fa
Feedback
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

رفتن به کانال در Telegram

News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

نمایش بیشتر
110 728
مشترکین
-10224 ساعت
-2787 روز
-1 09630 روز
آرشیو پست ها
"ልቤን" እያለ አረፈ ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ በድንገተኛ የልብ ህመም በዳግማዊ ምንልክ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሕይወቱ አልፏል። ትናንት "ልቤን" ብሎ ወደ ህክምና አምርቶ ነበር። ለሊቱን ሁሉ ሕክምና እየወሰደ ከአንድም ሁለት ጊዜ አሰቸጋሪ ደረጃ እየደረሰ በሕክምና ህይወቱ ተመልሷል። ይሁንና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የሆነው ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ ዛሬ ማለዳ ላይ አርፏል።
نمایش همه...
😭 116 40😢 9🤔 1
በሆንግ ኮንግ 128 ሰዎችን ለሕልፈት የዳረገው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ በሆንግ ኮንግ በጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 128 ደርሷል አሉ የአካባቢው ባለስልጣናት፡፡ ባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት በተከሰተው የእሳት አደጋ ለሕልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ ከ200 በላይ ሰዎች እስካሁን ያሉበት አልታወቀም፡፡ ከ4 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በሚኖሩባቸው የጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች የተከሰተውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የሆንግ ኮንግ የደህንነት ኃላፊ ክሪስ ታንግ ገልጸዋል፡፡ አደጋውን ለመቆጣጠር ከ2 ሺህ በላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ÷ በአደጋው ምክንያት በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ሰዎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡ ኃላፊው በሰጡት መግለጫ በሁሉም ሕንጻዎች ላይ የተገጠሙ የእሳት አደጋ የጥንቃቄ መልዕክት መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጡ እንዳልነበር አመልክተዋል፡፡ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ፖሊስ በይፋ ምርመራ መጀመሩንና መረጃዎችን እያሰባሰበ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡   T.me/ethio_mereja       ኢትዮ-መረጃ
نمایش همه...
70😢 13🤯 6👍 3🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
በሃዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ። ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማልበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል። ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። በዚህም ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ ሰዎች በየእለቱ የላብራቶሪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5 ቀን እስከ ህዳር 17 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትሯ በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 6ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክምና ላይ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል። በሌላ በኩል ሌሎች ሃገራት ላይ ተሞክሮ ለውጥ ያመጣ ዶሚድስፔር የተባለ ፀረ ህዋስ መድሃኒት ወደ ሃገር ቤት በማስገባት ለ16 የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በህክምና ላይ ላሉት 5 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሰጥተናል ብለዋል። መድሃኑቱ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መቅደስ በህክምና ላይ ያሉት 5ቱ ተጠቂዎች የማገገም ሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።በፅኑ ህሙማን ክፍል 1ታማሚ እንዳለ የተነገረ ሲሆን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።(ሸገር ራዲዮ)
نمایش همه...
75😱 11😭 9👍 5🤔 2👎 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው - ዶ/ር መቅደስ ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ። ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ እስካሁን የማርበርግ ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 73 ሰዎች መካከል 11ዱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና አምስቱ ደግሞ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ ከታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም 119 ሰዎች ነጻ መሆናቸው ተረጋግጦ ከማዕከል መውጣታቸውን ጠቁመዋል። የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው፥ የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በየኬላዎች የሚደረገውን ቁጥጥር የማጠናከር፣ የቅኝት ሥራዎችን የማስፋትና ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡ ማሕበረሰቡ ከጤና ሚኒስቴር የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በመተግበርና ጥቆማዎችን በመስጠት ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
نمایش همه...
42👍 3👎 1😁 1😱 1
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰጠውን የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰጠ ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች በልዩ መልኩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ማግኘት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶክተር ) መናገራቸው ይታወሳል ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተሩ ባስቀመጡት መመሪያ መሰረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰቷል ። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለአቶ ብዙአየሁ ታደለ የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የናሽናል ሲሚንቶ ሆልዲንግ ሼር ካምፓኒ ቦርድ ሊቀመንበር ሰቷል።ለከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ አምባሳደሮች ፣ ለሀገር ባለውለታዎች ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ልዩ ግልጋሎት የሚሰጥበት መገልገያ ቦታ መኖሩን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
نمایش همه...
45😁 12👍 5👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉135 ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251964439488 +251907232222 Telegram: https://t.me/OusmanTemer WhatsApp: https://wa.me/251964439488
نمایش همه...
20👍 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES ETHIO SPARK   ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ 🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች 🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች 🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች 🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና 🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  መስተንግዶ ጋር    እንጠብቆታለን።  ይደውሉ 👇 ☎️+251974967884 የፁሁፍ መልዕክት 👇👇 💌    @Dm4ethio 📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn Telegram link: https://t.me/EthioSpark16 You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0 Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/ Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/ Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark 🌐 Website:www.ethiospark16.com
نمایش همه...
22
#ኤርታሌ የፍንዳታው ድምፅ ጅቡቲ፣መቀሌ እና ደሴ ዙሪያ ተሰምቷል ። "ዛሬ የፈነዳው ተራራ በኤርታሌ አቅራቢያ የሚገኝ አዲስ ተራራ ሲሆን ከዚህ በፊት ምንም አይነት የእሳተ ገሞራ ምልክት አሳይቶ የማያውቅ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል ። ከፍንዳታው ሲወጣ የነበረው ጭስ አካባቢውን የሸፈነው ሲሆን በአቅራቢያ ያሉ መንደሮች የዛሬውን ውሎ ግማሽ ጨለማን የተላበሰ ቀን ነበር ያሳለፉት። ፍንዳታው በተከሰተበት ሰዓት የነበረው ድምፅ ከፍተኛ በመሆኑ በኤርታአሌ እና አፍዴራ ከተማ አቅራቢያ ንዝረት እና መጠነኛ መንቀጥቀጥ ያስከተለ ሲሆን ነዋሪዎች በድምፁ እጅግ ተደናግጠን በፍርሀት ተውጠን ነበር ሲሉ ክስተቱን አስረድተውናል። የድምፁ ስሜት እስከ ጅቡቲ ትግራይ እና ወሎ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ላይ እንደተሰማ በስልክ ያገኘናቸው ነዋሪዎች ነግረውናል ። ዛሬ የፈነዳው ተራራ ከዋናው የኤርታአሌ ተራራ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሶስት ቀን በፊት ጭስ መሰል ነገር ይታይበት እንደነበረው በስፍራው በእንስሳት ጥበቃ ላይ የተሰማራን ወጣት ማነጋገር ችለናል ። ተራራው ከዚህ በፊት ምንም አይነት ምልክት አሳይቶ እንደማያውቅ እና ከሶስት ቀን በፊት የተወሰነ ጭስ ማውጣት ጀምሮ ዛሬ ላይ ለጆሮ በሚከብድ መልኩ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ እንዳወጣ እና አካባቢውን በጥቁር ጭስ ወደ ጨለማነት እንደቀየረባቸውም ከመንደሩ ነዋሪ ጋር በነበረን ቆይታ ለመረዳት ችለናል ። ክስተቱ ከጠዋቱ 4:00- 7:00 ድረስ ድምፅ እያሰማ እንደነበር የስፍራው አስጎብኚ ገልፆልናል። የፍንዳታው ጭስ አመሻሹ ላይ ትንሽ የቀነሰ ሲሆን ቀን ላይ ከነበረው ጥቁር እና ጭጋጋማ አየር ወደ ነጭ አመድ መሰል ጭስ ተቀይሯል።" Via :-አፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
نمایش همه...
127😱 15🤯 6👍 5🤔 2
ገቢዎች ቢሮ በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚካሄድ የደረሰኝ ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ የሚገቡ፣ከከተማዋ የሚወጡና በከተማዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ የመኪና ኦፕሬሽን ስራዎች ማጠናከሩ ገልጿል። በዚህም ያለደረሰኝ የሚካሄዶ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የህግ ተጠያቂነት በአሸከርካሪዎች ላይ ጭምር እንዲሰፍን እያደረገ መሆኑ አሳውቋል። በአሁኑ ወቅት የደረሰኝ ቁጥጥሩ በቀን ብቻም ሳይሆን በለሊት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉ ያሳወቀ ሲሆን ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጦች ይዘው በተንቀሳቀሱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስጃለው ብሏል። ቢሮው የቁጥጥር ስራውን በየደረጃው ከተቋቋሙ ግብረ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት እያከናወነ ሲሆን በዚህም ተሸከርካሪዎች ዕለታዊ ደረሰኝ ሳይዙ በከተማዋ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ፣ከከተማው ሲወጡ ተገኝተው አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ ለእያንዳንዱ ለጫኑት ሸቀጥ ደረሰኝ እንዲቆርጡ ተደርጓልም ብሏል። በቀጣይም በከተማዋ ጭነት የጫኑ ማንኛውም አይነት ተሽከርካሪዎች፣ ለጫኑት ሸቀጥ ደረሰኝ እንዲቆርጡ ብቻም ሳይሆን አሽከርካሪዎቻቸው ላይም የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚደረግ መሆኑ አብራርቷል።
نمایش همه...
45👍 7👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
#Update ዛሬ 7 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ2 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። በአጠቃላይ በማርበርግ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10 የደረሰ ሲሆን ህይወታቸው እንዳለፈ የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 5 ደርሷል። እስካሁን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች የሉም። 5 ሰዎች ህክምና ላይ ይገኛሉ። በማርበግር ቫይረስ ዛሬም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።
نمایش همه...
46🤔 9😢 5😱 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
በማርበርግ በሽታ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰባቸው እንደማይሰጥ ነው የተነገረው። ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሏል። ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል። ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል። በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ነው የተባለው። ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም። እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፥ ህመሙ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል። ህመሙ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህመሙ ካለባቸው ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ከንክኪ የራቀ መሆን እንዳለበትም ተገልጿል። ማርበርግ እንደ ኮቪድ በአየር የሚተላለፍ ባይሆንም፥ከኮቪድ በበለጠ ህይወት የሚነጥቅ ነው ተብሏል። እንደ ወረርሽኙ ክብደት የሞት ምጣኔው ከ24 እስከ 88 በመቶ ይደርሳል። 33 ሰዎች ተመርምረው 6 ሰዎች ህመሙ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ሶስቱ ህይወታቸው ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ደግሞ በህይወት አሉ ተብሏል። ይህን መረጃ ያገኘነው ጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በማርበርግ በሽታ ምንነት ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ነው።
نمایش همه...
90🤔 12👍 6🤯 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MaburgVirus ዛሬ 5 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰው በማርበርግ ቫይረስ መያዙ ተገለጸ። የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 2 ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል። በዛሬው ዕለት 5 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተካሄደ ሲሆን፥ 2 ሰው በቫይረሱ መያዙንና 3 ሰዎች ደግሞ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል። በሽታው መከሰቱ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስካሁን 33 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን ቫንረሱ በ6 ሰዎች ላይ መገኘቱ በላብራቶሪ ተረጋግጧል። የጤና ሚኒስትሯ አሁን ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠው ሦስት ሰዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተገለጸ ሦስት ተጠርጣሪዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። 👉ማርበርግ ህክምና አለው? ህክምናው በአብዛኛው የሚያካትተው የሰውነት ፈሳሽ በግሉኮስ መተካት፣ በባለሙያ ክትትል ማድረግ እና ተጓዳኝ ችግሮችን ማከም ላይ ያተኩራል። እንዳስፈላጊነቱ የትኩሳት ማብረጃ እና የህመም ማስታገሻ መስጠት ይገባል። በጣም ደም መፍሰስ ላጋጠማቸው የደም ልገሳ ሊፈልጉ ይችላሉ። ከእነዚህ የህክምና ድጋፎች ባሻገር የሚሰጡ የጸረ-ቫይረስ ህክምናዎች የሉም። እስካሁን ለማርበርግ የተረጋገጠ እና ፍቃድ ያገኘ ጸረ-ቫይረስ መድሃኒት የለም። 👉ማርበርግ ክትባት አልተገኘለትም። 👉በምርምር ደረጃ ያሉ ጥቂት እጩ የማርበርግ ክትባቶች ጥናት እየተሰራባቸው እና እየበለጸጉ እንደሚገኝ የሚጠቅሱ መረጃዎች አሉ።
نمایش همه...
55👍 8😱 5
ት/ት ሚኒስቴር❗️ ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም! 📌ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡ በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡  ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡ ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡ በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡ በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡ ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡ ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡ ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡ በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡ በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል። የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡ ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
نمایش همه...
131👏 18😁 16👍 4👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
8
Photo unavailableShow in Telegram
ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን ሊቀጡ ነው ቀጪው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው!! ቢሮው ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው ያለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመመሪያው መሰረት #ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ ብሏል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታመነ ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል ብለውናል። ኃላፊው ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል ብለዋል። ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
نمایش همه...
56👏 13👍 5😁 3
የተቀናጣው የእራት ምሽት * የዋይት ሀውስን ቁልፍ ሰጡት አንተ የምንግዜውም ምርጥ ነህ ። ልጄ በጣም ያደንቅሃል። ዛሬ ዕርግጠኛ ነኝ ልጄ የበለጠ አባቱን ያከብራል ። CR-7 አንተ ለሁሉም ዓርዓያ የምትሆን የዓለማችን ምርጡ የምንግዜውም ኮኮብ ነህ ። እንኳን ወደ አሜሪካ በደህና መጣህ ። ይህ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የማድየራው ፈርጥ CR-7 ከሳውዲው ንጉስ ጋር በዋሽንግተን ነጩ ቤት ዋይት ሃውስ የነበረው ደማቅ አቀባበል ነው። ዓለምን እያነጋገረ ያለ የሁሉንም ትኩረት የሳበ የዓለማችን ዝነኞችን ያሰባሰበ ፖለቲካም እግር ኳስም ቢዝነስም የተዘየረበት የተቀናጣው የእራት ምሽት ነው። የሳውዲው ንጉስ መሃመድ ቢን ሰልማን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፖሩተጋላዊ የዓለማችን ኮኮብ ክርስትያኖ ሮናልዶ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢፋኒቶ ጨምሮ የቴስላው ቁጥር አንድ የዓለማችን ቢሊነየሩ ኤለን መስክ እንዲሁም በርካቶችን በአንድ ጠረጴዛ ያሰባሰበው ምሽት ነው ። ይህ በታታሪነት በድንቅ ተስጦኦና የማያባራ ሪከርድ ሰባሪ ብቃት CR-7 በተባለ የዘመናችን ወደር አልባ የእግር ኳስ የማይነጥፍ ብራንድ ውስጥ ተሟሽቶ የተዘየረው አይረሴው የነጩ ቤት ዋሽንግተን ዲሲ ውሎና ምሽት ነው። ይህ እግር ኳስ የ22 ተጨዋቾች ቅሪላ ማልፋት ለሚመሥላቸው ወገኖች ሁሉ እግር ኳስ የምድራችን ቁጥር አንዱ የዓለም ማህበረሰብን ድንበር አሻግሮ ሁሉን በአንድ ቋንቋ ያስተሳሰረው ታላቁ ፀጋ በረከት ስለ መሆኑ ዳግም ዘላዓለማዊ ማረጋገጫ የሰጠበት ታሪካዊው ቀንም ነው። (via :- Tribune sport)
نمایش همه...
83👍 14👎 4😁 3😱 2🥰 1🤔 1🤯 1
በሾላ ገበያ የሞቱ ዶሮዎችን በል’ተው ለገበያ ሊያቀርቡ ሲሉ ተያዙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከሰላም ፀጥታ ፅ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ በመሆን ባደረገዉ ድንገተኛ ኦኘሬሽን በሾላ ገበያ ህገወጥ የዶሮ እርድ ሲያከናዉኑ በነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ወስዷል። በተደረገው ክትትልና የተቀናጀ ኦፕሬሽን ግለሰቦቹ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ በነበረበት ሁኔታ የተያዙ ሲሆን በዚህም የታሸገ ዶሮ በቁጥር መቶ (100) ተበልቶ ለመታሸግ የተዘጋጀ አርባ ሁለት (42) ተይዟል። የሞቱ ዶሮዎችን ለህብረተሰቡ እና ለሆቴሎች ከመከፋፈላቸዉ በፊት እርምጃ መወሰዱን የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከር ጽ/ቤት አስታውቋል ። መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
نمایش همه...
38😱 11👏 6👎 3👍 1
ጥንቃቄ❗️#ማርበርግ_ቫይረስ #ሼር 📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንድን ነው? o የማርበርግ ቫይረስ  በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ነው። o በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል። 📌 የማርበርግ ቫይረስ ምልክቶች ምንድን ናቸው? 👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ሥር ደም መፍሰስ፤ 👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ 👉 ብርድ ብርድ ማለትና ራስ ምታት፤ 👉 የጡንቻና ጀርባ ህመም፤ 👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመምና ተቅማጥ፤ 👉 የምግብ ፍላጎት መቀነስና ትውከት 👉 ደረት፣ ጀርባና ሆድ ላይ ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ፤ 🔗ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከ2-9ቀናት ውስጥ የበሽታው ምልክቶች ይታያሉ። 📌 የማርበርግ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው? • በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም፣ ሽንት፣ እንባ ና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ግንኙነት፤ • በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች፣ እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣  መርፌና ሌሎች መገልገያዎች ጋር በሚኖር ንክኪ፤ • በቫይረሱ ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል። 📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው? o ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ፤ o ከታመመ ሰው ጋር ንክኪና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ተቋማት መሄድ፤ o ሞት በሚከሰትበት ወቅት አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀትና መቅበር፤ አላስፈላጊ ቀብር ሥነ-ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ። o ከታመመ ሰው ደምና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፤ o ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእንጅ ጓንት መጠቀም። o እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውኃ በአግባቡ መታጠብ።   T.me/ethio_mereja       ኢትዮ-መረጃ
نمایش همه...
63👍 12👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሴቶች መደፈራቸውንና ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል! ቢቢሲ ባሰባሰበው መረጃ ከሐምሌ 2015 እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ ከ8 ዓመት እስከ 65 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው አመለክቷል። ቢቢቢ በክልሉ ከሚገኙ 43 ጤና ጣቢያዎች እና ሕክምና ምንጮች ባገኘው መረጃዎች መሰረት ከሐምሌ 18/2015 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ 2,697 ሰዎች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል። ከእነዚህም ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው። ከተጎጂዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በደረሰባቸው ጥቃት በአባላዘር በሽታ ሲያዙ፤ በርካቶች ደግሞ ለእርግዝና እና ለከባድ የሥነ ልቦና ቀውስ ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ በርካታ የወሲባዊ ጥቃት ተጎጂዎች መገለልን በመፍራት፣ የአባላዘር በሽታ መያዛቸውን ወይም መፀነሳቸውን ላለማወቅ የተፈፀመባቸውን የመደፈር ጥቃት ሪፖርት ማድረግም ሆነ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት አይፈልጉም። የመድፈር ጥቃቶች በግጭቱ እየተሳተፉ ባሉት በሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች(በፋኖ እና በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች) እየተፈፀሙ ቢሆንም የጤና ባለሙያዎች ከፋኖ ታጣቂዎች በበለጠ የመንግሥት ወታደሮችን ማየታቸውን ተናግረዋል።(ምንጭ፣ቢቢሲ)
نمایش همه...
39😭 28🤯 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ያወጣው የሀገሪቱን የጉምሩክ ስርዓት ለማዘመን እና ከአለም አቀፍ መስፈርቶች በተለይም ከአለም ንግድ ድርጅት (WTO) ደረጃዎች ጋር ለማጣጣም ያለመ አዲስና ሁሉን አቀፍ የሆነ የጉምሩክ ዋጋ አተማመን መመሪያ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተገልጿል። አዲሱ መመሪያ ቁጥር 1080/2017 በገቢና ወጪ ዕቃዎች ላይ የሚጣለው ቀረጥና ታክስ የሚሰላበትን ዋጋ የሚወስንበትን ሥርዓት ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል። ይህን ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽኑ መመሪያው በሁሉም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ "ጥብቅ ዲስፕሊን" እንዲተገበር በህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም በላከው ደብዳቤው ትዕዛዝ ሰጥቷል። መመሪያው የዕቃዎችን የቀረጥ ዋጋ ለመወሰን በቅደም ተከተል ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን ስድስት ተዋረዳዊ ዘዴዎች አስቀምጧል። ዋነኛው ዘዴ የግብይት ዋጋ አተማመን ዘዴ (ለትክክለኛው ዕቃ የተከፈለው ወይም ሊከፈል የሚገባው ዋጋ) ነው። በአስመጪዎች ላይ የሚደረግ ጥብቅ ቁጥጥር ማጭበርበርንና የዋጋ ማሳነስን ለመከላከል፣ መመሪያው የተገለጸው የግብይት ዋጋ ውድቅ የሚሆንባቸውን ምክንያቶች በግልጽ አስቀምጧል። ከእነዚህም መካከል ትክክለኛ መረጃ አለማቅረብ፣ የሐሰት ሰነድ ማቅረብ ወይም ግዴታ የሆኑ ተጨማሪ ክፍያዎችን አለማካተት ይገኙበታል። የጉምሩክ ኮሚሽኑ ጥርጣሬ ካደረበት፣ አስመጪዎች ትክክለኛ የሕግ ማስረጃዎችን (እንደ ውልና በባንክ የተረጋገጠ ኢንቮይስ) በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። ይህ እርምጃ በሀገሪቱ የንግድ አስተዳደር ዘርፍ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማጠናከር ያለመ ትልቅ እርምጃ ሲሆን፣ አስመጪዎች ትክክለኛ መረጃን ብቻ እንዲያቀርቡ ግዳጅ ይጥልባቸዋል።(#capitalnews)
نمایش همه...
42👍 4