋሚ" የሚል ስም ለመለጠፍ ይሯሯጣል፣ መሠረት ሚድያ ግን ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።
በዚህ ሊንክ የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል በመሆን ስራውን የበለጠ ለማስፋት እና በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ስራ ለመጀመር እያደረግን ያለውን ዝግጅት ይደግፉ ⤵️
https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
❤ 466👍 232🙏 21😁 19🕊 10🤔 5😱 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ፅዳትም ሆነ ልማት ለራስ ነው... ነገር ግን እነዚህን ተግባራት በሁለት ቀን ውስጥ ያልፈፀመ ነዋሪ በአዋጅ እንደሚቀጣ ደብዳቤው ይጠቅሳል፣ ይህ ስፍራ ደግሞ ጡረተኞች በብዛት የሚኖሩበት አካባቢ ነው። ጥድፊያው ለምድን ነው? ይህን ሁሉ ለማድረግ ነዋሪው ሁሉ አቅም አለው ብሎ የወሰነውስ ማነው?
- ራዲየስ ማፅዳት
- ኮምፖስት ወይም ቀዝል ማዘጋጀት
- ያረጁ ዛፎችን እና አበባዎችን መከርከም
- ከርብ ስቶን መስራት እና ጥቁር በቢጫ ቀለም መቀባት
- በተሰሩ ከርብ ስቶኖች ውስጥ አበባ መትከል
- ቆሻሻ በአይነት መለየት እና ለፅዳት ማስረከብ
- አጥሮችን ግሬይ ቀለም መቀባት
- ካሜራ ማስገባት
- ወል ማውንት ማውጣት...
@EliasMeseret
😢 332❤ 117🤔 53😁 40👍 24😱 12🙏 10🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#የኢሚግሬሽንነገር በትናንትናው እለት መሠረት ሚድያ አዲሱ የኢሚግሬሽን ዌብሳይት መስራት እንዳቆመ አንድ መረጃ አጋርቶ ነበር። በደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ኢሚግሬሽን በፌስቡክ ጉፁ ላይ ማንኛውም ፓስፖርት ፈላጊ www.immigration.gov.et ላይ መመዝገብ እንደሚችል እና ዌብሳይቱ እንደሚሰራ ምላሽ ሰጠ።
ማንም ሊንኩን ከፍቶ ማረጋገጥ እንደሚችለው ዌብሳይቱ ዛሬን ጨምሮ ለበርካታ ቀናት መስራት አቁሟል፣ በርካቶችም እየተንገላቱ ይገኛሉ። በአካል ለሚሄድ እና ጉቦ እስከ 35,000 ብር ለከፈለ በውስጥ ይሰራሉ። ዌብሳይቱ በርካታ ሺህ ዶላሮች ወጥቶበት ዱባይ ባለ ካምፓኒ የተሰራው ነው።
ይህ ለረጅም ግዜ የቆየ ዝርፊያ አሁንም ቀጥሏል፣ በተቋሙ የሚቀርቡ ሪፖርቶች ግን ሁሉ ነገር የተስተካከለ እና ዜጋ በአሰራሩ ተደስቶ እንደሚወጣ ነው። ቢያንስ 'እንዴት የማይሰራ ዌብሳይት ይሰራል ተብሎ ይለጠፋል?' የሚለው ጥያቄ መልስ የለውም።
@EliasMeseret
👍 739❤ 185😢 110😁 71🤔 37🙏 18😱 11🕊 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከሰሞኑ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጭ የነበረው ቪድዮ እጅግ አሰቃቂ እና በክቡር የሰው ልጅ ላይ የተፈፀመ ነውር ነው፣ ማንም ሁሌም ሊያወግዘው የሚገባ ተግባርም ነው።
የቪድዮውን መውጣት ተከትሎ ይህ ምስል ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጭ ቆይቷል። ምስሉ “እውነት እያደረች ትጠራለች ተደብቃ አትቀርም! የጨካኙ የብልፅግና ድራማ በማስረጃ ተጋልጧል” የሚል ጽሁፍም ይዟል። ይህም በጭካኔ ድርጊቱ የመንግስት እጅ እንዳለበት ህዝብን ለማሳመን የተደረገ ሙከራ እንደሆነ አንዳንዶች ሲገልፁ ተስተውለዋል።
ይሁንና ምስሉ በ AI የተፈበረከ ሀሰተኛ ምስል እንደሆነ SynthID Detector በመጠቀም አረጋግጠናል።
ለዝርዝሩ የኢትዮጵያ ቼክ ዘገባን ያንብቡ: https://tinyurl.com/fake-ai-image
@EliasMeseret
👍 378❤ 143😢 42😁 27🤔 9😱 4🕊 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
መሠረት ሚድያ በአርሲ ዞን ውስጥ የማርበርግ ቫይረስ እንደተከሰተ ለሰራው ዘገባ የአካባቢው ባለስልጣናት "ውሸት ነው" የሚል ምላሽ ከሰጡ በኋላ ከታች የሚታየውን አበረታች የሆነ ምላሽ ለቲክቫህ ሰጥተዋል፣ መረጃውን እንደ ጥቆማ በመውሰድ እየተጠቀሙበትም እንደሆነ ተናግረዋል።
ውሸት ነው የሚለው ግዜውን ጠብቆ መታወቁ አይቀርም። በሚድያው በሽታው ተከስቶበታል በተባለው አካባቢ ናሙና የመውሰድ እና ግንዛቤ የማስጨበጫ ስራ ከተሰራ ግን ሌላው ትርፍ ነው።
የሚድያም ሚና እሱ ነው!
❤ 454👍 254😁 47🙏 30😢 15🤔 9😱 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
Join us now! Be part of the conversation ⤵️
መሠረት ሚድያ ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያደርገው ጥረት አካል የሆነው የፕሪሚየም አባልነት የ30% ቅናሽ ክፍት ተደርጓል፣ ይህን ሊንክ በመጠቀም አሁኑኑ ይቀላቀሉ። አንድም ሀገራዊ መረጃ አያምልጥዎ!
https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
❤ 136👍 38😁 36
ከሰሞኑ እየተዛመተ ባለው የማርበርግ ቫይረስ ዙርያ ግልፅነት የሌለው አካሄድ የበርካታ ሰውን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል!
መሠረት ሚድያ በጂንካ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከዘገበ ከስድስት ቀናት በኋላ ጤና ሚኒስቴር ማረጋገጫ ሰጠ፣ አሁንም እንደ አርሲ ባሉ አካባቢዎች ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። መረጃውን በፍጥነት ለህዝብ ይፋ አርጎ ሰው እንዲጠነቀቅ ማረግ አይሻልም?
በሽታው ገባባቸው በተባሉ አካባቢዎች ልየታ እስከሚደረግ ማንም ሰው እንዳይገባ እና እንዳይወጣ መደረጉ መልካም ቢሆንም ይህን ክስተት 'ገፅታ እንዳያበላሽ' በሚል መደበቁ በሰው ህይወት መቆመር ነው።
እነዚህ ከታች ስማቸው የተቀመጠ ሰዎች በአርሲ ሶን አሰኮ ወረዳ ሁሉቆ ቀበሌ ውስጥ ብቻ ህይወታቸውን እንዳጡ በመሠረት ሚድያ የተረጋገጡ ናቸው:
1. አሜ ሙሳ
2. ሳኒ አህመድ
3. አብራሒም ሃሚዶ
4. አብዱረማን በያን
5. ሙሃመድ አብዲ አብዱላ
6. ሙለታ ኢብሮ
7. ሆሴና ሙሜ
8. ህፃን መይሙና ሳና አህመድ
9. ህፃን ማሪፋ ሙሃመጥ
10. በጥሪያ ከማል ሙሜ እና
11./አሺረፋ አደም
የመሠረት ሚድያን ዘገባ ያንብቡ: https://meseretmedia.org/marburg-virus
😢 406❤ 161👍 57🤔 16🙏 15😱 11😁 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቲክቶክ ተሰላፊ ባልሆንም አንዳንዴ ጎራ እላለሁ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ግን አንዱ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ለማቅረብ እንኳን በሚቀፍ እጅግ አፀያፊ ስድብ ሲሳደብ ሰማሁ።
አፀያፊ ስድቡ እንደ ፌስቡክ ባሉ ፕላትፎርሞች ላይ ቀርቦ ቢሆን አንድ ቀን አይቆይም፣ ቲክቶክ ግን ቁጭ ብሎ እየተመለከተ ነው፣ ይህ ደግሞ ተቀባይነት የለውም። በፍፁም!
ለሚመለከተው የቲክቶክ የአፍሪካ ቡድን ጉዳዩን በግሌ በኢሜይል ዛሬ አሳውቄያለሁ። ሁሉም ሀይማኖት፣ ብሄር፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይለይ እንዲህ አይነት ፀያፍ ጥቃቶችን ሪፖርት ያድርግ። ወደፊትም በየትኛውም ሀይማኖት ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈፀም ህዝብ ተባብሮ ሊያዘጋ ወይም ኮንተንቱን ሊያስወርድ ይገባል።
@EliasMeseret
🙏 1 471👍 383❤ 255😁 41🕊 23🤔 10😢 6😱 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
'የወባ ወረርሽኝ ከ50 በመቶ በላይ ቀነሰ' የሚል አስገራሚ መረጃ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዴኤታው ለመንግስት ሚድያ ተናገረዋል። ይህ መረጃ የወጣው እንደ ዳውሮ ዞን ባሉ አካባቢዎች በአሁኑ ሰአት በየቀኑ በደርዘን የሚቆጠር የሰው ህይወት እየጠፋ ባለበት እና ሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ሞልቶ ሰው በየዛፍ ስር ተኝንቶ በሚታከምበት ወቅት ነው (ዝርዝሩን ያንብቡ: https://tinyurl.com/5wt7s29m)
የአለም ጤና ድርጅት የቅርብ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ ለአመታት የወባ ወረሽኝን በመከላከል ዙርያ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች እየተሸረሸሩ አሁን ላይ ከ7.3 ሚልዮን በላይ የወባ ተጠቂዎች መመዝገባቸውን ነው፣ ይህም የዛሬ ሁለት አመት ከነበረው እጥፍ ገደማ ማለት ነው።
ሰው ሲሞት ውሸት ነው፣ ወባ ሲከሰት እየጠፋ ነው፣ ህዝብ ሲራብ ምርት ጨምሯል፣ እገታ ጨምሯል ፀጥታው አስተማማኝ ነው... ከእውነት ጋር እንዲህ የተጣላን ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል።
ሁለት ማስረጃዎች ⤵️
https://www.doctorswithoutborders.org/latest/unprecedented-surge-malaria-cases-ethiopia#:~:text=More%20than%207.3%20million%20malaria,with%20previous%20and%20ongoing%20conflict.
https://www.nytimes.com/2024/10/25/health/malaria-ethiopia-deaths-cases.html#:~:text=Global%20Health-,Malaria%20Is%20Surging%20in%20Ethiopia%2C%20Reversing%20a%20Decade%20of%20Progress,an%20alarming%20spread%20of%20cases.
@EliasMeseret
😢 478👍 172❤ 122😁 20🙏 10🤔 6🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የእለት ጉርስ ለማግኘት የሚንከራተቱ ወጣቶች ከየመንገዱ ካለፍላጎታቸው እየታፈሱ የት እየተወሰዱ እንደሆነ የዛሬ ዓመት ገደማ ይህን አስፍሬ ነበር፣ መሠረት ሚድያም በምርመራ ዘገባዎቹ በተደጋጋሚ ሲጠቁም ነበር።
ቢቢሲ አማርኛ ዛሬ ባወጣው መረጃ መዳረሻቸውን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በመንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መርማሪዎች የተደረሰበትን አሳዛኝ የልጆቹን ሁኔታ ዳስሷል። እውነት አንዳንዴ ለግዜው ብትደበቅም መውጣቷ አይቀርም።
የቢቢሲን ዘገባ ለማንበብ:
https://www.bbc.com/amharic/articles/c74jrydd1vko?fbclid=IwdGRzaAOAZ61jbGNrA4BnqWV4dG4DYWVtAjExAHNydGMGYXBwX2lkDDM1MDY4NTUzMTcyOAABHpY2BelnU6mYkaIPuxmZ0t913CGOUnAWf_dbZZgb2ogXQNkSvD7ucKe44dzA_aem_Vt4a6vS40R1M2XEciTCECQ
@EliasMeseret
❤ 283😢 194👍 68🕊 8🙏 7😁 3🤔 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሊደገም፣ ሊደጋገም የሚገባው አሰራር!
መሠረት ሚድያ ላይ በቅርቡ የወጣ አንድ በከፊል የተሳሳተ መረጃ ነበር፣ መረጃውን ለማስተባበል ደግሞ ዜናው ላይ በስህተት ከተጠቀሱት ሁለት ግለሰቦች አንደኛዋ ከጠ/ሚሩ ጋር የጎንደር ጉብኝት ላይ እንዲሳተፉ ተደርገው ፎቶው ዛሬ በጠ/ሚር ቢሮ እና በመንግስት ሚድያዎች ላይ ተለቋል።
ይህ ብልሀት የተሞላበት እና በማስረጃ የተደገፈ ማስተባበያ በውጭ አለም በስፋት የሚሰራበት እና እሰረው፣ አሳደው ከሚለው በሀገራችን ከተለመደው የተለየ ነው፣ ወደፊትም ስህተቶች ሲኖሩ ሊደገም የሚገባው ስልት ነው። መሠረት ሚድያም እርምቱን ዛሬ አውጥቷል።
ለመሠረት ሚድያ በጠ/ሚር ቢሮ ደረጃ እንዲህ ምላሽ መሰጠቱ የሚድያውን ተደራሽነት፣ ተሰሚነት እና እድገት ጠቋሚ ነው። ከዚህ በፊት በዚህ ደረጃ ለአንድ ወይም ሁለት የውጭ ሀገር ሚድያዎች ምላሽ ሲሰጥ አስታውሳለሁ።
ይሁንና መሠረት ሚድያን በዚህ መልኩ የሚከታተሉት ከሆነ ሌሎች በሚያቀርባቸው እንደ መብት ጥሰት፣ ሙስና እና የዜጎች የዕለት ተዕለት ተማፅኖ እና እሮሮዎች ዙርያም በተመሳሳይ በከፍተኛ የመንግስት ደረጃ ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው እላለሁ።
#መሠረትሚድያ
@EliasMeseret
👍 700❤ 311😁 127🤔 26🕊 14🙏 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይህ እንግዲህ ባሳለፍነው ሳምንት 25 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በአርሲ ሐገረ ስብከት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ፣ ትናንት ተጨማሪ 5 ሰዎች በተመሳሳይ እንደሞቱ ለወጣው መረጃ ማርከሻ መሆኑ ነው።
የሀይማኖት አባት እና የሀገር ሽማግሌ ንፁሀን ህዝብ ሲጨፈጨፍ ሀዘኑን ገልጾ፣ ድርጊቱን አውግዞ እንዲሁም ወደፊትም እንዳይደገም ከህዝብና መንግስት ጋር ይመክራል እንጂ በሚጨፈጨፍ ህዝብ እንዲህ አይሳለቅም። ይህ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ግድያቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከማድረግ ውጪ ሌላ አላማ ያለው አይመስልም።
This is truly sad!
@EliasMeseret
😢 1 002👍 172❤ 123😁 26🕊 12🤔 9
ኦርቢት ኤሌክትሮኒክስ ቅጥ ያጣ ማስታወቂያውን አንስቷል፣ ወደፊት እንደማይደግመው ተስፋ እናደርጋለን።
@EliasMeseret
👍 359🙏 69❤ 43🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኦርቢት ኤሌክትሮኒክስ የሚሸጠውን ምርት ለማስተዋወቅ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ፊልም ላይ ኮኬይን በአፍንጫ የሚስቡትን አስመስሎ ሰርቶ ለቋል።
ፍፁም ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። ምን ለማስተላለፍ ተፈልጎ ነው?
ይህን ማስታወቂያ በአስቸኳይ ማንሳት አለበት፣ ሌላ ሀገር ቢሆን በህግም ሊጠይቅ የሚችልበት ጉዳይ ነው።
https://www.facebook.com/share/r/1CUgu33RFc/
❤ 327👍 189😁 99🤔 34🙏 21😢 12🕊 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
'አልጀዚራ' እና 'ኩኪስ'... ሁለቱ በጋዜጠኝነት ስም የሚንቀሳቀሱ አምታች ቡድኖች በኢትዮጵያ!
የኢትዮጵያ ሚድያን ቀረብ ብሎ የሚያውቅ 'አልጀዚራ' እና 'ኩኪስ' ስለሚባሉት ሁለት አምታች ቡድኖች ያውቃል። ምንድን ናቸው?
አልጀዚራ:
በዚህ ምድብ ያሉት ልክ እንደ አልጀዚራ ጋዜጠኞች ትልልቅ የቪድዮ እና የፎቶ ካሜራዎችን ተሸክመው በጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ ድግስ፣ ኮንሰርት፣ ኮንፈረንስ፣ የዝነኞች ቤቢ ሻወር፣ ሰርግ... ወዘተ በመሄድ ምስል የሚቀርፁ በመምሰል ይገኛሉ። ብዙዎቹ ግን ቪድዮ መቅረፅ የማይችሉ፣ ካሜራቸውን የውጭ በር ማለፊያ አርገው የሚጠቀሙ ናቸው፣ ከዛም የተገኘውን ምግብም ሆነ የኪስ አበል በመጠቀም ኑራቸውን ይገፋሉ።
ኩኪስ:
እነዚህኛዎቹ ቁጥራቸው በዛ ያለ ሲሆን አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ ክፍለ ሀገር ዝግጅት አለ ሲባል በፍጥነት በመገኘት ይታወቃሉ። ኩኪሶች የሚሰሩበት የሚድያ ተቋም የላቸውም፣ ስራቸው የሚሰጣቸውን መረጃ በግል የፌስቡክ ገፃቸው ማጋራት ነው። የጋዜጠኛ መለያ የሆኑትን እንዴት? መቼ? ለምን? የሚሉ ጥያቄዎችን አይጠይቁም። ተፅፎ የሚሰጣቸውን ጋዜጣዊ መግለጫ (press release) በቀጥታ ያጋራሉ፣ የኪስ አበል እና ኩኪስ/ድግስ ይቋደሳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ምስሉ ላይ የሚታዩት ትናንት ሱፐር ደብል ቲ መግለጫ ላይ የተገኙ ምድብተኞች ናቸው።
መሠረት ሚድያ የሰራውን ዘገባ ለማድበስበስ በተጠራ ፕሮግራም ላይ ሲገኙ ጫፉን ይዘው ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን ማቅረብ ሲገባቸው ተጽፎ የተሰጣቸውን ሲያጋሩ ውለዋል። በይዘት ብቻ ሳይሆን አንቀጽ በአንቀጽ ሲታይም ተመሳሳይ ነው። መሠረት ሚድያንም ምላሽ ወይም አስተያየት አልጠየቁም።
በነገራችን ላይ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ የተገኙት ምድብተኞች የባንክ አካውንት ቁጥራቸውን አስተላልፈዋል፣ ነገ ሰኞ ብር ይገባላችኋል ተብለዋል (መጠኑን አላወቅኩም)። ትናንት በሄዱበትም ጉዞ ላይም አለም ገና ከተማ በሚገኘው አለም ሆቴል ቁርሳቸውን እና ምሳቸውን ተፈውሰዋል።
ስንት ደግሞ ላቡን ጠብ አርጎ እየሰራ የሚዋከብ ጋዜጠኛም አለ። የእናት ሆድ ዝንጉርጉር!
ለማንኛው አንድ ወዳጄ እንዳለው 'ማስተባበያው ማስተባበል አልቻለም!'
@EliasMeseret
❤ 828👍 385😁 249😢 43🙏 33😱 14🤔 13🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ድራማ ሱፐር ደብል ቲ ጋዜጠኞችን ዛሬ ወስዶ አንዱ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት የነበረ እና ምስሉን አጋርቼ የነበረ ግለሰብን በነርቭ ጉዳት ዊልቼር ላይ እንደተቀመጠ በቪድዮ እንዲህ አስብሎታል።
"እዚህ ድርጅት ውስጥ በ sales ስሰራ ሳንቲም ጎሎብኝ ነበር። ወደ ፖሊስ ጣብያ ለጥያቄ በሄድኩበት በራሴ ምክንያት ስሜታዊ ሆኜ ከግድግዳ ጋር ተጋጭቼ እንጂ ምንም አይነት ድብደባ የደረሰብኝ የለም።" ቪድዮ: https://www.facebook.com/share/v/19rLpURdcG/
እንዲህ አይነት ጭካኔ በሰው ልጅ ላይ የሚያደርስ አካል ህግ ሊጠይቀው ሲገባ ይባስ ተጎጂዎችን እንዲህ ሰብስቦ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይሳለቃል።
ወንድሜ ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ!
@EliasMeseret
😢 586❤ 306😁 218🤔 57😱 27👍 19🙏 16🕊 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
#መልካምዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነውን Airbus A350-900 አውሮፕላን ዛሬ ጠዋት በቦሌ አየር ማረፊያ ይረከባል።
መለያው ET-BCE እንዲሁም የበረራ ቁጥሩ ET9201 የሆነው ይህ አውሮፕላን የኤርባስ ዋና ፋብሪካ መገኛ ከሆነው ቱሉስ፣ ፈረንሳይ ተነስቶ መብረር የጀመረ ሲሆን ከጠዋቱ 12 ሰዓት አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ምስሉ Live ከ Flight Radar የ 3D ምስለ-በረራ ላይ ከደቂቃዎች በፊት የተወሰደ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን!
@EliasMeseret
❤ 533👍 186🙏 28😢 6😱 3🕊 1
