en
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

Open in Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
194 696
Subscribers
-7124 hours
-977 days
-64730 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
በመተት አስፈራርታ 3 መቶ ሺ ብር ከግል ተበዳይ ልትቀበል ያለች ተጠርጣሪ መያዙን ፖሊስ ገለጸ። 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ በመተት በቤተሰብህ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ እያለች ስታስፈራራ የነበረችን ግለሰብ በቁጥጥር ሾር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ግለሰቧ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ወሎ ሰፈር አካባቢ ከሚገኝ አንድ ፕላዛ ውስጥ በጽዳት ሰራተኝነት እና በአሳንሰር ተቆጣጣሪነት ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን የግል ተበዳይ በዚሁ ህንጻ ላይ ከሚገኝ የአንድ የግል ድርጅት የፋይናስ ኃላፊ ናቸው። ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት ቃል የኔሰው የሚባል ግለሰብ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ቢኮሎ ከሚባል አካባቢ እንደሚደውል ገልጸው 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ ልጅህን የሰይጣን መሳቢያ አደርጋታለሁ የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት በማያውቁት ስልክ ተደውሎ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። ተጠርጣሪዋ የግል ተበዳይን በመከታተል ካጠናች በኋላ ማንነቷን በመደበቅ እና ድምጿን በመቀየር አስፈራርታ 25ሺ ብር  በባንክ እንዲያስገቡላት ካደረገች በኋላ ቀሪ 275ሺ ብር ለማስላክ ስትሞክር የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት መረጃና ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ልትያዝ ችላለች። በተጨማሪም ፖሊስ ግለሰቧ ለግል ተበዳይ ለመላክ ያዘጋጀችው የማስፈራሪያ  ጽሑፍ የእጅ ስልኳ ላይ መገኘቱን የገለጸ ሲሆን በቁጥጥር ሾር ውላ ምርመራ እየተጣራባት አስታውቋል። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
🤣 157❤ 55🤔 27👍 6👏 3😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
በቅርቡ ዛፍ በማቀፍ ጊነስ እውቅና የሰጣት ኬንያዊት በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እውቅና ተሰጥቷታል። ከቀናት በፊት የራሷን ሪከርድ ሰብራ ያለ ማቋረጥ ለ72 ሰዓታት ዛፍ ያቀፈችው ትሩፊና ሙቶኒ በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለ15 ቢሊየን ዛፍ የመትከል ዘመቻ በአምባሳደርነት ተሹማለች። ከአምባሳደርነት በተጨማሪ ከኬንያ የዱር እንስሳት አስተዳደርና ከኬንያ ቱሪዝም ቦርድ ለእሷና አብረዋት ለነበሩት ቡድኖቿ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ እንዲዝናኑ ሩቶ አዘዋል። ሙቶኒ የ72 ሰዓት ዛፍ የማቀፍ ተግባሯን ባለፈው በተካሄደው የአየር ንብረት ጉባኤ ወቅት በብራዚል ለማድረግ ፈልጋ አስፈላጊው ድጋፍ አልተደረገልኝም ያለች ሲሆን ዊሊያም ሩቶ ሜዳሊያ ከሰጧት በኋላ ብራዚልን ሄዳ እንድትጎበኝ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ዘገባው የኬንያንስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
🤣 90❤ 49👍 10🤔 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢሎን መስክ የተጣራ ሃብት 600 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ፎርብስ ይፋ አደረገ። የኢሎን መስክ የተጣራ ሃብት የስፔስ ኤክስ ዋጋ 800 ቢሊየን ዶላር መገመቱንና ለህዘብ ድርሻው ይሸጣል መባሉን ተከትሎ 600 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል። መስክ 500 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ላይ የደረሰ የመጀመሪያው የምድራችን ሰው ባለፈው ጥቅምት ወር የሆነ ሲሆን 600 ቢሊየን ዶላር ላይም የደረሰ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። መስክ የስፔስ ኤክስ የ42% ባለድርሻ ሲሆን የድርጅቱ ዋጋ ግምትና በቀጣይ አመት ለህዝብ ገበያ እንደሚቀርብ ከተነገረ በኋላ የኢሎን መስክ ሃብት በ168 ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 677 ቢሊየን ዶላር ደርሷል። ኢሎን መስክ ከስፔስ ኤክስ በተጨማሪ የቴስላ እና የኤክስ ኤአይ ተቋም ከፍተኛ ባለድርሻ ሲሆን እነዚህም ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው እየጨመረ ይገኛል። የኢሎን መስክን ሃብት መጨመር ተከትሎም የአለማችን 10 ሃብታም ግለሰቦች የያዙት የሃብት መጠን 2.5 ትሪሊየን ዶላር ተሻግሯል። በዚህ አመት ብቻ የአለማችን አስሩ ሃብታሞች ሃብት በ558.9 ቢሊየን ዶላር ጨምሯል ሲባል ዘጠኙ ከአሜሪካ ሲሆኑ ከአስሩ ስምንቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው። በዚህ አመት የኢሎን መስክ ሃብት በ205 ቢሊየን ዶላር ሲጨምር በሁለተኝነት የተቀመጠው የጎግሉ ላሪ ፔጅ ሃብት በዚህ አመት በ96.8 ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 265 ቢሊየን ደርሷል። በሶስተኝነት የጎግሉ ሌላኛው መስራች ሰርጂ ብሪን በ247 ቢሊየን ዶላር ሲቀመጥ የአራተኛ ስፍራውን የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ በ246 ቢሊየን ዶላር ይዞታል። መስክን ከወራት በፊት በመብለጥ የአለማችን ቱጃሩ ተብሎ የነበረው ላሪ ኤሊሰን ሃብቱ በ46.1 ቢሊየን በመጨመር በ238 ቢሊየን ዶላር አምስተኛ ሆኗል። ዘገባው የሮይተርስ እና አናዶሉ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 51👏 40🤣 17🤔 12🤯 10👎 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Show all...
❤ 14🤣 4👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኬንያ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርዓቶች ከእስራኤል ተረከበች። ኬንያ "SPYDER" እና "PYthon" የተሰኙ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ከእስራኤል ታጥቃለች። ራፋኤል አድቫንስድ መከላከያ ስርዓት በተባለ ተቋም የሚመረተው ስርዓት የአውሮፕላን፣ ድሮን እና ሚሳኤሎችን ስጋት መቀልበስ ይችላል ተብሏል። ኬንያ ስርዓቱን የታጠቀችው ከእስራኤል መንግስት በደገፈው የ26 ሚሊየን ዶላር ወይም 3.4 ሽልንግ ብድር ነው ተብሏል። ኬንያ "SPYDER" የተሰኘውን የአየር መከላከያ ስርዓትም ከኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ቀጥላ የታጠቀች ሶስተኛዋ የአፍሪካ ሃገር ሆናለች ተብሏል። የኬንያ የአየር መከላከያ ስርዓት ግዢ በኬንያና እስራኤል መካከል ያለውን ትብብር ያሳየ ነው ሲባል እንደ ድሮን ያሉ መሳሪያዎች እየታጠቀ ካለው አልሸባብ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከትም ይጠቅማል ተብሏል። ዘገባው የኬንያንስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 42👍 26🤣 21
00:23
Video unavailableShow in Telegram
አድናቆት የተቸረው ግለሰብ . . . ምን አድርጎ ይሆን ? በአውስትራሊያ በአይሁድ በዓል ላይ ጥቃት ሲፈፀም ጣልቃ የገባው ግለሰብ በብዙዎች አክብሮት ተችሮታል። እሁድ እለት ሁለት ግለሰቦች በቦንዲ የባህር ዳርቻ የአይሁድ በዓል ሲከበር ጥቃት ከፍተው 15 ሰዎች ተገድለዋል። በዚህ ጥቃት ወቅትም አንዱ ጥቃት ፈፃሚ ጥቃት እየፈፀመ በነበረበት ወቅት አንድ መንገደኛ ወደ ጥቃት ፈፃሚው ሮጦ ታግሎ መሳሪያውን ሲያስጥል የሚያሳይ ቪዲዮ ከተሰራጨ በኋላ ግለሰቡ ጀግና ተብሎ ተወድሷል። ግለሰቡ አህመድ አል አህመድ የተባለ የ43 አመት የፍራፍሬ ሱቅ ባለቤት ሲሆን መሳሪያውን ከነጠቀው በኋላ ጥቃት አድራሹ ወደኋላ ሲሸሽ መሳሪያውን አስቀምጦ ሲሄድ ይታያል። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ግለሰቡ እራሱን አደጋ ውስጥ ከትቶ መሳሪያ መንጠቁን ገልፀው በወቅቱ በደረሰበት ጉዳት በሆስፒታል ኦፕሬሽን እንደተሰራ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውስትራሊያ ለፀረ ሴማዊነት ቦታ የለም ሲሉ የአል አህመድ ዘመድ አል አህመድ በሁነቱ 2 ጊዜ እንደተተኮሰበትና በሆስፒታል እንደሆነ ገልጿል። ጥቃቱን የ50 አመት አባትና የ24 አመት ልጅ ሲፈፅሙ አባት በፖሊስ ተኩስ መሞቱና ልጅ ደግሞ ሆስፒታል መሆኑ ተገልጿል። ከተገደሉት 15 ሰዎች በተጨማሪ 40 ሰዎች ሲቆስሉ ጥቃቱን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ጨምሮ በርካቶቼ የፀረ ሴማዊነት የሽብር ጥቃት ብለውታል። ዘገባው ከአልጄዚራና ሲቢኤስ የተገኘ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
love_majewski_for_the_muslim_hero_that_disarmed_one_of_the_ter.mp48.17 KB
❤ 120😢 11🕊 7👏 5🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቁጥሮች ሾለ ሱዳን የሰብዓዊ ቀውስ ምን ይላሉ? - 21.2 ሚሊየን ሰዎች ወይም የሱዳን ህዝብ 45 በመቶ ከፍተኛ ለሆነ የምግብ ችግር ተጋልጠዋል። - 9.5 ሚሊየን ሰዎች የውስጥ ተፈናቃይ ሲሆኑ 4.35 ሚሊየን ሰዎች ሃገሪቱን ለቀው ተሰደዋል። - 10 ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል። - ከተፈናቀሉት መካከል 51% ያህሉ ህፃናት ናቸው። -  ከአሁኑ ጦርነት መጀመር በፊት 2.32 ሚሊየን ሰዎች ተፈናቅለው ነበር። - ከሃገር ከተሰደዱት መካከል 1.5 ሚሊየኑ ወደ ግብፅ፣ 1.25 ሚሊየኑ ወደ ደቡብ ሱዳን እና 1.2 ሚሊየኑ ወደ ቻድ ሲሰደዱ ከተሰደዱት መካከል 30 በመቶዎቹ የሱዳን ዜጋ አይደሉም። - በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡት ሆስፒታሎች ቁጥር ከ25 በመቶ በታች ናቸው። - በጤና መሰረተ ልማቶችና ባለሙያዎች ላይ 200 ጥቃቶች ተፈፅመዋል፤ 20 አምቡላንሶች ወድመዋል። - ከ123,000 በላይ ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው ከ3500 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ምንጭ: አልጄዚራ 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 23😢 20🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
📣 የጨረታ ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ (ፎረም ህንጻ) እና በአቡነ ጴጥሮስ ግቢ ህንጻ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል። 🏢 የሚከራዩ ቦታዎችና አገልግሎት የሚገኙባቸው ግቢዎች: ፎረም ህንጻ (12 ቤቶች) እና የአቡነ ጴጥሮስ ህንጻ (11 ቤቶች)። የሚውሉባቸው አገልግሎቶች: ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቅ፣ ለቢሮ፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለሾው ሩም፣ ለጂም እና ለዲስፕሌይ ስራ ሊውሉ ይችላሉ። 📝 የጨረታ ሰነድ ለማግኘት፡ ተጫራቾች የቦታ ስፋትና የኪራይ መነሻ ዋጋን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን በሚከተለው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ። AAU ድህረ ገጽ: https://www.aau.edu.et/announcements/detail?title=AAU~Rental~Spaces~Bid~Announcement~detailed~information~and~bid~documents 5 አድራሻ: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ 6 ኪሎ ዋናው ግቢ፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣ ቢሮ ቁጥር 314። ለተጨማሪ ጥያቄዎች 251-111220001 ወይም 09-98-656426 ላይ ይደውሉ።
Show all...
❤ 15👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርሪልስቴት፡ ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው። ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል 👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 106ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን አዋሬ 🎯65/35 አከፍፈል 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉 1መኝታ 78ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን 👉 3 መኝታ 117ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ  2.6 ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን 👉 157 ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን ቀሪውን 80% በ 15ዙር  ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ  ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት፤ * 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 0980782850
Show all...
❤ 6👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአዲሱ የአሜሪካ ውሳኔ ተጠቂ ይሆናሉ። አሜሪካ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጧ ይታወሳል። በዚህ ከለላ ስርም 5001 ኢትዮጵያውያን የህግ ከለላ ተሰጥቷቸው እንደነበርና 263 የሚሆኑ ተጨማሪ ዜጎች አመልክተው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል። ጊዜያዊ የህግ ከለላው መቼ ተሰጠ? አሜሪካ በፈረንጆቹ ታህሳስ 12,2022 በኢትዮጵያ የነበረውን  ግጭት ተከትሎ ለኢትዮጵያ ዜጎች ጊዜያዊ የህግ ከለላ መስጠት የጀመረች ሲሆን በሚያዚያ 2024 ዳግም ተራዝሞ ነበር። የጊዜያዊ የህግ ከለላው ለምን ተነሳ? አሜሪካ ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ከሚመለከታቸው የራሷ የመንግስት ተቋማት ጋር ንግግር በማድረግ የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ መገምገሙን አንስታለች። በግምገማው የተዳሰሱ ነገሮች - በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለ ግጭት ስለመኖሩ - ይህ ግጭት በመኖሩ ግለሰቦች ቢመለሱ የሚያጋጥማቸው የደህንነት ስጋት ስለመኖሩ - የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዳይመለሱ የሚያደርግ ከአቅም በላይ የሆነና ጊዜያዊ ችግር ስለመኖሩ - የኢትዮጵያ ዜጎች በጊዜያዊነት በአሜሪካ ቢቆዩ የአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም ስለመፃረሩ ከግምገማው በኋላ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እየተካሄደ ያለ ግጭት የተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ስጋት ውስጥ ይከታል የሚለውን መመዘኛ እንደማያሟላ ተቀምጧል። አሜሪካ በ2022 በትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የነበሩ ግጭቶች ይህ የጊዜያዊ ከለላ እንዲሰጥ ምክንያት ነበሩ ስትል የትግራዩ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቋጨቱንና በኦሮሚያም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አካል ጋር ክልሉ የሰላም ስምምነት መፈራረሙን፣ ታጣቂዎች መግባታቸውንና ከስምምነቱ በኋላ ግጭት መቀነሱንም አንስታለች። አሜሪካ የትግራዩ ጦርነት ሲገባደድ በአማራ ክልል ግጭት መቀስቀሱን ጠቅሳ በመንግስት እና ፋኖ መካከል ያለው ግጭት መቀነሱን ንፁሃን ግን ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩ አንስታለች። አሜሪካ ኢትዮጵያ ትኩረቱን መሰረተ ልማት እና የሰብዓዊ ልማት ግንባታ ላይ ያደረገ የ33.7 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ በጀት ማፅደቋን አንስታ እነዚህ ማሻሻያዎች የተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከት ነገር እንደሌለ ያሳያሉ ብላለች። የውስጥ መፈናቀሎች ቀንሰዋል ያለችው አሜሪካ የምግብ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች መሻሻላቸውን ለዚህም ማሳያው አሜሪካ ልሡ በሰሜን ኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ለጣምራ ኮሚቴ ማስተላለፏን አንስታለች። ከ2022-2025 ድረስ 2147 የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመመለሾ የጉዞ ሰነድ መጠየቃቸውንም በጥሩ ጎን ተመልክቼዋለሁ ብላለች። ከቪዛ ጊዜ በላይ መቆየትን በተመለከተ አሜሪካ ምን አለች? አሜሪካ በ2024 የኢትዮጵያ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ከቪዛ ጊዜ በላይ የመቆየት ምጣኔ ነበራቸው ብላለች። በዚህም: - ለB-1/B-2 ቪዛ የ8.27 በመቶ ከቪዛ ጊዜ በላይ የመቆየት ይህም ከአማካዩ በ250% እንደሚበልጥ - ለF,M እና J ቪዛ የ13.95% የመቆየት ምጣኔና ይህም ከአማካዩ በ330% እንደሚበልጥ እና የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ እንደሆነባትም ጨምራ ገልፃለች። ምን ያህል ሰዎች ከለላው ነበራቸው? የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ 5001 የኢትዮጵያ ዜጎች ይህ ከለላ ፀድቆላቸው ተጠቃሚ እንደነበሩ ሲገልፅ እንደ ባለፈው ህዳር መረጃ ተጨማሪ 263 ሰዎች ይህንን ከለላ ለማግኘት ጥያቄ አቅርበዋል። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 111😢 22🤔 5🤷‍♂ 2👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የምያንማር መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ዜጎቻቸውን እንዲቀበሉት ጥያቄ አቅርቧል። ምያንማርን እያስተዳደረ የሚገኘው ወታደራዊ መንግስት በማጭበርበሪያ ካምፖች የያዛቸውን የውጪ ሃገራት ዜጎች ሃገራቱ እንዲቀበሉት ጠይቋል። በቅርቡ በታይላንድ ድንበር አካባቢ በተደረጉ ዘመቻዎች በርከት ያሉ የውጪ ሃገራት ዜጎች መያዛቸው ሲታወስ እነዚህን የያዛቸውን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር ስለተቸገረ የዜጎቹ ሃገራት በተቻለ ፍጥነት ቶሎ እንዲቀበሉ ምያንማር ጠይቃለች። ምያንማር ዘመቻው ባለፈው ጥር ከተጀመረ ወዲህ ከ47 ሃገራት የተውጣጡ 13,272 የውጪ ሃገራት ዜጎችን መያዟን ስትገልፅ አብዛኞቹ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው አሁንም 1655 ያህሉ እዛው እንደሆኑ ገልፃለች። ከቀሩት መካከል ከ500 የሚበልጡት የቻይና ዜጎች ሲሆኑ ከ100- 300 የሚደርሱ #የኢትዮጵያ ዜጎች እንደዚሁም የቬትናም፣ የኬንያ፣ የኢንዶኔዥያ እና የህንድ ዜጎችም እንዳሉ ምያንማር አስታውቃለች። ምያንማር አብዛኞቹ ወደ ሃገራቸው ያልተላኩ የአፍሪካ ሃገራት ዜጎች ሃገራቸው በታይላንድም ይሁን በምያንማር ኤምባሲ ስለሌላቸው ነው ብላለች። ምያንማር በአመት 40 ቢሊየን ዶላር ለወንጀለኛ ቡድኖች የሚያስገኙ የማጭበርበሪያ ካምፖች መፍለቂያ ስትሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ የበርካታ ሃገር ዜጎች ተታለው በካምፖቹ በግዳጅ እንዲሰሩ ይደረጋሉ። ዘገባው የአሶሽየትድ ፕሬስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 71
Photo unavailableShow in Telegram
ዩዌሪ ሙሴቬኒ በተለምዶ "Gen Z" በመባል የሚጠሩትን የሃገሬውን ወጣቶች ተችተዋል። ከፈረንጆቹ 1997 -2012 ባለው የዲጂታል ዘመን የተወለዱ ሰዎች "Gen z" የሚል ስያሜ ሲሰጣቸው የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይኸንን ትውልድ ተችተዋል። ሙሴቬኒ " እኔ ወጣት ሳለሁ ሾለ አውሮፓ እግር ኳስ ሳይሆን ሾለ አፍሪካና ኡጋንዳ ነፃነት ነበር የማወራው" ያሉ ሲሆን " FRONASA[ የእሳቸው የትግል ድርጅት] ስንመሰርት እድሜዬ 26 ነበር" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ " እናንት Gen Z ትውልዶች ይበልጥ አሰፈላጊ ነው ብላችሁ የምታስቡት ነገር ምንድን ነው" ብለው በመጠየቅ" ስታወሩ የምሰማው ነገር' Vibe,Vibe,Vibe' ነው ፤ ለመሆኑ 'Vibe' ምንድን ነው? ምንድን ነው የምትበሉት? እንዴትስ ራሳችሁን ትከላከላላችሁ?" በማለት ትውልዱ ከብሔራዊ ጥቅምና ኢኮኖሚ ይልቅ ለሚመጡ ጊዜያዊ ነገሮች ትኩረት መስጠቱን ወቅሰዋል። ዘገባው ከPulse uganda የተገኘ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
📣 #Ad የፋይናንስ አማራጮችን በማስፋት የንግድ እንቅስቃሴዎን የሚያሳድጉበት ኢግዚቢሽን! ታህሳስ 8,2018፣ ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል አዲስ አበባ መግቢያ በነፃ!
Show all...
❤ 112👍 36🤣 6👏 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአውሮፓ ህብረት በሶማሊያ ላለው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ድጋፍ ዳግም መስጠት ሊጀምር ነው። የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ የቀጥታ የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ካቆመ ሁለት አመት ያለፈው ሲሆን ከሁለት አመት ቆይታ በኋላ ከ2026 ጀምሮ ድጋፍ ለመስጠት ማቀዱ ተዘግቧል። ህብረቱ ለተልዕኮው የሚሰጠው ገንዘብ፣ የቆይታ ጊዜና ሌሎች ነገሮች የህብረቱ 27 አባል ሃገራት ስምምነት ላይ ሲደርሱ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። የአውሮፓ ህብረት በሶማሊያ ላለው ተልዕኮ ፋይናንስ በመሰጠት ቀዳሚ የነበረ ሲሆን የአሁኑ እንቅስቃሴ ወደቀደመው ስፍራ ሊመልሰው ይችላል። በሶማሊያ ያለው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ከአሜሪካ ድጋፍ መቀነስ እና ተመድ በ2023 በወሰነው መሰረት ለአምስት አመት በጀት የሚሆን የ832 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ መዘግየት እየፈተነው ይገኛል። የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ አመታዊ በጀት 166.5 ሚሊየን ዶላር ሲደርስ የአውሮፓ ህብረት የሚሰጠውን ድጋፍ ወደ ሰብዓዊ ድጋፍ ብቻ በመገደብ በ2025 67 ሚሊየን ዩሮ ደግፏል። ተልዕኮው በፋይናንስ በሚፈተንበትና አልሸባብ ዳግም ባንሰራራበት ወቅት የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑ ይበል የሚያሰኝ ውሳኔ ሆኗል። ዘገባው የኢስት አፍሪካን ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 26🤣 2🤔 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
የፋይናንስ አማራጮችን በማስፋት የንግድ እንቅስቃሴዎን የሚያሳድጉበት ኢግዚቢሽን!! የፋይናንስ አቅርቦትን በአንድ ቦታ ላይ በሚያገኙበት ኤግዚብሽን ላይ በመገኘት ✨ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ዙሪያ ግንዛቤዎን ማሳደግ ይችላሉ ። ✨ ከባንኮች እና ማይክሮ ፍይናንስ ተቋማት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይፈጥራሉ። ✨ ከመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ቀጥተኛ ውይይትን ያደርጋሉ ። አጋጣሚውን ይጠቀሙ!! ታህሳስ 8,2018፣ ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል አዲስ አበባ መግቢያ በነፃ !!!
Show all...
❤ 8
Photo unavailableShow in Telegram
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!! 🌟አያት ግራንድ ሞል ✨ 3000 የንግድ ሱቆች ✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ ✨ከ 24 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው ✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል 🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ 🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ  በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!! 💥ለበለጠ መረጃ በ 251944856735 በቀጥታ @tegegne123 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
Show all...
❤ 9
Photo unavailableShow in Telegram
ደቡብ ሱዳን በተመድ ተልዕኮ ሾር ያሉ አውሮፕላኖችን ከስለላና ከሃብት ማሸሽ ጋር በተያያዘ እንዳይሰሩ ማድረጓን ገለፀች። ደቡብ ሱዳን በሃገሯ ላለው የተመድ ተልዕኮ በኮንትራት የሚሰሩ አውሮፕላኖች የተፈጥሮ ሃብቴን እያሸሹ ነው እንደዚሁም የስለላ መሳሪያ ተገጥሞላቸዋል ስትል ስሞታዋን አሰምታለች። የደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰማያ ኩምባ ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ አራት አውሮፕላኖች አገልግሎት እንዳይሰጡ መደረጉን አንስተዋል። ሚኒስትሩ ሁለት አውሮላኖች ያለ መንግስት እውቅና የስለላ መሳሪያ እና የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት  እንደተገጠመባቸውና የቀሩት ሁለቱ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን መካከል የተፈጥሮ ሃብት ሲያዘዋውሩ እንደተገኙ ገልፀዋል። ደቡብ ሱዳን ውንጀላው ተልዕኮው ላይ ሳይሆን አውሮፕላኖቹን በሚያስተዳድረው አካል መሆኑን ስትገልፅ በገለልተኛ ኮሚቴ ምርመራው መጠናቀቁንና ውሳኔ እንደሚሰጥበት ገልፃለች። ተመድ ከሩዋንዳ ወታደራዊ የአቪየሽን ድርጅት ጋር ኮንትራቱን በቅርቡ ማቋረጡ ሲታወስ፣ ደቡብ ሱዳን ከአሁኑ የአውሮፕላን ኦፕሬተር ውጪ ሌሎቹ ስራቸዉን  ቀጥለዋል ብላለች። ዘገባው የ Radio Tamazuj ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 47👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
ጋና ከሳይበር ወንጀሎች ጋር በተያያዘ 32 የናይጄሪያ ዜጎችን መያዟን ገለፀች። የጋና የሳይበር ደህንነት አስተዳደር ከብሔራዊ ደህንነት ቢሮው ጋር በመሆን የፍቅር ማጭበርበር(Romance Scam) ሲፈፅሙ ነበር ያላቸውን 32 የናይጄሪያ ዜጎች በቁጥጥር ሾር አውሏል። የናይጄሪያ ዜጎቹ በተያዙበት ወቅትም ለወንጀል ተግባሩ ሲጠቀሙባቸው ነበሩ የተባሉ 31 ላፕቶፖችና 15 የሞባይል ስልክ አብሮ ተይዟል። የኤሌክትሮኒክስ እቃዎቹ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ያለችው ጋና እርምጃው የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከልና የዲጂታል ደህንነትን ለማረጋገጥ የጀመርኩት እርምጃ አካል ነው ብላለች። ከቅርብ አመታት ወዲህ ምዕራብ አፍሪካ በተለይም ናይጄሪያ የሳይበር ወንጀሎችና ማጭበርበሮች መነሻ በመሆን እያገለገለች ስትሆን በርካቶችም በዚህ የማጭበርበር ተግባር ሚሊየን ዶላሮችን አጥተዋል። ኢንተርፖልም በተደጋጋሚ ጊዜ በቀጣናው ባደረጋቸው ኦፕሬሽኖች የተለያዩ አጭበርባሪዎችን መያዙን መግለፁ ሲታወስ ማይክሮሶፍትም በቅርቡ መቀመጫቸውን ናይጄሪያ ያደረጉ አጭበርባሪዎች የሚጠቀሙባቸውን ድህረገፆች መዝጋቱ ይታወሳል። ዘገባው ከሄራልድ ጋና የተገኘ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
📣 #Ads 🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች  ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ አድርገናል። ይደውሉ ☎️ 0900025097
Show all...
❤ 41🤔 4🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዚምባቡዌ በአንዳንድ የቢዝነስ ዘርፎች የተሰማሩ የውጪ ሃገር ዜጎች ባለቤትነታቸውን ለሃገሪቱ ሰዎች እንዲያስተላልፉ የሚያዝ ህግ አውጥታለች። ዚምባቡዌ ከታህሳስ ወር 2025 ጀምሮ በሚቀጥሉት 3 አመታት ውስጥ በውጪ ሃገራት የተያዙ በአንዳንድ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ቢዝነሶች አብዛኛውን ባለቤትነታቸውን ለሃገሬው ሰው እንዲያስተላልፉ አዛለች። በፀጉር ስራ፣ በዳቦ ቤት፣ በትራንስፖርት፣ በችርቻሮ ሱቅ የተሰማሩ የውጪ ዜጎች የድርጅታቸውን 75% ባለድርሻነት ለዚምባቡዌ ዜጋ እስከ 2028 ድረስ ካላስተላለፉ ስራቸው እንደሚዘጋና ለቀው እንደሚወጡ ዚምባቡዌ አዛለች። ትላልቅ የውጪ ኢንቨስተሮች ትልቅ መጠን ያለው ገንዘብ ኢንቨስት ካደረጉና ከ100 በላይ የዚምባቡዌ ዜጎችን ከቀጠሩ መስራታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል። የባንክ ዘርፉና ግዙፍ የማዕድን ማውጣት ስራዎች ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ ያለችው ዚምባቡዌ ውሳኔው ተራውን የዚምባቡዌ ዜጋ ለማነሳሳት ያለመ መሆኑን ብትገልፅም የውጪ ኢንቨስተሮች እንዳይሸሿት ተሰግቷል። በአፍሪካ አሁን አሁን ቀላል የሚባሉ ቢዝነሶች ላይ የውጪ ሃገራት ዜጎች እንዳይሳተፉ መከልከል እየተለመደ የመጣ ሲሆን ከወራት በፊት ታንዛኒያም የውጪ ሃገራት ዜጎች በ15 የቢዝነስ ዘርፎች እንዳይሳተፉ መከልከሏ ይታወሳል። ዘገባው የDW ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 42👏 16👎 13👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
የሊቢያ ትልቁ ሙዚየም ከጋዳፊ መውደቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከፍቷል። በትሪፖሊ የሚገኘው አስ ሳራያ አል ሃምራ በመባል የሚታወቀው የሊቢያ ብሔራዊ ሙዚየም ከ14 አመታት ቆይታ በኋላ ዳግም ተከፍቷል። የሊቢያ ትልቁ ሙዚየም በ2011 የወቅቱ የሃገሪቱ መሪ በነበሩት ሙሐመር ጋዳፊ ላይ አመፅ መቀስቀሱን ተከትሎ ተዘግቶ ቆይቷል። በ2021 ወደ ስልጣን የመጣው መቀመጫውን በትሪፖሊ ያደረገው የብሔራዊ አንድነት መንግስት በ2023 የሙዚየሙን እድሳት ያስጀመረ ሲሆን የዚህ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዲቤቢያ የሙዚየሙ መከፈት ሊቢያ ተቋማቷን ዳግም እየገነባች ስለመሆኗ ማሳያ ነው ብለዋል። በ10,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሙዚየም ግንባታው በ1980ዎቹ ሲደረግ ሙዚየሙ አሁን ለተማሪዎች ብቻ መከፈቱንና በመጪው አዲስ አመት ለሁሉም ሰው ክፍት እንደሚደረግ ተገልጿል። ከጋዳፊ መውደቅ በኋላ ትርምስ ውስጥ የከረመችው ሊበያ በዩኔስኮ በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ 5 መስህቦች አሏት። ሊቢያ በአሁኑ ጊዜ ተመድ እውቅና በሚሰጠውና በዋነኝነት በቱርኪዬ በሚደገፍ መቀመጫውን ትሪፖሊ ባደረገ መንግስትና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ግብፅ እንደዚሁም ሩሲያ በሚደገፈው መቀመጫውን ቤንጋዚ ባደረገው የካሊፋ ሃፍታር መንግስት እየተመራች ትገኛለች። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 43🕊 5👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ 🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄 🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት 💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር 💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር 💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ 🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ) 💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር 💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር 💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር በግንባታ ላይ የሚገኙ ይደውሉልን የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ! ☎️0900025097 #telegram (@SamuelMERITRealtor) https://t.me/addisapartmentforu
Show all...
❤ 9