en
Feedback
"ኡማ ቲቪ " Tv

"ኡማ ቲቪ " Tv

Open in Telegram

ለበለጠ ወቅታዊ መረጃወችን ለማገኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Show more
46 436
Subscribers
-524 hours
-1237 days
-52930 days
Posts Archive
Show all...
2
ያ ኢላሂ ... መስጅዶች ውስጥ የቤት ኪራይ መክፈል አቃተን፣ ልጆቻችንን የምንመግባቸው አጣን... የሚሉ ድምፆች እየበረከቱ ነው። ኑሮው ብዞዎችን እየፈተነ ነው። የሰው ፊት መቆም ከብዷቸው በየቤታቸው በችግር የሚሰቃዩ ቤቱ ይቁጠራቸው። ከምንም ጊዜ በላይ እርስበርስ ልንተዛዘን የሚገባን ጊዜ ላይ ነን። በዙርያችን፣ ጎረቤቶቻችን ያሉበት ሀል ማወቅ ባለን ነገር መተጋገዝ ይገባናል። አላህ ይሁነን!
Show all...
🙏 102👍 35😢 28 22
😢 62😭 35 16👍 7
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከአምቢያ መስጂድ ወጣት ጀምአ ጋር በመተባበር ታላቅ የደአዋ ፕሮግራም አከናወነ። የደአዋ ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድ ሸሪፍ እና የከፍተኛ ምክር ቤቱ ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ሺሐቡዲን ሼህ ኑራ እንዲሁም ሌሎች የስራ አስፈፃሚ አባላት እና የክፍለ ከተማው መጅሊስ አመራሮች ተገኝተዋል። በደአዋው ፕሮግራም ላይ ኡስታዝ ሱልጣን ኸድር "የአላህ ጥበቃ" በሚል ርዕስ ለታዳሚው ትምህርት ያቀረቡ ሲሆን የአላህ ጥበቃ በተሟላ መልኩ አጠገባችን እንዲኖር ከወንጀል የፀዳ ህይወት ሊኖረን ይገባል ብለዋል:: ሌላኛው ደአዋ አድራጊ ኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ ሲሆኑ "የእምነት አስፈላጊነትን" በተመለከተ መልእክት አስተላልፈዋል:: እስልምና ተፈጥሮአዊ ዲን በመሆኑ ትዕዛዛቱም ከውስብስብ ሀሳቦች የፀዳ እና በግልፅነት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ገልፀዋል:: በዚህ የደአዋ ፕሮግራም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ሸሀቡዲን ሼህ ኑራ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል:: ዋና ፀሀፊው በመልእክታቸው በዚህ አይነት የሰዎች ስብስብ ላይ ተገኝቶ ስለ እስልምና መስማት አስደሳች ነው በማለት ገልፀዋል:: ወጣቶች የእምነት ሀላፊነት ተረክበው እንዲሄዱ ከተፈለገ የእውቀትን አስፈላጊነት በተሻለ መልኩ መረዳት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል:: በዲጂታል ዘመን ላይ እንደመገኘታችን ወጣቶች ዘመኑ በሚጠይቀው መንገድ እውቀትን ለሰዎች ለማስተላለፍ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለወጣቶች የሚሆን የተሻለ አደረጃጀት በቀጣይ ለመስራት በእቅድ ላይ ስለሆንን ወጣቱ የሚጠቀምበትን እድል ለመፍጠር ተቀራርበን መስራት አለብን ሲሉ ገልፀዋል:: ወጣቶቾን ለዲን በሚጠቅም መኩል ለማብቃት ይህን መሰል የእውቀት ማግኛ መንገድ አስፈላጊ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል:: በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድ ሸሪፍ የተገኙ ሲሆን ወጣቶች ከብዙ አሳሳች ነገር ራሳቸውን አቅበው በዚህ መሰል የዲን ተግባር ላይ መሳተፍ መቻል ትልቅ እድል ነው ብለዋል:: ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ውጤታማ እንቅሰቃሴ እያደረገ መሆኑን አንስተው ወጣቱን ያሳተፈ ተግባር ላይ ጠንክረው እንዲሰሩ መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ መጅሊስ ወጣቱን በእውቀት እና በአመራር ልምድ አሳድጎ ነገ ተቋም የሚመራበትን እድል እንዲያገኝ አስቦ እየሰራ ስለሆነ ወጣቶች ተቋማችሁን በቅርበት ሆናችሁ እንድታግዙት በማለት መልእክት አስተላልፈዋል:: በዝግጅቱ ላይ የአንቢያ መስጂድ እና የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በመስጂዱ በመገኘት የደአዋ ፕሮግራሙን ተከታትሏል::
Show all...
27👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
አሰላሙ  አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ አር-ሪሳላህ የቁርዐን ማዕከል ለሙስሊሙ ኡማ አስደሳች ዜናን ይዞ መጥቷል ። በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ኢስላማዊ እውቀትን ከመሰረቱ በማስተማር ከዳር እስከ ዳር ተደራሽ ለማድረግ በእምነቱ ጠንካራ የሆነን ማህበረሰብ ለመፍጠር ዝግጅቱን ጨርሷል ። በአማርኛ በኦሮመኛ በጉራጌኛ በስልጢኛ እና በእንግሊዝኛ  ቋንቋዎች በኦንላይን  ለማስተማር በምዝገባ ላይ ይገኛል። በማዕከሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች                                📌 ቃኢደቱ ኑራኒያህ ለጀማሪዎች   📌 የቁርዐንን እያዩ ለማንበብ  ከመሰረታዊ የተጅዊድ ትምህርት ጋር 📌 ቁርአን ሂፍዝ ከተሟላ ሙራጅአ ጋር 📌የተርቢያ (የመልካም ስነምግባር ) ግንባታ እና ክትትል 📌 አጫጭር የአቂዳ የፊቂህ እና የ ሃዲስ ኪታቦች ይሰጣሉ የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ በመረጡት የሶሻል ሚድያ አማራጮች - በዙም - በቴሌግራም - በዋትስ አፕ - በኢሞ እንዲሁም በሌሎች አማራጮች ባሉበት ሁነው የእጅ ስልክዎን ብቻ በመጠቀም የሚሰጥ ይሆናል። የቂርአት ሰአቶች በሳምንት 6 ቀን ከ ፈጅር ብኋላ እስከ 1:00 ሰአት ከ 2:00 -6:00 ከ8:00 - አሱር ከ አሱር ብኋላ እስከ መግሪብ ከ ምሽቱ 2:00 - 6:00 ☎️ ለበለጥ መረጃ እና ለምዝገባ በ 0914696797 ወይም በ 0717189395 ይደውሉ 📱በቴሌግራም ለማናገር @A_Abuyasmin
Show all...
7😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
Great to see this! ዘምዘም ባንክ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የተከፈለ ካፒታል ሚኒማ በሟሟላቱ እንኳን ደስ ያለን!
Show all...
37👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን (ዶ/ር) የተመራው የአሊፍ ጀመኣ ልኡካን ቡድን በሀላባ ዞን የሚገነባውን ሱና ዩኒቨርሲቲ ጎበኘ! - ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ፥ ታህሳስ 5/2018 በሸይኽ ሙሐመድ ሀሚዲን (ዶ/ር) የተመራው የአሊፍ ጀመአ ልኡካን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚገነባውን ሱና ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በስፍራው በመገኘት ምልከታ አድርገዋል። በጉብኝቱ ላይ ከአሊፍ ጀመአ የተወከሉ መነሻቸው ከሀገራችን ከሁሉም አቅጣጫ የሆነ በኸይር ስራ ላይ በመሳተፍ የሚታወቁ በርካታ ወንድሞች በዶክተር ሸይኽ ሙሐመድ ሀሚዲን እየተመሩ ወደ ዮኒቨርሲቲው የግንባታ ስፍራ ተገኝተዋል፡፡ በሀላባ ዞን መጅሊስ ሰብሳቢ ሸይኽ ሁሴን መሀመድ የተመራውና ኡለማዎች፣ መሻኢኾችን የመጅሊስ አመራሮችንና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ያካተተው የሀላባ ጀመአ ደመቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። በጉብኝቱም ወቅት በርካታ ሀሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን ለዩኒቨርሲቲው የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት ስፍራ ከታሪካዊ የበደኔ አካባቢ አቅራቢያ መሆኑ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተገልጿል። ከዩኒቨርሲቲው ግንባታ በተጓዳኝ የትምህርት ስራ በአስቸኳይ መጀመር እንደሚገባው ስምምነት ላይ መደረሱም ነው የተገለፀው። የአክፍሮት ሀይላት እንቅስቃሴን በመግታት ዲነል ኢስላምን ለሌሎች ለማዳረስ የዲን እውቀት ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል። 📎 ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ በስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረው ሙሉ የቪዲዮ ዘገባ እንደደረሰን የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡ © ሀሩን ሚዲያ
Show all...
16🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
"ዛሬ የሰለፎችን ዓቂዳ አጥብቆ የያዘ ሰው እንደ 'ካፊር' ወይም 'መጤ' ተደርጎ የሚፈረጅበት ዘመን ላይ ደርሰናል!" "እስልምናን በ ወሕይ ሳይሆን በግሪክ ፍልስፍና (Philosophy) መነጽር የሚከተል መቷል" "50 ኪታብ በራሴ ስም አወስዳለሁ" ሲጠበቅ የነበረው የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት! #አፍሪካ_ቲቪ #የህይወት_ጎዳና
Show all...
54👍 6😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
እነሱ ሲያሰለጥኑ የእነሱን እንቶ ፈንቶ ተግተው የእነሱ ካድሬ እንዲሆኑላቸው ነበር ያሰቡ ወንድማችን ሸይኽ ሰዒድ አራጌ ግን ጥሩ አላማ ብሩህ አስተሳሰብ ስለነበራቸው አጋጣሚውን ለትልቅ አላማ ተጠቅመውበታል ሁል ጊዜ ፈር ቀዳጅ የሆነ ሰው ትልቅ ውለታ ነው ለታሪክ ትቶ የሚሄደው ከዚህ ቡሀላ በየዘርፉ የዚህ አይነት ስራ መስራት አለብን ሀገር በቀል የሆኑ መፅሀፎችን ማዘጋጀት አለብን ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት! #አፍሪካ_ቲቪ #የህይወት_ጎዳና
Show all...
34👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የዒልም መሰረት በማንበብ ነው የሚገኘው" ይህ በሸይኽ ሰዒድ የተዘጋጀው "ዓውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሀፍ በቅርቡ የደረሰኝ ቢሆንም የተወሰነውን ያክል ለማንበብ ሞክሬ ነበር በብዙ መልኩ የተደመምኩባቸው ቁም ነገሮች አሉ ። ሸይኽ ኢልያስ አህመድ የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት! #አፍሪካ_ቲቪ #የህይወት_ጎዳና
Show all...
23💯 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢስናድ የዲን አካል ነው, ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር በዝግጅቱ ላይ የታደሙት ሸይኽ ኤልያስ አህመድ፣ ኢስናድ በኢስላም ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና በማስረዳት፣ የእውቀት ምንጮችን በፅሑፍ በማዘጋጀት የቀደምት ሰለፎችን እምነት መጠበቅ ስለሚያስፈልገው ጉዳይ አጽንኦት ሰጥተዋል። ​ ​ሸይኹም "ኢስናድ የዲን አካል ነው፤ ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር"የሚለውን የአብደላህ ኢብኑ ሙባረክ ንግግርን በማውሳት ሰነድ ለሃይማኖታዊ ትምህርቶች እውነተኛነት እና ተዓማኒነት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል። ​ኢስናድ የእውቀት ምንጭነቱን ለማረጋገጥ እና ከስህተት ለመጠበቅ የሚያስችል መሠረታዊ የዲን መርህ ነው። ​ ​የዚህ ዓይነቱ የእውቀት ቅብብሎሽ እና የፅሑፍ ዝግጅት መዳከም፣ ውሸት መልኩን ቀይሮ እንዲመጣ በር እንደሚከፍት ጠቁመዋል። ​በተጨማሪም፣ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቁ የሃይማኖት የእምነት ርዕሶች እንደ የኺላፍ (የልዩነት) ርዕሶች እየተመሰሉ እንዲሰራጩ እንደተደረገ አውስተዋል። ​ ​እንደዚህ ዓይነቱ የእውቀት ዝግጅቶች ለሚነሱ ውዥንብሮችና የተዛቡ አመለካከቶች ዓይነተኛ መፍትሄ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል። ​እምነት ማለት የቀደምት ሰለፎች መንገድ እንደሆነ በማውሳት፣ ይህ እምነት የሚገነባውም በመረጃና በሰነድ የተደገፈ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። ​ በመጨረሻም ​ሸይኽ ኤልያስ አህመድ፣ ኢስናድ የዲን መሠረት መሆኑን አብራርተው፣ በውሸት የሚመጡ ውዥንብሮችን ለመከላከል የቀደምቶችን እምነት የሚጠብቁና በመረጃ የተደገፉ እውቀታዊ መጻሕፍት መዘጋጀታቸው እና የእውቀት ቅብብሎሹ መቀጠሉ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል። #ሱና_ዩኒቨርሲቲ | #አወሊያ | #የእውቀት_ብርሃን | #ለትውልድ_አሻራ | #አብሮነት °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ
Show all...
30👍 4
የእውቀት ቅብብሎሽ እና የሰለፎች መንገድ አስፈላጊነት ቀን: ታህሳስ 05, 2018 ዓ.ም. ቦታ: አዲስ አበባ፣ አወሊያ መመረቂያ አዳራሽ በሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረሕማን" መጽሐፍ ምርቃት ላይ የቀረቡ ወሳኝ ምክሮች በአወሊያ መመረቂያ አዳራሽ የተካሄደው የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረሕማን" መጽሐፍ ምርቃት ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪካዊ ፈተናዎች እና የዒልም (የእውቀት) ቅብብሎሽ ወሳኝ ሚና ላይ ትኩረት አድርጎ ተካሂዷል። ዝግጅቱ በዋነኝነት የታሪካዊ ውዥንብሮችን (እንደ አህባሽ አጀንዳ ያሉትን) ለመመከት እና የእምነትን ንጽህና ለመጠበቅ የፅሑፍ ሥራዎች እና ኢስናድ (የሰነድ ሰንሰለት) ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልቷል። ፕሮግርሙ ላይ የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ የነበሩት ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲንም  በንግግራቸው፣ ዑለማዎች የቀደመውን የእውቀት ውርስ ለመቀጠል እና ለትውልድ ለማሻገር፣ በሀገር ቋንቋ የተለያዩ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አደራ አሳስበዋል። በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት ሸይኽ ኤልያስ አህመድም በመረጃ እና በሰነድ የተደገፈ እውቀት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ኢስናድ የዲን አካል ነው፤ ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር" የሚለውን የአብደላህ ኢብኑ ሙባረክን ንግግር ጠቅሰው፣ በመረጃና በሰነድ የተደገፈ እውቀት ብቻ ከውሸቶች እና የተዛቡ አመለካከቶች (የእምነት ርዕሶችን የኺላፍ ርዕስ አድርጎ ከማቅረብ) እንደሚከላከል አብራርተዋል። ኡስታዝ አህመዲን ጀበልም በሰጡት አስተያየት፣ በሰለፎች አኗኗር (ሀያት) ላይ ብቻ ከማተኮር ጎን ለጎን፣ መሰረታዊ የሆነውን እምነታቸውን (አቂዳቸውን) ለመጠበቅ እና ትኩረት ለመስጠት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። በመጨረሻም፣ ዝግጅቱ ሁሉም ሙስሊሞች በተለይም ደግሞ ዑለማዎች የሰለፎችን ንጹሕ አቂዳ በመረጃ (ኢስናድ) ላይ ተመስርቶ እንዲያሰራጩና ለቀጣዩ ትውልድ በሀገር ቋንቋ የተሟላ የእውቀት ቅብብሎሽ አሻራ እንዲያስቀምጡ አሳስቦ ተጠናቋል። #ሱና_ዩኒቨርሲቲ | #አወሊያ | #የእውቀት_ብርሃን | #እስልምና_እና_ዕድገት | #ለትውልድ_አሻራ | #አብሮነት °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ
Show all...
22😡 2🙏 1
19🥰 7👍 5🤣 1😭 1
ወ/ት ለይላ ኑርሰቦን በተመለከተ ሰሞኑን የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የቆየ በመሆኑ፣ ጉዳዩን በተመለከተ ያለው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል። ወ/ት ለይላ ኑርሶቦ የተባሉ ዜጋችን በነብስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው ለረዥም አመታት በፍርድ ሲታይ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር እርቅ በማውረድ የገንዘብ ካሣ በመክፈል ቤተሰብ ምህረት እንዲያደርግላቸው በሽምግልና ስምምነት ላይ ተደርሶ፣ ኮሚቴ በማቋቋም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እርዳታ በማሰባሰብ የገንዘብ ካሣ ለተጎጅ ቤተሰቦች ተከፍሏል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶ፣ በቤተሰብ ደረጃ የተሰጠው ምህረት በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ ምህረቱ ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ ኤምባሲያችን ከሚመለከተው የሳዑዲ መንግስት ተቋማት ጋር ሲያደርግ የነበረውን የቅርብ ክትትል አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን እንገልጻለን። ©የኢትዮጵያ ኢንባሲ ሪያድ
Show all...
33
اللهم اني تبرأت من حولي وقوتي ولجأت إلى حولك وقوتك ياحي ياقيوم..
Show all...
👍 22 11🥰 3💯 2
Photo unavailableShow in Telegram
የተመድ መረጃ ========= በጋዛ ሰርጥ ከ140,000 በላይ ሰዎች በዝናብ ውሃ ተጎድተዋል፣ በጦርነቱ ሳቢያ በመቶ ሺዎች አልቋል፣ አስቸጋሪ በሆኑ ሰብአዊ ሁኔታዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ህይታቸው አልፈዋል። ቤቶችና መሰረተ ልማቶች በስፋት ወድመዋል። ወረራው እስራኤል በነዋሪዎች ላይ ቀጣይ የሚጥለው የእርዳት ገደብ ገደብ ያስፈራል ይህ የህዝቡን ስቃይ የሚያባብስ ነው። በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት ቤቶችን መልሶ መገንባትን እና ሰብአዊ አርዳታዎችን ያለ ገደብ መፍቀድ እንደሆነ አጉልቶ ያሳያል ያበጠው የእስራኤል ኢብሪት በቅርቡ ይተነፍሳል
Show all...
47😢 23
Photo unavailableShow in Telegram
#በኢራን የተደረገ አስገራሚ #ጥሎሽ ዶክተሩ ሙሽራ ዶክተሯን ሙሽሪት በሚገርም ጥሎሽ አግብቷታል ጥሎሹ 313 ቀዶ ጥገና ለድሆችና ለችግርተኞች በነፃ ማድረግ ነበር።
Show all...
141👍 47
በትላንትናው እለት በሀገረ አሜሪካ የTPS ከለላ ማብቃት የወጣው መግለጫ እና እንድምታው ምን ይመስላል :: ====================== የአሜሪካ የTPS ከለላ ማብቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የገጠማቸው የህልውና ስጋት ምንድነው ? ይህ ዜና ለብዙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ነው። አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ሰጥታው የነበረውን ጊዜያዊ የከለላ ሁኔታ (TPS - Temporary Protected Status) ለማንሳት የወሰነችው ውሳኔ ትርጉምና እንድምታው ምን ማለት ነው የሚለውን በሚከተለው መልኩ ይቀርባል። 1. ትርጉሙ ምንድን ነው? _____ TPS (Temporary Protected Status) ማለት በአገራቸው ግጭት፣ የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌሎች ያልተለመዱ ሁኔታዎች ባሉባቸው አገራት ዜጎች አሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት እንዲቆዩ፣ እንዲሰሩና ከስደት (Deportation) እንዲጠበቁ የሚሰጥ ፈቃድ ሲሆን። ውሳኔው ተነስቷል ማለትምን ማለት ነው ? _______ • በዚህ ከለላ ስር የነበሩ ኢትዮጵያውያን በህጋዊ መንገድ የመቆየትና የመስራት መብታቸው ያበቃል። • በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሌላ የቪዛ አይነት ካላገኙ ወይም አገሪቱን ለቀው ካልወጡ ወደ አገራቸው የመመለስ (Deportation) ሂደት ሊጀመርባቸው ይችላል። 2. ትንታኔ (Analysis) ይህ ህግ ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ይነካል ? ______ እንደ አሜሪካ የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) መረጃ፣ በአሁኑ ወቅት በግምት ከ4,500 በላይ ኢትዮጵያውያን በዚህ ከለላ ስር ይገኛሉ። በተጨማሪም፣ ከዚህ ቀደም በተደረገ ማሻሻያ እስከ 12,800 የሚደርሱ ወገኖች ለከለላው ብቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር። የአሜሪካ መንግስት ይህንን ውሳኔ ማስተላለፉ ከፖለቲካዊ እና ሰብአዊ አንጻር ሲታይ የሚከተሉት ክፍተቶች ይታዩበታል። ሀ. የሁኔታዎች አለመረጋጋት (Premature Decision): አሜሪካ "በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ተሻሽሏል" በሚል ሰበብ ይህን ልታደርግ ትችላለች። ሆኖም ግን፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በሌሎች አካባቢዎች አሁንም ግጭቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ባሉበት ወቅት ይህን እርምጃ መውሰድ የሰዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጥ ያልበሰለ ውሳኔ ነው የሚል የብዙዎቹ ቅሬታ ያመለክታል ። ለ. የጂኦ-ፖለቲካ ተጽዕኖ (Geopolitical Interests): ________ ብዙውን ጊዜ TPS የሚነሳው ወይም የሚራዘመው በአገራቱ መካከል ባለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ ተመስርቶ ነው። አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነቷን ለማደስ በምታደርገው ጥረት፣ "አገሪቱ ሰላም ናት" የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የሰዎችን ስደተኝነት እንደ ካርታ ልትጠቀምበት ትችላለች። ይህ ደግሞ ሰብአዊነትን ከፖለቲካ በታች ያደርገዋል። ሐ. የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ:: _____ ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ለዓመታት ኖረው፣ ግብር ከፍለውና ሰርተው ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ያናጋል። ይህ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ፍሰት (Remittance) ከመቀነሱም በላይ፣ በቤተሰብ መበተን ምክንያት ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ያስከትላል። በስተመጨረሻ ______ ጠቃሚ መረጃ፦ ከለላው በይፋ በዲሴምበር 12, 2025 የሚያበቃ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ሌላ ህጋዊ መንገድ እንዲፈልጉ ወይም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ እስከ ፌብሩዋሪ 13, 2026 ድረስ የ60 ቀናት የሽግግር ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ውሳኔው ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ተጨባጭ የጸጥታ ሁኔታ ጋር የማይመጣጠንና የዲፕሎማሲያዊ ግብይት ውጤት ይመስላል። ይህም በስደት ላይ ያሉ ወገኖችን ለከፍተኛ ስጋት የሚዳርግ ነው። ለበለጠ መረጃ በቅርብ የሚገኙ ጠበቆቻችሁን አናግሩ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
::::::::::ታላቅ የመፅሐፍ ምረቃ!::::::::::::: አውኑ ረህማን የተሰኘው የሸይኽ ሰዒድ አራጌ መፅሐፍ ነገ እሁድ ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ል ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት በአወሊያ መመረቂያ አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል። እርሶም በዚህ የመፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙልን ስንጋብዞ በታላቅ ደስታ ነው። °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
Show all...
18
አብደውም መንግስትን ሲፈሩ የነበሩ በርካታ ምሁራን የመንግስትን የአቋም ለውጥን ለማወደስ ተሽቀዳደሙ። «መሪ ማለት ሕዝቡን የመሰለ ነው።» በማለት ንጉሡን አወደሱ። ለንጉሣቸው ጭብጨባው ከዳር እስከ ዳር ቀጠለ። ከእብደት ዉሃ ያልጠጡና የመንግስትን አቋም ለማየት ተደብቀው የነበሩ ጤነኛ ምሁራንም ተስፋ ቆረጡ። አንዳንዶቹ «መንግስትንም ተቀላቅለን ትናንት መንግስት ዘንድ የነበረንን ቅቡልነትና ስፍራ ዛሬም ማጣት የለብንም» ብለው የእብደት ዉሃውን ጠጥተው ለማበድ ወሰኑ። ሆኖም እንደተርታው ሰው በየቤታችን መጠጣት የለብንም ሕዝብና መንግሥት እያየ በተዘጋጀ ሕዝባዊ መረድክ ላይ እንዲሆን ፈለጉ። ንጉሡም የነርሱን ሁኔታ ሲሰማ መድረኩን በሕዝቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ ለማጠናከር ሊጠቀምበት ፈለገ። መድረክ ተዘጋጅቶ ሕዝቡ በአደባባይ ተሰባስቦ እንዲገኝ ጥሪ ተደረገ። ጤነኛ ሆነው የቆዩት ጥቂት ምሁራን ሕዝብ በተሰበሰበት «በአደባባይ ንሰሃ ሊገቡና የኛን ፈለግ ሊከተሉ ነው» ተብሎ ሕዝቡ ሊታደም ቋምጧል። ተራ በተራ በመድረኩ ቀርበው የእብደት ዉሃውን ጠጡ። እነርሱም አበዱ። ልብሳቸውን አወላልቀው እርቃናቸውን ሆኑ። አንደኛው ለሕዝቡ «የትናንት ሁኔታችንን ሳስበው ይገርመኛል። ይህን የመሰለ ነጻነትና ከራስ ሕዝብ ጋር ራስን መሆንን ተቃውሜ የቆየሁት ምን ሆኜ ነበር?» እያለ ተናገረ። ከዳር እስከ ዳር ጭብጨባ ቀለጠ። ሕዝቡም በመንግስቱ ላይ አመኔታው ጨመረ። የመንግስትን የአቋም ለውጥ የተመለከቱ ነጋዴዎች በአጋጣሚው ለማትረፍ የእብደት ዉሃውን ማጣፈጫ እየጨመሩ የተለያዩ ቅርጽና ቀለም ባላቸው ጠርሙዞች አሽገው ለገበያ አቀረቡ። የማስታወቂያ እንደስትሪው «ዘመኑን የዋጀ መጠጥ!»፤ «የብልሆች መርጫ!» እያሉ ማስተዋወቅ ጀመሩ።ይህም የመጠጡን ተቃባይነት ጨመረ።እብደትም ንግድ። የሕዝቡን ፍላጎት መከተል የትርፍ ምንጭ ሆነ። የአንዱ የታሸገ ዉሃ ፋብሪካ ባለቤት ቀርቦም በሚዲያ ቦርጩ ገዝፎ እርቃኑን እየታየ ፦ «ካምፓኒያችን ከፍተኛ ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ የሕዝባችንን ፍላጎት ለማሟላት ዘመኑን የዋጀ ተወዳጅ ምርቶችን ለገበያ እያቀረብን ነው። ምርቶቻችን ሰፊ ተቀባይነት አግኝተዋል። ለበርካታ ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ እድል ፈጥረናል።በዘንድሮ የበጀት ዓመት ብቻ የሕዝባችንንና የመንግስታችን ዓላማ ከዳር እንዲደርስ የአዲሱን ዘመን ወጣቶችን ዝግጅቶችን ስፓንሰር እንደምናደርግ እናበስራለን። በዚህ ላቅ ያለ ኩራት ይሰማናል።» በማለት ገለጻ አደረገ። ቃለመጠይቁ ሲጠናቀቅ ሚዲያው አጭር ጭዉዉት ማቅረብ ጀመረ። ድራማውም ስነምግባርንና ወግን መከተልን፥ ሃይኖታዊ እሴትን መከተልን ኋላ ቀር፥ የድሮ ሸክም፥ሀገሪቱንና ሕዝቡን ነጻነት ነፍጎ ወደ ኋላ ያስቀረ እያለ ተዘባበተ። ቀጥሎም አርቲሰቶች እርቃናቸውን ሆነው በህብረት የሰሩትን ዝማሬ ቀረበ።ይዘቱም ተመሳሳይ ነበር። ቀጥሎም ታላቅ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ ተገለጸ። ታዋቂ ዘፋኞች፥ አርቲስቶች፥ የአዲሱ ተውልድ ተጽዕኖ ወጣት መሪዎች ይቀርባሉ ተባለ። በእለቱ በታላቁ አደባባይ ሕዝቡ ቀድሞ በመገኘት የዝግጅቱን መጀመር ይጠብቃል።ሁሉም እርቃኑን ነው። ወንድና ሴት ተደበላልቋል። መተፋፈር ኋላቀር የድሮ ስርዓት ተደርጎ በመታየቱ የሚተፋፈር የለም።እርቃኑን የሆነው የመድረክ መሪም በመድረክ ላይ ሽንቱን እየሸና የሽንቱን ድምጽ በማይክራፎን ለታዳሚው እንዲሰማ አደረገ።ከዚያም የዝግጅቱን መጀመር አበሰረ። ቀጥሎም «ኋላቀሮች እብዶች ይሉናል። እኛ የዳንን እንጂ እብዶች አይደለንም!» ብሎ መፈክር አሰማ። ሕዝቡም አብሮት ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ።ጭብጨባው ቀለጠ።ቀጥሎም የአዲሱ ትውልድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣት መሪ ወደ መድረክ ተጋበዘ። እርሱም እርቃኑን ነበር። በደረቱ ላይ «ተፈወስን» የሚል ንቅሳት ተነቅሷል። ልክ ወደ መድረኩ ሲወጣ ሕዝቡ በአድናቆት ጭብጨባና ፉጨት ተቀበለው።ንግግሩን ጀመረ። «እኛ ስነምግባር የሚሉት ታስረን ነበር። ወግንና ልማድ በሚሏቸው ጎታች አስተሳሰብ ታመን ነበር። ለቅዱሱ ዉሃችንና ለአዲሱ ዘመን ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ምስጋና ይግባቸውና ተፈወስን። ነጻነታችን ተጎናጸፍን። የድሮው ሕይታችን ከባድ፥ አጥፊና አሳዛኝ ነበር።ዛሬ ብርሃን አየን። ራሱን በልብስ የሚደብቅ ሰው ያለበት አካላዊ ችግር እንዳይታይበት የሚፈልግ ብቻ ነው። የጥንቶቹን ሕግ የሚያከብር፥ የአባቶቼን ልማድና ወግ የሚል ሁሉ አብድ ነው። አይደለም እንዴ?» ሲል ሕዝቡም «አብድ ነው!» ሲል አስተጋባ። ዛሬ አይናችን ተገለጠ።ሕይወት ሳትሸፋፈን እንዳለችው አየናት። ከናንተ መካከል ወደ ጥንቱ ኋላቀር ሕይወት መመለስ የሚፈልግ አለ?» ብሎ ጥያቄ አቀረቡ። ታዳሚው ከፍ ባለ አንድ ድምጽ «የለም!» በማለት ምላሽ ሰጠ።እርሱም «ፈጽሞ!» ሲል አከለበት። በእውነቱ እነዚህ የድሮ ቅሪቶች እኛ ያጣጣምነውን ይህን የጥፍጥና ሕይወት ቢረዱ እኛን ቀሊላቀሉ በተሽቀዳሙ ነበር።ሆኖም እብደታቸው ጋረዳቸው። እያንዳንዳችን በአከባቢያችን ሰፈር በጥንቱ ስርዓት መኖር የሚፈልጉ አንድም ሰው ካለ ከበሽታቸው ይፈወሱ ዘንድ ከቅዱሱ ዉሃ ማስጎንጨት ግዴታችን መሆኑን አንርሳ።» ብሎ ንግግሩን ጨረሰ። ሌላ ተረኛ ታዋቂ ምሁር ወደ መድረኩ ወጣ። ሕዝቡም በጭብጨባ ተቀበለው። «እንዴት እንደዳንን ተመልከቱ! የኋላቀሩ ስርዓት ምሁር ተብዬዎች ቅዱሱን ዉሃችንን ሕዝቡ እንዳይጠጣ አስጠንቅቀው ነበር።የሚገርመው እነርሱ አብደው ዉሃው ያሳብዳል አሉ። «ከናንተ መካከል ቅዱሱን ዉሃ ጠጥቶ ያበደ አለን?» ብሎ ጠየቀ። ሕዝቡም «የለም!» በማለት በከፍተኛ ጩኸት መለሰ። ወዲያው መረድክ መሪው ጣልቃ በመግባት ከኚህ ምሁር ቀጥሎ «እኛ ጤነኞች ነን» ሚል ዘፈን በታዋቂው አርቲስት እንደሚቀርብ አብስራለሁ አለ። ሙሁሩ ቀጠለ።በድጋሚ «ከኛ መካከል እብድ አለ?» በማለት ጠየቀ። ታዳሚው በጩኸት በድጋሚ ምላሽ ሰጠ። ምሁሩም «ተመልከቱ ብዛታችንን! ይህ እንደባህር አረፋ የበዛ ሕዝብ ይሳሳትልን?» ሲል ጠየቀ። «ፈጽሞ!» በማለት ምላሽ ተሰጠው።ታዳሚው ፉጨት፥ ጭብጨባ፥ ዳንስና ተጀመረ።ቀጥሎም ሰው ካገኘው ሰው መሳሳም ጀመረ።ግማሹ ወደ ወሲብ ገባ። ምሁሩ ቀጠል አድርጎ «ተመልከቱ ይህን ደስታ! ይህ ራሱ የጤናማነታችን ማሳያ ነው።ተደሰቱ» ብሎ ከመድረክ ወረደ። የሃይማኖት ተቋማት ተከታይ አጡ። አንዳንዶች ዘመኑን የዋጀ መሆን አለብን በማለት ሕዝቡ በሚፈልገው መልኩ ከመጽሐፍቶቻቸው የሰውን ልብ ይስባሉ የሚሏቸውን እየመረጡ ትምህርታቸውን አሰናዱ።በቤተ አምልኮ ዉስጥ እርቃናቸውን ለተሰባሰቡት ምዕመናን ሰባኪው «የመጨረሻ ዓላማችን ገነት መግባት ነው።ፈጣሪ በገነት ዉስጥ በመጀመሪያ አዳምና ሄዋንን የእርቃናቸውን እንዲኖሩ ያደረጋቸው።እርቃን መሆን ምን አዲስ ነገር አለው? ፈጣሪ ራቁት ፈጥሮ እኛ የርሱን ሥራ ለምን እንደብቃለን? በርሱ ሥራ እናፍራለን? ወይንስ በራሳችን? እስቲ ንገሩኝ» እያለ ስብከቱን ቀጠለ። በጣት የሚቆጠሩ ጥቂቶች ሊቃውንት ብቻ የእብደት ዉሃውን ሳይጠጡ ቀሪ ዘመናቸውን ተደብቀው በአቋማቸው ጸንተው ሊሞቱ ቆረጡ። አብዛኛው ሕዝብ የእብደቱን መንገድን ወዶና ፈቅዶ ተቀብሎ መኖር ቀጠለ። ንጉሡና ባለስልጣናት የእብዶች መሪ እብዶች ሆነው ስልጣናቸውን ማስጠበቅ ቻሉ። መንግስታቸውም ረጋ።
Show all...
19👍 8