ru
Feedback
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

Открыть в Telegram

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና | የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል! የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ "የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው " https://www.youtube.com/user/TheNahusenai Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Больше
10 829
Подписчики
-824 часа
-237 дней
-14230 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ሳንኮሎጂ| 6 አይነት መርዛማ ሰዎች 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት ፔጁንም Follow ያርጉ 1. ኃይል መጣጮች፣ • የመጨናነቅ ስሜት እንዲሰማህ ያደርጉሃል፣ • ያለ ምንም ምክንያት ያዋርዱሃል፣ • የሌሎችን መልካም ዕድል ማየት አይችሉም (ቢያዩም አይደሰቱም)፣ 2. ሀሰተኛ አመስጋኞች፤ • ሀሰተኛ ምስጋናዎችን ይሰጣሉ፣ • ስሜትን የመረዳት ችሎታ ይጎድላቸዋል፣ • ምቾት በማይሰማቸው ሁኔታዎች ውስጥ ያስገቡዎታል፣ 3. ተስፋ አስቆራጮች፣ • እነሱ የተሻለ ስሜት እንዲሰማቸው ለማድረግ አንተን ያዋርዱሃል፣ • ከህልምህ ያደናቅፋሉ፣ 4. ነቃፊዎች፣ • ውሳኔዎችህን አይደግፉህም፣ • የምታደርገውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይነቅፋሉ፣ 5. አታላዮች፣ • ሁሉንም ሰው ለመቆጣጠር ይሞክራሉ፣ • አንተን እና ሌሎችን እንደወደዱ ያስመስላሉ፣ 6. ተጎጂ መሳዮች፣ • ከሌሎች የማያቋርጥ ትኩረት ይፈልጋሉ፣ • ውድቀታቸውን እንደ ሰበብ አድርገው በብዛት ይናገራሉ፣ ለክረምት የምንሰጠውን የህይወት ክህሎት ስልጠና ለመሳተፍ 0912664084 ይደውሉልን
Показать все...
👍 15 10😁 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ሳይኮሎጂ| ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት ፔጁንም Follow ያርጉ 📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡ 📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡ 📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡ 📕በዙሪያህ ካሉ የሰዎች ጫጫታ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡ 📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡ t.me/psychoet
Показать все...
👍 8 7
#ሳይኮሎጂ| ደስተኛ ለመሆን የሚረዱ 10 የሕይወት መርሆዎች! 1.እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር!" ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ። 2."አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው!" <>~ ~<> <>~ <> የጎደለህ ምንድን ነው? ☞ያለህስ ምንድን ነው? ☞ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። 3."እራስህን ሁን!" <>~ ~<> <>~ <> በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤ 4."ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር!" <>~ ~<> <>~ <> አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነትጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር። 5.የውሸት ደስታን አትፈልግ!" <>~ ~<> <>~ <> በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤ 6."ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅንሁን!" <>~ ~<> <>~ <> ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤ 7."መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው!" <>~ ~<> <>~ <> ብዙሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው። 8. "የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን!" <>~ ~<> <>~ <> ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና? 9."መልካም አስብ መልካም ተናገር!" <>~ ~<> <>~ <> በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል። 10."ለምን እንደምትኖር እወቅ!" <>~ ~<> <>~ <> ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድንነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይለወጣል። ፈጣሪ ማስተዋሉን ያብዛልን! ሼር ሼር
Показать все...
24👍 9
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ሳይኮሎጂ| ብሩህ ቀን ይመጣል!!! 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት ፔጁንም Follow ያርጉ በጣም የምትወዱት ነገር ላጣችሁ፤ የትላንትናው ማንነት እና እኔነት ለረሳችሁ፤ የትዝታ አልጋ የዛሬ ማራፊያ ለሆናችሁ፤ ብሩህ ቀን ይመጣል። የምትወዱት አጣችሁ በትላንት ትዝታ የኋሌት ለምትቀዝፉ፤ ነገሮች እንዳሰባችሁት ሳይሆን የተገላቢጦሽ ለሆነባችሁ፤ የህይወት ጣዕሙ ለጣፋችሁ፤ ለሰው መልካም ሰርታችሁ በክፉ የተመለሰላችሁ፤ ትላንት ሰው የሚወደው ልባችሁ በወደዳችሁት እና ሁሉ ነገር በሰጣችሁ ሰው ከጀርባ የተወገችሁ፤ ህይወታችሁ ውስጥ የምታምኑት እና የልባችሁ የምትነግሩት ሰው ላጣችሁ፤ የበሰበሰ ዝናብ አይፈረም እንደሚለው የሀገሬ ተረት ማጣትም ማግኘት ምንም የማያስደስታችሁ፤ ባገኘችሁት ነገር ማደሰት የቆማችሁ ምክንያቱም ከዚህ በፊት የተደሰትኩባቸው ነገር አልበረክት ያላባችሁ፤ ግን አለ ብሩህ ቀን ሀዘን በደስታ ለቅሶ የሚቀየርበት አለ አንድ ቀን ። እና አይዞችሁ ማንም ከአጠገብ ኖሮ ባይሰማችሁ አይዞን ይታለፈል። ከሰው ጋር ስቀህ እና ደስ ብሎ ልብህ ውስጥ ያለው ክምር ሀዘን አይቀንስ ግን ይህን አስብ ብሩህ ቀን ይመጣል፤ ላይነጋ አይደለም የጨለመው፤ አንተ ብቻ እንዳይመስልህ በዚህ የህይወት ዓይነት ውስጥ የምታልፈው ሁሉም ነው ግን ሁሉም ስለሚደብቅ ነው፤ ሁሉም ህይወት ከብዶታል እና እኔ ብቻ ነኝ አትበል አብዛኛው እንዳተው ነው ህይወት የከበደው። ስለዚህ አይዞህ በርታ ይደረሳል፤ እምነት አድስ ከወደክበት ሰው እስኪያነሰህ አትጠብቅ፤ የጉዱህ ይቅር በል፤ ምክንያቱም ብሩህ ቀን ከፊትህ አለና። ✍ህልመኛው ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️❤️ @psychoet
Показать все...
24👍 9
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሳይኮሎጂ| አትፍዘዝ ልብ ብለህ ስማ ለሌሎች ያጋሩ ፔጁን Follow ያርጉ 1) "ክፉ ሰዎች ስህተትህን በሰዎች ፊት ይነግሩሃል፤መልካም ሰዎች ግን በስውር ያስተምሩሃል።" 2) "ከዘመኑ ጋር ራሳቸውን ያላሻሻሉ ሰዎች ትውልድን ሲጎትቱ ይኖራሉ።" 3) "የሰው ልጅ የተመኘውን በሙሉ ቢያገኝ እንኳን አንድ ቀን ያገኘውን ሁሉ ያጣዋል።" 4) "ተስፋን ማጣት ህይወትን ማጣት ነው፤የሚያኖረን ተስፋችን ነውና።" 5) "ብርቱ ሰው በሰው ወሬ መንገዱን አይስትም፤ለአሉባልተኞችም ጊዜ የለውም።" 6) "መሄድንና መተውን የሚያስተምሩን አብረውን እንዲቆዩ ብዙ የታገስናቸው ሰዎች ናቸው" 7) "የሚጎዱ ነገሮች ሁሉ ያስተምራሉ" 8) "ሰዎችን ማሸነፍ ቀላል ሊሆን ይችላል፤ማንነታቸውን ማሸነፍ ግን እጅግ ከባድ ነው።" 9) "ወደ ክብር የሚወስደው አቋራጩ መንገድ፤የምትመኘውን ለመሆን መጣር ነው።" t.me/psychoet
Показать все...
👏 17 16👍 3
#ሳይኮሎጂ| ስለ አስመሳዮች ፈጽሞ ችላ ልትሏቸው የማይገቡ እውነታዎች ሼር ይደረግ ፔጁንም Follow አርጉ ① በፊትህ ጥሩ መስለው ይቀርባሉ፤ ከጀርባህ ግን ያሙሃል። ② የሚፈልጉት ነገር ሲኖር ብቻ ያስታውሱሃል። ③ ከስኬትህ ይልቅ ውድቀትህን ያከብራሉ። ④ መጀመሪያ ይገለብጡሃል፤ ከዚያም ይፎካከሩሃል። ⑤ አንተ ስትፈልጋቸው ሁሌም “ቢዚ” ናቸው፤ ነገር ግን አንተ ለእነሱ ሁሌም እንድትገኝ ይጠብቃሉ። ⑥ ደጋፊ መስለው ይታያሉ፤ በድብቅ ግን እንድትወድቅ ይመኛሉ። ⑦ አብረውህ ይስቃሉ፤ ዞር ስትል ግን ዓይናቸውን ያቁለጨልጫሉ። ⑧ የሰራሃቸውን ስህተቶች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ያደረግክላቸውን መልካም ነገሮች ግን ይረሳሉ። ⑨ በ“ቀልድ” መልክ ይሰድቡሃል፤ ከዚያም “አንተ በጣም ስሜታዊ ነህ” ይሉሃል። ⑩ ስታድግ ይጠላሉ፤ ምክንያቱም የእነሱን ትንሽነት እንዲሰማቸው ያደርጋል። ⑪ ሆን ብለው ወደኋላ ሊያስቀሩህ መጥፎ ምክር ይሰጡሃል። ⑫ ላንተ የሚያጨበጭቡ ይመስላሉ፤ በውስጣቸው ግን ይቀናሉ። ⑬ ወሰንህን ባስቀመጥክ ቅጽበት “ራስ ወዳድ” ብለው ይጠሩሃል። @psychoet
Показать все...
21👍 8
አንድ ጊዜ አንስታይን እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ቀረቡለት ጠያቂ;- ብልህ ሰው ምን አይነት ሰው ነው? አልበርት;- ከእያንዳንዱ ሰው ሊማር የሚችል..... ጠያቂ;-ጠንካራ ሰው እንዴት ያለ ሰው ነው? አልበርት;-ስሜቱን መቆጣጠር የሚችል.... ጠያቂ;-እውነተኛ ሀብታም ሊባል የሚገባው እንዴት አይነት ሰው ነው? አልበርት;-በቃኝን የሚያውቅ...... ጠያቂ ;-ማነው የተከበረ ሰው? አልበርት;-ሰውን የሚያከብር...... ጠያቂ;-ምን አይነት ሰው ነው ቶሎ ነገር የሚገባው? አልበርት;-በትዕግስት ሰውን የሚያደምጥ...... ለሌሎች ያጋሩ ፔጁን Follow ያርጉ
Показать все...
28👍 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡ 📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡ 📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡ 📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡ 📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡ 📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡ 📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖 ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ሃሳቦች 📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖 ሜሎሪና - ታሪካዊ የሥነልቦና ልብወለድ በተገኘበት ይነበብ
Показать все...
👍 19 16
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት 1. ጥሩ አድማጭ መሆን ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡ 2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡ 3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡ 4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡ 5. አቀማመጥን ማስተካከል ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡ 6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡ 7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡ 8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡ 9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡ ተግባቦት የብዙ ሰው ችግሮ ነውና #share በማረግ ለሌሎች እነዚህን ቁልፍ ነገሮች እናሳውቅ ፔጃችንን #Like በማረግ በየቀኑ አዕምሮዎን በመልካም ሀሳብ ይመግቡ (በዘመነ ቴዎድሮስ) ©zepsychologist #ለሀገራችን ቸር ሳምንት ይሁንልን Join t.me/Psychoet በነፃ ሥነልቡና በአማረኛ ተማሩ!
Показать все...
22👍 5
በእራስ መተማመን ከተነበበ በኀላ #share ይደረግ ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡   በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው፡፡ በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy)  ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡ ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? ★የሚከተሉትን ነጥቦች እንያቸው 1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡ 2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች  ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡ 3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡ 4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡ 5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡ 6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡ 7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡ በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን  ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡ ሰላማችሁ ይብዛ………. መልካም ቀን ! © (ቁምላቸው ደርሶ) @psychoet
Показать все...
19👍 7
ሰላም ናሁሰናይ ፀዳሉ (የስነልቦናና የአመራር ባለሙያ) ነኝ፡፡  በዚህ ክረምት ምን ሊያደርጉ አስበዋል? ከራስ ጋር መግባባትዎ፣ ስራ ፈጣሪነትዎ፣ የገንዘብ አያያዝዎ፣ የተግባቦት ክህሎትዎ፣ የስሜት ብልሀትዎ እንዴት ነው? እነዚህንና ሌሎችንም መለወጥ፣ ማዳበር፣ መለማመድ የሚችሉበት 14ኛው ዙር የስነልቦናና የስብዕና ግንባታ ስልጠናችን ቀጥሏል፡፡ ለ6 ሳምንታት ብቻ ይቆያል፡፡  አድራሻችን ቦሌ ብራስ፣ መገናኛ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት (British School) አጠገብ፣ ዛሙ ፈርኒቸር ህንፃ ቁጥር 206 ነው 0912664084 ይደውሉ ይመዝገቡ፡፡
Показать все...
13
የዘራነውን ነው የምናጭደው እንደሚታወቀው ግንቦት፣ ሰኔ እና እስከ ሀምሌ አጋማሽ በሀገራችን ገበሬው መሬቱን ለሚዘራበት ሰብል የሚያርስበት ወቅት ነው። እናም ይሄ የሚዘራው ዘር የኩንታል ያህል መጠን ቢሆን ሲታጨድ ግን ብዙ ኩንታል እህል ይሰጣል። ይሄ የዘር ምሳሌ ለማንሳት የፈለኩበት ምክንያት በህይወታችን ላይ ነገ የምናገኛው ህይወት ዛሬ የምንሰራውን ወይም ደግሞ የምንዘራውን ነው። ጊዜ መሬቱ ሲሆን ስራችን ደግሞ ዘሩ ነው። ስለዚህ ጊዜ ተሰቶሃል በዚያ ጊዜ ላይ የምናደርገውን ነገር ደግሞ ነገ ላይ በብዙ የምናጭደው ነገር ነው። በህይወታች ላይ ነገ ማየት የምንፈልገው ፍሬያማነት ዛሬ በምናደርገው ታታሪነት እና ጠንካራ ሠራተኝነት ሳቢያ የሚመጣ ነው። የምታጭደው የምታዝራው ነገር በብዛት መሆኑን አትርሳ። በዕድሜ ላይ ጥቂት አመት ካላገጥክ ለአንተ፣ ለቤተሰብ፣ ለትዳር አጋርህ እና ለጎደኞችህ አልፎ ተርፎ ደግሞ ለሀገር የሚተርፍ ቀውስ ትፈጥራለህ። በተቀራኒው መልኩ ደግሞ ዛሬ መልካም ነገሮች ላይ ጊዜ የምታፈስ ከሆነ ነገ ለብዙዎች የሚተርፍ ነገር በአንተ ውስጥ ይገኛል። ስለዚህ እንጠንቀቅ! አሁን ጊዜ በሚበል መሬት ላይ እየዘራን እንደሆነና የሆነ ሰዓት ማጨዳችን እንደማይቀር ማወቅ አለብን። የምታጭደው ነገር ለአንተ ብቻ እንዳልሆነ በመገንዘብ ምን አገባኝነትን እና ግድየለሽነትን ከህይወት አጥፋ። ለምናደርገቸው ነገሮች በትኩረት እናደርግ። ምክንያቱም ዛሬ የምትዘራውን ነገር አውቀህም ሆነህ ሳታውቅም ብታደርግ ነገ ላይ ማጨድ አይቀርም። ነገ ላይ ፍሬው ሲመጣ ሳላውቅ ነው ብትል ማምላጫ መንገድ አይሆንህም። ስለዚህ ጊዜህ መሬት ሲሆን ስራክ ደግሞ ዘርህ እንደሆነ ተገንዘብህ እያንዳንዱ እንቅስቃሴህን ቃኝ። ዛሬ መልካም ዝራ፤ ነገ ብዙ መልካምነት ታጭደለህ! ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ©ህልመኛው 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት በዚህ ክረምት ጥሩ ዘር የሚሆን የስብዕና ግንባታና የሳይኮሎጂ ስልጠናችን በቀጣይ ሳምንት ስለሚጀምር 0912664084 በመደወል ይመዝገቡ። ስልጠናችን በአካልም በኦንላየንም ይሰጣል። Join and follow our page t.me/psychoet
Показать все...
16
💪በራስ መተማመንን ማጎልበት💪 Developing Self Confidence በራስ መተማመን ማለት ሰው ባለው ችሎታ፣ አካላዊ ውበትና ሁለንተናዊ ማንነት አለመፍራት እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ራስን መቀበል ማለት ነው፡፡ ትእቢት ፣ ትምክህት፣ ያልተገባ አውቃለሁ ባይነት እና ከመጠን ያለፈ ድፍረት በራስ መተማመን አይደለም። በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ብልሀቶች 🔥 ራስዎን ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር። 🔥 ያለዎትን ክህሎት እና ድክመት መለየት። 🔥 የአካላዊ ገፅታ ውበትን መጠበቅ ደግሞም የሰውን ትኩረት ከልክ ባለፈ ሁኔታ የሚስቡ ጌጣጌጦችንና ሜካፖችን አለመጠቀም። 🔥 ጥሩ እና ምቹ አለባበስ መልበስ። 🔥 ነቃና ቀልጠፍ ብሎ መራመድ ። 🔥 በሰው ፊት ሀሳብዎን መግለፅ ሲኖርብዎ ቀድመው በቂ ዝግጅት ማድረግ። 🔥 መልካም በሆነ የህይወት እንቅስቃሴ የበኩልዎን አስተዋፅዖ ማድርግ። 🔥 ጥሩ የሚሰሩ ሰዎችን ማድነቅ/ ማበረታታት። 🔥 ሰዎች የተቃወሙዎት ወይም የናቁዎት ሲመስልዎ በእርጋታ ምላሽ መስጠት። 🔥 ሰዎች ስህተትዎን ሲነግሩዎ በቀና ማየት(ስለሚጠሉኝ ነው አለማለት)። 🔥 እርዳታ ሲያስፈልግዎ ያለፍርሀት መጠይቅ። 🔥 ሰአት ማክበር። ©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት YouTube: Dink Mikir #Like #Share በማረግ ለሌሎችም እናስተምር ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ t.me/psychoet በቀጣይ ሳምንት የሚጀምረውን ስልጠናችንን ለመካፈል በ 0912664084 ይደውሉ።
Показать все...
👍 13 4
#ይሉኝታ እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ #ይሉኝታ_ምንድን_ነው? ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡ #የይሉኝታ_መንስኤዎች ✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት ✿በራስ መተማመን ማነስ ✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ ✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን ✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ ✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ #ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች ✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ? ✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ ✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ ✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ ✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር ✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር ✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል ©zepsychology ይሉኝታን ለማስወገድ ስልጠናዎቻችንን ለመውሰድ 0912664084 ይደውሉ
Показать все...
13👏 2👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
መልካም ዜና! 14ኛ ዙር የስብዕና ግንባታና የሳይኮሎጂ ስልጠና (Life Improvment Training)  ሀምሌ 8 ሊጀምር ነው። ስልጠናው ላለፉት 6 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ተግባራዊ ስልጠና ነው። 🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ፈልጎ ማግኘት 🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን 🔖ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም 🔖የስሜት ብልህነት 🔖ፍርሀት ማሸነፍና፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት 🔖ስራ ፈጠራና የገንዘብ አስተዳደር 📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦናን መረዳት 📖የሥነልቡና ቀውስና መፍትሄዎች መረዳት ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን! ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በስራ ቀናት (ከሰኞ - አርብ) በጠዋት በከሰአትና በማታ እንዲሁም ቅዳሜና እሑድ ይኖረናል። በአንድ ፈረቃ ጥቂት ብቻ ቦታ ስለሆነ ያለን ቀድመው ይመዝገቡ። ለመመዝገብ / መረጃ ለማግኘት 0960865151 ወይንም 0912664084 ይደውሉ። 🏠 አድራሻ :- ቦሌ ብራስ፣ መገናኛ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ዛሙ ፈርኒቸር ህንፃ ቁጥር 206 🖼🎁ለመለወጥ መወሰን እንጂ ሰበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!! ሕይወትዎን ለመቀየር አሁኑኑ ይወስኑ! ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ @psychoet
Показать все...
8👍 1👏 1
የስብዕና መዛባት (Personality Disorders) በዓለም ላይ ከሚኖሩ አጠቃላይ ህዝቦች ውስጥ ከ 1-20% የሚያህሉት ለተለያዩ ዓይነት የስብዕና መዛባት ችግሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡ የስብዕና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስንል ወደ አእምሯችን የሚመጣው መንገድ ላይ ጨርቁን ጥሎ የሚሄደው፤ አማኑኤል ሆስፒታል የተኛችው ፤ ወይም ደግሞ ሰውን በአረመኔያዊ ሁኔታ ገድሎ እስርቤት ውስጥ በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቀው ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን  በዓለም ላይ በጣም በጥቂቱ ከ 25 ሰው አንዱ  ለተለያየ ዓይነት የስብዕና መዛባት ተጋላጭ ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች የቤተሰባችን አካል፤ ጎረቤት፤ ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ለስብዕና መዛባት ዋና መንስኤዎች የትወልድ ሃረግ (Genettics)፤ በልጅነት ዕድሜ የሚደርስ አካላዊ፤ ወሲባዊና ስነልቦናዊ ጥቃት፤ እንዲሁም ያደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡ የስብዕና መዛባት ያለባቸው ሰዎች በአጠቃላይ በሶስት ቡድን (Clusters) ይከፈላሉ፡፡ ቡድን ሀ የስብዕና መዛባቶች (Cluster A Personality Disorders) 1. በምክንያት ያልተደገፈ ጥርጥር እና ከመጠን ያለፈ ሰዎችን ያለማመን ችግር (Paranoid Personality Disorder)፡- እነዚህ ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የትዳር ጓደኛቸው ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው ብለው ሊያምኑ ይችላሉ፡ ከአስር አመት በፊት ወልደው ያሳደጉትን ልጅ የእኔ አይደለም ብለው ሊክዱ ይችላሉ፤ ዙሪያ ገባውን ሁሉ በጥርጣሬ የሚመለከቱ እና ሰዎቸ በመሰረቱ አደገኞች ናቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፤ ለእነዚህ ሰዎች በቅንነት የወረወራችሁት ሃሳብ እንደ ጥቃት ሊቆጠር ይችላል 2. ከውጪዉ ዓለም ወይም ከእውነታው ሸሽተው  በራሳቸው አለም (ሃሳብ) የሚኖሩ (Schizoid Personality Disorder)፡- እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ዓለም አብዝተው የሚመሰጡ፤ በእውኑ ዓለም ተጨባጭ ያልሆኑ ሃሳቦችን የሚያልሙ ሲሆን ለማኅበራዊ ደንቦች ግድ የሌላቸውና ከሰዎች ጋር ስሜታዊ ትስስር ለመፍጠር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው 3. በአነጋጋራቸው፤ በባህሪያቸው፤ በአስተሳሰባቸው ላይ መዛባት ያለባቸው ሰዎች (Schizotypal Disorder):-  እነዚህ ሰዎች ከሌሎቹ የስብዕና መዛባት ዓይነቶች በተለየ መልኩ በቀላሉ ችግር ውስጥ እንደሆኑ በአነጋገራቸው፤ ከተለመደው ወጣ ባለው ባህሪያቸው እንለያቸዋለን፡፡ ምንአልባትም በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ “እብድ” የምንቆጥራቸው አብዛኞቹ የእዚህ ስብዕና መዛባት ተጋላጮች ናቸው ቡድን ለ የስብዕና መዛባቶች (Cluster B Personality Disorders) 1. ለማኅበረሰብ ህግና ደንቦች ግድ የሌላቸው (Antisocial Personality Dsiroder)፡- ሌሎች ሰዎች ላይ ሆን ብለው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት የሚያደርሱ፤ ርህራሄ የሌላቸው እና የሰዎችን ስሜት የማይረዱ፤ ባጠፉት ጥፋት መጸጸት የማይሰማቸው እና ከህይወት ተሞክሮ ትምህርት ወስደው ራሳቸውን ለማሻሻል የማይሞክሩ ናቸው:: ብዙ ጊዜ ጥቃት አድርሰው፤ወንጀል ፈጽመው ወደ ህግ ሲቀርቡ ብናያቸውም አብዛኞቹ ግን በረቀቀ መንገድ የሚንቀሳቀሱ፤ ከህግ ከለላ በቀላሉ የሚያመልጡና በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ሰዎች ናቸው 2. ስለራሳቸው ማንነት ማወቅ የተቸገሩ (Boarderline Personality Disorder):- እነዚህ ሰዎች  አበዝተው ባዶነት፤ የስሜት አለመረጋጋትና ፍርሃት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ቁጡዎች፤ ራሳቸውን ለመጉዳትና ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የስብዕና መዛባት በልጅነታቸው የጾታ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ላይ የተለመደ ነው፡፡ 3. በሰውነታቸው ያላቸውን መልካም ዋጋ የማይረዱ (Histrionic Personality Disorder)፡- እነዚህ ሰዎች የሌሎችን ትኩረት አብዝተው የሚሹ እና በዕቅዳቸው ሁሉ የሌሎችን አበረታችነት የሚጠብቁ ናቸው:: ሌላ ሰው ቀጥሉ ካላላቸው ምንም ዓይነት ውሳኔ ለመወሰን ይቸገራሉ፡፡ከመጠን በላይ ለውበታቸውና ለአለባበሳቸውም የሚጨነቁም ናቸው 4. ክፉ ሰዎች (Narcissistic Personality Disorder)፡- ሲበዛ ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች፤ በነገሮች ሁሉ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሰሉና በጣም ተቆጣጣሪዎች ናቸው፡፡ የዚህ ስብዕና መዛባት ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሌሎችን የሚቀርቡት በሆነ መንገድ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ሲያስቡ ብቻ ነው፡፡ እነሱ የፈለጉት ነገር ካለሆነ ለበቀል የሚጋበዙ ፤ዓለም በእነሱ ዛቢያ ብቻ የምትሽከረከር የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ቡድን ሐ የስብዕና መዛባቶች (Cluster C Personality Disorders) 1. ከማኅበራዊ ህይወት ራሳቸውን የሚያገሉ (Avoidant Personality Disorder)፡- ሲበዛ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው በዚህም ምክንያት ሰዎች ስለነሱ መጥፎውን እንደሚያወሩ የሚያስቡ፤ ሰዎች የወቀሷቸውና ያገለሏቸው የሚመስላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ራሳቸውን ከማኅበራዊ ህይወት ያገላሉ፡፡ ሰርግ እና ሃዘን ቤት መሄድ፤ ከጓደኞች ጋር ሻይ ቡና ማለት ያስጨንቃቸዋል፡፡ 2. በሌሎች ሰዎች ላይ ሲበዛ ጥገኛ የሆኑ ሰዎች (Dependent personality Disorder)፡- በራሳቸው መተማመን የሌላቸው፤ በዕለት ተዕለት ኑሯቸው ውስጥ የሌሎችን ውሳኔ የሚጠብቁ፡ ሲበዛ ሽቁጥቁጥና ለሰው አጎብዳጅ የሆኑ ሰዎች ናቸው 3. ስህተት አልባ ህይወት ፈላጊዎች (Anankastic Personality Disorder)፡- ለህጎች ፤ ስርአቶች ፤ ዕቅዶች ሲበዛ አብዝተው የሚጨነቁ፡፡ ያቀዱት ጉዳይ ካልተፈጸመ ዕረፍት የሚነሳቸው፤የሚለብሱት ልብስ መዛነፍ ወይም አለመተኮስ ቀኑን ሙሉ የሚረብሻቸው ሰዎች ናቸው፡፡ (በሰብለወንጌል አይናለም) @Zepsychologist ከእነዚ በአንዱ አልያም የተለየ የአዕምሮ ሕመም አለብኝ ብለው ካሰቡ ( በዚህ የሚጠቃ የቅርብ ሰው ካለ) የስነልቡና አማካሪዎች ጋር እንዲሄዱ እመክራለሁ ፡፡ የስነልቦና ስልጠናም መውሰድ ከፈለጋችሁ 0912664084 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል ፡፡
Показать все...
20👍 4
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ! #ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን #ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡ 1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። 2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። 3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡ 4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር። 5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡ 6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡ 7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው። 8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡ 9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል። 10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡ 11. የአዲስ መረጃ ቤተሰቦች፣ ሼር ማድረግ ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ ስለሚያውቁ ቀናቸውን የሚጀምሩት የኛን መረጃ ሼር በማድረግ ነው፡፡ ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!! ---------------------- ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ) 🎡@🎡መልካም ቀን     #Join   #Join     #Join       🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹              🚗 t.me/Psychoet👍
Показать все...
14👍 4😁 1
የአለማችን ነገርና ዩኒቨርስን የሚያስሰው የሠው ልጅ አእምሮ ገራሚ ናቸው። የወደፊቱ የአለም ሁኔታ በምን ይቋጭ ይሆን? መፍረስና መደፍረስ፣ ወይንስ ማደግና መሻሻል ፣ አስገኚው ይወቀው ሁለተኛውን እንዲሆን ይርዳን። ከFB መንደር የተገኘ t.me/psychoet
Показать все...
👍 6 1
ኢንቴሊጄንስ /Intelligence/ ይህ ፅንሰ ሀሳብ በብዙ ምሁራን፣ ሳይንቲስቶች፣ ፈላስፎች፣ የስነ ልቡና ሊቃውንት፣ ሌሎችም፣ ሌሎችም ለመተንተን ተሞክሯል። ፅንሰ ሀሳቡ ከእውቀት፣ ክህሎት ፣ምክንያታዊነት፣ ግንዛቤ፣ አመለካከት፣ አስተውሎት፣ ዝንባሌ፣ ራእይ፣ አተናተን፣ ችግር ፈቺነት ወዘተ ጋር የተገናኘ በመሆኑ አንዱን ስለ ፅንሰ ሀሳቡ ሲይዙ ሌላው ስለሚያመልጣቸው ሁለንተናውን የፅንሰ ሀሳብ ፍቺ ያገኘና ያስቀመጠ አልተገኘም፣ ግን በብዙ መልኩ ተሞክሯል። የሠው ልጅ የአእምሮ ውጤት ገራሚና አለማችንን ባያሌው የለወጠ፣ ያስተካከለ፣ ያኖረ፣ ያራመደ ፣ ያስዋበ ፣ የተነተነ፣ የተረዳ፣ ያጠና፣ በእጅጉ ለሠው ልጅ ኑሮና ሕይወት ያመቻቸ ነው። የሠው ልጆች እውቀትና ክህሎት የተለያዬ ነው። አንዱ በቀላሉ የሚረዳው ለሌላው ጉም እንደመጨበጥን ያህል ይከብዳል። ለምንድነው የእውቀትና ክህሎት ወዘተ ደረጃ /level of intelligence/ እንዲህ ሊለያይ የቻለው። አጥኚዎች በተለይም የሥነ ልቡና ሊቃውንት በአእምሮው በተከማቸው ግረይ ማተር ወይም እምቅ እውቀትና ክህሎት ወዘተ ክምችት ብዛትና ማነስ ነው ብለው ያምናሉ። በአእምሮው የግረይ ማተር ማነስና መብዛት የኢንተሊጀንስ ደረጃውን ለመረዳት እንደሚያስችልም ይረዳሉ። ይህ የሠው ልጅ አእምሮ ወለድ የሆነ እምቅ ችሎታ እንዴት ሊታወቅ ይችላል ? ከበድ ያለ ጥያቄና እምቅ ችሎታን በየዘርፉ ያነገቡ ምሁራን /intellects/ ሳያርፉ ከመረመሩት፣ ከተረዱት፣ ካጠኑት፣ ከተነተኑትና ካሳወቁት በመነሳት ልኬቱን በጥቂቱ ማለት እንችላለን። እስካሁን ኢንተሊጄንስን ለመለካት በውስጡ የያዛቸውን ፅንሰ ሀሳቦች ያካተተ በውጭኛው /knowledge,skill, reasoning, understandig, attitude, problem solving capacity, etc/ በማካተት ሁለንተናዊ የሆነ የእውቀትና ክህሎት ወዘተ ደረጃውን ለማወቅ በመጠኑም ቢሆን የሚያስችል IQ /Intelligence quotient/ የሚለውን መለኪያ በስምምነት ተቀብለዋል። ኢንቴሊጄንስ ኮሸንት የሁለት ብስለት ደረጃዎች ሬሺዮ ነው። አንደኛው የሠው ልጅ በአለም የኖረበት እድሜ ሲሆን /chronological age/ ሌላው የአእምሮ እምቅ ችሎታው /mental age/ ነው። እንግዲህ የነዚህ የሁለቱን ሬሺዮ ወስደን መቶኛውን ስናሠላ ነው የልኬት ጠቋሚውን የምናገኘው፣ እንደሚከተለውም ይቀመጣል። IQ = m/c * 100 IQ = intelligent quotient M= Mental age C=Chronological age ይህ የልኬቱን ጠቋሚ ይሰጠናል ማለት ነው። የአንድን ሠው ሜንታል ኤጅ ለመረዳት አእምሮ ፈታሽ ጥያቄዎች ይዘጋጃሉ ለምሳሌ እንደ አፕቲትዩድ ቴስት ያሉ። ጥያቄዎቹ በአእምሮ ውስጥ ያለውን እምቅ ችሎታ አጉልተው የሚያሳዩን ናቸው ለምሳሌ ቃላትን፣ ፅሑፎችን፣ ትንተናዎችን፣ የመገንዘብና የመረዳት ክህሎት / verbal- linguestic/ ካርታዎችን፣ ስእሎችን፣ የተቀረፁ ቢድዮዎችን፣ አቀማመጦችን፣ ከፍታ ዝቅታዎችን በአተኩሮት የመመልከት ብቃት / visual-spatial / ስሌትንና አመክኒዮን የመገንዘብ ደረጃ /logical- mathematical/ የአካል ክፍሎቻችንን ለምሳሌ አይንና እጅን ሌሎችንም የማናበብ ክህሎት ደረጃ / bodly - kinesthetic/ የራስን የውስጥ ክህሎት የመረዳት ደረጃ /intra personal/ ከሌላው ጋር በመናበብ አብሮነትን የመንተራስና የመጠቀም ደረጃ /inter personal / እነዚህን ሁሉ የሚያካትት ብቃት ባላቸው ምሁራን የሚዘጋጅ ነው ይህ የአእምሮ ብቃት መለኪያ። ምሁር /intelect/ የዩኒቨርሲቲን ደጃፎች ረግጦ ለብ ለብ በማድረግ ዲግሪን የጫነ ከመሠላችሁ ተሳሰታችኋል። ምሁራን እነደ ቤቶቤን የሙዚቃዊ ክህሎትን የተካኑ፣ እንደ ሼክስፕርና ሊዮ ቶሊስቶይ በቤርባል- ሊንጉስትክ ጥበብ የትለቀለቁ፣ እንደነ ሶቅራጢስ ፍልስፍናዊ ክህሎታቸውን ከሳይንሳዊ ጥበብ ጋረ ያዋሀዱ፣ እንደነ ሊዮናርዶ ተፈጥሯዊ ክህሎታቸውን በመጠቀም በስፓሻል ክነ ጥበባዊ እምቅ ችሎታቸው የትዬሌለ የደረሡ ፣ እንደነ አይሳክ ኒውተን በፈጠራ የተካኑ ናቸው ። አለም አቀፋዊ አስተሳሰባቸውም እጅጉን የላቀ እጅጉን የመጠቀ። ኢንቴሊጀንስ ኮሸንት እንደ ቦዲ ማስ እንዴክስ በቀላሉ ልንፈትሸው የምንችለው አይደለም፣ከበድ ያለና ብዙ ውጣ ውረድን የሚጠይቅ የእውቀትና ክህሎት ወዘተ ውጤት ነው። ፅንሰ ሀሳቡ ስፋትና ጥልቀት ስላለው እንዳላሠለቻችሁ ሌላ ግዜ ብመለስበት ይሻላል፣ የልኬት ጠቋሚዎችን ጠቁሜ ፅሑፌን ልቋጭ። እላይ በተሠጠው የስሌት ጠቋሚ መሠረተ ሀሳብ በመመርኮዝ የጥቆማ ውጤቶቹ የሚከተሉትን ያብራራሉ፦ ከ55 አስከ 69 ጥልቅ የአእምሮ ዘገምተኛነት / mild mental disability. ከ 70- 84 መጠነኛ የአእምሮ ዘገምተኝነት / border line mental disability/ ከ85 -114 አማካይ እውቀትና ክህሎት ደረጃ /average intelligence / ከ 115 - 129 ከአማካይ የላቀ እውቀትና ክህሎት ደረጃ / above average or bright / ከ 130 - 144 መለስተኛ ተሠጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / moderately gifted / ከ 145 - 159 ከፍተኛ ተሠጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / highly gifted / ከ 160 - 179 በጣም ከፍተኛ ተሰጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / exceptionaly gifted / ከ 180 በላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ ተሰጥኦን ያነገበ የእውቀትና ክህሎት ደረጃ / profoundly gifted / ገራሚ ነው፣ ሁሉንም ደረጃዎች ያነገቡ የሠው ልጆች በአለማችን ሞልተው ተርፈዋል፣ አለምን ትጉሃኑ ወደ ሞባይል ቴክኖሎጂ ሲያሻግሯት አናሳዎችም ቁልቁል እየረገጧት ነው። ተንታኞች ብዙ ብዙ ይላሉ ስለ ሠው ልጅ አእምሮ ስፋትና ጥልቀት፣ ሁሉን መዘርዘር አይቻልም፣ ከበድም ይላል፣ ለያንዳንዱ ፅንሰ ሐሳብ ትንተና ትልቅ መፅሐፍ አይበቃም። እውቀት ፣ጥበብ፣ ክህሎት ፣ መረዳት፣ መተንተን፣ መፍትሔ ማመንጨት ሁሉም ወርቃዊና ብሩኅ አእምሮ ባላቸው የሠው ቅመሞች እየተተነተኑ ነው፣ እነደነዚህ ያሉ ምሁራን በክህሎታቸው ንዋይ ሰብሳቢዎችና በቁጭታ ተቺዎች ሳይሆኑ አንቂዎች፣ መካሪዎችና አስተማሪዎች ናቸው የተግባርም ሠዎች፣ ሳይጠቀሙ ጠቃሚዎች፣ የሕይወትን ጎዳናና መንገድ ተረጂዎች፣ አጥፊዎች ሳይሆኑ አልሚዎች፣ ታካቾች ሳይሆኑ ታታሪዎች። የነርሱ መኖር አለምን ያኖራታል ፣ይጠብቃታል። በአለም የኑክለር ቃታ ለመሳብና የሠውን ልጅ ከምድር ገፅ ለማጥፋት የሚቃጡትን ሸውራራና በትምክሂት የተወጠሩትን ፖለቲከኞች ይመክራሉ፣ ያስተምራሉ ይመልሳሉ። የአንድን ድርጊት ውጤት ቀድመው ይረዳሉ በአለማችን የተከማቹትን የኑክለር አረሮችን ሠውን ለማጥፋት እንዳይጠቀሙ በማሥጠንቀቂያ ደወላቸው ያሥጠነቅቃሉ። እስካሁን ተረጋግተን እንድንኖር አብቅተውናል የወደፊቱን እግዜር ይወቀው። በስእሉ ሦሥት የአሜሪካ ፕሬዚዴንት የነበሩትን እናያለን ክሊንተን ከሦሥቱ ከፍተኛ የሌኬት ጠቋሚ የተጎናፀፈ ሲሆን ቡሽ መጨረሻ ነው፣ ኦባማ በሁለቱ መሐከል የሚገኝ። የወቅቱ ፕሬዚዴንትም IQ ቢታወቅ መልካም ነበር፣ አለምን ለማውጣትም ሆነ ለማውረድ ሥልጣን ስላለው።
Показать все...
👍 4