134 016
Subscribers
-1424 hours
-1207 days
-28530 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ አርቲስት ችሮታው ከልካይ፣ አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ ወዘተ... እባካችሁ ይህን ህዝብ አታዘርፉ!
"ያለ ምንም ኤምባሲ ኢንተርቪው ሰዎች ወደ ጣልያን እና ካናዳ እየሄዱ መሆኑን ሰምታችኋል? ወደነዚህ ሀገራት ለመሄድ የኤምባሲ ኢንተርቪ ሳይሆን ፓስፖርት እና የእኛ እጅ ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ" (ቪድዮ: https://www.facebook.com/share/v/16iWpRzpFp/)
"ካናዳ በፓስፖርት ብቻ ኑልኝ እያለች በአዲስ ዓመት እዚህ ልታሳልፉ ነው? (ቪድዮ: https://www.facebook.com/share/v/19xypxrE9b/)
ይህ እንግዲህ ከሰሞኑ 'Fly Addis' በተባለ ድርጅት ዝነኛ ግለሰቦችን በመጠቀም እያሰራጨ ያለው የተሳሳተ፣ አንዳንዴም ነጭ የማጭበርበር ተግባር ነው። በዚህ ድርጊት ላይ ከላይ ከተጠቀሱት ግለሰቦች በተጨማሪ ሌሎች እውቅ ግለሰቦችን በማሳየት ህዝብን በዚህ መልኩ እያሳሳቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ነው።
የሚያስተዋውቁት ስልክ የማይሰራ ሲሆን በአካል የሚሄዱትን ግን ገንዘብ እየተቀበሉ ይገኛሉ፣ አብረናቸው እንሰራለን የሚሏቸውን ተቋማትም ለማናገር ሞክሬ 'ፍፁም ውሸት' የሚል ምላሽ ነው ያገኘሁት።
መች ይሆን ይህ ህዝብ እንዲህ አይነት ድርጊት ሀሰተኛ መሆኑን አውቆ የሚጠነቀቀው?
የመንግስት አካላትስ እንዴት ቁጥጥር ማድረግ ተሳናቸው?
ታዋቂ አርቲስቶች/ግለሰቦችስ ለምን እንዲህ አይነት ድርጊት ላይ ይሳተፋሉ።
በተመሳሳይ 'ፊን ቴክ' የተባለው ድርጅት የሰራው ስራም ተጋልጧል (ሊንክ: https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/c6d?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7)
ከዚህ በፊትም ብዬዋለሁ፣ ብራንድ አምባሳደር ምናምን እየተባለ ታዋቂ ግለሰቦችን በካሜራ እያሳዩ ህዝብን መዝረፍ በጣም ተለምዷል፣ ለዚህ ደግሞ የፕሮግራም አዘጋጁ አብርሀም ግዛው ብዙዎቹ ላይ በአንድም በሌላ መልክ እየተሳተፈ ነው።
ህዝቡን አትዝረፉ፣ አታዘርፉ፣ ካልሆነ በስም እየጠራን ማጋለጥ እንቀጥላለን።
@EliasMeseret
❤ 515👍 128😢 104🙏 28🤔 9😱 4🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
ልብ ያለው ልብ ይበል 😀 ኧረ ተከርባቹን የቀድሞ ሚኒስቴር ዴኤታ እየሰማችሁት፣ ከባድ attention ይፈልጋል።
#useless
@EliasMeseret
😁 923👍 113❤ 85🙏 15😢 14🤔 2😱 2🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ህዝቡምንይላል "ከሚከተሉት ግለሰቦች ውስጥ ለህዳሴ ግድብ ዕውን መሆን 'በአንፃራዊነት' ከፍተኛውን ድርሻ የተወጡት ማን ናቸው?" ለሚለው ጥያቄ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ በ6 ሰዓት ውስጥ ብቻ 24,500 ሰው ድምፅ ሰጥቷል። ውጤቱም የሚታየው ነው፣ መልካም አዳር!
@EliasMeseret
❤ 642👍 268😁 64🙏 56😢 18🤔 8😱 4
Photo unavailableShow in Telegram
ከ585,882 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መሀል ያለፉት 48,920፣ የወደቁት ደግሞ 536,962 ሆነዋል። በሌላ አገላለፅ 91.6% ተማሪዎች ወድቀው 8.4% ብቻ አልፈዋል ነው።
ለዚህ የትምህርት ስርዐቱን የሚመሩት አካላት በዋነኝነት፣ መንግስትም በየደረጃው ሀላፊነት ወስዶ ምን እየሆነ እንደሆነ ለህዝብ ሊያስረዱ ይገባል።
ይህ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ትውልድ ምን ሊሆን ነው? ከሰሞኑ እየታፈሰ ወደ ጦር ማሰልጠኛ እንደሚገባው ትውልድ እጣ ፈንታቸው ይሆን?
ያሳዝናል!
@EliasMeseret
😢 943❤ 129😁 115👍 62🤔 61😱 35🙏 14🕊 5
#ህዝቡምንይላል ከሚከተሉት ግለሰቦች ውስጥ ለህዳሴ ግድብ ዕውን መሆን "በአንፃራዊነት" ከፍተኛውን ድርሻ የተወጡት ማን ናቸው?Anonymous voting
- አፄ ኃይለ ላሴ
- ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ
- ጠ/ሚር ሐይለማርያም ደሳለኝ
- ጠ/ሚር አብይ አህመድ
- ኢ/ር ስመኘው በቀለ
❤ 1 447👍 343😁 334🙏 100🕊 77🤔 46😢 18😱 17
ትናንት ምሽት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዳጊዎች ለዛሬ ጠዋቱ ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ልምምድ እያረጉ በነበረበት ወቅት የመድረክ መደርመስ አደጋ አጋጥሟቸው ተጎድተዋል፣ በርካታ ቤተሰብ ለሊቱን ሙሉ በየሆስፒታሉ በዋይታ እና ለቅሶ ሲንከራተት ነው ያደረው።
ትናንት ምሽት ተጎጂዎቹን ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በየሆስፒታሉ እየዞሩ የጎበኙ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች እንዲዘግቡ አልተፈቀደላቸውም፣ ባለስልጣናቱም እንደተለመደው በማህበራዊ ገፆቻቸው እንኳን አላጋሩትም።
የሚያሳዝነው ደግሞ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች ተብለው የተመረጡት እነዚህ ታዳጊዎች የአዲስ አመት በዓልን ጨምሮ ለበርካታ ቀናት ከቤተሰብ ተለይተው ስድስት ኪሎ ካምፓስ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው የቆዩ ነበሩ።
በአደባባይ የደረሰ አደጋን በዚህ ደረጃ መሸፈን ምን ያስፈልጋል?
ለማንኛውም ለታዳጊዎቻችን ፈጣሪ ይድረስላቸው፣ በቶሎ ይማራቸው።
መሠረት ሚድያ ላይ ለሁሉም ክፍት ተደርጎ የቀረበውን ይህን መረጃ ያንብቡ ⤵️
https://tinyurl.com/4s2tz2ju
😢 420❤ 143👍 30😁 12😱 11🕊 11🤔 6
የ 'ብራንድ አምባሳደር' በሚል የምትሰየሙ አርቲስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች በስማችሁ የሚደረግ አላግባብ ነገር ካለ ቀድማችሁ ንቁ፣ ባይሆን እንኳን ዘግይታችሁ ስታውቁ ለህዝብ አሳውቁ።
እዚህ ጋር አንድ እና ሁለት ሚሊዮን ብር እያሳየ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚጫወት ስላለ ተጠያቂነት ስለሚይመጣ ይታሰብበት። በዚህ ዙርያ የመሠረት ሚድያ ዘገባ ⤵️
https://tinyurl.com/2ckvm8ba
👍 212❤ 73😁 42🤔 13😱 8
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
መልካም አዲስ ዓመት!
@EliasMeseret
🙏 444❤ 175👍 57🕊 33
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንድ ሰው በዛሬው ዕለት ሊሰማው የማይፈልገው ግን ጥሬ ሀቅ!
በያዝነው የ2017 ዓ.ም ብቻ የኤሌክትሪክ ደንበኞች ላይ 400 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ የሆነ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተደርጓል፣ ለዚህ ደግሞ አይ ኤም ኤፍ (IMF) የሰጠው ብድርን አያይዞ ያስተላለፈው ቀጭን ትዕዛዝ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል።
የትውልድ ቅብብሎሽ የሆነው ህዳሴ ዛሬ ተመርቋል፣ ይሁንና የሚያመነጨው ሀይል ወደ ህዝብ ደርሶ ሀይል ወደየገጠሩ እና መንደሩ ካልገባ እና በተቃራኒው የዋጋ ጭማሪ ከገጠመው ህዝቡ 'ለምን?' የሚል ጥያቄ ማንሳት ብቻ ሳይሆን 'ግድቡ የኔ ነው' ማለት ማቆሙ አይቀርም። በተመሳሳይ ዳንጎቴ ይገነባዋል የተባለው የማዳበርያ ፋብሪካ ለገበሬው ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ ይባስ ከጨመረበት ብሎ እንደማሰብ ነው።
ህዳሴ 'ዳግማዊ አድዋ ነው' ከተባለ ከአበዳሪዎቹ የሚደርስ ጫናን በተቻለ መጠን ለማስቆም ባይቻል ለመቀነስ መጣር አለብን። ከእነሱ በሚመጣ ጥያቄ ዜጎች ከዓመት በፊት ለኤሌክትሪክ ከሚከፍሉት አሁን አራት እና አምስት እጥፍ ሲከፍሉ ማየት ከእንደዛሬው ካለ የደስታ ዜና ጋር አብሮ ሲታሰብ ይከብዳል።
አሁን ላይ በኤሌክትሪክ እየተንበሸበሹ ያሉት እንደ ቻይና እና ኤምሬትስ ካሉ ሀገራት የሚመጡ የክሪፕቶ ማይኒንግ (crypto mining) ኩባንያዎች እና ለእነሱ ኤሌክትሪክ ሲሸጥ ሞቅ ያለ የድለላ እና የኪስ ገንዘብ የሚያገኙት የመንግስት ሀላፊዎች ናቸው (በዚህ ዙርያ መሠረት ሚድያ ላይ በቅርቡ ዘገባ ይኖራል)።
መልካም አዳር!
@EliasMeseret
❤ 1 071👍 424🙏 90😢 28🤔 25🕊 10😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
በህዳሴ ግድብ ዙርያ የኢትዮጵያን ድምፅ ካሰማንባቸው አለም አቀፍ ዜናዎች በከፊል!
ከሁሉም 'Ethiopia to fill disputed dam, deal or no deal' የሚለው ልዩ ዘገባ ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ባይደረስም ውሀ ሙሌት ልትጀምር እንደሆነ የታወቀበት የመጀመርያው አለም አቀፍ ዜና ነበር፣ የግብፁ ፕሬዝደንት በብስጭት በቀጥታ ምላሽ የሰጡበትም ነበር።
#ItsMyDam
👍 420❤ 206🙏 27😁 23😱 5🤔 2🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
በትውልድ ቅብብሎሽ እውን የሆነ ድንቅ የሀገር ኩራት!
#ItsMyDam
❤ 764👍 163🙏 30🕊 9😁 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኮንፈረንስ በተካሄደ ቁጥር ይህ ድርጊት ለምን?
በየአመቱ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባን ጨምሮ በጣም ብዙ አለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ከ10 ዓመት በላይ አዲስ አበባ ላይ በጋዜጠኝነት ተካፍያለሁ። ታድያ በዚህ ሁሉ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች መንገድ ሲዘጋ በትራንስፖርት እጥረት ይንከራተቱ ይሆናል እንጂ ካለፈው አንድ እና ሁለት ዓመት ወዲህ እንደሚደረገው ዘግናኝ የሆነ አፈሳ እና ወደ ማጎሪያ ቦታ መጣል ሰምቼም፣ አይቼም አላውቅም።
ከሰሞኑ በርካቶች በአዲስ አበባ ይካሄዳል የተባለውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ የአፍሪካ-ካሪቢያን ስብሰባ እና የግድቡ ምርቃት ተብሎ የዚህ ድርጊት ሰለባ እየሆኑ ነው። መሠረት ሚድያ እንደዘገበው አንዳንዶቹ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ውሃ ልማት አካባቢ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኝ 'ማቆያ' በሚባል መጋዘን ውስጥ ተይዘው ይገኛሉ።
ብትሩ በተለይ የኔ ብጤዎች እና በመንገድ ዳር ስራ ላይ የተሰማሩት ምስኪን ዜጎች ላይ ማረፉ ያሳዝናል። ለምሳሌ ዛሬ አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር እንግዳ ይመጣል ተብሎ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ የኔ ብጤዎች በሙሉ ተጭነው ተወስደዋል።
አንድ የአይን እማኝ እንዳለኝ "በአሁን ሰአት በአራት ፓትሮል በተኙበት እየቀጠቀጡ እንደ ኩንታል ማዳበሪያ እየጫኗቸው ነው፣ አካለ ጎዶሎ አልቀረ፣ የልጅ እናት አልቀረ።"
ሌላ የደረሰኝ ምስክርነት እንዲህ ይላል: "አንድ የልጅ እናት ጨቅላ ልጇን አዝላ ከፀጥታ ሀይሎች ለማምለጥ ስትሞክር ህፃኑ ወድቆ ጭንቅላቱ ተሰንጥቆ ደም በደም ሆኖ ፊቱ በደም ተሸፍኖ ነበር። ምስሉን በስልኬ ላስቀር ሞክሬ ፍርሀት ስላለ ተውኩት፣ ሰውን በተኑት።"
ታድያ ኮንፈረንስ በተካሄደ ቁጥር ይህ ድርጊት ለምን?
@EliasMeseret
😢 709❤ 192👍 51😁 21🤔 9🕊 8😱 6
ስለ ህዳሴ ግድብ ሲነሳ የታላቁ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት አባ በቀለ ትዝ ይላሉ!
በአንድ ወቅት አባ በቀለ ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ሰምቼ "ምን እናግዝዎ?" ስላቸው "አሁን አቅሜም እየደከመ ነው፣ ልጄ ስመኘው በህይወት ቢኖር ኖሮ ማረፊያዬ መካነ መቃብር እና የዲያቆናት መፅሀፍ ማንበብያ ትንሽ ዳስ ስራልኝ እለው ነበር" አሉኝ። አስቡት፣ የህዳሴ ግድብን የሚያክል ፕሮጀክት የሚመራ ኢንጂነር ወላጅ አባት!
ያንን ተከትሎ መረጃውን እዚሁ ማህበራዊ ሚድያ ላይ አጋርቼ በሁላችሁም በተደረገ ርብርብ ከግማሽ ሚሊየን ብር ተሰባብስቦ ያሰቡትን ሁሉ አሰርተው በ96 አመታቸው አርፈዋል።
የኢ/ር ስመኘውን ህይወት ባይመልስም ቢያንስ ህዝብ አባታቸውን በዚህ መልኩ መካሱ ደስ ያሰኛል።
@EliasMeseret
🙏 835❤ 358👍 100😢 33🕊 13😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
የ #ItsMyDam ታሪክ!
ጉዳዩ የሆነው የዛሬ አምስት አመት ገደማ ነው። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በስካይላይት ሆቴል በግድቡ ዙርያ ውይይታቸውን አድርገው እኩለ ለሊት ገደማ ላይ ካለ ስምምነት ጨረሱ።
የውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከስብሰባው መጠናቀቅ በሁዋላ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አንዲት ለውጭ ሀገር ሚድያ የምትሰራ ጋዜጠኛ "ግድቡን ማነው የሚያስተዳድረው?" የሚል ጥያቄ ሰነዘረች። ኢ/ር ስለሺ በመገረም "ሌላ ማን ያስተዳድረዋል? ግድቡ የኔ ነው... It's my dam" የሚል መልስ ሰጡ።
ከመሸ የተጠናቀቀው ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ አልቆ ወደ ቤት እየተመለስኩ የኢ/ር ስለሺ "ግድቡ የኔ ነው... It's my dam" የሚለው አባባል በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ። ሀሳቤ የነበረው ይህ ድንቅ አባባል በሌሎች ሚድያዎች ባይቀርብ ተረስቶ እንዳይቀር ነበር።
ከዛም ንግግሩ ያለበትን ቪድዮ በፌስቡክ፣ ትዊተር እና ቴሌግራም አካውንቶቼ ላይ ከቀናት በኋላ ለቀቅኩት፣ በርካታ ሰዎችም ንግግሩን ሼር እና ሪትዊት አደረጉት። ከዛ በሁዋላ ያለው ታሪክ ነው!
በቅርብ አንድ የመንግስት ሀላፊ እንዳሉት ንግግሩ "ታግሎ ማታገያ" ከመሆኑም በላይ #ItsMyDam የኢትዮጵያውያን ሶሻል ሚድያ ተጠቃሚዎች በግድቡ ዙርያ መነቃቂያ፣ ለግድቡ የሎተሪ ሽያጭ ማካሄጃ፣ የቴሌቭዥን ማስታወቂያዎች ማጀብያ፣ የቲሸርቶች እና ማስኮች ማጌጫ፣ ለግብፅ ሚድያዎች አጭር መልስ መስጫ...ወዘተ ሆኗል።
#ItsMyDam
@EliasMeseret
❤ 851👍 218🙏 52😁 30🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከሰሞኑ ኦቪድ በተባለው ድርጅት ዙርያ በተለያዩ ሚድያዎች መረጃ ሲወጣ ፋናዬ 'ኦቪድ የማነው?' ብሎ ማርከሻ እና ማደንዘዣ መሰል ቪድዮ ለቋል።
ኧረ እንከስሀለን ብለው ሲዝቱብኝም ነበር፣ የት ደርሶላቸው ይሆን?
@EliasMeseret
😁 290🤔 53❤ 36👍 18😢 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን።
@EliasMeseret
🙏 146❤ 86👍 41😁 35🤔 8😢 4
Photo unavailableShow in Telegram
ከቅርብ ወራት በፊት በመግስት ሚድያዎች "ንፁሀን ዜጎችን ሲገድሉ፣ ሲደፍሩ፣ ሲዘርፉና ሲያፈናቅሉ ነበሩ" የተባሉ ታጣቂዎች አሁን "የወርቅ ማሽንና ትራክተር ቀረበላቸው" ተብሎ በነዚሁ የመንግስት ሚድያዎች ሲነገር መልዕክቱ ምን ይሆን? ነፍጥ አንግቦ መንቀሳቀስ ወርቅ ያስገኛል?
የቀድሞ ታጣቂዎችን በስርዐቱ እና የሀገር አቅም በፈቀደ መጠን ማቋቋም ተገቢ ነው፣ በዚህ መልኩ ያውም በመንግስት ሚድያ 'ወርቅ በወርቅ ሊሆኑ ነው' አይነት ዜና ሎሎችን ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ ሊስብ ስለሚችል ቢታሰብበት።
As the saying goes, messaging is everything!
@EliasMeseret
👍 457😢 140❤ 123😁 73🤔 24😱 6🙏 5🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ ላላት 130 ሚልዮን ገደማ ህዝብ ያለው 42 የሚሆን የመንግስት ዩኒቨርስቲ ነው፣ ይህም ለ3 ሚልዮን ህዝብ አንድ ዩኒቨርስቲ ማለት ነው። ከህዝብ ብዛት ስሌት በመነሳት የዩኒቨርስቲ ቁጥሮች ሲታይ ኢትዮጵያ በአለም ይቅርና በአፍሪካም እጅግ ዝቅተኛ የዩኒቨርስቲ ቁጥር (density) ካላቸው ሀገራት አንዷ ነች።
በየዓመቱ ደግሞ 40 ሚልዮን ተማሪ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እየተማረ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ይጥራል፣ ያልማል።
ታድያ በዚህ መሀል እነዚህ ዩኒቨርስቲዎች መስፈት ካላሟሉ እንኳን እንዲያሟሉ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ የሚገባው የትምህርት ሚኒስቴር ዘግቷቸው አዳሪ ትምህርት ቤት ሊያረጋቸው እንደሚችል ይዝታል።
እርግጥ ነው በመላ ሀገሪቱ የአዳዲስ መንገዶች፣ የኢንደስትሪ ፓርኮች፣ የዩኒቨርስቲዎች፣ የሆስፒታሎች ወዘተ ግንባታ ድሮ ከነበረበት ፍጥነት ካሽቆለቆለ ዓመታት ተቆጥረዋል።
በዚህ አያያዝ ግን ቀድመው የተሰሩ መንገዶችን መጠገን ስላልተቻለ ይታረሱ፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች ማምረት ስላልቻሉ የካድሬ ማሰልጠኛ ይሁኑ... እንዳይባል ስጋት ያለው ሰው ቢኖር አይደንቅም።
@EliasMeseret
❤ 518😁 237👍 87🙏 56😢 52🤔 11😱 7🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ የማዳበርያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ሊሳካ መሆኑ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ከርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ወጪ ከመታደጉ በተጨማሪ በማዳበርያ እጦት ለሚሰቃየው አርሶ አደር ትልቅ ብስራት ነው። ዳንጎቴ በዘርፉ የካበተ ልምድ ስላለው በተባለው 40 ወራት ግዜ ውስጥ ያጠናቅቀዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሏል።
#ThisIsBig
❤ 742👍 351🙏 67😁 39🤔 11🕊 5😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ድርጊት በተለይ በአዋሽ ባንክ እና በአማራ ባንክ በስፋት እየተስተዋለ ነው። የሚሰቃዩት ሰራተኞች አፋጣኝ ምላሽ ይፈልጋሉ... በዚህ መልኩ ሰራተኛን ማሰቃየት ተገቢ አይደለም፣ ጉዳዩ መፍትሄ ካልተሰጠው መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ተከታታይ ዘገባዎቹን ማቅረብ ይቀጥላል፣ ከብሔራዊ ባንክ ምላሽ አካተን በቅርቡ ሌላ መረጃ እናቀርባለን።
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/b4c?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
👍 287❤ 130😢 53🙏 42😁 18🤔 10🕊 1
