ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
Открыть в Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Больше44 133
Подписчики
Нет данных24 часа
-747 дней
-34830 день
Загрузка данных...
Похожие каналы
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Облако тегов
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Входящие и исходящие упоминания
---
---
---
---
---
---
Привлечение подписчиков
декабрь '25
декабрь '25
+13
в 0 каналах
ноябрь '25
+17
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '250
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '25
+527
в 0 каналах
Get PRO
август '250
в 0 каналах
Get PRO
июль '250
в 0 каналах
Get PRO
июнь '25
+1 187
в 0 каналах
Get PRO
май '250
в 0 каналах
Get PRO
апрель '250
в 0 каналах
Get PRO
март '250
в 0 каналах
Get PRO
февраль '250
в 0 каналах
Get PRO
январь '25
+374
в 0 каналах
Get PRO
декабрь '24
+656
в 0 каналах
Get PRO
ноябрь '24
+1 121
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '24
+1 636
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '24
+1 245
в 0 каналах
Get PRO
август '24
+4 194
в 0 каналах
Get PRO
июль '24
+725
в 0 каналах
Get PRO
июнь '24
+1 126
в 0 каналах
Get PRO
май '24
+620
в 0 каналах
Get PRO
апрель '24
+1 991
в 0 каналах
Get PRO
март '24
+707
в 0 каналах
Get PRO
февраль '24
+793
в 0 каналах
Get PRO
январь '24
+871
в 0 каналах
Get PRO
декабрь '23
+505
в 0 каналах
Get PRO
ноябрь '23
+254
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '23
+2 051
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '23
+257
в 0 каналах
Get PRO
август '23
+13
в 0 каналах
Get PRO
июль '230
в 0 каналах
Get PRO
июнь '23
+7
в 0 каналах
Get PRO
май '23
+262
в 0 каналах
Get PRO
апрель '23
+19
в 0 каналах
Get PRO
март '23
+102
в 0 каналах
Get PRO
февраль '23
+49
в 0 каналах
Get PRO
январь '230
в 0 каналах
Get PRO
декабрь '220
в 0 каналах
Get PRO
ноябрь '220
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '22
+36
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '22
+134
в 0 каналах
Get PRO
август '22
+71
в 0 каналах
Get PRO
июль '22
+99
в 0 каналах
Get PRO
июнь '22
+62
в 0 каналах
Get PRO
май '22
+62
в 0 каналах
Get PRO
апрель '22
+37
в 0 каналах
Get PRO
март '22
+59
в 0 каналах
Get PRO
февраль '22
+46 444
в 0 каналах
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 15 декабря | 0 | |||
| 14 декабря | +2 | |||
| 13 декабря | 0 | |||
| 12 декабря | 0 | |||
| 11 декабря | +1 | |||
| 10 декабря | 0 | |||
| 09 декабря | 0 | |||
| 08 декабря | 0 | |||
| 07 декабря | 0 | |||
| 06 декабря | 0 | |||
| 05 декабря | +4 | |||
| 04 декабря | +4 | |||
| 03 декабря | 0 | |||
| 02 декабря | +2 | |||
| 01 декабря | 0 |
Посты канала
ቢቢሲ 6 የኢትዮጵያ ቲክቶከሮች የማህበረሰቡን ስነምግባር አላከበሩም በሚል በተለይ በአለባበስ ምክንያት መታሰራቸዉን የዘገባ ሽፋን ሰጥቶታል።
#ዳጉ_ጆርናል
1 28720
| 2 | መምህሯን አስገድደው የደፈሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሀርቡ ጂባት ቀበሌ ውስጥ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል የፈፀሙት ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ
የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ በዬራ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት 1ኛ ተከሳሽ ማሞ ዘነበ
2ኛ ተከሳሽ ቢቂላ ፍቃዱ የካቲት 27ቀን 2017 ዓ.ም ከለሊቱ 7ሰዓት ድርጊቱን መፈጸማቸው ተገልጿል ። ተጎጂዋ በመምህርነት ሞያ ስታገለግል የነበረች ሲሆን በር ሰብረው በመግባት የግብረ ስጋ ድፍረት በደል እንደፈፀሙባት በማስረጃ ተረጋግጧል።
ሁለቱ ተከሳሾች በመምህሯ ላይ ድርጊቱን ከፈፀሙ በኋላ ወዲያው ለፖሊስ ደውላ በማሳወቋ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጎጂዋ የጤና ምርመራ የተደረገላት ሲሆን በውጤቱም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል በግዳጅ እንደተፈፀመባት መረጋገጡም ከጤና ተቋም የተገኘው ማስረጃ ማረጋገጡን ገልፀዋል ።
ፖሊስ በመምህሯ ላይ የተፈፀመውን የግብረ ስጋ ድፍረት በደል በማስረጃዎች አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኳል።
አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን ማስረጃ ተመልክቶ በወንጀል ህግ ቁጥር 620 እና 605 መሰረት ክስ የመሰረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 39ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች የሃይል ድርጊት በመጠቀም አስገድደው የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀማቸውከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት በማስከተላቸው እያንዳዳቸው በአስራ አንድ አመት እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ በዬራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል | 5 164 |
| 3 | ከሀገራችን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አንዱ የሆነውን ቲክቶክ በመጠቀም ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችና ምስሎችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ግለሠቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።
በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ስነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ ዜና በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባራትና ትውልድን ለማነጽ መጠቀም ሲገባ ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ።
#ዳጉ_ጆርናል | 1 609 |
| 4 | No text | 1 535 |
| 5 | በመተከል ዞን የኮሌራ በሽታን ሙሉ በሙሉ መከላከል አልተቻለም ተባለ
የበሽታው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወረዳ ላይ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ወደ ሌሎች ወረዳዎች እየተዛመተ በመሆኑ ከምን ጊዜም በላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ያስፈልጋል ተብሏል።በመተከል ዞን ወረዳዎች የኮሌራ በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም የበሽታውን ስርጭት ሙሉ በሙሉ መከላከል አለመቻሉን የመተከል ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል።
የመተከል ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ታረቀኝ አርገታ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በዞኑ የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል ዘርፈ ብዙ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም የበሽታውን ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ ዜሮ ማድረግ አልተቻለም።በሽታውን ሙሉ ለሙሉ ለመከላከል ባለመቻሉ የዞኑ ጤና መምሪያ ከክልል ጤና ቢሮና ከዞን የሚመለከታቸው ወረዳዎች ጋር መክሯል ።ይህን የበሽታ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወረዳ ላይ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ወደ ሌሎች ወረዳዎች እየተዛመተ በመሆኑ ከምን ጊዜዉም በላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት እገዛና እና ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ዶ/ር ታረቀኝ ተናግረዋል ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥርና ምላሽ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መብራቱ በጉኖ በበኩላቸው የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ቁርጠኝነት እና ቅንጅታዊ አሰራር በተፈለገው ልክ አለመሆኑን ተናግረዋል።በዚህም የተነሳ የአጭር ጊዜ የድርጊት መረሀ ግብር ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባት አለበት ብለዋል።የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል ከጤና መዋቅሮች በዘለለ የሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች በትኩረት መስራት እንዳለባቸዉ አቶ መብራቱ በማንሳት ለስራ መሳካት በቢሮ በኩል አስፈላጊው የማቴሪያል እና የቴክኒክ እገዛ እንደሚደረግ ገልጸዋል ።ከህገ ወጥ ወርቅ ቁፋሮ መበራከት ጋር ተያይዞ የንፁህ የመጠጥ ዉሀ እና የመፀዳጃ ቤቶች በበቂ መልኩ አለመኖር ለችግሮች መባባስ አይነተኛ መንስዔ መሆናቸው በመድረኩ ተጠቁሟል።
ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል | 1 624 |
| 6 | No text | 1 545 |
| 7 | በአሜሪካ ኮንግሬስ አባል ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በሌሎች እምነት አማኞች ላይ እየተፈጸመ ነዉ ላሉት ጥቃት ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ ተባለ
በአሜሪካ ኮንግሬስ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባሉ ኤርል በዲ ካርተር፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የሓይማኖት ተከታይ ማኅበረሰቦች ላይ ይፈጽሙቸዋል ላሉት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ አሜሪካ ማዕቀብ እንድትጥል የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አቀረቡ።
ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ፣ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም እና ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የተመረጡ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሁሉንም ዲፕሎማሲ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙ ይጠይቃል።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የሌሎች ኃይማኖቶች ተከታዮች የጦር ወንጀልና ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎች እንደተፈጸሙባቸው የሚያሳዩ ሁኔታዎች መኖራቸውንም የውሳኔ ሃሳቡ ይገልጣል። | 1 574 |
| 8 | የሾንኬ መንደርን በአለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተባለ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት የሾንኬ መንደርን በአለም አቀፍ ቅርስነት መዝገብ ውስጥ እንዲሰፍር ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ።
ይህን ባለ ብዙ ታሪክ መንደር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ እሴቶች በጥናት እንዲለዩ ለማስቻል ለወሎ ዩኒቨርስቲ ደብዳቤ ተልኳል ሲሉ አቶ አበበ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
የሾንኬ መንደር ከከሚሴ ከተማ በምሥራቅ አቅጣጫ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደዋ ጨፋ ወረዳ ጅሮታ በሚባል ቀበሌ የሚገኝ ታሪካዊ መንደር ነው። ከአርጎባ ብሔረሰብ መኖሪያ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆንም ይህንን ድንቅ መንደር ሼህ ፈቄ አሕመድ የተባሉ የሃይማኖት አባት እንደመሰረቱት ይነገራል፡፡
ተራራማ ቦታ ላይ በድንጋይ፣ በአፈር እና በወይራ እንጨት በተለየ መንገድ የተሠራ መንደር እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ውቡ መንደር ሦስት መስጅዶች እና አምስት መቶ የሚኾኑ መኖሪያ ቤቶችን ስለመያዙ ይነገርለታል።
ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል | 3 792 |
| 9 | ዩክሬን ሞስኮን ጨምሮ ከባድ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጥቃት እየፈፀመችብኝ ነው ስትል ሩሲያ አስታወቀች
ሞስኮን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ዩክሬን ቢያንስ 287 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም ከፍተኛ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ሩሲያ ሐሙስ እለት ተናግራለች። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሞስኮ ክልል ቢያንስ 40 ሰው አልባ አውሮፕላኖች የተተኮሱ ሲሆን በከተማዋ ከ22 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖራል ሲሉ አስታውሰዋል።
የጉዳቱ መጠን እስካሁን ባይገለፅም የአውሮፕላን በረራዎች ከሁሉም የሞስኮ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ እንዲዘዋወር ተደርጓል።እ.ኤ.አ. በየካቲት 2022 ሩሲያ ዩክሬንን የወረረች ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የዩክሬን አንድ አምስተኛ ግዛት ተቆጣጥራለች። ሩሲያ ትንሿን ጎረቤቶቿን በሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች መደብደቧን ቀጥላለች፤ በቅርቡ የኃይል ዘርፉን ኢላማ ማድረጓ ይታወሳል።
ዩክሬን በዚህ አመት የሩሲያ የነዳጅ ፋብሪካዎችን እና የነዳጅ ተርሚናሎችን በሰው አልባ አውሮፕላኖች ለማውደም ተንቀሳቅሳለች። የዩክሬን የባህር ላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ረቡዕ እለት በሩሲያ ዘይት ንግድ ላይ የተሳተፈየነዳጅ ጫኝ መርከብ በዩክሬን ብቸኛ የኢኮኖሚ ዞን በጥቁር ባህር በኩል ወደ ሩሲያ ኖቮሮሲይስክ ወደብ ሲጓዝ በመምታት ጉዳት ማድረሱን የዩክሬን ባለስልጣናት መናገራቸው ይታወሳል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል | 4 201 |
| 10 | ባለፉት 5 ወራት 61 አሽከርካሪዎችን በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ተጠያቂ መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታወቀ
👉 ከ 1.3 ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ጉዳት ካሳ ተከፍሏል
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አምስት ወራት ውስጥ 61 የመሰረተ ልማት የንብረት ጉዳት ካሳ ግምት ለመልሶ ማልማት የሚውል ገንዘብ ማስከፈሉን አስታወቋል።ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ የምህንድስና ስራዎችን በሰፊው እያከናወነ ቢሆንም አንዳንድ አሽከርካሪዎች በሚያደርሱት ግጭት ምክንያት በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡
የመሰረተ ልማት የማስተዳደር ስልጣንና ተግባር መሰረት የመንገድ ደህንነት መሰረተ ልማቶች በተገቢው መንገድ አገልግሎት እንዲሰጡ ከመጠበቅ ባለፈ ጉዳት የሚያደርሱትንም አካላት ተጠያቂ ያደርጋል፡፡በፓርኪንግ መሰረተ ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የመሰረተ ልማት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ግሩም ተመቻቸ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ከትራፊክ ፖሊስ በመጣ ሪፖርት መሰረት 61 አሽከርካሪዎች ባደረሱት ጉዳት ግምታዊ ክፍያ ፈጽመዋል፡፡
በዚህም መሰረት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የለሙ የትራፊክ ምልክቶች፣ የትራፊክ መብራቶች፣ ቦላርድ፣ ሴፍቲ ሮለር እና የእግረኛ ብረት አጥሮች ላይ በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ውስጥ ጉዳት ያደረሱ 61 አሽከርካሪዎች አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ አስራ አራት ሺ ብር እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት ራሳቸውንና ህብረተሰቡን ከትራፊክ አደጋ እንዲጠብቁና የሀገር ሀብት የሆኑትንና በውጪ ምንዛሪ የሚገዙትንና የሚለሙትን የመሰረተ ልማት አውታሮች ከማውደም ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ አቶ ግሩም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል | 4 435 |
| 11 | No text | 5 011 |
| 12 | የምያንማር ወታደራዊ ኃይል በሆስፒታል ላይ በፈፀሙው የአየር ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ተገደሉ
ረቡዕ ምሽት በምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የምያንማር ጦር የአየር ድብደባ በመፈመሙ ቢያንስ 34 ሰዎች ሲሞቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል። ሆስፒታሉ የሚገኘው በራኪን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ምሩክ-ዩ ከተማ ላይ ነው። አራካን የተሰኘው ጦር አካባቢውን የሚቆጣጠር ሲሆን የሀገሪቱን ወታደራዊ አገዛዝ ከሚዋጉት በጣም ጠንካራ የጎሳ ኃይሎች መካከል አንዱ ነው።
እ.ኤ.አ. በ 2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ከተቆጣጠረ እና የእርስ በርስ ጦርነት ካስነሳ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሞተዋል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል ። ከቅርብ ወራት ወዲህ ወታደራዊ ግዛቱን ከጎሳ ተኮር ታጣቂ ቡድኖች ለማስመለስ የአየር ድብደባውን አጠናክሮ ቀጥሏል። በምያንማር ጦር የአየር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ፓራግላይደሮችን የተሰኙ መሳሪያዎችን አሰማርቷል።
ምያንማር ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምታካሂደው ምርጫ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ድምጽ ለመስጠት በዝግጅት ላይ እያለ ይህው ጥቃት የደረሰ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የጦር ኃይሉ የሰጠው መግለጫ የለም። ነገር ግን፣ በቴሌግራም ላይ የሚገኙ የወታደራዊው ኃይል ደጋፊ አካውንቶች የዚህ ሳምንት ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። የአራካን ጦር ቃል አቀባይ ካኢንግ ቱካ እንደተናገሩት አብዛኞቹ ሰለባዎች በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ ንፁሃን ታካሚዎች ናቸው ብለዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል | 4 617 |
| 13 | በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የነዳጅ ምርት በቁጥጥር ስር መዋሉን የጉራፈረዳ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ
መነሻዉን ሚዛን አማን ከተማ በማድረግ ወደ ዲማ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 54 በርሜል ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጉራፈርዳ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር ኩራቱ በላቸዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በጉራፈረዳ ወረዳ ባደረገዉ ድንገተኛ ፍተሻ ህገወጥ ምርቱን የያዙ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል ።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች ከእያንዳንዳቸው 27 በርሜል ናፍጣ በሊትር ሲሰላ በሺዎች የሚቆጠር የናፍጣ ምርት በህገወጥ መንገድ ከገበያ ተደብቆ ለግል ጥቅም ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ዉሏል ።
የነዳጅ አቅርቦት ፍትሃዊ እንዲሆንና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለበት ወቅት እንዲህ ያሉ ህገወጥ ተግባራት በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ማህበረሰቡ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ከፖሊስ ጎን መቆም እንዳለበት ኢንስፔክተር ኩራቱ ጨምረዉ ለጣቢያችን ገልፀዋል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል | 4 822 |
| 14 | አሚጎስ ከኖታ ካርስ ጋር በመተባበር 6ኛ ዙር የመኪና ርክክብ አካሄደ
👉አሚጎስ ከኖታ ካርስ ጋር በመተባበር ለደንበኞቹ 14 የ BYD ኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል
አሚጎስ በአሁኑ ወቅት የአባላቱበላይን ቁጥር 13ሺ በማድረስ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት አካብቷል። በተጨማሪም በቅርቡ የሚከፈቱትን ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ጨምሮ በአዲስአበባ 10፣ በክልል ከተሞች ደግሞ 7 ቅርንጫፍ ቢሮዎችን መክፈቱን ብስራት ሰምቷል። በቅርቡ በአሶሳ፣ በሀዋሳ እና በጅማ ቢሮዎቹን ለመክፈት ዝግጅቱን አጠናቋል።
የአሚጎስ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ርእሶም፤ ድርጅታችን ከተለያዩ የመኪና አስመጪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለደንበኞቹ የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል።
አሚጎስ ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ እና በዓለምአቀፍ ህብረት ስራ ጥምረት ተሳታፊ ለመሆን የበቃ ሲሆን፣ አለምአቀፉ የህብረት ስራ ማህበር ኮንፌዴሬሽን ኢንተርናሽናል ኮፕሬቲቭ አልያንስ፣ አሚጎስ በተሳተፈባቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አድናቆትን አግኝቷል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ህብረት ስራ ማህበራት መካከል በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እውቅናን ስለማግኘቱ ብስራት ሰምቷል። አሚጎስ እስከ 10 ዓመት ድረስ የብድር መመለሻ ጊዜ ለደንበኞቹ ያመቻቸ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከፍ ያለ ብድር እስከ 20 ሚሊየን ብር ለደንበኞቹ አመቻችቷል።
በሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል | 5 066 |
| 15 | የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የብሩንዲ ጦርን የዋሽንግተን የሰላም ስምምነትን ጥሷል ስትል ሩዋንዳ ከሰሰች
ሩዋንዳ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የብሩንዲ ጦር ረቡዕ እለት በዋሽንግተን የሰላም ስምምነት ላይ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተፈራረመ በኋላ በምስራቅ ኮንጎ ያለውን ብጥብጥ ለማስቆም የነበረውን ሂደት ጥሰዋል ስትል ከሳለች። የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሩዋንዳ በደቡብ ኪቩ ግዛት ለተከሰቱት የተኩስ አቁም ጥሰቶች፣ ቀጣይ ጥቃቶች እና ውጊያዎች ተጠያቂ ልትሆን አትችልም ብሏል።
ሩዋንዳ እንዳስታወቀችው የኮንጎን ጦር እና የብሩንዲ ጦር ከጥምረቱ ጋር፣ ሚሊሻዎችን እና የውጭ ቅጥረኞችን ጨምሮ፣ በሩዋንዳ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የሲቪል መንደሮች ላይ ስልታዊ በሆነ መንገድ የቦምብ ጥቃት በማድረስ፣ ተዋጊ ጄቶችን በመጠቀም እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በማጥቃት ከሳለች።
ሰኞ ዕለት የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር ሩዋንዳ በዩናይትድ ስቴትስ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ጥሳለች ሲሉ ከሰዋል። የቡሩንዲ ጦር የኮንጎ መንግስት ለመደገፍ በደቡብ ኪቩ ወደ 20,000 የሚጠጉ ወታደሮችን አሰባስቧል፣በተለይም የባንያሙሌንጅ መንደሮች ላይ ከበባ አድርገዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል | 4 717 |
| 16 | ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ
#ለቪትስ
#ለያሪስ
#ለዲዛየርና ስዊፍት
#ለኮሮላ
#3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን
👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም)
👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን
👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን | 5 370 |
| 17 | የብራዚል የቀድሞ ፕሬዝዳንት የእስር ጊዜ ለመቀነስ በተደረገ ጥረት በምክር ቤት ውስጥ ግብግብ ተፈጠረ
የብራዚል ወግ አጥባቂ የሕዝብ እንደራሴዎች የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዣሂር ቦልሶናሮን የእስር ጊዜ የሚቀንስ ሕግ ለማጽደግ ጫና ሲያደርጉ በምክር ቤት ውስጥ ግብግብ ተነሳ።የፀጥታ ኃይሎች ምክር ቤቱን ለማረጋጋት ሲሞክሩ ግብግቡ የተነሳ ሲሆን፤ አንድ ግራ ዘመም ሕግ አውጪ ከምክር ቤቱ በፖሊስ ታጅበው እንዲወጡ ተደርጓል።
ቦልሶናሮ እአአ በ2022 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ መፈንቅለ መንግሥት አሲረዋል በሚል ክስ የ27 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከያዝነው ወር ጀምሮ የተፈረደባቸውን የእስር ጊዜ ጀምረዋል።የቦልሶናሮ ወግ አጥባቂ ደጋፊዎች ከመፈንቅለ መንግሥት ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ክሶች የሚያስከትሉትን የእስር ጊዜ የሚቀንስ ሕግ ለምክር ቤት አቅርበዋል።
ሕግ አውጪዎቹ፤ ቦልሶናሮ ከሥልጣን ሲወርዱ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጥሰው የገቡ ደጋፊዎቻቸው ነጻ የሚወጡበትን መንገድ ለማግኘትም እየሞከሩ ነው።የቦልሶናሮ ጠበቆች እንዳሉት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ከእስር ቤት እንዲወጡ የቀረበው ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ አላገኘም።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል | 6 384 |
| 18 | የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳወቀ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።
አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህል ለመጫን የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
#ዳጉ_ጆርናል | 6 511 |
| 19 | በበሬ ግብይት ያልተስማማውን ሻጭን የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ገም ቀበሌ ገም ገነት ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።
የግል ተበዳይ የራሱን በሬ ለመሸጥ ወደ ገበያ እየወሰደ እያለ ተከሳሽ ገረመው ኪዲሺ በሬዉን እኔ በ40 ሺህ ብር ልግዛህ ይለዋል፡፡ሻጭም በተጠራው ግምት ባለመስማማቱ ጨምር ይለዋል፡፡ገዥውም አልጨምር ሲል ሻጭ በሬዉን ወደ ገበያ ይዞ በመሄድ በሬውን በ52 ሺህ ብር ይሸጣል፡፡
በመቀጠልም የሸጠበትን ብሩን ይዞ ወደ መኖሪያው ቤቱ በመሄድ ላይ እያለ ቂም የቋጠረው ተከሳሽ መንገድ በመጠበቅ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ለምን አልሸጥክልኝም በሚል በዱላ ደብድቦ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ከጨና ወረዳ ፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ግለሰቡን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ 539 ንዑስ 1 ሀ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ በፈፀመው ሰዉ የመግደል ወንጀል ክስ መስርቶበት ካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀርበዋል።
የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ግለሰቡ ላይ የመሰረተውን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሰው ምስክሮችን አድምጦ ተከሳሹን ጥፋተኛ ነው ሲል የጥፋተኝነት ብይን ይሰጣል።
በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ገረመው ኪዲሺን በ15 አመት እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል | 6 158 |
| 20 | ጉግል 'ዐይን ላይ የሚደረግ ኮምፒውተር' የተባለ በኤአይ የሚሠራ ስማርት መነጽር ለገበያ ሊያቀርብ ነው
ጉግል በመጪው የአውሮፓውያን ዓመት በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሚሠራ ስማርት መነጽር ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ።ከዚህ ቀደም ስማርት መነጽር ለማቅረብ ያደረገው ጥረት ባይሳካም በቅርቡ እንደ አዲስ መነጽሩን የሚያስተዋውቅ ይሆናል።ጉግል በአውሮፓውያኑ 2013 መነጽሩን ሲያስተዋውቅ የወደፊቱ ቴክኖሎጂ ማሳያ ተደርጎ ተወስዶ ነበር።
መነጽሩ ከዐይን በላይ ጎልቶ የሚታይ ስክሪን የተገጠመለትም ነበር።መነጽሩ በ2015 (እአአ) ከገበያ ውጪ ቢደረግም አሁን ግን በድጋሚ ለማቅረብ ጉግል ወስኗል።ሜታ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ ስማርት መነጽር ያስተዋወቀ ሲሆን፤ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ገዝተውታል።የጉግል ስማርት መነጽር ከሌሎች የጉግል ምርቶች ጋር የተሳሰሩ ናቸው። መነጽሩን የሚያደርጉ ሰዎች እንደ ጄምኒ ያሉ የጉግል መተግበሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ።
ጄምኒ በጽሑፍ እና በድምጽ ለጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ የጉግል ቻትቦት ነው።ጉግል ለገበያ ከሚያቀርባቸው መነጽሮች አንደኛው ስክሪን የሌለው ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በመነጽሩ ሌንስ ላይ ስክሪን የተገጠመለት ነው።የቴክኖሎጂ ተንታኝ ፓውሎ ፔስካቶሬ "ጉግል ከቀደመው ስህተት መማር አለበት። ከዚህ ቀደም መነጽሩን ያስተዋወቀው መውጣት ከነበረበት ጊዜ ቀድሞ ነው" ብለዋል።ጄምኒ ቻትቦት ስኬታማ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የጉግል ስማርት መነጽር ውጤታማ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል | 6 159 |
