ch
Feedback
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

前往频道在 Telegram

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

显示更多
222 262
订阅者
-13524 小时
-6137
-2 27430
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
17
照片不可用在 Telegram 中显示
ፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ‼️ ከጥፋቱ የማይመረው ጉጅሌው የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በመግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 በመደብደብ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል። በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም የአዛውንቶች የህወሓት ጉጅሌ በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል። ይህ የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም ጉጅሌው ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል። ይህ ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው ተስፋ ቢሱ የህወሓት ጉጅሌ ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የዜጎች ደህንነትና የወሰኑን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራስን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ እንገልፃለን። በተያያዘ ዜና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በፌስቡክ ገፃቸው የህወሓት ጦር አፋር ድረስ ዘልቆ ጦርነት መክፈቱን አረጋግጠዋል። በጉዳዩ ላይ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ስለትንኮሳው ከፌዴራል መንግስትም ፣ ከህወሓት እንዲሁም ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል የተባለ ነገር የለም። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
280😭 76😁 25👍 24😡 8😱 7🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
17😱 2🔥 1🎉 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የ34 ዓመቱ ዞህራን ክዋሜ ማምዳኒ የኒው ዮርክ ከንቲባ ሆኖ ተመረጠ‼️ በአሜሪካ ትልቋ ከተማ ኒው ዮርክ ለከንቲባነት በመመረጥ የመጀመሪያው ሙስሊም በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ዞህራን የኒው ዮርክ ከንቲባ እንዲሆን ንቅናቄ ያደረጉ እና ድምጽ የሰጡ ነዋሪዎችን በሳይጠቅስ አላለፈም። “የመናውያን የመደብር ባለቤቶች፣ ሴኔጋላውያን የታክሲ ሹፌሮች፣ ኡዝቤክስታናውያን ነርሶች እና ኢትዮጵያውያን ‘አክስቶች’” ሲል ድጋፍ የሰጡትን ዘርዝሯል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
385🙏 37😁 32👍 22🔥 15😡 10😱 8
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
24🔥 2😁 2
ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳዮች የተሰጠ መግለጫ‼️ ማንነት ተኮር ጥቃቶች ይቁሙ። መንግስት የዜጎችን ደህንነት ያስከብር። ፍትህ በማንነታችው ብቻ ተለይተው ለተጠቁ ዜጎች! በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮችን ኢላማ ያደረጉ አሰቃቂ ጥቃቶች መፈጸማቸውን መሰረት በማድረግ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ተቋማዊ ስምሪት ወስደን በአካባቢው ተገኝተን ለማጣራት ጥረት አድርገናል። በመሆኑም ጥቅምት 14 ለ15 2018 ዓ.ም. እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ 19 /2018 ዓ.ም. ኃይማኖት እና የእምነት ተቋማትን ኢላማ ባደረጉና በትጥቅ በታገዙ አካላት በርካታ አማኞች ከመገደላቸውና ከመጎዳታቸው በተጨማሪ በርካቶች መፈናቀል፣ የግል ንብረቶች እና የእምነት ተቋማት ውድመት መከሰቱን አረጋግጠናል። ይህ ማንነት ተኮር ጥቃት የበርካታ ዜጎችን ህይወት ከመቅጠፉም በላይ ከፍተኛ ቁሳዊ ውድመት እያስከተለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን የሰሞኑ አሰቃቂ ድርጊት ከቀድሞዎቹ የሚለየው በርካታ የዞኑን አካባቢዎች (ወረዳና ቀበሌዎች) ያካለለ፤ በዘመቻ መልኩ የተፈጸመ እና ከፍተኛ ጉዳት የተመዘገበበትና በድገግሞሽ መፈፀሙ ስር የሰደደ መሆኑን የሚያስገነዝብ እንዲሁም የአካባቢውን መንግስታዊ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር የተጠያቂነት ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ሆኖ አግኘተነዋል፡፡ በመሰረቱ አብን የትኛውንም አይነት ማንነትና አካባቢ መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶች በጽኑ ማውገዙ እንደተጠበቀ ሆኖ ችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ ህገ-መንግስታዊና አካታች መዋቅራዊ ስርዓት እንዲሰፍን መንግስት፣ ሁሉም የፖለቲካ ኃይል፣ የዲያጶራ ማህበረሰብና ልሂቃን ታሪካዊ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ጥሪ እናስተላልፋለን:: ይህ አሰቃቂ እና ያልተቋረጠ ተደጋጋሚ ግፍ በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ባለበት ሁኔታ በተጓዳኝ ሁለት እጅግ አሳፋሪና አደገኛ የማህበረ-ፖለቲካ ዝንባሌዎች ጎልተው ተስተውለዋል:- ሀ. ይህ በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ጥቃት እና ብሶት ፍፁም እንዳይታወቅ እና እንዳይነገር ከውስጥ እና ከውጭ በሸፍጥ የተሰለፉ በተቋማት ውስጥ የተኮለኮሉ ግለሰቦች እና ለ. የተፈጠረውን ችግር በህዝባችን ማህበራዊ ውቅር ውስጥ የተነዙ ስሁት ትርክቶች ውርስ እና ተፈፀሙ ያሏቸውን የታሪክ ቅራኔዎች ማወራረጃ አድርገው የሚያቀርቡ ከታሪክም ካሉበት ተቋም ዓላማና ተልዕኮ ያልተማሩ የሁለት መንገድ ተጓዦችና ግጭት ጠማቂዎች በተጎጅዎች ላይ ጥላቻን ሲያስተላልፉ ተመልክተናል። በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ አይነቱን የተዛነፈ የሀሳብና የተግባር አካሄድ በመራቅና በማስተካከል የቀደመ ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ እያስተላለፍን። 1. በመንግስት በኩል፤ ሃገራዊና ቀጠናዊ የፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳዬችን በግልፅና በኃላፊነት ስሜት ለመፍታት አስፈላጊውን ትጋት እንዲያደርግና እንዲያስተካክል፣ ችግሮቹ ተባብሰው ወደ ለየለት ግጭት ከመገባቱ በፊት ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ በጥብቅ እናሳስባለን። 2. የፌደራል የጸጥታ አካላት ጣልቃ እንዲገቡ፣ ተጠያቂነትንና ፍትህን ሊያሰፍን የሚችል ገለልተኛና ግልጽ ምርመራ እንዲከናወን እና ዘላቂ የፖለቲካና የህግ መፍትሄዎችም ተግባራዊ አንዲደረጉ በአጽንዖት እንጠይቃለን፡፡ 3. የወደሙ እምነት ተቋማት ተመልሰው እንዲገነቡ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ እና የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ወደቅያቸው መልሶ በማስፈር ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኙ መንግስት እና ሁሉም የሚመለከተው አካል እርብረብ እንዲደርግ ጥሪ እናቀርባል፡፡ በመጨረሻም አብን በተፈጸመው ድርጊት የተሰማውን ከፍተኛ ሀዘን እየገለፀን ለሟች ቤተሰቦች ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መጽናናትን እንመኛለን፡፡ ጥቅምት 24/ 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
353👍 51😁 50💔 27😡 15🙏 13🔥 9
照片不可用在 Telegram 中显示
18
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
11
照片不可用在 Telegram 中显示
ዶናልድ ትራምፕ በናይጄሪያ ክርስትያኖች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያ በመጥቀስ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ዛቱ‼️ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ናይጄሪያ በክርስትያን ዜጎቿ ላይ የሚፈጸም ስቃይን ቸል ብላለች በማለት ከወነጀሉ በኋላ የመከላከያ ሚኒስቴር ለወታደራዊ እርምጃ እንዲዘጋጅ ማዘዛቸውን ተናገሩ። ናይጄሪያ ይህንን የዶናልድ ትራምፕን ውንጀላ በተደጋጋሚ አስተባብላለች። ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በአገሪቱ የሚገኙ ክርስትያኖች ላይ "የጅምላ ግድያ" ይፈጸማል ሲሉ ጽፈው፣ የአገሪቱ መንግሥት "በፍጥነት እርምጃ" የማይወስድ ከሆነ "ለናይጄሪያ የሚሰጠውን እርዳታ እና ድጋፍ ወዲያውኑ እናቆማለን" ሲሉ ዝተዋል። አርብ ዕለት እንዲሁ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ላይ ይደርሳል ያሉትን መጠነ ሰፊ መከራ እና ግድያ በመጥቀስ አገሪቱን "አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ በተለየ መልኩ የምትታይ" በሚል መፈረጇን አስታውቀው ነበር። ቅዳሜ ዕለት የናይጄሪያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ባወጣው መግለጫ የዶናልድ ትራምፕን ፍረጃ ውድቅ አድርጎታል። የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር የሱፍ ቱጋር በሰጡት መግለጫ የትራምፕ አቋም በናይጄሪያ ያለውን እውነታ አያሳይም ብለዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
357👍 69😁 56🙏 13😡 12🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
18
照片不可用在 Telegram 中显示
በታንዛኒያ  ተቃውሞ በትንሹ 700 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ‼️ በታንዛኒያ ከምርጫ ሂደት ጋር ተያይዞ  በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በትንሹ 700 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ የተቃዋሚው ፓርቲው ቻዴማ፣ አጠቃላይ ምርጫውን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 700 ገደማ ነው ብሏል፡፡ ከ500 በላይ ሰዎች ሞተዋል - ምናልባትም በመላው አገሪቱ  ከ700 እስከ 800 ይሆናሉ” ሲል የደህንነት ምንጭ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ተናግሯል፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
😭 142 87👍 10💔 8👏 3😁 2🕊 2
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
20
ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ!! የአባታችን የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ሞት በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ የሐዘን ድባብ ፈጥሮብን መቆየቱ ይታወቃል። ተቀዳሚ ሙፍቲ እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስ በብዙ መልኩ ኢስላምንና ሙስሊሞችን ሲያገለግሉ የኖሩ አባት ነበሩ። በተለይ ለአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ደግሞ ተቋሙን በመሪነት ከአስር ዓመታት በላይ የመሩና አሻራቸውን ያስቀመጡ መሪያችን እንደመሆናቸው ኃዘናችን ጥልቅ መሆኑን ከዚህ በፊት ባወጠናቸው ተከታታይ መግለጫዎች መግለጻችን ይታወሳል። አሁን በድጋሚ አላህ (ሱ.ወ) ምህረቱን እንዲለግሳቸዉና ጀነተል ፊርደዉስን ማረፊያቸዉ ያደርግላቸዉ ዘንድ አላህን እንማጸነዋለን። በማስከተልም ከሰሞኑ ከታዩ ሁነቶች ጋር በተያያዘ በቀጣይ ነጥቦች ላይ የምክር ቤቱን አቋም እንደሚከተለው ለመግለጽ እንወዳለን። 1. ለሕዝበ ሙስሊሙ አንድነት የመስራት ታሪክ ያላቸው ሙፍቲ ሞት ሕዝባችን በሀዘን ዉስጥ በነበረበት ሁኔታ ከቀብር ስፍራቸው ጋር ተያይዞ አላስፈላጊ የሆኑ ንትርኮች መነሳታቸው አሳዝኖናል። መሰል ዉዝግቦች ስሜትና ቡድንተኝነት ሲታከልባቸው ሙፍቲ ሲለፉለት የነበረውን አንድነትን ከማስጠበቅ በተቃራኒ ሕዝባችንን ወዳልሆነ ንትርክ፣ ጭቅጭቅ እና ክፍፍል የሚያመራ አደገኛ ነገር ነው። 2. ተቀዳሚ ሙፍቲ የተቀበሩበት ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽን በደብዳቤ ቁጥር አ/አ/ፕ/ል/ኮ02/910/2013 በቀን 05/10/13 በተፃፈ ደብዳቤ ከቅይጥ መኖሪያነት ወደ መካነ መቃብርነት የተቀየረ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ስለሆነም ስፍራውን በአዲስ አበባ ውስጥ እንደሚገኙት የሕዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብሮች በመቁጠር በአስራ ሁለተኛ መካነ መቃብርነት እውቅና ሰጥተነዋል። በመሆኑም የመቃብር ስፍራውም ተጨማሪ የማስፋሪያ ጥያቄ ለመንግስት ከማቅረባችን በተጨማሪ እንደሌሎቹ መካነ መቃብሮች ማንኛውም ሙስሊም ሲሞት የሚቀበርበት በመሆኑ ለመካነ መቃብሩ አስፈላጊውን ጥበቃ፣ ድጋፍ እና ክትትል በመጅሊሱ በኩል እንደሚደረግለት ማሳወቅ እንወዳለን። ስለሆነም ከአሁን በኋላ ከመካነ መቃብሩ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት አጀንዳዎች ሊቆሙ እንደሚገባ አናሳስባለን። 3. ከዚህ በኋላ የተለያዩ አጅንዳዎችን ምክንያት በማድረግ በሕዝባችን መካካል ክፍፍልን የሚፈጥሩና የሚያባብሱ እንዲሁም ሰላምን የሚያደፈርሱ ንትርኮች፣ ጭቅጭቆች እና ውግዘቶች እንዲቆሙ እናሳስባለን። ዉይይትን፥ መማማርንና መተሳሰብን ዓላማ ያላደረጉ መልዕክቶች በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በማንኛውም መድረክ እንዳይተላለፉ ጥሪ እናደርጋለን። 4. ለየትኛውም ሃይማኖታዊ አለመግባባቶች መፍትሄ ፍለጋው መንገዱ አላህ እንደነገረን መመለሻችን ቁርኣንና የነብያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ፈለግ(ሱና) ዋቢ በማደረግ ሊሆን ይገባል። በዚህ ረገድ አርዓያዎቻችን መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ.) እና ሰሀቦቻቸው(ረ.ዐ.) ናቸው። ዑለሞችና ዱዓቶች የሕዝባችንን የዲን ግንዛቤና እውቀትን ለማስፋት የምታደርጓቸው አስተምህሮቶች፥ ዳዕዋዎች፥ በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ጥረቶች ከስሜት በራቀ፤ በእውቀት፣ በጥበብና በለዘብታ ቃል የተላበሰ መሆኑን ባረጋገጠ መልኩ ሊቀጥል እንደሚገባ እናሳስባለን። 5. አንዳንድ አካላት የተፈጠረውን ሁኔታ ሲጠብቁት እንደነበረ መልካም አጋጣሚ በማየት የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎትና ዓላማን ለማሳካት ሕዝቡን የሚያሳዝኑ ድርጊቶችንና ንግግሮችን በማድረግ የሕዝባችንን ሐዘን አባብሰዋል። ምክር ቤቱ በምርጫ የተጣለበትን ታላቅ አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዚህ ረገድ ማንኛውንም የሕዝባችንን አንድነትና ጥቅሞችን የሚጎዱ አካላትንና አካሄዶችን ፈጽሞ እንደማይታገስ በጥብቅ ለማሳሰብ አንወዳለን። 6. በመጨረሻ በተከበሩ አባታችን ህልፈት ከፍተኛ ሀዘን ላይ ከሚገኙት ቤተሰቦቻቸው ጋር በመነጋገር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ የሚዘከሩበትና መልካም ሥራዎቻቸው ቀጣይነት እንዲኖራቸው የምናደርግበት ተቋም ጉዳይ ጥናት እየተደረገበት መሆኑን እየገለፅን ሙፍቲ ሐጂ ዑመርን ጨምሮ ሕዝበ ሙስሊሙን በማስተማርና አንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩና በሞት የተለዩንን እንደነ ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፥ ሐጅ ሙሐመድ ራፊዕ፥ ሐጅ ዘይኑ ሙቅና፥ ሐጅ ሙሳ ኪኪያና ሌሎችም ታላላቅ ዓሊሞቻችንንና ዱዓቶቻችን አላህ ጀነተል ፊርደውስን እንዲለግሳቸው አላህን እንማጸነዋለን። ሕዝበ ሙስሊሙም የእነርሱን መልካም አርዓያነትን በመከተል ኢስላማዊ እውቀት እንዲሰራጭና የሕዝበ ሙስሊሙ አንድነት እንዲጠናከር የየበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ እናደርጋለን። አላህ ሃይማኖታችንን፥ሀገራችንን እና ሕዝባችንን ከክፉዎች ተንኮል ይጠብቅልን። ጥቅምት 20 ቀን 2018 የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
显示全部...
458👏 35😁 25👍 21😱 8😡 7🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
9
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
18😱 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለ ቀይ ባሕር ያደረጉትን ንግግር "ቅዠት" ስትል ያጣጣለችው ኤርትራ መሪዋ ወደ ግብፅ ማቅናታቸው ተገለጸ‼️ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል "የብልጽግና የአሰብ ቅዠት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ይመስላል" በማለት የኢትዮጵያን መንግሥት ሲወነጅሉ፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ ወደ ግብፅ ተጉዘዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
😁 178 114🕊 16😡 11
照片不可用在 Telegram 中显示
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
显示全部...
33👏 3
照片不可用在 Telegram 中显示
በአሜሪካ በህገወጥ መንገድ ይኖሩ ከነበሩት መካከል 1.6 ሚሊየን ያህሉ በፈቃዳቸው ከአሜሪካ ወጥተዋል ተባለ‼️ የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነ በፈቃዳቸው ከወጡት በተጨማሪ 500 ሺህ ሰዎች እንዲወጡ መደረጋቸውን አስታውቋል። አሜሪካ በፈቃዳቸው ለሚወጡ ሰዎች የ1000 ዶላር ክፍያን እንደምትፈፅም ስትገልፅ የቆየች ሲሆን የአውሮፕላን ጉዞ ወጪንም ትሸፍናለች። ቢሮው በፓናማ በኩል የሚገቡ ስደተኞች 99.99% ቀንሷል ሲል እየመጡ ያሉትም ድንበራችን ጋር ሳይደርሱ እየተመለሱ ነው ሲል ገልጿል። ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሃገራቸው ያሉ ስደተኞችን በገፍ እንደሚያስወጡ ሲያስታውቁ የቆዩ ሲሆን ለዚሁ አላማም ከፍተኛ የገንዘብ በጀት መያዙ ተገልጿል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
194👏 22😱 6🔥 5
照片不可用在 Telegram 中显示
ቀይ ባህርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ‼️ የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን። ይህንን በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያን የቀይ ባህር የማጣት ውሳኔ ማን ወሰነ ብለን ስንፈልግ ተቋማት አልገቡበትም። ይህን የሚያህል የህልውና ጉዳይ ማን እንደወሰነ መጠየቅ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም። ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ ስታደግ ለቀጣናውም ልማት ምንጭ ትሆናለች። የምንፈልገው በትብብር ማደግ ነው። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
star reaction 2 315👍 99😁 17😱 13🙏 10🔥 1
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ‼️ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል። በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ። ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
显示全部...
star reaction 1 92😁 17🙏 9👍 7🔥 5