en
Feedback
የስብዕና ልህቀት

የስብዕና ልህቀት

Open in Telegram
68 961
Subscribers
No data24 hours
-137 days
-96730 days
Posts Archive
`` በክረምት ጥልቀት ውስጥ የማይጠፋ በጋ በራሴ ላይ አገኘሁ። አእምሮ በውጥረት ልባችንን በህመም የሚሞላ መከራ እስካልገጠመን ድረስ ምን ያህል ጠንካራ እና ኃያል እንደሆንን አናስተውልም። በሁላችንም ውስጥ ታላቁን ተራራ የመቋቋም ድፍረት እና ችሎታ እንዳለን ስንገነዘብ፤ በመንገዳችን ላይ ያለው ከባድ ጊዜ ለጥንካሬ የተዘጋጀ ግብዣ አድርገን እንወስደዋለን። ያለደም ስርየት የለም!፤ የምንነጻው ስንጨማለቅ ነው.. ``   አልበርት ካሙስ የስብዕና ልህቀት @human_intelligence
Show all...
👍 27 8👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
👍 17
በህይወት ኑባሬ ፡ ለከፍታ የገነባው ነው ድልድይ አዳልጦን  : ከመተታነንስ አረንቋ ራሳችን እናገኘዋለን ፡፡ በመኖር ፍቅር ተጠምደህ ለአዝማናት የገነባኽው  የህልም ማማ ቅንጣት በምትመስል ሰበብ ሲናድ ፡ሲፉረከረክ  ታገኘዋለህ፡፡ በይሆናል ጅማሮ ፡ በአዕምሮህ የፈተልከው የሀሳብ ዝሐ ፡ ብል በልቶት የመዳረሻህ ፍኖት ብዙ አድካሚ እና አሰልቺ የህይወት ደፋ ቀና  ወስዶት ልም ገላህን ድካም ቢገርፍህም ፡ የህይወት  መርህ ሻገር ሲልም ውበት  ነው፡፡ እናም አንዳንድ መሸነፍ የሚመስሉ ስኬቶችን  መቀብል ማመን  አለብህ፡ አለመቻልህን  ስታውቅ  አታስመስል፡ በመንተልህ ጭቃ ገብተህ ፡አትላቁጥ  በእልህኝነት ፡ ስካር ለሌላ የድካም ቋት አትሰናዳ  ፡ በስሁት መንገድ ብርሃን አትፈልግ...ለአዕምሮህ ፡ አለመቻልህን እመንለት ፡ ለልብህ የማይበርድ ፡ህመም  ለገላህ የማይሽር ቁስል አትሁንባት ፡፡ © የአባ ልጅ ነኝ የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Show all...
19👍 14
እስቲ ና ዝቅ በል ውረድ ወደ መሬት አይተህ ብትረዳው አይንህ ቢመለከት የኛን ኑሮ የኛን ህይወት 🎶 🎶 🎶 🎶 የናንተ ቁምነገር የናንተ ክርክር ጥማድ ለኔ አይገዛ አያድስም ሞፈር የሚታይ የሚናፈሰው በየሞገዱ ላይ ቅንጣት ደስታን እንጂ የኛን ችግር አያይ 🎶 🎶 🎶 🎶 ናቲ ማን እመነኝ
Show all...
Nhatty_Man_ናቲ_ማን_እመነኝ_Lyric_Video_Emenegne_New_Ethiopian_Music128k.m4a4.34 MB
👍 63 7👏 6🤔 1
Repost from TgId: 1173613158
"ራሳችንን ብናጠፋ ይሻለናል" (ተስፋአብ ተሾመ) * * * ዶክተሮች "ብንሄድ ይሻለናል" እያሉ ነው። መሰረት ሚዲያ በሰራው ዜና በኑሮ ጫና የተነሳ የጤና ባለሞያዎች "በጋራ እራሳችንን እና.ጥፋ" የሚል እቅድ ይዘዋል። ምክኒያቱ የኑሮ ጫና ነው። ጥያቄያቸው ከመንግሥት ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም። አንዳንድ ሐኪሞች ኩላሊታቸውን መሸጥ ፈልገው ሳይሰምርላቸው ቀርቷል። ስለዚህ መፍትሄው ራስን መግ.ደል መስሏቸዋል። መምህራን የኑሮ ጫናን መቋቋም እንዳቃታቸው ይታወቃል። በቀን ሶስቴ ለመብላት የሚቸገሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን አሉ። ደሞዛቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን አያሟላም። መምህራን ፥ጋዜጠኞች ፥ ዶክተሮች ወዘተ ከደህነት ወለል በታች ናቸው። ድህነታቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን የማይሞላ ነው። በሐገራችን የሚቸገሩት ስራ አጦች ብቻ አይደሉም። ሰዎች ስራ እየሰሩ በቀን 3ቴ መመገብ የማይችሉ ሆነዋል። ልጆች ሳለን ዶክተር መሆን ብርቅ ነገር ነበር። ዶክተር የሆነ ያልፍለት ነበር። ዛሬ ግን ዶክተሮች ረሀብተኞች ሆነዋል። ሐገሬውን ተመልከቱ። ራስን ማጥፋት መደበኛ ሆኗል። "ኮሪደር ልማት" የሚሉት መንግስታዊ ስላቅ ቤታቸውን እያፈረሰባቸው ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች አሉ። ኑሮ ከብዷቸው ራሳቸውን የገደ.ሉ ጥቂት አይደሉም። ይህ ሁሉ ሳያንሰን ዶክተሮች "በጋራ ሰብሰብ ብለን ራሳችንን እናጥፋ" እያሉ ነው። የአረብ ፀደይ የሚባለውን አብዮት የቀሰቀሰው ቡአዚዝ የሚባል ወጣት ራሱን በእሳት አቃጥሎ መግደ.ሉ ነበር። ቡአዘዝ ራሱ ላይ የለኮሰው እሳት አብዮት ወልዶ ሹማምንትን ላይ ነደደ። በእርግጥ የቡአዚዝ እሳት ስንጥር ነው። የግመልን ወገብ የሰበረ ስንጥር! አንድ ግመል ብዙ ሸክም ነበረበት። ጀርባው ላይ ከአቅሙ በላይ የተጫነ ሸክም ያለበት ግመል አንዲት ስንጥር ስትጨመርበት ወገቡ ተሰበረ። የግመሉን ወገብ የሰበረው ስንጥሩ ሳይሆን የቀደመው ጭነት ነው። የቡአዚዝ ራሱን ማጥፋት ስንጥር ሆኖ የአረብን አብዮት ቀሰቀሰ። ስለ እኛ ሐገር መገመት አይቻልም። በየእለቱ ሕዝቡ ላይ ሸክም ይጫንበታል። ዜጎች ሸክሙ አጉቡጧቸዋል። በዚህ ሁሉ መሐል ትልልቅ አእምሮዎች እየመከኑ ነው። ባለ ተስፋ ወጣቶች ተስፋ እያጡ ነው። ራስን ማጥፋት መፍትሄ እየሆነ ይመስላል። @Tfanos
Show all...
😢 34👍 27 2
Photo unavailableShow in Telegram
👍 52 2👏 1
የጠፋብን ውስጥ፣ የምንፈልገው ውጭ አንድ ሰው አንድ ቀን ማታ እቤቱ እያለ ውድ የተባሉ እቃዎቹን ከሚያስቀምጠበት ሳጥን ውስጥ አንድ በጣም የሚወደውን ዳይመንድ መርጦ አወጣና በእጁ ይዞ እየተመለከተው ሳለ፣ በድንገት መብራጥ ጠፋበት፡፡ ልክ መብራቱ እንደጠፋበት በእጁ የያዘው ውድ ዳይመን ከእጁ አመለጠውና ወደቀ፡፡ ወዲያውኑ ሊፈልገው ቢሞክርም ጨለማ ነበረና የት እንደገባ እስከማይገኝ ድረስ ጠፋበት፡፡ ብዙ ሞክሮ ሲደክመው ከቤቱ ወጣ ሲል የመንገድ መብራቶች አካባቢውን ደመቅ አድርገው አብርተውት ተመለከተ፡፡ ከዚያም፣ “የጠፋብኝን ዳይመንድ እቤቴ ጨለማ ስለሆነ ስላላገኘሁት እዚህ ብርሃን ያለበት ቦታ ልፈልገው” ብሎ በማሰብ መፈለጉን ተያያዘው፡፡ ያንን በማድረግ ላይ እያለ አንድ በአካባቢው የሚዘዋወር ፖሊስ አገኘውና፣” ምን እየፈለክ ነው” አለው፡፡ ሰውዬውም መልሶ፣ “ዳይመን ከእጄ ወድቆ ጠፍቶብኝ ነው” አለው፡፡ ፖሊሱም ትንሽ ካፋለገው በኋላ ሲደክመው፣ “ለመሆኑ የቱ ጋር ነው የጠፋብህ” ብሎ ጠየቀው፣ ሰውየው፣ የጠፋብኝማ እቤቴ ነው፣ ነገር ግን  እቤቴ መብራት ስለሌለና ጨለማ ስለሆነብኝ ነው እዚህ መብራት ያለበት ቦታ መፈለግ የጀመርኩት” አለው ይባላል፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ይህ ይሆን! እኛው ውስጥ የጠፋብንን ነገር ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሰው ጋር፣ ሌላ ሁኔታ ውስጥ ስንፈልግ መባዘናችን! እኛው ጋር ካለው የዝቅተኝነት ስሜት፣ ራስን ያለመቀበል ቀውስ፣ የመገፋት ህመምና የመሳሰሉት “ጨለማዎች” የሰወረብንን ውድ ነገር ሌላ ቦታ እንፈልገዋለን፡፡ “ሰዎች ቢቀበሉኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ከተቀበሉን በኋላ ደግሞ ሰዎቹ ትተውን እንዳይዱ እንጨነቃለን፡፡ “ሃብት ብናገኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ካገኘን በኋለ ደግሞ ሃብቱ እንዳይከስር ስንጨነቅ ቁጭ ብለን እናድራለን፡፡ “ዝነኛ ብሆንና Follower ባገኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ካገኘን በኋላ ግን እያንድንዱ unfollow ያደረገን ሰው ሁኔታ ይጫጫነናል፡፡ ውስጣችሁ የጠፋባችሁን ነገር ሌላ ቦታ አትፈልጉት፤ ፈጽሞ አታገኙትም፡፡ በመጀመሪያ የጨለመባችሁንና ግራ የገባችሁን ነገር ፈጣሪ ይፍታላችሁ፡፡   ዶ/ር እዮብ ማሞ የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Show all...
👍 70 14👏 3🥰 2🙏 2
ወደ አሜሪካን ጎት ታለንት ( American Got Talent) ከሚመጡ ተወዳዳሪዎች መሃል Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) የምትባለውን ብዙዎች አይረሷትም፡፡ ተወዳዳሪዋ ወደ መድረክ በመጣች ጊዜ የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል አለች" ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድንው የምታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውም ባንድ አፍ እሺ ቀጥይ አሉ:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው:: ከዚያም ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ፣ ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል ስትል ሳይመን በድንጋጤ ተመለከታት ፡፡ ቀጠለና ሀዋርድ "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" አላት ተገርሞ!! Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በሗላ የዳኞች ውሳኔ የሚሰጥበት  ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት፡ "ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች:: ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱ ዓይኖቹ ፈሰሱ:: ከፊቱ ያለውን ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም  አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች  አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ  ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!! በአንድ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "ፈጣሪ አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰደውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም  "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የፈጣሪን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትልም ነበር፡፡በመጨረሸም እንዲህ ነበር ያለቸው፦ "ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!" @shewitdorka
Show all...
👍 118 49🥰 11🙏 5🔥 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
Repost from TgId: 1163708603
❤❝ትዝታ ማለት በህይወት ረቂቅ ሚስጥር ውሰጥ የምናገኘው የፍቅር ትሩፋት ፤ የትናንት አስቤዛ ለነገ መጓዧ በትናንት እውነታ ውስጥ ሺህ ዛሬን ማንገሻ ነው ። በርግጥ ሁላችንም የተዘበራረቀውን የህይወታችንን ዳስ ለማደስ ስንቴ ምሶሶዎቻችንን አፈረስን ፤ በመጥበቅ እና በመመላላት ትርጉማችንን አረከስን .........?? እስከ ምንስ ድረስ ነው የትዝታ እውነታ ጠፍቶብን "ትዝታ " ብለን ሚዛን የማይደፋውን የእንክርዳድ እሳቤያችን ውስጥ ለመደበቅ ያለ ስሙ ያለ ማእረጉ የምንከተው መቀመቅ ? ወዴትስ ነው ዛሬን ከእኛ አሽሸን በራዕያችን አድማስ ተንሸራተን ትናንት ውስጥ ምንኮበልለው.......?? ትዝታ ማለት ከዛሬ መደበቂያ ሳይሆን ለነገ መወንጨፌያ የፅናት በትር ናት።❞ ✍ህሊና በላይነሽ @zephilosophy
Show all...
35👍 13🤔 2
"ዋጋ አውጪለት" (መልአኩ ስብሐት ባይህ) * በመንታ መንገድ ላይ መንታ ልቤን ይዤ አንድዜ ደንዝዤ አንድዜ ፈዝዤ ። ምግባሬን ከምግባርሽ ሳማታ ሳላጋ ሳጣልዝ ሳውታታ ። በውጥንጥን ውጥን ስመትር ስለካ በጭንቅንቅ ጭንቀት ስጋግር ሳቦካ ። በፋኖሱ መሀል ጮራውን እያየሁ ከጮራው መሀከል ያንቺን ወዝ እሻለሁ ። ደሞ አንድዜ ቆም ዘገም - ዘገም ቆም እላለሁ አሁንም ከዚያው ነኝ በዛው እነጉዳለሁ ። የኋሊት መመለስ ቀልቤን ቢከጅለው እኔ ግና እዛው ነኝ - እዛው ፣ እንደተውሺኝ አለሁ ። ትንቢታዊ ነገር ለነፍሴ ሲነገር ። መንታ መንታን ወልዶ መንታ እየፀነሰ ለስሜ ማበሻ ምጡ እየቀነሰ ። በነጸብራቅሽ ውጋጋን በጭላንጭሉ ትልምሽ ስር ካንቺነትሽ ስፍር ላንቺነትሽ ክብር ። እንደ ወፍ ዘራሽ በድንገት ከሥርሽ ስክመት በቅዬ ተንጋልዬ ተጋድሜ ተጠቅልዬ ። በልባምነቴ ቡርቅቅ ውግዝ በአንጀታምነቴ ሽምቅ ከለል ሸክፌሽ ስካለል ። ፍቅሬ ፍቅሬ ምሥጢረ ወክሬ ፍቅሬ ፍቅሬ ዙፋነ ወክብሬ ፍቅሬ ፍቅሬ መስዋዕተ ወዝክሬ እያልሁ አዘግማለሁ ቃላቶች ስላጣሁ ቃላት እተክላለሁ ልሳኔ ተዘግቶ እነጋገራለሁ ሙገሳ ጠፍቶብኝ አሞካሽሻለሁ ውዴ ውዴ ውዴ ውዴ እልሻለሁ ባንቺ ውድ መሆን እርካሽ ሆኛለሁ ። የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Show all...
👍 17 10🔥 3👏 2
...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ። ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ። የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን። "አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል። የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።" ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::'' ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው። ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው" አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል። ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው። አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር:: "ፍቅር መተወን አይችልም በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት። መፅሀፍ-አለመኖር ደራሲ- ዳዊት ወንድማገኝ የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Show all...
64👍 40👏 2🥰 1
ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ የሚያደርጉ 10 መንገዶች #Share (ላገባም ላላገባም የሚሰራ ነው።) __ የፍቅር ተፈጥሮአዊ አካሄድ አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የፍቅር ግንኙነቱ ሲጀመር የነበረው ፍቅር በሂደት እየቀነሰ የነበረው እንዳልነበረ ሊሆን ሁሉ ይችላል፡፡ በመሰረቱ ካልታረመ፣ ካልተኮተኮተ፣ በጥቅሉ አስፈላጊው እንክብካቤ ካልተደረገለት ዝም ብሎ ማበቡን እና መልካም ፍሬ ማፍራቱን የሚቀጥል ምንም ነገር የለም፡፡ ያልተሰራበት ግንኙነት እጣ ፈንታው ደስታ አልባ መሆን ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባሉ፣ ለብዙዎች ምሳሌ ሆነው የሚቀርቡ የፍቅር ግንኙነቶች እንኳን ፍፃሜያቸው የማታ ማታ መራራቅ አልፎ ተርፎም መለያየት ሊሆን ይችላል፡፡ ትልቁ የፍቅር ሕይወት ፈተና ሲጀመር የነበረው ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ ማድረግ ነው፡፡ ምንም እንኳን ፍቅርን ለመመስረት ሁለት ሰዎች አስፈላጊ ቢሆኑም እንዲፀና እና ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ለማድረግ ግን አንድ ሰውም በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ኃላፊነቱን ግን አስቀድሞ መውሰድ ይጠይቃል፡፡ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ነው የሚያድረው፡፡ ክፍቱን የተተወ ቤት ውስጥ ብዙ ነገር ገብቶ ይወጣል፤ ብዙ ነገር እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ያለመጠባበቅ የቻልነውን ያህል ለማድረግ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ውጤቱ ላይ ትኩረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ዋናው ነገር ከእሷ ወይንም ደግሞ ከእሱ መምጣቱ ሳይሆን ዞሮ ዘሮ የሁለቱ የፍቅር ግንኙነት ጣፋጭ እና ፅኑ መሆኑ ነው፡፡ ፍቅራችሁ የሚፀናበት ይበልጥ የፈካ እና የደመቀ፣ ዘመናትን የተሻገረ መሆን የሚችለው ያለመጠባበቅ ኃላፊነት ወስዳችሁ መስራት ያለባችሁን መስራት ስትችሉ ነው፡፡ ምንም ተባለ ምንም አንድ ሰው ሁልጊዜም ኃላፊነቱን መወጣት መጀመር አለበት፡፡ በራሱ ሊንቀሳቀስ እና ሊለወጥ የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ የትዳር ግንኙነት ሲሆን ደግሞ ለማደስ ጥረት ካልተደረገ ወደ መፍረሱም ሊያቀና ይችላል፡፡ ቀጥሎ የትዳር ህጎች ከሚል መጽሐፍ ውስጥ ያገኘናቸውን 10 ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ ያደርጋሉ የሚባሉ ህጎችን አለፍ አለፍ ብለን እናስቃኛችሁ፡፡ እነዚህ ተግባራት ላገቡ ብቻ ሳይሆን ላላገቡና በፍቅር ግንኙነት ላሉም የሚጠቅሙ ተግባራት ናቸው ፡፡ 1✍ስሜትን የሚያነቃቁ ነገሮችን ማድረግ መቼም አብሮ ሲኖር የሚያጋጭ፣ የሚያቀያይም፣ ቅሬታ የሚፈጥር ወዘተ ብዙ ነገር ይኖራል፡፡ ስሜት ይህንን ተከትሎ ይቀዘቅዛል፡፡ ፍቅር ስሜትም ነው በአንድ ጎኑ፡፡ በመሆኑም ስሜትን የሚያነቃቃ ደስታ የሚፈጥር ነገር ማድረግ የአድናቆት አስተያየት መስጠት ለአብነት ያህል አስፈላጊ ነው፡፡ ስራዬ ብላችሁ ማድነቅን ተለማመዱ፡፡ “ትላንት ማታ ጓደኛዬ ቤት በጣም ተጫዋች ሆነህ ነበር ያመሸኸው፤ ደስ ብሎኛል”፣ “አምሮብሻል” ወዘተ ዓይነት አድናቆት ሊሆን ይችላል፡፡ ከትችታችን ይልቅ አድናቆታችን በጣም መብለጥ ይኖርበታል፡፡ 2✍ትችትን መቀነስና አድናቆት መጨመር በአንፃሩ ትችት ትዳር ሲመሰረት አካባቢ አስፈላጊ ነው ይላሉ ብዙ ሰዎች፡፡ ጊዜ በነጎደ ቁጥር ግን ሰዎች ለትችት አለርጂክ መሆን ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ትችትን መቀነስ አንድ አንድ ነገሮችን አይቶ እንዳላዩ ማለፍም ያስፈልጋል፡፡ መነገር አለበት የምንለው ነገር ካለም ከሁለት እና ሶስት አረፍተ ነገር ባልበለጠ እርዝማኔ መገልፅ ይመከራል፡፡ እርግጥ ነው ለትዳርና ፍቅር መጽናት አስፈላጊ የሆኑ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ከሆኑ፤ ግንኝነቱን በማይጎዳ መልኩ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው፤ ምክኒያቱም አለባብሰው ቢያርሱ በአፈር ይመለሱ እንዳይሆን፡፡ ስለዚህ ትችቱ ለፍቅር ግንኝነቱ ሲባል እንጂ እጸጽን ነቅሶ ለማውጣትና የእራስን ትክክለኝነት ለማጉላት መሆን የለበትም፡፡ ትችት በምንሰጥበት ጊዜ ከጥሩ ጀምረን መሀል ላይ ትችታችንን ገልጸን ከዛም በአድናቆት ወይም በበጎ ነገር መደምደም ይመከራል (ሳንድዊች እስታይል እንደሚባለው)፡፡ 3✍አዳማጭ ሁኑ ማደመጥ ለፍቅረኛችን ወይንም ለትዳር አጋራችን የምንሰጠው ትልቁ ስጦታ ነው፡፡ ትርጉም መስጠታችሁን፣ ተሳሳተ የምትሉትን መረጃ ማስተካከላችሁን ጥላችሁ በሙሉ ልባችሁ ማዳመጥ ጠቃሚ ነው፡፡ 4✍ራሳችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ ለራሳችሁ፣ ጓደኞቻችሁ፣ ቤተሰባችሁ ወዘተ ከትዳራችሁ በተጨማሪ ጊዜ መስጠት ጥሩ ነው፡፡ የግላችሁ ጊዜ ማሳለፊያ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ በራሳችሁ እና በራሳችሁ ጉዳይ ላይ ምንም ትኩረት የማታደርጉ ይልቁንም ሙሉ ትኩረታችሁ የትዳር አጋራችሁ ላይ ከሆነ ተቺዎች ወይንም ደግሞ ጭንቀታሞች ትሆናላችሁ፡፡ እያንዳንዷን እዚህ ግባም የማትባል ጉዳይ እያነሳችሁ ስትጥሉ አሰልቺ እና አፋኝ ዓይነት ግንኙነት እንዲኖራችሁ ታደርጋላችሁ፡፡ 5✍ይቅርታ ጠይቁ ምንም እንኳን ለተፈጠረው ችግር የእናንተ እጅ ድርሻ ትንሽ እንደሆነ ብታስቡም “እኔ ይኼ ችግር እንዲፈጠር ለተጫወትኩት ሚና ይቅርታ ይደረግልኝ” ማለትን ተለማመዱ፡፡ 6✍ይቅርታ ካልተጠየኩኝ ሞቼ እገኛለሁ አትበሉ አንድ አንድ ጊዜ ይቅርታ ሳይጠይቁ ሰዎች መተዋቸውን፣ ለውጥ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሊገልፁ ይችላሉ፡፡ይቅርታ ካልተጠየኩ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ግን አላስፈላጊ ተደራራቢ ችግር ይፈጥራል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ተፈላጊው ለውጥ መምጣቱ ነው፡፡ 7✍ዘወትር ፈላጊዎች አትሁኑ በስሜት የራቀ የሚመስል ሰው ጫና ሲደረግበት ይበልጥ ይርቃል፡፡ መተንፈሻ አየር መስጠት፣ ራስ ላይ ትኩረት ማድረግ በአንፃሩ የራቀንም ያቀርባል፡፡ የት ወጣች የት ገባች ውጤታማ አይደለም፡፡ 8✍ሀሳባችሁን አጭር እና ለስላስ በሆነ መንገድ ግለፁ ደጅ ደጁን የሚል ሰው አንድ አንድ ጊዜ ህመም የሚፍጥረበትን የቃላት ልውውጥ ሽሽት ውስጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሀሳብን አጠር አድርጎ፣ በተለሳለሰ መንገድ መግለፅ ጥሩ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ድምፅንም ጭምር ዝቅ አድርጎ መናገር ተገቢ ነው፡፡ ከጣራ በላይ ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገር ቁጣ ይመስላል፤ ከሆነም በዛ መልኩ መግለፁ አስፈላጊ አይደለም፤ ከመፍትሄነት ይልቅ የባሰ ችግር ፈጣሪነቱ ይጎላል፡፡ 9✍ሁሉን መስዋዕት አታድርጉ ተለዋወጭ ሰው መሆን አስፈላጊ ባይሆንም ሁሉንም ነገር ለእርስ በእርስ ግንኙነቱ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን አይመከርም፡፡ ጫና እየተደረገባችሁ ሁሉንም እምነታችሁን፣ ምርጫችሁን እና መንገዳችሁን ገደል አትክተቱ፡፡ 10✍በመጠኑም ቢሆን ሁለታችሁም የግልጊዜ ይኑራችሁ ሰዎች በባህሪያቸው የሚሳቡት ከእርስ በእርስ ግንኙነቱ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ የሚወዳቸው የራሱ ነገሮች ወዳሉት ሰው ነው፡፡ የመጽሐፍት ክበብ፣ በጎ ፍቃድ፣ ዋና ወዘተ ሊሆን ይችላል ባላችሁ ትርፍ ጊዜያችሁ መሞከሩ ይመከራል፡፡ ለብቻችሁ የሚኖራችሁ ጊዜ በጋራ ለሚኖራችሁ ጥሩ ቆይታ አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡ሁሌ አብሮ መሆን መዛዛግና መሰለቻቸት ሊፈጥር ይችላል ፡፡ በነጋሽ አበበ የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Show all...
👍 128 26🙏 4
“I believe in the sun even when it is not shining and I believe in love, even when there’s no one there. And I believe in God, even when he is silent. I believe through any trial, there is always a way But sometimes in this suffering and hopeless despair My heart cries for shelter, to know someone’s there But a voice rises within me, saying hold on my child, I’ll give you strength, I’ll give you hope. Just stay a little while. I believe in the sun even when it is not shining And I believe in love even when there’s no one there But I believe in God even when he is silent I believe through any trial there is always a way. May there someday be sunshine May there someday be happiness May there someday be love May there someday be peace….” – Unknown Author የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Show all...
👍 55 22🔥 3👏 2😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
How to find inner peace
Show all...
👍 25 3
አደጋን ተጋፈጥ ከብዙ ሰዎች የበለጠ ውድቀት ይገጥመኛል፡፡ በንግድ ሥራዬ ውድቀት ግጥሞኛል፡፡ በማህበራዊ ግንኙነት ውድቀት ገጥሞኛል፡፡ በሕይወቴ ብዙ ጊዜ ውድቀት ይገጥመኛል፡፡ ይህ ለምን እንደተከሰተ በመገረም አስባለሁ፡፡ በውድቀቴ እማረር ነበር፡፡ አሁን ግን ገብቶኛል፡፡ ውድቀት ከታላቅ ደረጃ ለመድረስ የሚከፈል ዋጋ ነው፡፡ ውድቀት የታላቅ ስኬት መሠረታዊ ግብአት ነው፡፡ አዲስ ነገር በመፍጠር ጠቢብ የሆነው ዴቪድ ኬሊ ይህን ብሏል፡- «ቶሎ ውደቅና ፈጥነህ ተነሥ››.. ከምቾት ቀጠናህ ሳትወጣና በተጠና መልኩ አደጋን ካልተጋፈጥህ ልታሸንፍ አትችልም፡፡ ብዙዎቻችን የምንኖረው የደህንነት ስሜት በሚፈጥርልን በሚታወቅ «ወደብ› ላይ ሆነን ነው። ለሃያ ዓመታት አንድ ዓይነት ምግብ ስንመገብ ኖረናል፣ ለሀያ ዓመታት በአንድ ሥፍራ ተወስነን ኖረናል፤ ለሀያ ዓመታት በአንድ መንገድ ተመላልሰናል፣ ለሀያ ዓመታት አንድ ዓይነት አስተሳሰብ አንጸባርቀናል። በዚህ መልኩ አስደሳች ሕይወት ለመምራት አይቻልም፡፡ እስከዛሬ ስትሰራ የኖርከውን መሥራት ከቀጠልክ እስከዛሬ ስታገኝ የቆየኸውን ማግኘትህን ትቀጥላለህ፡፡ አይንስታይን እብደትን የገለጸው «ተመሳሳይ ነገር እየሰሩ የተለየ ውጤት መጠበቅ» በማለት ነው። እውነተኛ ሐሴትን ልትጎናጸፍ የምትችለው አደጋን ተጋፍጠህ ወደ ታላቁ ባሕር ቀዝፈህ ስትገባ እንጂ ከወደብ ላይ ተወስነህ ስትቆም እይደለም፡፡ ውድቀት ደረጃህን ከፍ የማድረግ ሂደት አካል ነው። በምድሪቱ ላይ የሚገኙ ግዙፍ ስኬታማ ተቋማት ስኬትማ ከመሆናቸው በፊት ብዙ ውድቀትን አስተናግደዋል፡፡ በጣም ስኬታማ ሰዎች ከተራ ሰዎች ይበልጥ ውድቀት አስተናግደዋል።  ለእኔ፣ ውድቀት ለመሞከር ና ለመድፈር አለመቻል ነው። እውነተኛ አደጋ ያለው አደጋ አልባ ሕይወት በመምራት ነው፡፡ ማርክ ትዌይን ትዝብቱን እንዲህ ሲል አስፍሯል፡- ‹ከሀያ ዓመታት በኋላ ከሠራሃቸው ይልቅ ባልሰራሃቸው ነገሮች ትበሳጫለህ›› ስለዚህ፣ ከዛሬ ጀምር፡፡ ✍️ሮቢን ሻርማ share : @Human_Intelligence
Show all...
👍 79 9🔥 5🤣 1
🔑Conditioned Mind "It is not because things are difficult that we do not dare; it is because we do not dare that things are difficult." - Seneca --- 🔆በሕንድ መንደሮች ውስጥ ሲዘዋወር የቆየ አንድ እንግዳ ሰው ነዋሪዎቹ ዝሆኖቻቸውን የሚጠብቁበት መንገድ ግራ አጋብቶታል... እጅግ ግዙፍ የሚባሉ ዝሆኖች በቀላሉ ሊበጠሱ በሚችሉ ገመዶች ታስረው በጸጥታ የመቆማቸው ምስጢር እውነትም እንቆቅልሽ ነበር... 'እንዴት ሊሆን ይችላል?'... ⚜️ግራ መጋባቱ እየቀጠለ ሲሄድ ወደ አንድ የዝሆኖች አሰልጣኝ ዘንድ ቀርቦ 'ይህን እንዴት ማድረግ ቻላችሁ?... ዝሆኖች በምድር ላይ በጉልበታቸው ተስተካካይ የሌላቸው ፍጥረታት መሆናቸው ይታወቃል... በዚህ ሰላላ ገመድ ታስረው እንዲቆዩ ያደረጋቸው ምስጢር ምንድነው?...' ሲል ጠየቀ... 'ደህና...' አለ ዝሆኖችን የሚገራው ሰው... በእንግዳው ሰው ጥያቄ አንዳችም መገረም ሳያሳይ... 'በዚህ ገመድ መታሰር የሚጀምሩት ከደረጁ.. ጉልበት ካበጁ በኋላ አይደለም... ገና ግልገል ሳሉ ነው... በዚያ የማለዳ ዕድሜ አሁን የምታየው ገመድ እነርሱን አስሮ ለመቆየት በቂ ነበር... እየቆዩ ሲሄዱ ገመዱን የሚበጥስ አቅም ቢፈጥሩም በልጅነታቸው የታተመባቸው እምነት ግን ዛሬም ገመዱን መበጠስ እንደማይችሉ ይነግራቸዋል'... 🔆ሰውየው በጥበባቸው ተገረመ... ግዙፉን ዝሆን ለማሰር ግዙፍ ሰንሰለት አላስፈለጋቸውም... አስተሳሰባቸውን የሚያስር የማለዳ ልማድ በቂ ነበር... ነገሩ ሰንሰለት ካሰረው ልማድ ያሰረው ነው... 'ልማድ ከብረት ይጠነክራልና' ሼክስፒር እንዳለው... 🔆የኑረት ውበት በየደረሱበት መጠየቅ... የሰውነት ከፍታም በየመዳረሻው መርቀቅ ቢሆንም ከተነገረው ዘሎ 'ለምንና እንዴት' ለማይል አዕምሮ የነበረን ማስጠበቅ እንጂ 'አዲስ ነገር' ማፍለቅ አይሆንለትም... የኑረት ስኬትም ሆነ ውድቀት በእምነትህ ልክ ይገነባል... ቡድሃ "All that we are is the result of what we have thought. The mind is everything. What we think we become. " የሚለውን ቃል በትምህርቱ መጀመሪያ ላይ ያስቀመጠው ለዚሁ ነበር... 💫የምታምናቸውን ነገሮች ለምን እንዳመንካቸው ጠይቀህ ታውቃለህ?... የተቀበልካቸውን እሳቤዎች ልክነት በ'እንዴት' ዓይን መዝነህ ታውቃለህ?... የነገሩህን መጽሐፍትና ያስተማሩህን አንደበቶች መርምረህ ታውቃለህ?... እርግጠኛ ስለሆንክባቸው ጉዳዮች ቢያንስ ለራስህ በታማኝነት የምታቀርበው መልስ አለህ?... ወይስ እንደ ግዙፉ ዝሆን በሰላላ የአስተሳሰብ ወደሮ ታብተሃል?... መጠየቅስ አድክሞህ ይሆን?... Wynn Bullock የተባለ ሰው... "If you stop searching, you stop living, because then you're dwelling in the past. If you're not reaching forward to any growth or future, you might as well be dead." ብሎ ነበር... ሶቅራጥስ በበኩሉ "The unexamined life is not worth living" ብሏል... ✨ከማለዳ ውልደት እስከ ውድቅት ህልፈት የምትሳበው ኑረት ሁለንተናዋ በጠነከረ ልማድ የተቀየደ ነው... ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ የትወናዋን አካሄድ የሚወስንላት መራሔ ተውኔት ልማድ ወይም እምነት ይባላል... የምታምነውን ነው የምትሆነው... ግና.. የማለዳ እምነትህ ረፋድ ላይ... የረፋድ እሳቤህ ቀትር ላይ... የቀትር ግንዛቤህ በተሲዓት... የተሲዓት እውነትህ በምሽት ካልተመረመረ ከልማድ እስረኛነትህ ሳትፈታ ውድቅትህ ይመጣል... "The world is a prison and we are the prisoners.Dig a hole in the prison wall and let yourself out." ይልሃል ሩሚ... 🔑'ተለምዷል' የሚልህ ሰው ሲበዛ ጠርጥር... ቅኝት ነው... 'ምንም ማድረግ አይቻልም' ካለህ ተቃኝቷል በቃ... 'ያለ ነው'... 'ባሕል ነው'... 'አሰራር ነው'... 'እከሌ የሚባል ሰው ወይም መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል'... ወዘተረፈዎች የቅኝት መገለጫዎች ናቸው... እዚህ መንደር ውስጥ 'ለምን' ባይ የተገኘለት የእብደት ታፔላ ይለጠፍለታል... 🔆ዕድሜ ልኩን ጥርሱን ሳያጸዳ የኖረ ሰው ለተወሰኑ ቀናት ብሩሽ ተጠቅሞ በመተዉ የአፉን ሽታ ቢያስተውል ሊል የሚችለው አንድ ነገር 'የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል' ነው... ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት ሽታውን ተላምዶት ስለቆየ 'አፍህ ይሸታል' ቢሉት አይቀበልም ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳት ይጀምራል... ተለማምዶ እስኪዘነጋው ድረስ... ጠረን እንድትለይ የሚረዱህን 'ብሩሾች' ስንቴ 'ያሸታሉ' ብለህ ጣልክ?... ስንቴስ ወደ ቀደመ ሽታህ ተመለስክ?... ኒቼ በተወልን ድንቅ መስመር የማያልቀውን እንጨርስ... "If you have a 'why' to live by, you can live with any 'how'." የ'ለምን' እና 'እንዴት' ድፍረት ይስጠን!!                  ሰላም...❤️                              ✍ ደምስ ሰይፉ @Human_Intelligence
Show all...
👍 83 9🔥 4🥰 4
የአንተ ክብረ-ወሰን ምንድን ነው? ፈላስፋው አርተር ሾፐን-አወር ይህን ተናግሯል፡፡ ‹‹ብዙ ሰዎች የራሳቸውን የራእይ ገደብ የዓለም ወሰን አድርገው ይወስዳሉ፡፡ ጥቂቶች ግን እንዲያ አያስቡም፤ ከእነርሱ ጎራ ተሰለፍ፡፡» በጣም ጥልቅ ነጥብ ነው፡፡አሁን የምትኖረውን ሕይወት ባለህ አቅም ልክ እየኖርክ ነው?? ምናልባት ነገሮችን የምትመለከተው በፍርሐት፣ በገደብና በሀሰተኛ ግምት እይታ ይሆናል። የመስኮትህን መስታወት ወልውለህ ወደ ውጭ ስትመለከት አዲስ አማራጮችና እድሎች ይከሰታሉ፡፡ ዓለምን የምንመለከተው እንደሆነው ሳይሆን እኛ እንደሆንነው መሆኑን አስታውስ፡፡ ከአስርት ዓመታት በፊት ደስታ የራቀው ጠበቃ ሆኜ ሕይወቴን የምመራበት የተሻለ መንገድ እየፈለግሁ ሳለ ይህ ሐሳብ ሕይወቴን ለውጦታል፡፡ ከ1954 ዓ.ም. በፊት የአንድ ማይል ርቀትን ከአራት ደቂቃ በታች በሩጫ ሊሽፍን የሚል ሯጭ እንደማይኖር ይታመን ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ሮጀር ባኒስተር ይህን ክብረ ወሰን ከሰበረ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የእርሱን ክብረወሰን በርካታ አትሌቶች ለማሻሻል በቁ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ምን እንደሚቻል ለዓለም እርሱ አሳይቷልና፡፡ ከእርሱ በኋላ የሮጡ አትሌቶች አዲስ ማነፃፀሪያ ነጥብ አግኝተዋል። ያን እምነት ታጥቀውም ሰዎች የማይቻለውን ለማድረግ በቁ፡፡ የአንተ ክብረ-ወሰን ምንድን ነው? ለመሆን እንደማትችል ለማድረግ እንደማትችል፣ ልታገኝ እንደማትችል በማሰብ ስለራስህ የያዝከዉ የውሽት ግምት ምንድን ነው? አስተሳሰብህ እውነታህን ይፈጥራል፡፡ እምነቶችህ ድርጊቶችህን ስለሚመሩ ከአስተሳሰብህ ጋር በሚቃረን መልኩ ፈጽሞ ምንም ነገር አታደርግም፡፡ የሕይወትህ ደረጃ የአስተሳሰብህ ደረጃ ነፀብራቅ ነው። በሕይወትህ አንዳች ነገር ሊከሰት እንደማይችል ካሰብክ ያን ግብ እውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን የምትወስድበት አንዳችም መንገድ አይኖርም፡፡ የ«አይቻልም» አስተሳሰብህ ራሱን እውን ያደርጋል። በራስህ ላይ የምትፈጥረው ገደብ መድረስ ከሚገባህ የታላቅነት ደረጃ እንዳትደርስ ጠልፎ የሚጥልህ ሰንስለት ነው፡፡ ✍️ሮቢን ሻርማ Share : @Human_Intelligence
Show all...
👍 59 10
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም!! በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር! "ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው:: ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው:: ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ:: እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:- ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም ! እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም ! ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው ! እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም ! ወንድምህ ቢስት በቅን መንፈስ አቅናው ! እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት! የስብዕና ልህቀት
Show all...
👍 126 44🙏 10🔥 4