መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿
Открыть в Telegram
☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ። ☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ አየር ጤና እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን 📞#0918834904 📞#0915310455 መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan
Больше119 968
Подписчики
-17824 часа
-1 0237 дней
-4 79730 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
ስለ ቀና ምስክርነትዎ እጅግ በጣም እናመሰግናልን::እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልዎት🙏
ዕፀ-ተሐድሶ በአዲስ ዓመት
(እርጅና እና ሞት ያለጊዜው እንዳይመጣ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🆕የተሐድሶ አጠቃቀም:-
👉ሰባት የአደይ አበባ ጫፉን በእርጥቡ ቀጥፈው በንፁሕ እቃ በመደቆስ በንፁህ የአንድ ሾርባ ማንኪያ ማር ወይም ጣዝማ ለውሰው!
👉የቅዱስ ዮሐንስ ዕለት ከ ጧቱ 12:00 ሰዓት በማር የተለወሰው የአደይ አበባ ቅይጥ ላይ !
👉ከመዝሙረ ዳዊት -መዝሙር :28
አምጽኡ ለእግዚአብሔር ውሉደ አማልክት የሚለውን እስከ መጨረሻ ሰባት ጊዜ ጸልየው መላ ቤተሰብ የቅዱስ ዮሐንስ ዕለት ምግብ ሳይቀምሱ የአደይ አበባ ውኅድ በትንሿ የስኳር ማንኪያ ይቅመሱ::
🆕የተሐድሶ ጥቅም:-
🌿በአዲስ ማንነት መነሳት
🌿በአዲስ ውበት ማንፀባረቅ
🌿ለአዲስ ስራ መነሳሳት
🌿ከመቅሰፍ/ከአደጋ መከለል(በእግዚአብሔር ኃይል)
🌿ያለዕድሜ ማርጀትን በቃኝ ማለት
🌿በጤና ሙሉ መሆን....ያጠቃልላል::
ይህ ተግባር የቀድምቶቹ አበው ስራ ነው::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
“ወትባርክ አክሊለ ዓመትከ ወይፀግቡ ጠላተ ገዳም ወይረውዩ አድባረ በድው። "
እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ
አዲሱ ዓመት የደስታ፣የፍቅር፣የሰላም የይቅርታ ዓመት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችን ነው።
መልካም በዓል 🌻
መልካም አዲስ ዓመት!!🌻
❤ 5👍 2
🌼 እንኳን ለ 2018 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ 🌼
ℹℹℹℹℹℹℹℹℹℹℹℹℹ
ድንገታዊ ሀዘን ድብርት ተስፋ መቁረጥ መረበሽ የተለያዩ የህይወት ቀውስ ህመም ድህነት መነጫነጭ የትዳር መበላሸት አልያም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘት በስራችን አለመርካት ብራችን አለመባረክ ፍርሀት ፍርሀት ማለት አለመረጋጋት መቃዠት የአእምሮ ጭንቀት የበታችነት ስሜት መሰማት የትዳር አጋር ማጣት እጣፈንታን መበላሸት
እነዚህ እና የመሳሰሉት ቀውሶች በክፉ መናፍስት አማካኝነት የሚመጡ ችግሮች ናቸው።
✔እኛ ማድረግ ያለብን _ በጸሎት ማሸነፍ
✔️ እኛ ማድረግ ያለብን __ በጸሎት መዋጋት
✔እኛ ማድረግ ያለብን_ በጸሎት መከላከል
✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴✴
ክፉ መናፍስትን ማራቅ ካለብን ለፈጣሪየችን ከልብ በሙሉ እምነት በሙሉ ንጽህና መለመን ዋነኛው መፍትሔ ነው።
እምነታችን ጠንካራ ሆነ ማለት በእምነት የገነባነው የክፉ ክፉ መናፍስትን መከላከያ አጥር ጥሶ የሚገባ አንድም ክፉ መንፈስ አይኖርም ማለት ነው።
🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗🔗
ከዚ ሁሉ ርቀን በፈተና የወደቅን እንደሆነ ግን ክፉ መናፍስቶች ያስጨነቁን እንደሆነ ግን ! የመውጭያ ቀዳዳ ክፉ መናፍስቶች የቆለፉብን እንደሆነ ግን! መላው ቅጡ ጠፍቶብን አማራጭ ሲጠፋብን ግን ወደ ተሻለው መፍትሔ መሔድ አማራጫችን እናድርግ።
✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔
አንደኛው እና ዋነኛው መፍትሔ በየእምነታችን ያሉ የእምነት ትቋሞች በመሔድ እውነተኛው መፍትሔ ምናገኝበት መንገድ መጥረግ ይኖርብናል።
ሁለተኛው በየ ቤታችን የጸሎት መጻሕፍቶችን በመጠቀም ክፉ መናፍስትን ማስጨነቅ እና እንዲርቁን ማድረግ በጸሎት በስግደት ለፈጣሪያችን በመማጸን ማሰወገድ።
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
ሦስተኛው እና የመጨረሻው አማራጭ ደግሞ ይህ ሁሉ ነገር አድርጋቹ አልሳካ ቢላችሁም ቅሉ ፈጣሪ በሰጣቸው ጸጋ እና ጥበብ በፈጣሪ ሀይል እና በዕጽዋት ቅመማ የክፉ መናፍስት ጸር ወይንም መትሔ ወደሆኑ ለእውነት ያደሩ ጥበባኞች ጋር በመሔድ ሙሉ መፍትሔውን መውሰድ ትችላላቹ።
እውቀቱ የእግዚአብሔር ነው
መፍትሔው የእግዚአብሔር ነው
ጥበቡ የእግዚአብሔር ነው
ከእግዚአብሔር ኃይል እና ጥበብ ውጭ ችግሮችን ማንም ሊፈታ አይችላም።
የከበዱ እና በሳይንሱ ዓለም መፍትሔ የላቸውም ተብለው ህዝቡ ሁሉ ተስፋ የቆረጠባቸው ችግሮች በሙሉ የእግዚአብሔር ጥበብ ይፈታቸዋል።
በሳይንሱ ዓለም እጽዋቶች እየተቀመሙ ለመድሓኒትነት ውለው በክኒን መልኩ እንድሚፈውሱ ሁሉ
አባቶች መሥሠረት አድርገው ያቆዩል በባህል ህክምና እና በጥበብ ተክነው በተለያዩ ዕጽዋቶች እና ልዩ የፈጣሪ ጥበብን በመጠቀም ሙሉ መፍትሔ የመስጠት ዓቅም አላቸው።
ጥበብን እናከብራት ዘንድ የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔር መፍራት ነው። እንደተባለው
💚ሰላም 💛ፍቅር ❤️ጤና ከሁላችን ቤት ይግባ።
ኢትዮጵያን ከነህዝቦችዋ ፈጣሪ ይባርካት።
መርጌታ አምደ ብርሃን !!!
❤ 10👍 3
== ግሩማን አራዊት ===
✦ግሩማን አራዊት ተብለው የሚጠሩት ብሔሞት እና ሌዋታን የተባሉ ሁለት ግዙፋን አራዊት ናቸው፨
✦እነዚህ ሁለት ግዙፍ አራዊት በጣም ከመግዘፋቸው የተነሳ ምድርን እንደ ቀለበት ከበው የያዙ ናቸው፨እነዚህ አራዊት በግዝፈት የሚደርስባቸው የለም፨
✦ከሰው እይታ ውጪ ናቸው፨ምክንያቱም ከሰው ልጅ እይታ ውጪ በሆነ ቦታ ስለሚኖሩ ነው፨
✦ጾታቸውን ስንመለከት ብሔሞት ተባዕት ሲሆን ሌዋታን ደግሞ እንስት ነች፨
✦ብሔሞት በየብስ ላይ ይኖራል፨በአንጻሩ ሌዋታን በውሃ ውስጥ ትኖራለች።ምግባቸውንም ከየሚኖሩበት ስፍራ ያገኛሉ፨
✦እነዚህን ግሩማን አራዊት አንዳንድ የበቁ አባቶች በፈጣሪ ፈቃድ ተመልክተወቸዋል፨ለዚህም ሔኖክ አንዱ ምሳሌ ነው፨አንዳንድ አባቶች እኒህን ፍጥረታት ከመመልከት አልፈው ለማዘዝም በቅተዋል፨
✦እንደ ማንኛውም ፍጥረት ምድባቸው ከ፳፪ቱ ስነ ፍጥረታት ነው፨
የበለጠ ለማወቅና ለመረዳት አክሲማሮስ የተሰኘውን ጥንታዊ የስነ ፍጥረት መጽሐፍ መመልከት ይቻላል፨
❤ 1
00:53
Видео недоступноПоказать в Telegram
IMG_8990.MP44.42 MB
🌦🌦የአየር ጠባይ በሚቀያየርበት ጊዜ 🌦🌦
ኢንፍሉዌንዛ/ፍሉ
ይህ ህመም በክረምት ወራት የሚሰራጭ ቢሆንም ከአንድ ሰው ወደሌላው ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ።
ሲጀምርም ራስን ማዞር ማቅለሽለሽ የሰውነትን አካል ማድቀቅ ማድከም ማተኮስ ማዛል ይታይበታል ።
ጉሮሮውንም መዝጋት ጉልበት ማድከም ሳል በአፍንጫ ላይም ፈሳሽ ይፈጥራል ።
ለዚህ መድሀኒቱ አስቀድሞ
1. ቁንዶ በርበሬ ወይም ሎሚ ያለው ጅንጅብል ነጭ ሽንኩርት እነዚህን የመሰሉ በቀን እንደሻይ ሶስት ጊዜ መጠጣት ነው ።
2. በሕመሙ ከተያዙ የባህር ዛፍ ቅጠል ወይም የዳማ ከሴ ቅጠል ቀቅሎ መታጠንና መተኛት ነው ወይም የውሻ ኩስ ታጥኖ ተሸፋፍኖ መተኛትና ሲነቁ ለብ ባለ ውኃ ገላን መታጠብ ነው ።
3. የጦስኝ የዳማ ከሴ የዝንጅብል የከርቤ ሻይ የብርቱካን የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ነው ።
❤ 7
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
ዕጽዋቶችን ማቅረብ ለምትሹ ውድ ቤተስቦች ከስር ያስቀመጥኳችው እጽዋቶችን ስለምፈልግ ዋጋ በስምምነት በንጽህና ልያቀርብልኝ የሚችል ሰው ቢኖር በ 0918834904 ይደውልልኝ::
☘የሚገባውን ክፍያ ከፍየው የሚያቀርብልኝ ሰው ቢኖር እጅጉን ደስ ባለኝ።ከዚህ በፊት የጠየኳችሁ የወርቅ በሜዳ ሥርም በተጨማሪ የሚያቀርብልኝ ሰው ቢኖር ውለታ እከፍላለሁ።እታዘዝማለሁ።
☘️የዕፀ-ኢየሱስ ሥር 10 ኪሎ
☘️የፍየለ ፈጅ ሥር 10 ኪሎ
☘️የ ዕፀ አንበሳ ሥር 5 ኪሎ
☘️የታርይገማ/ድርሽት ሥር 10 ኪሎ
☘️የሰላቢላ ሥር 10 ኪሎ
አመሰግናለሁ::
❤ 9
ገንዘብዎ ላይ በረከት አጥተዋል?
✔️የገንዝብ መበተን ዋነኛ ምክንያቶች!
#የሴት ዛር መንፈስ
#የገርጋሪ መንፈስ
#የዝሙት መንፈስ
#የልጅነት ቁራኛ ዓይነ ጥላ
#የቤተሰብ ዛር መናፍት
#የሰላቢ መተት እና መናፍስቶች የበረከት ማጣት ችግር የሚፈጥሩ ናቸው::
✔️ገንዘብ አልመበርከት ምክንያቶቹ!
👉🏾አልባሌ የሆኑ ወጪዎች
👉🏾እቃ መበላሸት
👉🏾በተደጋጋሚ በመታመም የሕክምና ወጪ ማብዛት
👉🏾በብድር መልኩ በመውጣት ገንዘቦትን ባለመምለስ
👉🏾ለዝሙት ስራ
👉🏾ዕዳ ውስጥ በማስገባት ሁሌም ሕይወትዎ በብድር መታሰር
👉🏾በተልያየ ምክንያት ገንዘቦት መወረስ
👉🏾በይሉኝታ ገንዘብን እየሰጡ ማባከን
ወዘተ...
💵የገንዘብ አልመበርከትን ከላይ የተጠቀሱት ክፉ መናፍስቶች የሚፈጥሩት ችግር መሆኑን ተረድተን ወደ መፍትሔ ስንሔድ...👇🏾👇🏾👇🏾
#የእንቧጮ ተቀጽላ
#የሥረ-ብዙህ ሥር
#የምስሮች ተቀጽላ
እነዚህ ሶስቱም ተቀጽላ እኩል በአንድነት ወግጠው ነፍተው አንድ የሾርባ ማንኪያ ከ 3 የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር ለውሰው!
መዝሙር ፡ ዘዳዊት ፡
፩አምጽኡ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ውሉደ ፡ አማልክት ፤
አምጽኡ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እጓለ ፡ ሐራጊት ፤
፪አምጽኡ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ክብረ ፡ ወስብሐተ ።
አምጽኡ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ስብሐተ ፡ ለስሙ ፤
ስግዱ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ በዐጸደ ፡ መቅደሱ ።
፫ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ላዕለ ፡ መየት ።
አምላከ ፡ ስብሐት ፡ አንጐድጐደ ፤
እግዚአብሔር ፡ ላዕለ ፡ ማያት ፡ ብዙኅ ።
፬ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ በኀይል ፤
ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ በዐቢይ ፡ ስብሐት ።
፭ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይቀጠቅጥ ፡ አርዘ ፤
ወይቀጠቅጦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለአርዘ ፡ ሊባኖስ ።
፮ወያደገድጎ ፡ ከመ ፡ ላህመ ፡ ለሊባኖስ ፤
ወፍቁርሰ ፡ ከመ ፡ ወልድ ፡ ዘአሐዱ ፡ ቀርኑ ።
፯ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመትር ፡ ነደ ፡ እሳት ።
ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያድለቀልቆ ፡ ለገዳም ፤
ወያድለቀልቆ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለሐቅለ ፡ ቃዴስ ።
፰ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያጸንዖሙ ፡ ለኀየላት ፤
ወይከሥት ፡ አዕዋመ ፤
ወበጽርሑ ፡ ኵሉ ፡ ይብል ፡ ስብሐት ።
፱እግዚአብሔር ፡ ያስተጋብኦ ፡ ለማየ ፡ አይኅ ፤
ወይነብር ፡ እግዚአብሔር ፡ ወይነግሥ ፡ ለዓለም ።
ወይሁቦሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኀይለ ፡ ለሕዝቡ ፤
እግዚአብሔር ፡ ይባርኮሙ ፡ ለሕዝቡ ፡ በሰላም ።
☝☝☝ይህንን የመዝሙረ ዳዊት ጸሎት ከላይ በተዘጋጁት ተቀጽላዎች 3 ጊዜ ጧት በባዶ ሆድ ጸልየው ጧት ጧት በባዶ ሆድ ለ 3 ቀን ይውሰዱ::
በረከት የሚያሳጣ ማንኛውም ክፉ መንፈስ ያል ምንም ጥርጥር በ እግዚአብሔር ኃይል ይነሳል::
🙏 የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
📞0918834904
📞0915310455
@merigetaamedeberhan
❤ 2
