TIKVAH-ETHIOPIA
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
نمایش بیشتر1 574 943
مشترکین
+7524 ساعت
+6507 روز
+76130 روز
آرشیو پست ها
ሽንሺቾ ?
በከምባታ ዞን፣ በሽንሺቾ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ ዋና አስፓልት መንገድ ነገ ለሚካሄድ የሰርግ መልስ ፕሮግራም በድንኳን ተዘግቶ መዋሉን ፤ እስከ ምሽት ድረስም እንደዛው እንደነበር ፤ በዚህም ምክንያት በርካቶች መጉላላታቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
መንገዱ በሁለቱም በኩል ማለትም በመሄጃውም በመምጫውም በኩል ተዘግቶ ስለነበር ተሽከርካሪዎች ማለፍ ሳይችሉ እንደቀሩና እንደተጉላሉ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
አማራጭ መንገድ ተጠቅሞ ውስጥ ለውስጥ ሲሄድ የነበረ ጭድ የጫነ አይሱዙ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪክ ገመድ በመንካቱ መቃጠሉን አክለዋል።
መንገዱ በርካታ ተሽከርካሪዎች የሚተላለፉበት ነው ፣ አምቡላንስም ሰዎች ይዞ ያልፋል መንገዱ በመዘጋቱ የሚፈጠረው ችግር ብዙ ነው ይሄ እንዴት አይታሰብም ሲሉ ጠይቀዋል።
ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ምን አሉ ?
" እሁድ ታህሳስ 5 ለሚደረግ የመልስ ፕሮግራም ተብሎ ዋናዉ አስፓልት በድንኳን ከቅዳሜ ለሊት ጀምሮ ተዘግቷል።
ተለዋጭ ተብሎ በተዘጋጀዉ መንገድ እየሄደ ያለ ጭድ የጫና አይሱዙ መኪና ከመብራት ጋር ተገናኝቶ በተፈጠረ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የመኪናዉ ሹፌር መኪናዉን ነፃ ወደ ሆነ ቦታ በመንዳት ዘሎ የወጣ ሲሆን በሰዉ ሕይወት ላይ ጉዳት አልደረሰም።
ከዚህ ባለፈ የመንገዱን መዘጋት ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ተኩስም ነበር። አሁን ላይ አንደኛው ድንኳን ተነስቷል። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች በሰጡት ቃል እና በክስተቱ ዙሪያ የከተማው አመራሮች ምላሽ እና ማብራሪያ የሚሰጡ ከሆነ አዘጋጅቶ ያቀርባል።
@tikvahethiopia
2.22 MB
😡 1 031❤ 716😢 65😭 49🤔 33💔 21🙏 14😱 10👏 8🕊 7🥰 3
ኡጋንዳ ከኢትዮጵያ፣ ከሱማሊያ እና ከኤርትራ ወደ ሀገሯ ለሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች መብት መስጠት ማቆሟ ተነግሯል።
ይህን ተከትሎ ሪፊውጂስ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፣ ሀገሪቱ የስደተኛነት መብት መስጠት ማቆሟ " አሳሳቢ እርምጃ ነው " ሲል አውግዟል።
" በዜግነት ላይ ብቻ ተመስርቶ ጥገኝነትን መከልከል የዓለም አቀፍ የስደተኞች ሕግን የሚጥስ ነው። አዲሱ ገደብ እነዚህን ስደተኞች ሕጋዊ አጣብቂኝ ውስጥ በመክተት ለከፋ ብዝበዛና ጥቃት ይዳርጋቸዋል " ብሏል።
" ይህ ውሳኔ ኡጋንዳ ቀደም ሲል ስደተኞችን በመቀበል ያላት ኩሩ ልማድ የሚጻረር ነው " ሲል ገልጿል።
ድርጅቱ ኡጋንዳ የደረሰባት ከፍተኛ የእርዳታ ቅነሳ የጥገኝነት ሥርዓቷን ችግር ውስጥ መክተቱን አምኗል።
በተለይም ዩናይትድ ስቴትስ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ኡጋንዳ ለመላክ ስምምነት ብትፈርምም፣ የራሷን እርዳታ መቀነሷ ለችግሩ መባባስ ምክንያት መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል።
ለዓመታት ኡጋንዳን ሲያሞግሱ የቆዩ ለጋሽ መንግሥታት አሁን ቃላቸውን ለስደተኞችም ሆነ ለአስተናጋጅ ማኅበረሰቦች በሚሰጡት ተጨባጭ ድጋፍ በማረጋገጥ፣ ኡጋንዳ የገጠማትን የገንዘብ ችግር እንዲያቀልሉ ጥሪ ማቅረቡን #ካፒታል_ጋዜጣ ዘግቧል።
ኡጋንዳ በአሁን ሰዓት በርካታ የኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ስደተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች። በርካታ ኢትዮጵያውያንም እዛው ኡጋንዳ መቀመጫቸውን አድርገዋል።
ስደተኞች ኡጋንዳን አንድም ባላት መልካም የስደተኛ አቀባበል እንዲሁም ወደፊት ወደ ሌላ ሀገር ለመሸጋገር ይመርጧታል።
ከአሁን በኃላ ግን ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ የሚሄዱ ስተደኞችን ላለመቀበል/ መብት ለመንፈግ እንደወሰነች ተነግሯል።
@tikvahethiopia
❤ 553😭 161🤔 38🙏 18👏 16😡 12🥰 7💔 5😢 4🕊 3😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በማርበርግ ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ሪፖርት ተደርጓል።
በዛሬው ዕለት በማርበርግ ቫይረስ ሳቢያ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ዕለታዊ የምርመራ ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ይህም በማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎችን ቁጥር ወደ 9 ከፍ አድርጎታል።
39 ምርመራዎች ተከናውነው አዲስ የቫይረሱ ተጠቂ ባይመዘገብም ህክምና ላይ ከነበሩት ሁለት ታካሚዎች የአንዱ ህይወቱ ማለፉን ተጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
😢 345❤ 210😭 139🙏 27🕊 25💔 19😱 9🤔 7
" ለመደብደብ ይጋበዛሉ፣ መሳሪያ ይዘው ነው የሚያስፈራሩት፣ የመንግስት የጸጥታ አካላቶች ናቸው፣ ኬላ ብለው ገመድ በዘረጉበት ቦታ ላይ በርካታ መኪኖች ቆመዋል፣ ከርቀት ቦታ የመጣ አሽከርካሪ አማራጭ ስለሌለው እየከፈለ ነው የሚሔደው " - ሹፌሮች
➡️ " ይህን የወሰነው የወረዳው አስተዳደር ነው፣ ህጋዊ በሆነ መንገድ ደረሰኝ እየተቆረጠ ነው መዋጮ የሚከፍሉት፣ ከዚህ በፊትም ለ11 አመታት መዋጮ ስናስከፍል ነበር፣ የዘንድሮውም ለ12ኛ ጊዜ ነው " - የማሌ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ አሸከር ከተማ " ለዶኦሞ የዘመን መለወጫ በዓል የምናከብርበት ብር አምጡ " በማለት የመንግስት የጸጥታ አካላቶች መንገድ ላይ ገመድ በመዘርጋት ኬላ አዘጋጅተው ከአንድ አሽከርካሪ እስከ 2 ሺህ ብር ድረስ እያስከፈሉን ነው ሲሉ የተለያዩ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።
አሽከርካሪዎቹ " ለዘመን መለወጫ በዓል እንዴት ገንዘብ አዋጡ እንባላለን ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ላይ በዝርዝር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠ ሹፌር ምን አለ ?
" ከድርጅት የሙዝ ምርት ጭኜ ስወጣ መሽቶ ስለነበር አሸከር ከተማ የደረስኩት 10:00 ነው።
በቦታው ላይ የነበሩ የታጠቁ ሰዎች መንገድ ላይ ገመድ ዘርግተው የዘመን መለወጫ 1 ሺህ እና 2 ሺህ ክፈል አሉኝ።
ይህን አልከፍልም የጫንኩት ወደ ሶማሌ ላንድ እና ጅቡቲ ኤክስፖርት የሚደረግ በካርቶን የታሸገ ሙዝ ነው፣ ከድርጅቱ የተሰጠኝ ደብዳቤ አለ፣ በግሌ የማደርገው ነገር የለም፣ ምርቱን በአስቸኳይ ማድረስ አለብኝ ልቀቁኝ ብላቸውም ' አንሰማም ' በማለት ለ4 ስአት አስቁመው አሳድረውኛል።
በስአቱ ምርቱን ወደ አዲስ አበባ እንዳደርስ ለላከኝ ድርጅት ማሳወቅ አልቻልኩም፣ ምክንያቱም ማሳወቅ የምችለው ከ2 ስአት በኋላ ነው፣ ከጠዋቱ 2:00 ስአት አካባቢ ሲሆን ሙዙ ከሚበላሽ በማለት ከራሴ ከኪሴ 1 ሺህ ብር ከፍዬ ጉዞየን ቀጥያለሁ።
በስፍራው የነበሩ አካላቶች ሹፌሮችን ለመደብደብ ይጋበዛሉ፣ መሳሪያ ይዘው ነው የሚያስፈራሩት፣ የመንግስት የጸጥታ አካላቶች ናቸው፣ መንገድ ላይ ገመድ ወጥረው ነው እንደዚህ የሚያደርኑት። ኬላ ብለው ገመድ በዘረጉበት ቦታ ላይ በርካታ መኪኖች ቆመዋል፣ ከርቀት ቦታ የመጣ አሽከርካሪ አማራጭ ስለሌለው እየከፈለ ነው የሚሔደው፣ በዚያው አካባቢ ያሉት ደግሞ ቆመው ይከራከራሉ።
በሁሉም ቦታ ትብብር እንዲደረግልን ድርጅቱ የጻፈውን ደብዳቤ እንኳ ማየት አይፈልጉም፣ በየትኛውም ቦታ እስካሁን ኬላ ላይ አስቁመውኝ ተንገላትቼ አላውቅም፣ ኬላዎች እንዲነሱ ከተደረገ በኋላ ግን ዛሬ አንገላቱኝ፣ ለማን አቤት እንበል ?
መንግስት ኬላዎች እንዲነሱ አድርጓል። ስለዚህ ለምንድን ነው የምንከፍለው ? ብለን ስንጠይቃቸው ' ለዘመን መለወጫ መዋጮ አምጡ ነው ' የሚሉት። እኛ መንገደኛ ሹፌሮች ነን፣ መንገዱ የፌደራል ነው፣ የአካባቢው ነዋሪ አይደለንም፣ በዓሉ የሚመለከተው አካል ለምን አያዋጣም ? የቀን አበላችን 500 ብር ነው፣ እኛ በአንድ ኬላ 1000 ብር ከፍለን ምን ልንበላ ነው ? ስንላቸውም ' ምን አገባን ' ከማለት ውጪ ምላሽ አይይጡንም።
መንግስት በየቦታው ያሉ ኬላዎች እንዲነሱ አዝዞልን ደስ ብሎን አመስግነን ሳንጨርስ በድንገት በስውር የሚዘረጉ ገመዶች አሉ፣ የቅጣት ተመን የሌላቸው፣ ደስ እንዳላቸው የሚያስከፍሉ፣ ለልማት እንኳ ቢሆን ችግር የለውም፣ የዘመን መለወጫ አዋጡ ማለት ግን ከባድ ነው፣ የአካባቢው ባለስልጣናት በፍጥነት እልባት ሊያበጁለት ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማሌ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኮፒያን ትንብትን ስለ ጉዳዩ አነጋግሯል።
እሳቸውም " አሁን ላይ በማሌ ማህበረሰብ በየአመቱ ለሚከበረው የዶኦሞ የዘመን መለወጫ በዓል ዝግጅት እያደረግን ነው " ብለዋል።
በመሆኑም በዓሉን በማስመልከት የባለሁለት እግር አሽከርካሪዎች ከ300 እስከ 500 ብር እና መኪኖች ደግሞ ከ1 ሺህ እስከ 2 ሺህ ብር እንዲያዋጡ እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ለዘመን መለወጫ በዓል እንዴት ከአሽከርካሪ መዋጮ ይጠየቃል ? በምን አግባብ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳንላቸው ጥያቄ ምላሽ ያሉትን ሰጥተዋል።
ኃላፊው " ይህን የወሰነው የወረዳው አስተዳደር ነው፣ ህጋዊ በሆነ መንገድ ደረሰኝ እየተቆረጠ ነው መዋጮ የሚከፍሉት፣ ከዚህ በፊትም ለ11 አመታት መዋጮ ስናስከፍል ነበር፣ የዘንድሮውም ለ12ኛ ጊዜ ነው፣ የሚከፍሉት ትንሽ ብር ነው " ብለዋል።
አያይዘው " ይህ መዋጮ አዲስ ነገር አይደለም፣ ለዲሽታ ጊና በዓልም በጅንካ ከተማ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ሲዋጣ ነበር፣ ሁሉም አሽከርካሪ ይከፍላል፣ ይህን መንግስትም የወረዳውም አስተዳደር የሚያውቀው ጉዳይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
12.76 MB
26.31 MB
1.14 MB
9.26 MB
❤ 896😭 343😡 263🤔 31🙏 16😢 12🕊 10😱 7💔 7🥰 4
" ስልክ የተሰረቀባችሁ ግለሰቦች በአካል በመቅረብ ስልካችሁን ለይታችሁ ውሰዱ " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ውድ ዋጋ ያላቸው ስልኮች ላይ ትኩረት በማድረግ የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ከ30 አይፎን ስልኮችን ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:00 ሰዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም. ሲ 5 መቶ ቤቶች አካባቢ አንድ ግለሰብ የዋጋ ግምቱ 100 ሺ ብር የሚያወጣ ኤስ 23 አልትራ ሳምሰንግ ሞባይል እንደተቀሙ ለሲ. ኤም.ሲ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ፡፡
ፖሊስ ጣቢያው የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ክትትል ያደርጋል። ወንጀሉ ከተፈፀመበት ስፍራ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ በሁለተኛው ቀን የግል ተበዳይን ሞባይል ስልክ የቀሙትን ምስጋናው አለማየሁ፣ ሄኖክ ወርቁ እና ኢዮብ ወርቁን የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያውላል።
በቀጣይነት በተሰራ ምርመራን የማስፋት ተግባር በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 አያት ዞን አምስት ኮንዶሚኒየም 3ኛ ፎቅ ላይ ምስጋናው አለማየው የተባለው ተጠርጣሪ ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ የግል ተበዳይን ስልክ ጨምሮ 41 ስማርት ስልኮች ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊድ ከዚህ በፊት ስልክ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ስልካቸውን እንዲለዩ ጥሪ አስተላልፏል።
አያይዞም ባሰራጨው መልዕክት መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራት የተከራዮችን ማንነት የማጣራት ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝቧል፤ ግዴታቸው በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስቧል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
❤ 1 664👏 626🙏 98😱 44😭 29🤔 23🕊 21🥰 17😢 16😡 13💔 12
#Hawassa
አብራው ያደረችውን ሴት ያደሩበት አልጋ ክፍል ውስጥ ገድሎ ሊሰወር የሞከረ ተጠርጣሪ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋዎች ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ሽመልስ ብሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፥ በሀዋሳ ከተማ ባህል አደራሽ ክፍለ ከተማ አዳሬ ቀበሌ ልዩ ስፍራው " ምስክር ፔንስዬን " ተብሎ በሚጠራው ቦታ ባዳሶ አብደላ የተባለ ግለሰብ ቤተልሔም ዳንኤል ከተባለች ሴት ጋር አብሮ ለማደር በገቡበት አልጋ ቤት ውስጥ አንቆ በመግደል ለመሰወር ሲሞክር በሕብረተሰቡና በፖሊስ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።
ፖሊስ ባደረገዉ ምርመራና ማጣራት ግለሰቡ ሟቿን ከላይ ወደ ተጠቀሰዉ አልጋ ቤት ይዟት ከገባ በኋላ ለጊዜዉ በዉል ባልታወቀ ያለመግባባት አንገቷን በእጁ አንቆ ከገደላት በኋላ ከአከባቢው ሊያመልጥ ሲሞክር ጠቁ።ቋል።
ይህም ለዐቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገብ መቅረቡን የገለፁት ኢንስፔክተር ሽመልስ ጉዳዩን የተመለከተዉ የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ወንጀለኛውን በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
❤ 554😢 243😭 104😡 72🕊 23💔 20🙏 15🤔 14👏 9😱 4🥰 2
"በሰሞንኛው ጥቃት ብቻ ከ10 በላይ ንጹሐን ተገድለዋል፤ የቆሰሉም በርካቶች ናቸው" - የጋምቤላ ነዋሪዎች
"ከስድስት ሰዎች በላይ ህይወታቸው አልፏል፤ የቆሰሉም ከስድስትና ሰባት በላይ አሉ - የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክር ቤት አባል
ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ንጹሐን መገደላቸውን፣ የሰዎች እንቅስቃሴ መገደቡን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ በሰሞንኛው ጥቃት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ የቆሰሉትም በርካቶች ናቸው" ያሉ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል እየገለጹ ነው።
በተለይ አቦል ወረዳና ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢዎች "ንጹሐን ዜጎች እየተገደሉ" መሆኑን፣ ጥቃቱ ከዚህ ቀደምም የነበረ ሲሆን፣ በሰሞንኛው ሁነት ደግሞ "የጸጥታ አካላት ጭምር ሟችና ቆስለኛ" መሆናቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች ከስፍራው ወጥተዋል።
ግድያው የሚፈጸመው በተለይ ተሳፋሪዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ መንገድ ዳር በማድፈጥ በተሽከርካሪዎች ጭምር ሲሆን፣ የክልሉ ፓሊስ በበኩሉ፣ ተሳፋሪዎች ላይ ሞትና የመቁሰል ጥቃት መድረሱን ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወቃል።
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከቀናት በፊት፣ "በከተማችን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ከጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰው ከህዳር 30/2018 ዓ/ም ምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን" ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩን ይዞ ስለጥቃቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ የክልሉን ባለስጣናት የጠየቀ ሲሆን፣ የሰላምና ጸጥታ ቢሮው ፈቃደኛ አልሆነም። በስልክ የጠየቃቸው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ደግሞ፣ "በኋላ ደውሉ አሁን ስብሰባ እየመራሁ ነው። ከአንድ ሰዓት በኋላ ደውሉ" ቢሉም በድጋሚ ሲደወል ስልክ አያነሱም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ በሰሞንኛው ጥቃት "ንጹሐን ተገድለዋል፤ የጸጥታ አካላትም ተገድለዋል፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል፤ ምን ያክል ሰዎች ተገድለዋል? ሲል የጋምቤላ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ አስቲንን ጠይቋቸዋል።
የጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ?
"ከስድስት ሰዎች በላይ ህይወታቸው አልፏል፤ የቆሰሉም ከስድስትና ሰባት በላይ አሉ።
የተፈጠረውን ግጭት ግጭት ነው ብሎ ለማሰብ ትንሽ ያስቸግራል። ለምሳሌ ጋምቤላ ከተማ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ፤ አንድ ሰው ሁለት ሰዎች ላይ ጥይት ተኩሶ አንዱ ህይወቱ አልፎ አንዱ ቆስሏል።
ከዚያ በኋላ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ደግሞ በጋምቤላ ወረዳ ከላሬ ሲመጣ በነበረ መኪና ጥይት ተተኩሷል፤ እነማን እንደሆኑ አልታወቁም፤ ዳርና ዳር ጫካ ስለሆነ ከጫካ ወጥተው ነው ጥቃት የፈጸሙት። እዛም የተጎዱ ሰዎች አሉ። አንድ ቡድን ከሌላ ቡድን ጋር የመጋጨት አይነት ነገር ነው፤ ይሄ ግን ጥቃት ነው። የተወሰኑ ግለሰቦች በሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙበት ነው።
ግጭት የሚመስለው ሰው ተደናግጦ አንዱ ወደራሱ አካባቢ ሌላውም ወደራሱ አካባቢ ይሸሻል። ይህ ነው ግጭት ተብሎ የተወሰደው እንጅ በግለሰብ ደረጃ የተፈጸሙ ጥቃቶች ናቸው ያሉት።
ጋምቤላ ወረዳ በተፈጸመው የመኪና ጥቃት የተጎዱት ሦስት ሰዎች ናቸው። ወረዳው ላይ የተወሰኑት ነዋሪዎች "ሆ" ተብለው ተነስተው ወደ አመራሮች ወዳሉበት ግቢ ሊገቡ ሲሉ ፓሊስ ባደረገው መከላከል፤ አንድ የፌደራል ፓሊስ ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ሌላ ፓሊስም ቆስሏል። ከማህበረሰቡም አንድ ሰው ህይወቱ አልፏል። አሁን ተረጋግቷል" ብለዋል።
በሰሞንኛው ጥቃት የሟቾች ቁጥር " ከ10 በላይ" እንደሚሆን፣ ከዚህ በፊት የተገደሉት ደግሞ "ከ40 እንደሚበልጡ " ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፤ እርስዎ ደግሞ የሰሞኑ ሟቾች " ከ6 በላይ" ናቸው ብለዋል፤ በትክክል የሟቾች ቁጥር ስንት ነው? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
እሳቸውም፣ " የሟቾቹን ቁጥር በትክክል መረጃ መውሰድ አለብኝ፣ አሁን ካልኩት በላይ ሊሆን ይችላል የሰማሁትና የተነገረኝን ነው የገለጽኩት። ምክንያቱም የቆሰሉም አሉ፤ ቆስለው የሞቱ አሉ፣ ስለዚህ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል። ከ10 በላይ ሊሆኑ ይችላሉ " ብለዋል።
" 'ከ40 በላይ ሰዎች ሞተዋል' የሚባለው፣ ሰዎች ተጣልተው አንዱ አንዱን ሊገድል ይችላል። ይሄ የቆየው የብሄር አስተሳሰብ ወደ ቡድን ይወሰዳል። ነገሩን በጣም ለማጋጋል የሞቱ ሰዎችን ቆጠራ ይጀምራሉ፣ ይሄን የሚያደርጉት ቅስቀሳ ለማድረግ ነው። ችግሩ እንዲቀጥል፣ እንዳይረጋጋ አረቄ ቤት የሞተውን ሁሉ ይቆጥራሉ " ሲሉም አክለዋል።
ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲያስረዱም፣ " የማረጋጋት ሥራ እየሰራን ነው ያለነው። ወንጀል የፈጸመ በግሉ እንዲጠየቅ፣ የህዝብ ውይይት እያደረግን ነው። ሥራዎች በነበሩበት መንገድ እንዲቀጥሉ፣ ተቋማት ወደነበሩበት ሥራ እንዲገቡና አካባቢው በሙሉ የተረጋጋ እንዲሆን እየሰራን ነው " ብለዋል።
የክልሉ መንግስት በበኩሉ፦
የክልሉ መንግስት፣ ትላንት በጋምቤላ ከተማ አመራሮችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሰሞንኛው ጥቃት ማብራሪያ የጠየቃቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስብሰባ መቀጠመጣቸውን ከጠዋት ጀምረው ሲገልጹ ቆይተዋል።
የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ " ሰሞኑን በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው " የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በመድረኩ መናገራቸውን ይፋ አድርጓል።
" ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር የማዋል ስራ " እንደሚቀጥል መናገራቸውን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል። (ጉዳዩን ተከታትለን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 601😭 138😡 15😢 14🕊 14💔 10🙏 9😱 6👏 3🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
#MPESASafaricom
⏳💰የመጨረሻው የበሽ ዕጣ ሊወጣ 2ቀን ብቻ ቀረው! የቀሩት ሚሊየነሮች እነማን ይሆኑ? ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ፤ ሚሊየነር የመሆን እድሎን ያስፉ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን: https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#furtheraheadtogether
#Besh
❤ 144😢 7😡 5😭 2🥰 1
ከዘጠኝ ቀናት ቆይታ በኋላ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው መገኘቱን ሪፖርት ተደርጓል።
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በተደረጉ ምርመራዎች ምንም አይነት አዲስ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዘ ሰው ሪፖርት ሳይደረግ ከቆየ በኋላ በዛሬው ዕለት አንድ ሰው የማርበርግ ቫይረስ ተጠቂ ሆኖ መገኘቱን ዕለታዊ የምርመራ ሪፖርቱ ጠቁሟል።
የጤና ሚኒስቴር በጂንካ ከተማ የተከሰተው ወረርሽኝ የማርበርግ ቫይረስ ሆኖ መገኘቱን ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ያወጀው ህዳር 5/2018 ዓም በሰጠው መግለጫ ነበር።
ወረርሽኙ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን የመመርመር፣ የመለየት እና የማከም ስራዎች እየተሰሩ የሚገኝ ሲሆን በየዕለቱ በሚከናወኑ ምርመራዎች አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ፣ ህይወታቸው ያለፈ፣ ያገገሙ እንዲሁም በህክምና ላይ የሚገኙ ታካሚዎችም ይፋ እየተደረጉ ይገኛል።
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በርካታ ምርመራዎች ቢደረጉም ምንም አይነት የማርበርግ ቫይረስ ተጠቂ ሳይገኝ ቆይቶ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት አንድ ሰው የቫይረሱ ተጠቂ ሆኖ መገኘቱን ዕለታዊ የምርመራ ሪፖርቱ ያሳያል።
በህዳር 18/2018 ዓም በቫይረሱ ሳቢያ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ከተጠቆመ ወዲህ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ስለመኖሩ የተገለጸው ህዳር 23/2018 ዓም ነበር።
በዕለቱ 221 ምርመራዎች ተከናውነው አንድ ሰው ላይ ቫይረሱ መገኘቱን ከተገለጸ ወዲህ ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይመዘገብ ቆይቷል።
በዛሬው ዕለት በተከናወኑ 56 ምርመራዎች ውስጥ አንድ ሰው ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ያመለክታል።
በአጠቃላይ እስካሁን 1765 ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን በ 14 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።
በቫይረሱ ሳቢያ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 4 ሰዎች ደግሞ አገግመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀል ችለዋል።
በአሁኑ ሰአት ህክምና በመከታተል ላይ የሚገኙት 2 ታካሚዎች ናቸው።
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ምንም አይነት አዲስ የማርበርግ ቫይረስ ተጠቂ ሪፖርት አለመደረጉን ተከትሎ ወረርሽኙ ጠፍቷል የሚሉ ሳይንሳዊ ያልሆኑ አስተያየቶች ሲዘዋወሩ ነበር።
በዛሬው ዕለት በተከናወነ ምርመራ አዲስ የቫይረሱ ተጠቂ መገኘቱ ወረርሽኙ አሁንም ስጋት መሆኑን የሚያመላክት ከመሆኑ በላይ ስለወረርሽኙ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተላለፉ የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀጠል እንዳለባቸው ያመላከተ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 1 404😭 302🙏 84💔 45🤔 30😱 26😢 25👏 20🥰 18🕊 17😡 17
" በሀገሬ ለመቆየት ህጋዊ መሰረት የሌላችሁ የኢትዮጵያ ዜጎች በ60 ቀናት ከሀገሬ ውጡ " - አሜሪካ
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰጥታ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት አንስታለች።
የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም ለኢትዮጵያ ተሰጥቶ የነበረው የጊዜያዊ ከለላ መብት መነሳቱን አስታውቀዋል።
አሜሪካ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ወደ ሃገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎች ጊዜያዊ ከለላ( Temporary protected status) ትሰጥ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያም ይኸው መብት ነበራት።
አሜሪካ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሃገሯ የሚኖሩ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ጦርነትን ጨምሮ በአንዳንድ ምክንያቶች ወደመጡበት ሃገር መመለስ ለማይችሉ ሰዎች ይህንን ከለላ መስጠት ጀምራ ነበር።
ይህ ከለላ የሚሰጣቸው ዜጎችም የሃገራቸው ሁኔታ እስኪሻሻል በአሜሪካ የመኖርና የመስራት መብት ሲሰጣቸው ከአሜሪካ ከመባረር ይጠበቁ ነበር።
አሜሪካ" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች ደህንነት ላይ ስጋት አይፈጥርም" ያለች ሲሆን በዚህም የተነሳ ይኸው ከለላ መነሳቱን አስታውቃለች።
አሜሪካ ሌሎች በአሜሪካ ለመቆየት ህጋዊ መሰረት ካላቸው ኢትዮጵያውያን ውጪ የኢትዮጵያ ዜጎች በ60 ቀናት ከሃገሯ እንዲወጡ አሳስባለች።
ቀድመው ከአሜሪካ ለሚወጡ የትኬት ወጪያቸው እንደሚሸፈን፣ የ1000 ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥና ለወደፊቱ ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድል እንደሚኖራቸው ገልፃለች።
ከፈረንጆቹ የካቲት 13 በኋላ ከለላው እንደሚያበቃ ገልፃ ያለ ከለላው በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደምታስር እና ከሃገሯ እንደምታባርር አስጠንቅቃለች።
አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተመሳሳይ ከለላ የነበራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜጎችን መብት አስንታለች።
Via @tikvahethmagazine
❤ 1 400😭 756👏 104😡 88💔 68😱 46😢 42🤔 35🙏 26🕊 20🥰 14
#GlobalBank
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በብሔራዊ ባንክ የተጠየቀውን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል በቀድሞ በማሟላት ወደ 5 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልፀዋል። ካለፈው ጋር ሲነፃፀርም 102% እድገት አሳይቷል።
ባንኩ በዚህ ዓመት 7.53 ቢሊዮን ብር አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ሰብስቦ አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘቡን መጠን 25.75 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፣ ይህም 41% እድገት ኣይቷል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከዓለም አቀፍ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ጋር ተዳምሮ በሀገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ሁኔታው አለመረጋጋት ያሳየ ቢሆንም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ፣ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ 1.17 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል፡፡
በዲጂታል አገልግሎት ዘርፍ ባንኩ በሞባይል፣ በኢንተርኔት እና በUSSD አገልግሎት በመስጠት 636,000 ተጠቃሚዎችን አገልግሏል።
ባንኩ፥ ከካቻ ፋይናንሺያል ጋር በመተባበር የዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን በኢንሹራንስ ዘርፍ የመጀመሪያው የኢንሹራንስ አረቦን ብድር አገልግሎት ጀምሯል።
በቅርንጫፍ ስፋትም ባንኩ በዚህ ዓመት 12 አዳዲስ ቅርንጫፎች በመከፈት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 237 አድርሷል በፕሪሚየም ቅርንጫፎቹ በስታዲየም እና በሜክሲኮ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።
ባንኩ፥ በ2025 ዓ.ም በአፍሪካ ባንክና ኢንሹራንስ አዋርድ ላይ የአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ሽልማት እና ከኢንተርናሽናል ስትራቴጂክ አሊያንስ ማዕከል የዲጂታል ፈጠራ እና ልህቀት ሽልማት አግኝቷል።
ባንኩ ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም 13ኛ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ያካሂዷል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ – “ለጋራ ስኬታችን”
❤ 493👏 36😡 16🙏 12😭 11🤔 8😢 7🕊 6🥰 4
" ከነገ ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት፤ መንገድ የዘጋችሁበትን አጥር አንሱ ፤ መንገዱንም ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን " - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
በአዲስ አበባ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ አካላት ከነገ ጀምሮ በ7 ቀናት ያጠሩትን አጥር እንዲያነሱ ማሳሰቢያ ተላለፈ።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ በህገ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች ታጥረው የተዘጉ መሆናቸውን አመልክቷል።
" ድርጊቱ የህብረተሰቡን በመንገድ ሀብት የመጠቀም መብት እየተጋፋ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ የትራፊክ እንቅስቃሴው እንዲስተጓጎል አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል " ብሏል።
በመሆኑም፤ በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ አካላት በሙሉ ከነገ ቅዳሜ ታህሳስ 4 ቀን 2018 ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት፤ መንገድ የዘጉበትን አጥር እንዲያነሱና መንገዱን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል።
በተጠቀሰው የጊዜ ደገብ ውስጥ አጥር የማያነሱ አካላትን በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ አስጠንቅቋል።
ይህ ጉዳይ በበርካታ ሰዎች ዘንድ ጥያቄ የሚነሳበት ነው።
የዛሬ 5 ዓመት መሰል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ የተለያዩ ሰፈሮች ያሉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የዘጉ አጥሮች እንዲነሱ የማድረግ ስራ ተጀምሮ እስከመጨረሻው ድርሰ ሁሉም ሰፈር ሳይተገበር ተቀዛቅዞ እንደቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስታውሳል።
በተለያዩ ሰፈሮች ውስጥ ለውስጥ በር ያላቸው አጥር ያጠሩ አካላት ፦
- ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ የማድረግ፤
- ጥበቃዎችን በማስቆም ክልከላ የማድረግ፤
- ትንሽ ሲመሽ በሩን የመዝጋት፤
- የተሽከርካሪ እና ሰው መተላለፊ እንዳይኖር የማድረግ በአጠቃላይ የህዝብን መንገድ እንደግል ርስት ይጠቀሙታል የሚሉ ቅሬታዎች ይነሳሉ።
ከዚህ ባለፈ ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ የሚያደርጉ አስቸጋሪ የሆኑ ግዙፍ የኮንክሪት የፍጥነት መገደቢያ የተደረገባቸውም ሰፈሮች ብዙ ናቸው።
" የህዝብ መገልገያ የሆኑ መንገዶችን አጥረው ለግል / ለሰፈርተኛ አገልግሎት ብቻ አውለዋል " የተባሉ አካላት ከነገ አንስቶ በ7 ቀን ያጠሩትን አጥር እንዲያነሱ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የፌደራል ግብር ከፋዮች በኮቴ ክፍያ፣ ነጋዴዎች ደግሞ በግብር ሰብሳቢዎች ስነ ምግባር ጉድለት መማረራቸው ዛሬ በነበረ የፓርላማ ውሎ ተነስቷል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ የኬላ ጉዳይ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ መቆየቱን፤ እስካሁን ግን መፈታት እንዳልተቻለ ተናግሯል፡፡
የኮቴ ክፍያና የገቢ ሰብሳቢ ሰራተኞች ስነ ምግባር ጉዳይ ለህዝብ ተወካዬዎች ምክር ቤት እና ሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረቡን የፕላን ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግሮ፤ ለዚህም ማብራሪያ እንዲሰጠው የገቢዎች ሚኒስቴርን ጠይቋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ይህን የጠየቀው ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የገቢዎችን ሚኒስቴርን የ4 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርትን ባደመጠበት ወቅት ነው፡፡
የቋሚ ኮሚቴውን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የገቢ ዘርፍ ንዑስ ሰብሳቢ አቶ ደበበ ምን አሉ ?
በክልሎች የማዘጋጃ ቤቶች በገቢ ስም ሀገር አቋራጭ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የተቋቋሙ ኬላዎች ለንግድ ስርዓቱ እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ህገ ወጥ ኬላዎች፤ ግብር ከፋዬች ምርትና ግብዓት በሚያጓጉዙበት ወቅት የኮቴ ክፍያ እና ሌሎች ስያሜዎችን በመስጠት አንዳንድ ጊዜ ተሸከርካሪው በያዘው ምርት መጠን በማባዛት እንዲከፍሉ መገደዳቸውን አስረድተዋል፡፡
ይህም ለተደራራቢ ግብር ስለዳረጋቸው ቅሬታችውን ለምክር ቤቱ እና ለሚመለከታቸው አካለት ማቅረባቸውን አስታውሰው፤ ለምን ችግሩን መፍታት እንዳልተቻ ጠይቀዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ምን አሉ ?
የኬላ ጉዳይ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመው፤ አስካሁን ግን መፈታት እንዳልተቻለ አስረድተዋል፡፡
የኮቴ ክፍያ የፌደራል ግብር ከፋዬችን ስራ እና ግብይት እንደሚረብሽ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን እንደሚያቀጨጭ የተወያየንበት ጉዳይ ቢሆንም ችግሩን ማስቀረት አልተቻለም ብለዋል።
የጭነት ተሽከርካሪዎች ለሚያገኙት የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በመነሻቸው እና መዳረሻቸው ላይ ብቻ እንዲከፍሉ ከስምምነት ቢደረስም ከህግ ውጭ በየከተሞች በጫኑበት ልክ እየተሰላ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡
የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ምን አሉ ?
" ጉዳዩን የማያውቀው የስራ ሃላፊም ሆነ የመንግስት ተቋም እንደሌለ አስረድተው ችግሩን ለመፍታት ግን ፍላጎት የለም " ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ምላሽ የጠየቀበት ጉዳይ በገቢ ስብሳቢ ባለሙያዎች ስነ ምግባር ጉድለት መማረርን የተመለከተ ነው፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ከሰራተኛው የስነ ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ በተለይም ፦
- በኦዲት፣
- በክትትል፣
- በቁጥጥር ምክንያት ከፍተኛ ምሬት ከነጋዴዎች እንደሚነሳ አስታውሶ ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ እንዳለ ጠይቋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር፤ የስራተኞችን የስነ ምግባር ጉድለት ሊያስቀር እና ችግሩንም ለማቅለል የሚረዳ አዲስ የኦዲት መመርያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን ተናግሯል፡፡
በለፉት አራት ወራት ከ170 በላይ በለሙያዎች ላይ የስነ ምግባር እርምጃ እንደተወሰዳቸው የተናገሩት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስተር አይናለም ንጉሴ ከዚህ ውስጥ 10ሩ ከስራ ተባረዋል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ ችግሩን ለማቃለል ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ አሰራር መዘርጋት መጀመሩን አብራርተዋል፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
❤ 639👏 51😭 18🕊 11😢 7🥰 5😱 5
" ደንበኞች በአካል ሳይገኙ አካውንት መክፈት የሚያስችላቸው ስርአት የፋይናስ ተቋማት ሲስተሙ እስካላቸው ድረስ ተፈቅዷል " - የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም
ከህዳር 16 ፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እና በሌሎች 26 የክልል ከተሞች የማይክሮ ፋይናንስ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰጠው መመሪያ መሰረት መሆኑን አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ በማይክሮ ፋይናንስ ዘርፍ ደንበኞች በአካል ሳይገኙ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት (Digital Remote Customer Onboarding) በፋይዳ መታወቂያ መፈቀዱም ተገልጿል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ሳሚናስ ሰይፉ " አንድ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ይህንን ሲስተም ዘርግቼ በአፕልኬሽንም ሆነ በሌላ አማራጮች ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አካውንት እንዲከፍቱ ማድረግ እችላለሁ ቢል ከእዚህ ቀደም የብሔራዊ ባንክ ይህንን ፈቃድ ባለመስጠቱ አይቻልም ነበር " ብለዋል።
አሁን ፋይዳ እንደ አንድ አስቻይ የመተማመኛ ማዕቀፍ መሆን በመቻሉ ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ባንክን ጨምሮ ሪሞት ኦንቦርዲንግ(ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አካውንት መክፈት የሚያስችላቸው ስርአት) ሲስተሙ እስካላቸው ድረስ መፈቀዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳሚናስ ሰይፉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ዝርዝር ሃሳብ ምን አሉ ?
" ፋይናንሻል ሴክተሩ ላይ እንደሚታወቀው አካውንት ሲከፈት ፋይዳን አስገዳጅ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል።
ስራው ሁሉም ጋር መጥራት ስላለበት እና የሚቀር መኖር ስለሌለበት ፋይዳን አስገዳጅ የማድረጉ ስራ ይቀጥላል ፣ አሁን ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አዲስ አካውንት ለመክፈት ፋይዳ አስገዳጅ ወደሆነበት አሰራር ገብተዋል ወደ ሌሎችም ፋይናንሻል መስኮች መግባቱ አይቀርም።
ከህዳር 16/2018 ዓ/ም ጀምሮ አዲስ አበባን ጨምሮ የኢትዮጵያ 26 ከተሞች ላይ ሙሉ በሙሉ አዲስ ማይክሮ ፋይናንስ ላይ የሚከፈቱ አካውንቶች በፋይዳ ብቻ ሆነዋል።
በተጨማሪ እስከዛሬ ማይክሮ ፋይናንሶች ላይ Customer Remote Onboarding አገልግሎት የለም ነበር ፣ይህ ማለት አንድ ሰው አካውንት ሲከፍት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ቅርንጫፎች እየሄደ ነበር አካውንት የሚከፍተው ፣አሁን ግን ፋይዳ በመምጣቱ ተቋማቱ ሲስተሙን ከዘረጉ ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ ሆነው ደንበኞች አካውንት እንዲከፍቱ ማድረግ ይችላሉ።
አንድ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ይህንን ሲስተም ዘርግቼ በአፕልኬሽንም ሆነ በሌላ አማራጮች ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አካውንት እንዲከፍቱ ማድረግ እችላለሁ ቢል ከእዚህ ቀደም የብሔራዊ ባንክ ይህንን ፈቃድ ባለመስጠቱ አይቻልም ነበር።
የማይቻለው አመቺ እና አስቻይ ሁኔታዎች የሉም ተብሎ ታስቦ ስለነበር ነው ፣አሁን ፋይዳ እንደ አንድ አስቻይ የመተማመኛ ማዕቀፍ መሆን በመቻሉ ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ባንክን ጨምሮ ሪሞት ኦንቦርዲንግ (ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አካውንት መክፈት የሚያስችላቸው ስርአት) ሲስተሙ እስካላቸው ድረስ ተፈቅዷል።
ይህ ግን እንደየተቋማቱ አቅም ይወሰናል ለምሳሌ፦ አንድ ባንክ ወይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ይህንን ሲስተም ካልዘረጋ አሁንም የደንበኞች አካውንት በቅርንጫፍ ሊያስከፍት ይችላል፣ እችላለሁ አቅሙ አለኝ ወይም ወደ ፊት ይህንን ሲስተም እዘረጋለሁ ለሚል ግን ፕላትፎርሙ ተፈቅዷል" ብለዋል።
(የማይክሮ ፋይናንስ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ የተደረገባቸው ክልል ከተሞችን ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
Photo unavailableShow in Telegram
#DW : ዶቼ ቨለ ሬድዮ በዘላቂነት ታገዱብኝ ስላላቸው ሁለት ዘጋቢዎች በተመለከተ " ያለምንም ተጨባጭ ማብራሪያ ስራቸውን እንዲያቆሙ መደረጉ ተቀባይነት የለውም " ሲል ገልጿል።
" ውሳኔውን እቃወማለሁ " ብሏል።
ዶይቸ ቬለ፥ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን (EMA) በትግራይ እና አማራ ክልሎች ውስጥ ሲዘግቡ የነበሩ ወኪሎቹን እስከወዲያኛው በቋሚነት ማገዱን አመልክቷል።
" ለእግዱ ግን ተጨባጭ ምክንያት አልቀረበልኝም " ሲል ገልጿል።
ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉንም ማለትም ዘጠኝ ዘጋቢዎች በጊዜያዊነት የታገዱ ሲሆን ሰባቱ በዚህ ሳምንት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ እንደተፈቀደላቸው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ አሳውቋል።
ዶቼ ቨለ በጀርመን ሀገር መቀመጫውን ያደረገ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ሲሆን በየዕለቱ የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት እያቀረበ ረጅም አመታት አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ ባሉት ወኪሎቹ የአማርኛ ዘገባዎችን ለአድማጮቹ ያደርሳል።
@tikvahethiopia
❤ 259🤔 36😡 13😢 8🙏 6🥰 1
#IGAD #Eritrea
ኤርትራ፣ " ህጋዊ ማንነቱን እና ስልጣኑን በአግባቡ አልተረዳም ፤ ስትራቴጂካዊ ጥቅም ማረጋገጥ አልቻለም ፤ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስፈን አስተዋጽኦ አላደረገም " በማለት የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ን ለቃ ወጥታለች።
ኢጋድ ኤርትራ ከአባልነት መውጣቷን በተመለከተ በሰጠው ቃል ፤ " ተጨባጭ የሆኑ ተቋማዊ ወይም ፖሊሲ ለውጦች ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ምክረ ሃሳብ ሳታቀርብ ለመውጣት መወሰኗ አሳዝኖኛል " ብሏል።
ዋና መቀመጫውን ጅቡቲ ያደረገውን ይህንን ድርጅት ፦
- ኢትዮጵያ፣
- ጂቡቲ፣
- ኬንያ፣
- ሶማሊያ፣
- ሱዳን እና ኡጋንዳ የመሠረቱ ሲሆን ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን በኋላ ላይ ነበር የተቀላቀሉት።
በኃላም ኤርትራ ለረጅም ዓመታት ከድርጅቱ ራሷን አግልላ ቆይታ ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ወደ ኢጋድ የተመለሰችው። አሁን ዳግም ለቃ ወጥታለች። #BBC
@tikvahethiopia
Photo unavailableShow in Telegram
www.desktutorial.com
በኢትዮጲያ የመጀመሪያ የሆነዉ በኦንላየን አስተማሪዎችና ተማሪዎችን (ከ 1ኛ - 12ኛ ክፍል) የሚያገናኝ የጥናት ፕላትፎርምን ይቀላቀሉ፡፡
መምህራን እና ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ጥናት የሚያካሄዱብት፤ ከ 1200+ መምህራን የሚገኙብት፡፡
Desktutorial.com ይጎብኙ በቀላሉ አስጠኝ ይቅጠሩ፡፡ ለ6ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሃገር አቀፍ ፈተናዎች ማዘጋጃ ጥናት ጀምረናል፡፡
How it works:
Sign up → choose a tutor → join your virtual class (whiteboard, video, audio, quizzes, and more) → recording is saved automatically.
Sign up now: www.desktutorial.com
Email: info@desktutorialsolutions.com
❤ 124🕊 7😢 6🙏 5👏 2😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቴሌ ብር ሱፐርአፕ
ስጦታው ጨምሯል!
ቴሌብር ሱፐርአፕ አውርደን ስንጠቀም 100 ሜ.ባ የነበረው ስጦታ ወደ 500 ሜ.ባ ከፍ ብሏል!
default pin ስንቀይር የ15 ብር ስጦታ፤ ከ100 ብር በታች አየር ሰዓት ስንሞላ 15% ስጦታ፤ 100 ብር እና ከዚያ በላይ አየር ሰዓት ስንሞላ 25% ምርቃት፤ በቴሌብር ጥቅል ስንሞላ 10% ተጨማሪ ወደ ስልካችን በቀጥታ ይገባል!
በቴሌብር ስንመረቅ እንዲህ ነን!
*127# ደውለን ወይም ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
❤ 203😡 12🙏 8🥰 1😱 1
#SocialMedia🚫
በአውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ተደረገ።
ሀገሪቱ እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ሬዲት ባሉ መድረኮች ላይ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዳይኖራቸው የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አድርጋለች።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ይህንን አዲስ ህግ ካላከበሩ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡
የሃገሪቱ መንግስት እገዳው ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው ብሏል።
ህጉ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች በቀጥታ እንዲወጡ/እንዲወገዱ ተደርገዋል።
አውስትራሊያ ውስጥ የትኞቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሕጉን እንዲተገብሩ ይገደዳሉ ?
እንደ:-
- ቲክቶክ፣
- ዩትዩብ፣
- ኢንስታግራም፣
- ፌስቡክ፣
- ስናፕቻት፣
- ሬዲት፣
- ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር)፣
- ትዊች፣
- ኪክ፣
- ትሬድስ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች አገልግሎት እንዳያገኙ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡
ዋትስአፕ ፣ ሜሴንጀር፣ የኢሜል አገልግሎቶች ፣ የኦንላይን ላይ ጨዋታዎች እና የተለያዩ ትምህርታዊ መሳሪያዎች ከእገዳው ነፃ ሆነዋል፡፡
የእገዳው ግቡ ምንድነው?
- ልጆችን ከሳይበር ጥቃት ፣ ማዋረድ ፣ ከክፉ ሃሳቦች ፣ ስድብ መከላከል፡፡
- የልጆችን የአእምሮ ጤና መጠበቅ፡፡
እገዳው እንዴት ይሰራል?
መተግበሪያዎቹ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ለምሳሌ ፡- የፊት ዕድሜ ግምት ፣ የዶክመንት ማጣራት ፣ ሌሎች ምክንያታዊ የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ (ከ16 ዓመት በታች ልጆች አካውንት እንዳይከፍቱ ያላቸውንም እንዳይጠቀሙ)።
በእርግጥም ኩባንያዎቹ ህጉን ተግባራዊ ያደርጋሉ?
ትልልቆቹ ኩባንያዎች ህጉን ለመተግበር ተስማምተዋል። እንደ ሜታ (ፌስቡክ ፣ ኢንስታግረም እና ትሬድስ ) እንዲሁም ቲክቶክ ተጠቃሚዎችን ማሳወቅ ፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን አካውንት ማስወገድ ጀምረዋል፡፡
ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር ) በይፋ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አልገለፀም ፤ ነገር ግን ኩባንያው ህጉን የግድ ተግባራዊ እንዲያደርግ በመንግስት በዝርዝር ከተቀመጡት የማህበራዊ ሚዲካ ኩባንያዎች መካከል ነው።
ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ እና ማሌዥያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት መንግስታት የአውስትራሊያን አካሄድ ለመተግበር እያጤኑ ነው።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በህግ የከለከለች ቀዳሚ ሀገራ ሆናለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው ያሰባሰበው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#SocialMedia🚫
በአውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ተደረገ።
ሀገሪቱ እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ሬዲት ባሉ መድረኮች ላይ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዳይኖራቸው የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አድርጋለች።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ይህንን አዲስ ህግ ካላከበሩ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡
የሃገሪቱ መንግስት እገዳው ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው ብሏል።
ህጉ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች በቀጥታ እንዲወጡ/እንዲወገዱ ተደርገዋል።
አውስትራሊያ ውስጥ የትኞቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሕጉን እንዲተገብሩ ይገደዳሉ ?
እንደ:-
- ቲክቶክ፣
- ዩትዩብ፣
- ኢንስታግራም፣
- ፌስቡክ፣
- ስናፕቻት፣
- ሬዲት፣
- ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር)፣
- ትዊች፣
- ኪክ፣
- ትሬድስ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች አገልግሎት እንዳያገኙ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡
ዋትስአፕ ፣ ሜሴንጀር፣ የኢሜል አገልግሎቶች ፣ የኦንላይን ላይ ጨዋታዎች እና የተለያዩ ትምህርታዊ መሳሪያዎች ከእገዳው ነፃ ሆነዋል፡፡
የእገዳው ግቡ ምንድነው?
- ልጆችን ከሳይበር ጥቃት ፣ ማዋረድ ፣ ከክፉ ሃሳቦች ፣ ስድብ መከላከል፡፡
- የልጆችን የአእምሮ ጤና መጠበቅ፡፡
እገዳው እንዴት ይሰራል?
መተግበሪያዎቹ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ለምሳሌ ፡- የፊት ዕድሜ ግምት ፣ የዶክመንት ማጣራት ፣ ሌሎች ምክንያታዊ የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ (ከ16 ዓመት በታች ልጆች አካውንት እንዳይከፍቱ ያላቸውንም እንዳይጠቀሙ)።
በእርግጥም ኩባንያዎቹ ህጉን ተግባራዊ ያደርጋሉ?
ትልልቆቹ ኩባንያዎች ህጉን ለመተግበር ተስማምተዋል። እንደ ሜታ (ፌስቡክ ፣ ኢንስታግረም እና ትሬድስ ) እንዲሁም ቲክቶክ ተጠቃሚዎችን ማሳወቅ ፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን አካውንት ማስወገድ ጀምረዋል፡፡
ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር ) በይፋ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አልገለፀም ፤ ነገር ግን ኩባንያው ህጉን የግድ ተግባራዊ እንዲያደርግ በመንግስት በዝርዝር ከተቀመጡት የማህበራዊ ሚዲካ ኩባንያዎች መካከል ነው።
ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ እና ማሌዥያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት መንግስታት የአውስትራሊያን አካሄድ ለመተግበር እያጤኑ ነው።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በህግ የከለከለች ቀዳሚ ሀገራ ሆናለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው ያሰባሰበው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
