68 961
Subscribers
No data24 hours
-137 days
-96730 days
Posts Archive
አስገራሚ የሆኑ የሳይኮሎጂ (psychology) ግኝቶችና እውነታዎች
1)በጥናቶች መሰረት ገንዘብን ንብረት ማካበት ላይ ከማዋል ይልቅ በ experience(በተግባር ነገሮችን ማየት) ላይ ማጥፋት የበለጠ ደስተኛ ያደርጋል።
2) በደስተኞች ሰዎች እራሳችንን መክበብ ወይም ከደስተኞች ጋር ብዙ ጊዜ አብሮ መሆን እራሳችንንም ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናል።
በPsychoneuroendocrinology journal ላይ የታየ አዲስ ጥናት መሰረት ደስታም ሆነ ጭንቀት ተላላፊነት ባህሪይ አለው፡፡ እና ከየትኛውም አይነት ሰዎች ጋር መሆን የኛ ስሜት ላይ በዛው መሰረት ተጽዕኖ ያደርጋል፡፡
3) ዘፈን ስለ ማንኛውም ነገር ያለን አመለካከታችን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል:
በ Groningen University በተካሄደው ጥናት መሰረት ዘፈን አመለካከታችን ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በተለይ አሳዛኝ ዘፈን እና የደስታ ዘፈን ስንሰማ ስለአለም ያለን አመለካከታችን ላይ በዛው መሰረት ተጽእኖ ያደርጋል፡፡
4) ብዙ የዛሬ ልጆች(በተለይ ምዕራባዊያን) በ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ ከነበሩት የአእምሮ በሽተኞች ተመሳሳይ መጠን ያለው ጭንቀት አለባቸው።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የዛሬ ሰው ከድሮው ሰው እጅግ በበለጠ ሁኔታ ጭንቀት አለበት። ለዚህ ምክንያት ከሆኑት አንዳንዶቹ ሱሰኛ መሆን፣ ከህብረተሰቡ ጋር ብዙ ተቀራራቢነት አለመኖር፣ ስራ መቀያየር፣ የኑሮ ቦታ መቀያየር አንዳንዶቹ ናቸው፡፡
5)ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ገንዘብን ለሌሎች ማዋል በራስ ከማዋል የበለጠ ደስታን ይሰጣል:
በ Harvard buisness school በተደረገው ጥናት መሰረት ሰዎች ለሌሎች ሰዎች ገንዘብ ሲሰጡ ከማይሰጡ ይልቅ የበለጠ ደስተኞች ናቸው፡፡
6) ገንዘብ ደስታን ሊገዛ ቢችልም ከተወሰነ የገንዘብ መጠን ካለን በኋላ ግን መጨመሩ ደስታችን ላይ ብዙም ለውጥ አያመጣም።
7) አንዳንድ እንደፀሎት እና ቤተ ክርስቲያን መከታተል አይነት ሃይማኖታዊ ልምዶች የአእምሮን ጭንቀት ይቀንሳሉ:
“The American Psychiatric Publishing Textbook of Mood Disorders” ባጠናው ጥናት መሰረት ሃይማኖታዊ ልማድን የሚያዘወትሩ ሰዎች ከማያዘወትሩት ሰዎች በጭንቀትና በሌሎች የአእምሮ ችግሮች ለመሰቃየት ያላቸው እድል በጣም ያነሰ ነው፡፡
8) ከ 18 እስከ 33 አመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ዕድሜ ክልል ካሉ ሰዎች የበለጠ ጭንቀት አለባቸው፡፡ ከ33 አመት በኋላ የጭንቀት መጠን እየቀነሰ ይሄዳል፡፡
9) እራስን በቂ ተኝቻለሁ ብሎ ማሳመን በቂ ባይተኛ እራሱ ካለማሳመኑ ይልቅ በዕለት ተግባራችን ላይ የተሻለ ንቃት እንዲኖረን ያደርጋል።
በJournal of Experimental Psychology በታተመው ጥናት መሰረት ጥናት የተደረገባቸው ሰዎች በቂ ሳይተኙም ከበቂ በላይ ተኝታችኋል ተብለው ሲነገሩ ካልተነገሩት ይልቅ እጅግ የተሻለ ንቃትና የንቃት ተግባር አሳይተዋል፡፡
10) አእምሮአቸው ብሩህ የሆኑ ሰዎች ስለራሳቸው ዝቅ አድርገው ነው የሚያስቡት፡፡ ብሩህ ያልሆኑና ብዙም የማያውቁ ሰዎች ግን በተጋነነ መልኩ ስለራሳቸው ከፍ ያለ ስሜት አላቸው፡፡
11) ከአሁን በፊት የተደረገ ክስተትን ስናስታውስ በሚያስገርም ሁኔታ ድርጊቱን ሳይሆን የምናስታውሰው አሁን ካስታወስነው በፊት ስለሱ ያስታወስንበትን ጊዜ ነው፡፡
12) አፍ ከፈቱበት ቋንቋ ውጪ ሌላ ቋንቋ ከቻሉ ውሳኔዎችን በሌላኛው ቋንቋ መወሰን ውሳኔው የበለጠ ምክንያታዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
ምንጭ:-/psychology.html
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
👍 52❤ 8🤔 1
የህይወት ክህሎት
ሕይወት ክህሎት ነው። እንደየትኛውም ክህሎት መሠረታዊ ሕግጋቱን ካወቅህና ለመለማመድ በቂ ጊዜ ከመደብህ በኋላ የተሻልክ ለመሆን ትችላለህ፡፡ ለሕይወት ራስህን አሳልፈህ ስትሰጥ ጠቢብነትን ልትጎናጸፍ ትችላለህ፡፡በሕይወት ታላቅ ለመሆን ትችል ዘንድ ማድረግ የሚኖርብህ ሦስት ነገሮች ተከታዮቹ ናቸው፡
1.ለሕይወት ትኩረት ስጥ፡ - በህይወትህ ለምን ዓላማ ለመቆም እንደምትፈልግ፣ ከእስካሁኑ ኑሮህ ምን እንደተማርክ እንዲሁም ትተኸው የምታልፈው ልምድ ምን እንደሚሆን ለማሰብ ጊዜ መድብ፡፡ ጊዜ ዳግም ላይመለስ ደቃቅ አሸዋ በጣቶቻችን መካከል ሾልኮ እንደሚፈስሰው ሁሉ ያመልጠናል፡ : ተሰጥዖህ ምን እንደሆነ ለማወቅ ቀኖችህን ተጠቀም፡፡ ኤርማ ቦምቤክን ንግግር ያስታውሰኛል ፡- ‹‹በሕይወቴ ፍፃሜ ከእግዚአብሔር ፊት ስቆም «የሰጠኸኘን መክሊት በሙሉ ተጠቅሜአለሁ ለማለት እችል ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
ዘወትር ማለዳ ከዓለም ጋር ከመደባለቅህ በፊት ማስታወሻ የመጻፍ ልምድ አዳብር፡፡ ቀኑን በስኬት እንዳጠናቀቅህ ይሰማህ ዘንድ ማከናወን ስለሚኖርብህ ግቦች አስብ፤ በጽሑፍ
አስፍራቸው፡፡ አጥብቀህ ስለምትይዛቸው እሴቶችህ አስብ፤ ካለፈው እለት የቀሰምከውን እውቀት አስብ፡፡ ይህም ከስህተትህ እንድትማር መንገድ ይሆነሀል።
2.ሕይወትን አጣጥሞ መኖር፡- ከዘመናት ተሞክሮዬ አንድ ነገር ተምሬአለሁ፡- ሕይወት የምትመልስልህ የሰጠሃትን ነው፡፡ ትናንት ምሽት ከጓደኞቼ ጋር ራት እየተመገብን ሳለ ስለ ግብ ማስቀመጥ መነጋገር ጀመርን። ከመካከላችን አንዱ ‹‹ነገር ግን በሕይወት እርግጠኛ ለመሆን ሳንችል ግብ ለምን እናስቀምጣለን?›› በማለት ጠየቀ፡፡ የእኔ ምላሽ ይህ ነበር፡- ‹‹በሕይወት እርግጠኛ ለመሆን አለመቻል ታላቅ የመሆን ኃይልህን ተግባራዊ ማድረግ አይኖርብህም ማለት አይደለም፡፡ ግቦችህን አስቀምጥ፡፡ እቅዶችህን ንደፍ፣እርምጃ ውሰድ ፤ ሕልሞችህን እውን ለማድረግ ትጋ፡፡ የግል ኃላፊነት ማለት ይኸው ነው፡፡ ነገር ግን የቻልከውን ነገር ሁሉ ከፈጸምክ በኋላ የተቀረውን ነገር ሁሉ ለሕይወት ተወው፡፡
3.በሕይወት ሀሴት አድርግ፡- ሕይወትን ቀላል አድርገን አንመለከትም፡፡ ነገር ግን የቢሊየነሩም ሆነ የጎዳና አዳሪው መጨረሻ ሞት መቀበር ነው፡፡ ሁላችንም ወደ አፈር እንመለሳለን፡፡ ስለዚህ እንዝናና። ሚግለን ማክላፍሊን እንዳለው ‹‹ጥቂቶቻችን ግሩም ልብ-ወለድ ልንጽፍ እንችላለን፧ ሁላችንም ግን ያን ልብ-ወለድ ልንኖር እንችላለን፡፡››
✍️ ሮቢን ሻርማ
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
👍 43❤ 12
The person you will be in 10 years depends on the:
⭐️skills you learn
⭐️books you read
⭐️habits you create
⭐️network you build
⭐️mindset you develop
Start investing in yourself today.
Your future is written in the present.
@Human_intelligence
🔥 39👍 14❤ 7
የህይወት ወሳኝ ጥያቄዎች
ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች መነሻ ሀሳቦች እንዲሆናችሁ ብዬ ነው ያቀረቡኩት እናንተ የራሳችሁን ጥያቄ መፍጠር ትችላላችሁ።
1.በህይወቴ ላሳካው የምፈልገው አላማ እና ራዕይ ምንድን ነው?? ከአምስት ወይም ከአስር አመት በኋላ ራሴን የት ማግኘት እፈልጋለሁ ??
2.አሁን ያሉኝ ሕልሞች እና ግቦች ከጥቂት አመታት በፊት ከነበረው በጣም የተለዩ ናቸውን? ከተለዩ ለምን?
3.አሁን ባለው ህይወቴ ከቀጠልኩ ከአምስት እና ከአስር አመት በኋላ ምን አይነት ህይወት ሊኖረኝ ይችላል??
4.ለስኬት የሚያስፈልገው ፅኑ ፍላጎት ፣ ቁርጠኝንት እና ትጋት አለኝ ወይ፤ ከሌለኝ ለምን?
5.ህይወቴ ውስጥ ደስታ፣ ሰላም እና ፍቅር አለ ወይ? ከሌለኝ ለምን?
6.በህይወቴ የተሰጠኝ ፀጋ ፣ክህሎት ወይም ተሰጥዖ ምንድነው?? እንዴትስ ልጠቀምበት አስቤያለሁ??
7.በምኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ምን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ? ከዚህ በኋላስ ምን ለማድረግ አስቤያለሁ?
8.መጥፎ ልማዶች(ሱስ) አለብኝ ወይ?? እንዴት ነፃ መሆን እችላለሁኝ?
@Human_intelligence
👍 45❤ 2
ህይወታችሁን መርምሩ
የላቀ ምላሽ ለማግኘት ቁልፉ የላቀ ጥያቄ ማቅረብ ነው። የምትጠየቁት ጥያቄ ልህቀት ለህይወት ያላችሁን ግንዛቤ ይወስናል። በደመነፍስ የምትኖሩትን ህይወት እንድትመረምሩ እና የህይወታችሁን አላማ እና ጉዞ እንድታውቁ ያደርጋችኋል።ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች አስተውላችሁ መልሱ።
1.ራሳችሁ በፈለጋችሁት እና በፈቃዳችሁት ሳይሆን ሕይወት የመረጠችላችሁን ኑሮ እየኖረችሁ ቢሆንስ?
2.ፈፅሞ ያላገኛችሁት ወይም ደግሞ ያለ ፍርሃት እና ሰቀቀን በነፃነት እንዲኖር ያልፈቀዳችሁለት ማንነት ቢኖርስ?
3.ላለመውደቅ ስትሉ በተለይ ደግሞ ሌሎችን ለማስደሰት እነርሱ በቀየሱላችሁ መስመር ብቻ እየኖራችሁ ቢሆንስ?
4.ከዚህ በፊት ፈፅሞ ያላሰባችኋቸውና ገሃድ እንዲወጡ ያልፈቀዳችሁላቸው ውስጣዊ ግጭቶች እንዳሉ ብትረዱስ
5.በማትፈልጉበት እና በማታውቁት ዓለም በመደባችሁ የአኗኗር ስፍራ ተወስናችሁ ፤ ዕለት በሳምንት ፣ሳምንት በወራት ፣ወራት ደግሞ በዓመታት እየተተኩ ዘመናችሁን በከንቱ እያባከናችሁ ቢሆንስ?
እነዚህ የቢሆንስ ጥያቄዎች ያላችሁበትን ሕይወት የሚገልፁ ከሆነ አሁኑኑ ከዚህ ህይወት ለመውጣት ወስኑ!! መጥፎም ጥሩ ዜና ልንገራችሁ መጥፎው ዜና ይሄንን ሕይወት መርጣችሁ እየኖራችሁ መሆኑ ሲሆን ጥሩው ዜና ደግሞ ከዚህ ህይወት መውጣት ትችላላችሁ። ሕይወታችሁን በፈለጋችሁበት መልኩ ለመቅረፅ ሙሉ ነፃነት አላችሁ።ዛሬ የላቀ ሕይወት መምራት የጀመራችሁበት እለት እንደሆነ አስቡ።
✍ፊል ማክግሮው
የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence
👍 31🔥 5❤ 2
አዲስ ዓመት የህይወት አላርም ነው!
(New Year is an alarm for Life)
(እ.ብ.ይ.)
ሰው በጊዜ ሰንሰለት የተሸመቀቀ ፍጥረት ነው፡፡ ሰው በዘመናት መካከል የሚመላለስ ነገር ግን ዘመኑ ቶሎ የሚያልቅ ምስኪን ነው፡፡ ሰው ትንሽም ነው ትልቅም ነው፤ ብዙም ነው ጥቂትም ነው፤ ደግም ነው ክፉም ነው፤ አዋቂም ነው አላዋቂም ነው፤ ብልጥም ነው ሞኝም ነው፡፡ ሰው የህይወት ዘመኑ አጭር ነው፡፡ በዚች አጭር የህይወት ዘመኑ ውስጥ ግን ብዙ ማንነቶችን ያስተናግዳል፤ የተለያዩ ስሜቶች ይንጡታል፤ የማይሆነው የለም፡፡ በዚች አሳስቃ በምታልቅ እድሜ ውስጥ ስንቶቻችን እራሳችንን ትተን የእኛ ባልሆነ ህይወት ውስጥ እንደምንዳክር ሳስበው ይገርመኛል፡፡
የሰው ህይወቱ መገባደጂያ ጊዜ አለው፡፡ ነገር ግን ሕይወቱ የሚያበቃበትን ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት (Expired Date) አያውቅም፡፡ ግን የሆነ ጊዜ ላይ ያበቃል፡፡ አንድ ቀን የመጨረሻውን ራት ይበላል፡፡ የሆነ ጊዜ ላይ የሚናገራቸው ቃሎቹ የመጨረሻ ንግግሮቹ ይሆናሉ፡፡ በሆነ ክፉ ቀን የደም ዝውውሩ ይቆማል፡፡ በሆነ ደስ በማይል ቀን የልብ ምቱ ቀጥ ይላል፤ ትንፋሹ ይቋረጣል፡፡ ድካሙ፣ ልፋቱ መና ሆኖ ይቀራል፡፡ መፍጨርጨሩ፣ ዓላማው፣ ግቡ፣ ውጥኑ፣ ትልሙ፣ ፍላጎቱ፣ ምኞቱ ውሃ ይበላዋል፡፡ ትዕግስቱ፣ ብስለቱ፣ እውቀቱ፣ ወረቀቱ፣ ኩራቱ፣ ትዕቢቱ፣ መወጣጠሩ፣ ንቀቱ አፈር ከድሜ ይገባል፡፡ ሞቱ ልክ ህይወቱ እንደተሰጠው አብሮ ተሰጥቶታል፡፡ ከሞት የሚቀር ማንም ጀግና፣ ማንም ፈሪ የለም፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከተራው እስካለባለስልጣኑ፣ ትንሹ ትልቁ፣ ሃብታሙ ድሃው በሞት መጠቅለያ ይጠቀለላል፤ መኖሩ ይደመደማል፤ ውጣ ውረዱ ያቆማል፤ አንደበቱ ይዘጋል፡፡ ማንም ከሞት ማምለጥ አይችልም፡፡ ዋናው ጉዳይ ሞትን አውቆ መኖር ነው፡፡ መኖር ብቻ ሳይሆን መሞትም ዕጣ ፋንታችን መሆኑን መረዳት አኗኗራችንን ያስተካክላል፡፡ ሞትን መፍራት ሳይሆን ሞት እንዳለ ማወቅ ሕይወታችንን የተሻለ ያደርጋል፡፡
በርግጥ ከሞት ይልቅ አሟሟት ያስፈራል፡፡ በምን ይሆን የምሞተው ብሎ ማሰቡ ራሱ ያስጨንቃል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የተፈጠርነው ልንኖር ብቻ ሳይሆን ልንሞትም ነው፡፡ ይሄ ያገጠጠ ሃቅ ነው፡፡ የትኛውም ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ሟች ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ ያለው ከሞት በፊት ያለው ሕይወታችን ወይም አኗኗራችን እንዴት ያማረ ይሁን የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
ወዳጄ ሆይ.... የአዲስ ዓመት መጥፎ ዜናው ዕድሜህ አየበረረ መሆኑ ነው፤ ጥሩ ዜናው ግን የዕድሜህ አብራሪው አንተው ራስህ መሆንህ ነው፡፡ ጥሩ አብራሪ ካልሆንክ ይዘህ የምትከሰከሰው ውዱን የሕይወት ዘመንህን ነው፡፡ አዲስ ዓመት አዲስ የበራራ መስመር ነው፡፡ አዲስ በረራ አዲስ አስተሳሰብ ይፈልጋል፡፡ አዲስ ዓመት የህይወት አላርም የሞት ነጋሪት ነው፡፡ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ከምንኖርበት የዕድሜ ቁጥር እየተቀነሰ መሆኑን ማወቅ ግድ ይለናል፡፡ ዕድሜህን ማቆም አይቻልህም፡፡ ሞትን ከህይወትህ ማስቀረት አትችልም፡፡ አለመናደድን፣ አለመፍራን፣ አለመቆጣትን፣ አለመውደድን፣ አለማፍቀርን፣ አለመደሰትን፣ አለማዘንን፣ አለመበሳጨትን፣ አለመጠላትን፣ አለመካድን፣ አለመታለልን ወዘተ ጥሩም ሆኑ መጥፎ ስሜቶችን ከህይወትህ መደምሰስ አቅም የለህም፡፡ ስሜትህ ከአንተነትህ፣ ከነፍስያህ፣ ከህልውናህ፣ ከሩህህ ጋር ተሳስሯል፡፡ አንተ የምትችለው ከፍ ዝቅ የሚያደርጉህን ስሜቶች መቆጣጠር ብቻ ነው፡፡ ያንተ ችሎታ ዘመንህን በትክክለኛው መስመር ማብረር መቻሉ ላይ ነው፡፡ ስሜቶችህ ጎጂ እንዳይሆኑ በቁጥጥርህ ስር ልታውላቸው ካልቻልክ ዘመንህን የሚያበርረው አንተ ሳትሆን ውጫዊ ወጀቡ ነው ማለት ነው፡፡ ስሜትን መግራት መቻል የዕለት ተዕለት ልምምድን ይሻል፡፡ ት/ቤቶች፣ ዩንቨርስቲዎች፣ የትምህርት ተቋማት ባጠቃላይ ስሜትህን እንዴት ትቋቋመው ዘንድ እንደምትችል አያስተምሩህም፡፡ እነሱ የሚያስቆጥሩህ ቀለም ለእንጀራ ብቻ የሚሆነውን ነው፡፡ ሶሻል ሚዲያው፣ ቲቪው፣ ሬዲዮው ባዲስ ዓመት ሙዚቃ፣ በእንቁጣጣሽ ዘፈን፣ በአሸሼ ገዳሜ፣ በአስረሽ ምቺው፤ አቅልህን ያስቱሃል እንጂ ትኩረትህን ሰብስበህ የቀሩህን ዘመናት እንዴት በብልሃት እንደምትኖር አይነግሩህም፡፡ ሁሉም ትኩረትህን ነጣቂ፣ መረጋጋትህን ሰራቂ ነው፡፡ አንተ ቶሎ ካልነቃህ የሚያፈዝህ ዙሪያህን ከብቦሃል፡፡ ንቃ በአዲስ ዓመት!
ቸር የመንቃት ዘመን!!
መልካም አዲስ ዓመት!
ኢትጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!
-----------------------------------
እሹቱ ብሩ ይትባረክ
@EshetuBirruYitebarek
👍 68❤ 13👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
አዲሱ አመት የሰላም፤የፍቅር፤ የሰኬት አመት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን !!
መልካም አዲስ አመት!!
👍 44❤ 7👏 4
Tells how to Analyze, Understand, and Predict People’s Emotions, Thoughts, Intentions, and Behaviors.
Patrick_King_Read_People_Like_a_Book_How_to_Analyze,_Understand.pdf1.19 MB
🔥 10👍 3😢 1
ቀላሉን ነገር አታካብደው
ደራሲ:- ዶክትር ሪቻርድ ካርሰን
ትርጉም:- ዶክትር ዮናስ ላቀው
@zephilosophy
@zephilosophy
ቀላሉን ነገር አታካብድ @ETHIO_PDF_BOOKS.pdf34.33 MB
👍 19❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
ያሳለፍነው ቢያሳምመን አልገደለንም። ኒቼም እንዳለው የማይገድለን ህመም ጠንካራ ያደርገናል። ትናንትናን በጨለማ ውስጥ ወድቀናል ፡ ዛሬ ውጥንቅጡ የወጣ ነው፤ ቢሆንም የተሻለ ቀናት፣ የተሻለ ነገ፣ የተሻለ እኔ ከጠራ መንገድ ጋር ይጠብቀናል። ህመም inevitable.. ፀፀትም past thing.. ተስፋ ግን Existence ነው።🔥 76👍 39❤ 23👏 6
በአንድ ወቅት አንድ ባለሀብት የመሞቻውን ቀን ከመልዓከ ሞት ይነገረውና በጣም ይደነግጣል፡፡ ከቆይታ በኀላ ግን "ገና እኮ ለመሞት 2 ዓመት ይቀረኛል፤ ለምን እስከዛ ድረስ በደንብ አልዝናናም?" በማለት ከእራሱ ጋር ይማከርና ቀሪ ሁለት ዓመቱን በተሳካ ሁኔታ እና ደስተኛ ሁኖ ለማሳለፍ የተለያዩ እቅዶችን አወጣ፡፡
እናም ሰውየው አለም ላይ አለ የተባለ ባለሀብት ነበረና የተለያዩ ሀገራትን እየዞረ መጎብኘት ጀመረ፡፡ ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን እና መጠጦችን እንደጉድ ይመገባል፤ ይጎነጫል፡፡ ሁለት አመቱን እንደዚህ በተድላ ካሳለፈ በኀላ ሊሞት አንድ ቀን ሲቀረው መልዓከ ሞት ወደ እሱ ይመጣል፡፡
"ነገ ልወስድክ እመጣለው፤ እናም እስካሁን ያላደረካቸውና ምትፈልጋቸው ነገሮች ካሉ ጨራርሰከ ጠብቀኝ" ይለዋል፡፡
ባለሀብቱም ይሄን ሲሰማ በጣም ተረበሸ፡፡ "እኔ አለማችን ካለቻቸው ሀብታሞች ሁሉ ትልቁ ነኝ፤ አለም ላይ በስሜ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች አሉኝ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አውሮፕላንና መርከቦች አሉኝ፤ የተለያየ ሀገር በጣም ቅንጡ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች አሉኝ፤ በስሜ መቁጠር የሚከብድ ገንዘብ በባንክ አለኝ፤ እና እባክህ ከእነዚህ ሁሉ የፈለከውን ውሰድና ዘላለም የመኖር ዕድልን ስጠኝ" በማለት ጠየቀ፡፡
መልዓከ ሞትም የጠየቀው ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለው መለሰለት፡፡
ባለሀብቱ ቀጥሎም "እሺ ያለኝን በሙሉ ውሰድና ተጨማሪ 1 ዓመት ስጠኝ" ብሎ ጠየቀ፡፡ አሁንም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመቀጠል 1ቀን ፣ 1 ሰዓት ፣ 1ደቂቃ እንዲጨምርለት ጠየቀው፡፡ መልዓከ ሞት ግን ትሞታለክ በተባለው ቀንና ሰዓት ልወስድክ እመጣለው ብሎት ሄደ፡፡
✍የሁላችንም መጨረሻ ይሄው ነው፡፡ ዛሬ ላይ ስመጥር ከሆኑ ባለሀብቶች መሀከል አንዱ እንሆን ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ በዓለም ካሉ አዋቂዎች እና ምሁሮች አንዱ እንሆን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የትኛውም ሀብታችን ፣ የትኛውም ዕውቀታችን አይደለም ሞትን እንድናመልጥ በህይወታችን ላይ የአንድ ሰከንድ ዕድሜን አይገዛልንም፡፡
ታዲያ ያለን ሀብት ፣ ዕውቀት ፣ ዝና ይሄን ማድረግ ካልቻለ ለምን ለሰዎች ክፉ እንሆናለን? ለምን እራስ ወዳድ እንሆናለን?
ዛሬም ፣ ነገም ፣ ከነገ ወዲያም ሁሌም ለሰዎች መልካም እናስብ፤ መልካም እናድርግ፡፡
🙏መልካም ምሽት🙏
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
👍 110❤ 27
ጊዜ ያላችሁ አይምሰላችሁ!!!
አንድ እድሜውን ሁሉ ሰዎችን በሕይወት ክህሎት ዙሪያ በማስተማር ያሳለፈ የእድሜ ባለጠጋ፣ “ወጣቶች ሊሰሩት ከሚችሉት ስህተት እጅግ የከፋው የትኛው ነው?” ተብሎ ሲጠየቅ፣ ከልምዱ በመነሳት እንዲህ ሲል መለሰ ይባላል፣ “ብዙ ጊዜ እንዳላቸው ማሰብ”፡፡
ልጆች ተጫውተው ለማለፍ ያላቸው ዓመታት አስቡት! እጅግ ውስን ነው!
ወጣቶች ለትምህርትና ማሕበራዊ ግንኙነትን በማዳበር ለመብሰል ያላቸው ዓመታት አሰላስሉት! ጥቂት ናቸው!
ጎልማሶች በስራው ዓለም ባላቸው ስምሪት ለአሁኑ ቤተሰባቸው ፍላጎትና ለወደፊት የሽምግልና እድሜያቸው ለማስቀመጥ ያላቸውን የእድል መስኮት አስቡት! ብዙም አይደለም!
እነዚህ ጊዜያቸውን ጠብቀው የሚመጡ ሂደቶች በትክክለኛ የጊዜ አጠቃቀም ብልሃት ካልተያዙ በብርሃን ፍጥነት ያልፋሉ፡፡ አንዴ ካለፉ ደግሞ አይመለሱም፡፡
“የአፍሪካ ጊዜ”
እንደ አፍሪካዊ፣ ከዚያም ጠበብ ሲል እንደ ኢትዮጵያዊ፣ የጊዜ አጠቃቀም ሁኔታችን ምን ያህል የተበላሸ እንደሆነ ለማወቅ ምንም አይነት ጥናታዊ አቅርቦቶችን ለማግኘት መጣጣር የለብንም የራሳችንንና በአካባቢአችን ያለውን የጊዜ አጠቃቀም ሁኔታና ዝንባሌ ማጤኑ ከበቂ በላይ ነው፡፡ ለአንድ ስብሰባ ስንጠራ በሰዓቱ ብንደርስ የሚገጥመንን ቁጭ ብሎ ያልመጡትን የመጠበቅ ሁኔታ ወይም ደግሞ በሰዓቱ መድረስ የሚሰጠንን “የመዋረድና የመናቅ” መንፈስ ስለምንፈራው ዘግይቶ መድረስ እንመርጣለን፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የማይቋረጥን ዑደት ፈጥሮብናል፡፡ የሰርጎቻችንን ሁኔታ እናስባቸው፡፡አንድ ሰው የሰርግ ጥሪውን አክብሮ በሰዓቱ ቢገኝ ከአንድና ከሁለት ሰዓታት በላይ ቁጭ ብሎ ሰርጉ እስኪጀመር መጠበቅ የተለመደ ነው፡፡
አንድ የጋና ተወላጅ እንዲህ ሲል ተናግሯል፣ “ክፍለ ዓለማችን ሳታድግ የመቀጠሏ ዋነኛ ምክንያት በጊዜ ላይ ያለን ግድ የለሽ ዝንባሌና ማሻሻል ያለብን የጊዜ አባካኝነት ዝንባሌ ነው፡፡ ሰዓትን ያለማክበር ችግራችን ከልክ ያለፈ ከመሆኑ የተነሳ ቀጠሮን አለማክበርና በሰዓት አለመገኘት
የአፍሪካ ጊዜ በመባል ተቀባይነት አግኝቷል”::
እንደሚታወቀው ሁሉ ሁላችንም እንደማንኛውም በቀደሙት ዘመናት ኖረው እዳለፉ ሰዎች በቀን ውስጥ 24 ሰዓታት አሉን፡፡ ነገር ግን በዚህ በምንኖርበት ክፍለ- ዘመን ያለው የኑሮ ጫናና ሩጫ እነዚህን ቢሰራባቸውም ሆነ ባይሰራባቸው ከማለፍ ፍንክች የማይሉ ሰዓታት አጭር ያደርጋቸዋል፡፡ የየቀኑ ሩጫና መጨናነቅ ቀኑ እንደ አንድ ደቂቃ ታጥፎ የሄደ እስኪመስል ድረስ ያዋክበናል፡፡ ያለን ምርጫ አንድ ነው፣ ሰዓትን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር!
ይህንን አስበህ ታውቃለህ? ሰዓትህን በአግባብ በመጠቀም ሁኔታዎችን ካልመራሃቸው ሁኔታዎች ራሳቸው አንተን ይመሩሃል፡፡ በሰዎችም በቀላሉ የምትመራና የምትነዳ ሰው ትሆናለህ፡፡ ውጤቱም የምርታማነትና የስኬታማነት መቀነስ ነው፡፡
ጊዜህን በአግባብ የመጠቀም ብቃት እንደጎደለህ ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እራስህን መጠየቅ ትችላለህ፡-
• አንድን የጊዜ ገደብ ያለውን ስራ ለመጨረስ ዘወትር በመጨረሻው ሰዓት የመሯሯጥ ባህሪ አለህ?
• አብዛኛውን ጊዜ ለቀጠሮም ሆነ ለሌላ የጊዜ ገደብ የመዘግየት ዝንባሌ አለህ?
• በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ በላይ ቀጠሮ ወይም ፕሮግራም በመያዝ ግራ የመጋባት ባህሪይ ያጠቃሃል?
ለእነዚህና ለመሰል ጥያቄዎች ያሏችሁ መልሶች “አዎን” ከሆነ፣ ስለጊዜ አጠቃቀማችሁ በሚገባ አስቡበት
ጊዜ ያላችሁ አይምሰላችሁ!!
"ጊዜ በረረ፣ጊዜ አለፈ፣ ጊዜ ሄደ የሚሉ አገላለፆች በሙሉ መፅናኛ ናቸው፡፡ እውነቱን ካየነው እያለፍን ያለነው በየ ጊዜው ቁልቁል እየፈሰስን ያለነው እኛ እራሳችን ነን፡፡ ነገር ግን ጊዜ እንደሚያልፍ እኛ እንደ ምንቆይ ሁሉ ጊዜ ያልፋል እያልን ማሰባችን ተያይዘነዋል፡፡ "
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence👍 51❤ 5👏 4🙏 4
የት እየሄድክ ነው?
“ወዴት እንደሚሄድ ለሚያውቅ ሰው ይህች ዓለም መንገዱን ትለቅለታለች::”
/ Emerson/
የት እየሄድክ ነው? ወዴት እያቀናህ ነው? የህይወት ግብህስ ምንድነው? በምድራዊ ቆይታህ ምንን ማሳካት ትመኛለህ?
ከአስር ዓመት በኋላ ራስህን ምን ቦታ ላይ ደርስህ ማግኘት ትፈልጋለህ?
እየሰራኸው ደስታን የሚለግስህ፣ ባይከፍሉህ እንኳ በነፃ ልትሰራው ፍቃደኛ የሆንከው የስራ መስክ የቱ ነው? በራስህ በማንነትህ) ላይ ደስተኛ ነህን?
በተከፈተው በር ሁሉ ዘው ብለህ የምትገባው፣ ለቀረበው ምግብ ሁሉ እጅህን የምትሰነዝረው፣ ያገኘኸውን ሁሉ ጓደኛህ የምታደርገው፣ከፊት ለፊትህ በአጋጣሚ ለመጣው ስራ ሁሉ ደፋቀና የምትለው ለምን ይመስልሃል?
የእድገት ጉዞህ የኋልዮሽ የሆነበት ምክንያቱ ምንድነው?ጊዜያዊ ደስታን በሰጠህ ጉዳይ ላይ የተጠመድከው ለምን ይሆን?
ገበያ አንድን ነገር ልትገዛ ሄደህ ሌላ ነገር ገዝተህ የምትመለሰው ለምን ይመስልሃል?
📙የህይወት ግብህን ቅረፅ
✍️ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
👍 62👏 5❤ 3
ለዝግጅት እረፍት የለም!
#repost
ከምንም ነገር ማረፍ ትችላለህ፣ ነገ ሕይወት ለሚያቀብልህ ፍልሚያዎች የመዘጋጀትን ጉዳይ አስመልክቶ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ማረፍ አትችልም፡፡ በየቀኑ ራስን ማዘጋጀት፣ ማሰልጠንና እየበሰሉ መሄድ የግድ ነው፡፡
የኦሊምፒክ ውድድር የሚመጣው በየአራት አመቱ ነው፣ የስፖርተኞቹ ልምምድና ዝግጅት ግን በየቀኑ ነው፡፡ ፈተና የሚመጣው በሴሚስተሩና በአመቱ መጨረሻ ነው፣ የተማሪዎቹ ጥናትና ዝግጅት ግን በየቀኑ ነው፡፡ ጦርነት የሚመጣው አንዳንድ ጊዜ ነው፣ የአንድ ሃገር የውትድርና ስልጠናውና ዝግጅቱ ግን በየቀኑ ነው፡፡ የግል ሕይወት ፈተናው የሚመጣው አልፎ አልፎ ነው፣ በአመለካከትና በስሜት ጽንአት የማደግ ዝግጅቱ ግን በየቀኑ ነው . . . የቀረውን የዝግጅትና የፍልሚያ መስክ ዝርዝር አንተ ቀጥልበት፡፡
በሕይወትህ የሚገጥሙህን ግጥሚያዎችና ፍልሚያዎች የማሸነፍህን ወይም የመሸነፍህን ጉዳይ ከሚወስኑ ዋና ዋና ነገሮች መካከል አንዱ ቀድመህ የመዘጋጀትህና ያለመዘጋጀትህ ጉዳይ ነው፡፡ የብዙ ሰዎች ሕይወት ለወደፊት የሕይወት ግጥሚያና ፍልሚያ የተዘጋጀ አይደለም፡፡ ስለሆነም፣ ሁኔታው አፍጥጦ ሲመጣ ነው መፍትሄ ለማግኘት መሯሯጥ የሚጀመሩት፡፡
ሳይዘጋጁ መፋለም ያለው ችግር በስልጠና ራሱን ያላዘጋጀ ማንነት ፍልሚያ ሲመጣ አቅም ከማጣቱም ባሻገር ለምክርና ለድጋፍም ዝግጁ አለመሆኑ ነው፡፡ በዝግጅት ያልዳበረው ደካማ ማንነቱ ችግሩ በድንገት ሲመጣ ከሚከተለው መደናገር ጋር ተደምረው ውስጡን ያዝሉታል፣ አቅም ያጥረዋል፣ ግራ ይጋባል፣ ነገን መጋፈጥ ያስጠላዋል . . . ፡፡
ነገ የሚኖርህ ማሕበራዊ ሕይወት፣ የፍቅርና የትዳር ሕይወት፣ የባለሞያነት ሕይወት . . . ፍልሚያን ይዘው እንደሚመጡ በማወቅ ዛሬ መዘጋጀትህን አትርሳ፡፡ “እንዴት ልዘጋጅ?” ካልክ ለመንደርደሪያ የሚከተሉትን ተጠቀምባቸው . . .
• አንብብ! አድምጥ! ሰልጥን!
• በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ስታልፍ ከሁኔታው ባለመሸሽ ለትምህር ልቦናን በመክፈት ትምህርት አጠራቅም፡፡
• የሌሎችን ስኬትና እድገት ለቅንአትና ለፉክክር ሳይሆን ለመነሳሳት ተጠቀምበት፡፡
• የሌሎችን ስህተትና ውድቀት ለፍርድና ለወሬ ሳይሆን ለትምህርት ተጠቀምበት!
ከምንም ነገር እረፍ በየቀኑ ከመዘጋጀት ግን በፍጹም አትረፍ!
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
🔥 26👍 18❤ 7
የአዕምሯችን ሁለት ገፅታዎች
ያለህ አንድ አዕምሮ ብቻ ቢሆንም ይሔው አዕምሮህ ሁለት የተለያዩ ባህሪያት ያላቸው የተግባር ክፍሎችን የያዘ ነው:: ይህን በሁለቱ መካከል ያለውን ድንበር የአዕምሮ ህክምና ተማሪዎች በሚገባ ያውቁታል፡፡ ሁለቱ የአዕምሮህ ተግባራት የተለያዩ ናቸው:: እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ተግባርና ኃይል ያላቸው ናቸው፡፡
እስከ ዛሬ ያሉቱን የአዕምሮ ክፍሎች ተግባራት ለመለየት ብዛት ያላቸው ስሞች ጥቅም ላይ ውለዋል:: ከእነዚህም መካከል ህሊናና ውስጠ ህሊና ፣ ያንቀላፋው አዕምሮና ንቁ አዕምሮ፣ ጠሊቅ የሆነውና ጠሊቅ ያልሆነው አዕምሮ ፣ ፈቃደኛውና ፍቃደኛው ያልሆነ አዕምሮ ወዘተ.. እነዚህ ሁሉ መልእክታቸው ምንም ይሁን ምን ሁለትዮሻቸውን ለማሳየት ሲባል ነው ጥቅም ላይ ያዋሉት።
ህሊናና ውስጠ ህሊና ራሳቸውን የቻሉ አዕምሮዎች አለመሆናቸውን ልትገነዘቡ ይገባል፡፡ ነገር ግን እነዚህ አንድ አዕምሮ ውስጥ ያሉ የአዕምሮ ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን መገንዘብ ያሻል፡፡ ህሊና (አዕምሮ) አገናዛቢውና አሳቢው አዕምሮ ነው፡፡ ምርጫዎችህን የሚወስነው ይህ ክፍል ነው፡፡ ለምሳሴ :- ምን አይነት መፅሀፍ መግዛት እንዳለብህ ፣ምን አይነት ቤት መግዛት እንዳለብህና ፣ምን አይነት የሴት ጓደኛ ወይም ሚስት ሊኖርህ እንደሚገባ የሚመርጠው ይህኛው የአዕምሮ ክፍል ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ካለምንም የህሊና (የአዕምሮ) ምርጫ ልብህን ፣ እስትንፋስህን እንዲሁም ወሳኝ አካላዊ ሂደቶችን የሚቆጣጠረው ውስጠ ህሊና የሚባለው የአእምሮ ክፍል ነው።ከእነዚህም በተጨማሪ የምግብ መፍጨትና ፤ የደም ዝውውር ካለምንም መቋረጥ _ ይቀጥላሉ ይህም የሚሆነው በውስጠ ህሊና አማካኝነት ሲሆን ካለምንም የህሊና ጣልቃ ገብነት ነው፡፡
ውሰጠ ህሊና የሚቀበለው ሃሳብ ያተመውን ወይም በአዕምሮህ ያመንክበትን ሀሳብ ነው። ውስጠ ህሊና ስለሚቀበለው ሀሳብ ምንነት የሚመሰከተው ጉዳይ የለም የሰጠኽውን ከመቀበል ውጭ ::በዚህም ውስጠ ህሊና እንደ ህሊና (አዕምሮ) አያመዛዝንም አይጠይቅም። ሀሳቦቹ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆናቸውን አይመረምርም ከዚያ ይልቅ እንደ ሀሳቦቹ ባህሪ ምላሽ ነው የሚሰጠው:: ውስጠ ህሊና ልክ የትኛውንም አይነት (መጥፎም ይሁን _መልካም) ዘር እንደሚቀበል አፈር ይመሰላል። ሀሳቦችህ ዘሮች ናቸው አሉታዊና አፍራሽ እሳቤዎች ህሊናህ ውስጥ ሲኖሩ አሉታዊ በሆነ መልኩ ስራቸው መስራት ይቀጥላሉ፡፡ ይፍጠንም ይዘገይም እነዚህን ነገሮች በውጫዊው ህይወትህ አንደ ተሞክሮ መከሰታቸው አይቀሬ ነው፡፡
ውሰጠ ህሊናህ ሀሳቦችህ መጥፎም ይሁን መልካም እውነትም ይሁን ሀሰት እነዚህን ተመርኩዞ ምላሽ ከመስጠት ውጭ ሌላ ነገር አይመሰከተውም፡፡ ለምሳሌ በአዕምሮህ የሆነን ነገር እውነት ነው ብለህ ብትወስደው ምንም እንኳ ነገሩ ውሸት ቢሆንም ውስጠ ህሊናህ እንደ አውነት ነው የሚቀበለው፡፡ ውጤቱም ይህን ህግጋት ያስገባ ነው የሚሆነው፡፡
በርካታ ሳይኮሎጂስቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለሙያዎች አዕምሯቸው - ለነገሮች ፈጣን ምላሽ የመስጠት ችግር ባለባቸው ሰዎች ላይ ባካሔዱት በርካታ ሙከራዎችና ምርምሮች እንዳረጋገጡት ውስጠ ህሊና በማመዛዘን ሂደት ወሳኝ የሆኑ ምርጫዎችንና ንፅፅሮችን አያካሒድም፡፡ ውስጠ ህሊና አዕምሮ እውነት አደርጎ የተቀበለውን የተኛውንም አይነት ሀሳብም ሆነ አስተያየት ይቀበላል፡፡ ምንም እንኳ ጉዳዩ ሀሰት ቢሆንም ሀሳቡ ወይም አስተያየቱ አንድ ጊዜ ተቀባይነት ካገኘ በዚህ በተሰጠው ሀሳብ ባህሪ ላይ ተመርኩዞ ምላሽ ይሰጣል፡፡
ውስጠ ህሊና ምንም ያህል በሚሰጠው አስተያየት ተፅዕኖ እንደሚያድርበት በሚገባ ለመገንዘብ አንድ ምሳሌ እንመልከት አንድ ሳይኮሎጂስት ወይም ሳይካትሪስት አንዲትን ሴት ንጉሱን ናፓሊዮን ቦናፓርቲ ወይም ድመት አሊያም ደግሞ ውሻ መሆኗን ቢነገራትና የሙከራዋም ጊዜ አስከሚጠናቀቅ ድረስ ስብዕናዋ ሁሉም ተቀይሮ አንደ ናፖሊዮን አልያም አንደ ድመቷ ትሆናለች፡፡ ሙከራውን በበላይነት የሚመራው | ባለሙያ “ነህ/ሽ” ያለውን ነገር ነው የሚሆነውም የሚያምነውም፡፡
እነዚህ ቀላል ምሳሌዎች በህሊና (በአዕምሮ) ማለትም በአመዛዛኙና በውሰጠ ህሊና ከሁሉም ውጭ የሆነው ምንም ምርጫ የማያደርገውና የተሰጠውን ሁሉ በሚቀበለው መካከል ያለው ልዩነት በሚገባ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ እሳቤዎችህን አመለካከቶችህን በመምረጥ በሕይወትህ የተባረከ የተፈወሰ እንዲሁም የተነቃቃ በማድረግ ህይወትህ በደስታ የተሞላ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
በአንተ ላይ የሚከሰቱት የትኞቹም ነገሮች ቀድሞ አዕምሮ ውስጥ የነበሩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሀሳቦች በህገ - እምነት አማካኝነት በውስጠ ህሊናህ ውስጥ በመታተማቸው ነው:: የተሳሳቱ ወይም የተዛቡ ዕንሰ ሀሳቦችን ለውስጠ ህሊናህ ብታስተላልፍ አነዚህን ለማስተካከል (ለማረም) ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ሁኔታ ነው፡፡ ይህንንም ማስተካከያ በአስቸኳይ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ እንዴት? ይህን ለማድረግ ለውስጠ ህሊናህ በተደጋጋሚ ገንቢና በቀናነት የተሞሉ እሳቤዎችን በመስጠት ነው:: እነዚህን አዘውትረህ ስትደጋግማቸው ውስጠ ህሊናህም ይቀበላቸዋል፡፡ በዚህ መልኩም አዲስ፣ ጤናማ የሆኑ አሳቤዎችን እንዲሁም በፀጋ የተሞላ ህይወትን በውስጠ ህሊና ውስጥ መፍጠር ትችላለህ፡፡
የአዕምሮህ (ህሊና) ተለምዷዊው አስተሳሰብ በውስጠ ህሊናህ ውስጥ ጥልቅ የሆነ ልማድ ይፈጥራል፡፡ ተለምዷዊው አሳቤዎችህ በፀጋ የተሞሉ፣ ሰላማዊ እንዲሁም ገንቢ ከሆኑ ውስጠ ህሊናህም ፀጋን፣ ሰላምን እንዲሁም ገንቢ ሁነቶችን በመፍጠር ምስሉን ይሰጥሃል።
ምንጭ The power of Your subconscious mind
ፀሀፊ ዶ/ር ጆሴፍ መርፌ
ይቀጥላል ...
👍 42❤ 10
