Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Open in Telegram
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Show more162 914
Subscribers
-124 hours
+1537 days
+51830 days
Posts Archive
05:59
Video unavailableShow in Telegram
प्रधानमंत्री मोदी जी आपकी इथियोपिया यात्रा व भारत और इथियोपिया के संबंधों को मजबूत करने के आपके निरंतर प्रयास के लिए आपका धन्यवाद । हमारे बढ़ते रणनीतिक संबंध एक महत्वपूर्ण पड़ाव है और हमारे दोनों देशों के बीच और गहरे संबंधों और प्रगति का नया अध्याय प्रारम्भ कर रहे हैं । Narendra Modi
18.98 MB
05:59
Video unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን በመጎብኘትዎ እና የኢትዮጵያ እና ህንድን ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አቀርባለሁ። ትስስራችንን ወደ ስትራቴጂያዊ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔም በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ትብብራችንን ለማላቅ እና የጋራ እድገትን ለመተለም አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን የሚያመለክት ታሪካዊ እጥፋት ነው።
Thank you, Prime Minister Narendra Modi , for your visit to Ethiopia and for your continued efforts to strengthen India–Ethiopia relations. Our elevated ties to a strategic level marks an important milestone and opens a new chapter of deeper cooperation and shared progress between our two countries.
18.98 MB
ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት አድርገናል። ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል። በሁለቱ ሀገራት መካከል በጉምሩክ የጋራ አስተዳደር ድጋፍ፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ምስረታ የመግባቢያ ሥምምነቶችን እንዲሁም በአለምአቀፍ የሰላም ማስከበር ላይ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እና የሚያጠናክረውን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ሥራ የመግባቢያ ሥምምነት የፊርማ ሥነሥርዓት ላይም ተገኝተናል። ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ስትሆን የዛሬዎቹ ውይይቶች እና ሥምምነቶችም ለጋራ ጥቅም በተለያዩ ዘርፎች ያሉንን ትብብሮች ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኛ አቋም ያሳያሉ።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ለይፋዊ ጉብኝት በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ሲሆን ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው።
It is my great pleasure to receive Prime Minister Narendra Modi of India for his official visit. His presence underscores the growing ties between our two countries, and I look forward to meaningful engagements that will further deepen our cooperation across shared priorities.
06:49
Video unavailableShow in Telegram
የአንዳችን ለሌላችን ውበት፤ የአንዳችን ለሌላችን ክብር የሆንባትን ሀገር ኢትዮጵያ፤ አንዱ ዝቅ ሌላው ከፍ ብሎ ሳይሆን ሁላችን እኩል ሆነን በወንድማማች ዐይን ተያይተን በመደመር እሳቤ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን ማሻገር አለብን። በአባቶቻችን ደም የወረስነውን ነጻነት የኢትዮጵያን ብልጽግና በማረጋገጥ ማጽናት ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
28.17 MB
16:37
Video unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በሕብር ቀለም የተሳለች፣ ሕብር ቋንቋ የሚነገርባት፤ በሕብር ደም የተገነባች እንዲሁም በሕብር ጥበብ የምትሻገር ሀገር ናት። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የነበሩ፣ የሚኖሩና ጸንተው የሚቀጥሉ ናቸው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር በገዥ ትርክት ተሸምነን ተቋማዊ ለውጥን እያጠናከርንና ብሔራዊ ጥቅማችንን እያሳካን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን።
38.05 MB
ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሃፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር እ.ኤ.አ በ2027 አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ 32 በማዘጋጀት ረገድ በጋራ ስለምንሰራባቸው መንገዶች ተወያይተናል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ብሎም ዋና ፀሃፊው ከቡድናቸው ጋር በመሆን ኮፕ 32 ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እተማመናለሁ።
I had a fruitful discussion with the Executive Secretary of UN ECA Claver Gatete on the needs and modalities of working together to deliver a truly African COP in 2027. I am confident that the Economic Commission for Africa with the ES and his team will contribute immensely in making COP 32 a remarkable success for Africa.
በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ ክፍል ሁለት
https://youtu.be/nZJ5ZO69mTA
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ጠዋት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዘዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰንን አግኝቼ በቀጠናዊ የጸጥታ እና የበለጠ ትብብር ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።
I welcomed General Dagvin R. M. Anderson, Commander of the U.S. Africa Command, this morning for a constructive exchange on regional security and opportunities for enhanced cooperation.
የሲንጋፖርን ስኬት እና ትምህርት የሚሰጡ የልማት ጉዞ ልምዶችን ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር “የሀገር ግንባታ፣ አለማትን ማገናኘት” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ወግ ተካፍለናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በሀገር ግንባታ፣ በአመራር ዘዴ፣ በኢኮኖሚ ለውጥ እና በጂኦፖለቲካ ላይ ላካፈሏቸው ሀሳቦች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
Taking time to learn from one another through a fireside chat entitled “Building Nations, Bridging Worlds,” with Prime Minister Lawrence Wong as he shares the successes and lessons from Singapore’s growth. I’m grateful for Prime Minister Wong’s insights on nation building governance and leadership, economic transformation.
የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብያለው።
ውይይታችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለንን ግንኙነት ለጋራ ነጋችን ወሳኝ በሆኑ መስኮች በጋራ ለመሥራት በምናደርገው ጥረት ውስጥ አንድ ጠቃሚ ርምጃ ነው። በተለይም በክሂሎት ልማት እና የካርበን ብድር ትብብር ላይ ያደረግናቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ጽኑ እና ለነገው ገበያ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞችን ለማፍራት ብሎም በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ዘላቂ፣ ዝቅተኛ ካርበን የሚያወጣ እድገት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው።
ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችንም ክብር ይሰማናል። በላቀ ተግባራዊ ትብብር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስን በማልማት፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በገንዘብ ልውውጥ ቴክኖሎጂ፣ ሳይበር ደኅንነት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለንን ትብብር ለመጠቀም እጅግ ሰፊ አቅም አለን።
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ማታ አዲስ አበባ ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብያቸዋለው። ይህ ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት አጋርነትን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ ሲሆን፣ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር እድሎችን ለመዳሰስም ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
I am pleased to welcome Prime Minister Lawrence Wong of Singapore on his official visit to Ethiopia. This visit marks an important step in strengthening our partnership. I look forward to productive discussions and to exploring new areas of cooperation between our two nations.
በቡድን 20 ጉባኤ ያደረኳቸውን ሁለትዮሽ ውይይቶቼ የመጨረሻ የሆነውን ውይይት ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለምአቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ አተኩረን አከናውነናል።
The last of my bilaterals at the G20 Summit was with Prime Minister Giorgia Meloni, where we discussed global and regional affairs, as well as key bilateral issues between our countries.
ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር በነበረን ውይይት በኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ለማጠናከር ውይይት አድርገን ነበር። ከኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ቁልፍ መዳረሻዎች አንዷ የሆነችው ኔዘርላንድ ኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብር ለማድረግ ጉልህ አቅም አላት። የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ትብብርን አስመልክቶም እድሎቻችንን ለመመልከትና የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በጉብኝቶች እና የልውውጥ መርሃ ግብሮች እንድንከውን በውይይቱ ሀሳብ አንስቻለሁ።
During our meeting with Prime Minister of the Netherlands, Dick Schoof, we discussed ways to further strengthen the strong ties between Ethiopia and the Netherlands. As one of our key export destinations, the Netherlands offers significant potential to expand investments and economic cooperation. I also highlighted climate action collaboration and explored opportunities to deepen bilateral relations through visits and exchanges.
በቡድን 20 ጉባኤ ያደረኳቸውን ሁለትዮሽ ውይይቶቼ የመጨረሻ የሆነውን ውይይት ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለምአቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ አተኩረን አከናውነናል።
The last of my bilaterals at the G20 Summit was with Prime Minister Giorgia Meloni, where we discussed global and regional affairs, as well as key bilateral issues between our countries.
