en
Feedback
Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

Open in Telegram

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Show more
162 895
Subscribers
-124 hours
+1537 days
+51830 days
Posts Archive
07:08
Video unavailableShow in Telegram
የተጠናከረ ግንኙነት ለጋራ ብልጽግና Strengthening Our Ties for Mutual Prosperity
Show all...
21.68 MB
ባለፈው ዓመት ወደ ማሌዥያ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ካደረኩኝ አንድ ዓመት በኋላ፣ የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን በኢትዮጵያ ተቀብያለሁ። ይህ የጉብኝት ልውውጥ ጥልቅ አጋርነታችንን የሚመሰክር ሲሆን ይህም በርካታ ቁልፍ ሰነዶችን በመፈረም ተጠናክሯል። የመግባቢያ ሰነዶቹ በቱሪዝም፣ በጤና፣ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር የትብብር መስክ ላይ ያተኮሩ ናቸው:: ባደረግነው የሁለትዮሽ ውይይት፣ ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር እና ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠናል። Last year, I made an official visit to Malaysia, and one year later, I have the honor of welcoming Honorable Dato’ Seri Anwar bin Ibrahim, Prime Minister of the Federation of Malaysia. This exchange of visits is a testament to our deepening partnership, further strengthened by the signing of several key documents: a Memorandum of Understanding on Cooperation in the Fields of Tourism and Health, an Agreement on Air Services, and a collaboration document between the Kuala Lumpur City Council and the Addis Ababa City Administration. During our bilateral talks, we reaffirmed our shared commitment to further solidify and expand our cooperation.
Show all...
ክቡር የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። ጉብኝትዎ በማሌዢያ እና ኢትዮጵያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ውስጥም በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት ነው። I warmly welcome Honorable Dato’ Seri Anwar Ibrahim to Ethiopia—the Land of Origins, on his three-day official visit. Your presence is a true testament to the growing friendship and solidarity between Ethiopia and Malaysia, and it comes at a pivotal moment for our nation.
Show all...
17:24
Video unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያየሁት ነገር፤ ሰው የጠራ ራዕይ ካለው ፣ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚሠራ ከሆነ አንድን ነገር ባየው ልክ ማሳካት እንደሚችል ፤ ኢትዮጵያ ብቃት ያላት ሀገር እንደሆነች ነው።
Show all...
34.46 MB
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ጽሕፈት ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት በመለወጥ መሃል ከተማ ወደ ቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንፃ አዛውሯል። በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አስደናቂ የግንባታ ለውጥ እና ዘመናዊ የመሥሪያ ሥፍራ ጥበብን በማሳየት ለሠራተኞቹ እጅግ ምቹ የሆነ ስፍራንም መፍጠር ችሏል። ተቋሙ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሕይወታችንን በፍጥነት በመቅረጽ ውስጥ ያለውን ስፍራ በሚያንፀባርቅ እና ሀገራችንም በዚህ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በንቁነት መሳተፏን በሚያረጋግጥ መንገድ ከፍታ ላይ ደርሷል። ኢንስቲቲዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እያደረገ ያለው የመሪነት አስተዋፅኦውን እየተወጣ ሲሆን በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ትላልቅ የመረጃ ቋቶች፣ የመረጃ ፍለጋ፣ ሮቦቲክስ እና ኢመርሲቭ ቴክኖሎጂዎች አቅሙን በማጎልበት ላይ ይገኛል። በቅርቡ የተጀመረው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርት አፕ መዐከል ደግሞ ይኽንን ከባቢ የበለጠ ያጠናክረዋል። ዜጎች ሀሳብ ብቻ ይዘው በመምጣት ፕሮቶታይፕ ለመፍጠር፣ ለማባዛት ብሎም ከግሉ ዘርፍ ኢንቬስተሮች ጋር እንዲገናኙ እድል ያመቻቻል። እስከ አሁን 200 ሀሳብ ፈጣሪዎች በዚህ እድል ተጠቅመዋል።
Show all...
09:54
Video unavailableShow in Telegram
Jaalalli Walloorraa maddu Itoophiyaa maraaf ga'aadha
Show all...
25.55 MB
ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ። በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስከአሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል። የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የ1.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ ናቸው። የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን ያሳያሉ። በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Africa has spoken with one voice at the 2025 UN Climate Change Conference (COP 30) in Belém, Brazil and the world has listened. Ethiopia extends its heartfelt gratitude to the African Group of Negotiators for their unanimous endorsement of Ethiopia’s bid to host COP 32 in Addis Ababa in 2027. We are grateful for the opportunity that the Conference of the Parties is giving us to spearhead the collective effort to tackle one of the most daunting challenges faced by humanity. We are honored to be entrusted by the global community with such an important responsibility. This recognition reflects confidence in Ethiopia’s leadership in climate action and its capacity to host major global events. Ethiopia remains fully committed to delivering a robust and meaningful outcome and inclusive COP 32 that advances collective action against climate change. Building on the momentum of the Second Africa Climate Summit, https://www.facebook.com/share/16oLQ13neN/
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ። ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ።
Show all...
02:51
Video unavailableShow in Telegram
በባህር ዳር ከተማ በነበረን ጉብኝት የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እንዲሁም ከተማዋን ለቱሪዝም ዘርፍ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተመልክተናል። የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ደረጃውን የማሻሻል ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ነው። ስታዲየሙ 52 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ የሚችል ሲሆን የወንበር መግጠምና የሳር ንጣፍ ስራዎች ተጠናቀዋል። የመብራት ዝርጋታን ጨምሮ ሌሎች የስታዲየም ውስጥ መሰረተ ልማቶችም በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን መሠረት በማድረግ በባህር ዳር ጣና ሀይቅ ዳርቻ እየተገነባ ያለው ፈለገ ጊዮን ሪዞርትን የተመለከትን ሲሆን ሪዞርቱ ወደ ስራ ሲገባ የከተማዋን ተሪዝም ከማነቃቃት ባሻገር ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በባህር ዳር እያስገነባ ያለው የኢትዮ-ፌሪስ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት በጣና ሃይቅ ዳርቻ እየተከናወኑ ካሉ ሌሎች የልማት ስራዎች ጋር ተደምሮ ባህር ዳርን ወደ አዲስ የከተሜነት ምዕራፍ ለመሸጋገር ትልቅ ሚና ያበረክታል።
Show all...
11.72 MB
02:39
Video unavailableShow in Telegram
በጎርጎራ ጣናነሽ የተሰኘችዉን ጀልባ ሥራ አስጀምረናል። በጣና ውሃ ላይ እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኤኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች። ከ180 ተጓዦች በላይ የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ ለጉብኝት፣ ለመዝናናት እና አስደማሚውን የጣና ሀይቅ የተፈጥሮ ከባቢ ለመጎብኘት ወደ ጎርጎራ ኤኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ የበለጠ ምቹ አድርጋዋለች። In Gorgora, we’ve launched the long-awaited voyage of the Tananesh Ferry, now gracefully cruising the waters of Lake Tana, connecting Bahir Dar City with the newly established Dine for Generations project — Gorgora Eco Lodge. With a capacity of over 180 passengers, Tananesh makes the remarkable Gorgora Eco Lodge more accessible than ever before; a truly worthy destination to visit, relax, and admire the breathtaking natural beauty of Lake Tana.
Show all...
7.08 MB
12:18
Video unavailableShow in Telegram
ጉልበት ይሸሻል፣ ጊዜ ይሸሻል፣ ስልጣን ይሸሻል፣ ሁሉ አላፊ ነው ፣ የማያልፈው እንደዚህ ያለው ታላቅ ስራ ነው።
Show all...
25.26 MB
02:07
Video unavailableShow in Telegram
በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል። Daawwannaa Goondaritti taasifneen haala hojii Misooma Jallisii Magac gamaaggamneerra. Piroojektichi hektaara 870 irra kan buufate yoo ta'u, lafa hektaara 17,000 dhiyeessii jallisiitiin misoomsa jedhamee eegama. Hojii ijoo piroojektichaa kan ta'e laga jallisuun haala milkaa'een xumurameera. Hojiiwwan hafanis yeroo qabameef keessatti hojjetamaa jiru. Jallisiin Magac wayita xumuramu homishtummaa qonnaa naannichaa kan guddisu ta'a.
Show all...
45.01 MB
08:10
Video unavailableShow in Telegram
የገጠር ሽግግርን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ የእርሻ ማሽነሪዎችን ማበራከት ነው ።
Show all...
28.53 MB