ch
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

前往频道在 Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

显示更多
194 690
订阅者
-7124 小时
-977
-64730
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእያንዳንዱ መንገደኛ የ890 ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል። ደቡብ አፍሪካ በሁለት በረራዎች ወደ ሃገሯ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓጓዙ 14 ኢትዮጵያውያንን እና 16 የባንግላዴሽ ዜጎችን ከሰዎች ዝውውርና የተሳሳተ ቪዛ ጋር በተያያዘ ከያዘች በኋላ መንገደኞቹን ባጓጓዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ቅጣት መጣሏን የሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞቹን ሰነድ በተገቢ መልከ ሳያጣራ ወይም በአጠራጣሪ ሁኔታ ስር በማጓጓዙ በእያንዳንዱ መንገደኛ 890 ዶላር ወይም 15,000 የደቡብ አፍሪካ ራንድ እንዲከፍል ተቀጥቷል። ደቡብ አፍሪካ የያዘቻቸው 30 ሰዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገች መሆኗን እና አሻራቸውን እየወሰደች መሆኗን ገልፃለች። ደቡብ አፍሪካ የምርመራው ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ሁሉም ሰዎች ወደመጡበት ሃገር ይመለሳሉ ያለች ሲሆን ሰዎቹንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደመጡበት እንዲመልስ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪነት አዛለች። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
🤣 116 78😢 30👍 14👎 12🤔 5💔 4
照片不可用在 Telegram 中显示
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰጥታ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት አንስታለች። የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም ለኢትዮጵያ ተሰጥቶ የነበረው የጊዜያዊ ከለላ መብት መነሳቱን አስታውቀዋል። አሜሪካ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ወደ ሃገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎች ጊዜያዊ ከለላ( Temporary protected status) ትሰጥ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያም ይኸው መብት ነበራት። አሜሪካ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሃገሯ የሚኖሩ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ጦርነትን ጨምሮ በአንዳንድ ምክንያቶች ወደመጡበት ሃገር መመለስ ለማይችሉ ሰዎች ይህንን ከለላ መስጠት ጀምራ ነበር። ይህ ከለላ የሚሰጣቸው ዜጎችም የሃገራቸው ሁኔታ እስኪሻሻል በአሜሪካ የመኖርና የመስራት መብት ሲሰጣቸው ከአሜሪካ ከመባረር ይጠበቁ ነበር። አሜሪካ" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች ደህንነት ላይ ስጋት አይፈጥርም" ያለች ሲሆን በዚህም የተነሳ ይኸው ከለላ መነሳቱን አስታውቃለች። አሜሪካ ሌሎች በአሜሪካ ለመቆየት ህጋዊ መሰረት ካላቸው ኢትዮጵያውያን ውጪ የኢትዮጵያ ዜጎች በ60 ቀናት ከሃገሯ እንዲወጡ አሳስባለች። ቀድመው ከአሜሪካ ለሚወጡ የትኬት ወጪያቸው እንደሚሸፈን፣ የ1000 ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥና ለወደፊቱ ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድል እንደሚኖራቸው ገልፃለች። ከፈረንጆቹ የካቲት 13 በኋላ ከለላው እንደሚያበቃ ገልፃ ያለ ከለላው በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደምታስር እና ከሃገሯ እንደምታባርር አስጠንቅቃለች። አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተመሳሳይ ከለላ የነበራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜጎችን መብትም ማንሳቷ ይታወሳል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
👎 78 67👍 24😢 19🤣 12👏 4🕊 3
照片不可用在 Telegram 中显示
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰጥታ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት አንስታለች። የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም ለኢትዮጵያ ተሰጥቶ የነበረው የጊዜያዊ ከለላ መብት መነሳቱን አስታውቀዋል። አሜሪካ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ወደ ሃገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎች ጊዜያዊ ከለላ( Temporary protected status) ትሰጥ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያም ይኸው መብት ነበራት። አሜሪካ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሃገሯ የሚኖሩ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ጦርነትን ጨምሮ በአንዳንድ ምክንያቶች ወደመጡበት ሃገር መመለስ ለማይችሉ ሰዎች ይህንን ከለላ መስጠት ጀምራ ነበር። ይህ ከለላ የሚሰጣቸው ዜጎችም የሃገራቸው ሁኔታ እስኪሻሻል በአሜሪካ የመኖርና የመስራት መብት ሲሰጣቸው ከአሜሪካ ከመባረር ይጠበቁ ነበር። አሜሪካ" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች ደህንነት ላይ ስጋት አይፈጥርም" ያለች ሲሆን በዚህም የተነሳ ይኸው ከለላ መነሳቱን አስታውቃለች። አሜሪካ ሌሎች በአሜሪካ ለመቆየት ህጋዊ መሰረት ካላቸው ኢትዮጵያውያን ውጪ የኢትዮጵያ ዜጎች በ60 ቀናት ከሃገሯ እንዲወጡ አሳስባለች። ቀድመው ከአሜሪካ ለሚወጡ የትኬት ወጪያቸው እንደሚሸፈን፣ የ1000 ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥና ለወደፊቱ ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድል እንደሚኖራቸው ገልፃለች። ከፈረንጆቹ የካቲት 13 በኋላ ከለላው እንደሚያበቃ ገልፃ ያለ ከለላው በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደምታስር እና ከሃገሯ እንደምታባርር አስጠንቅቃለች። አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተመሳሳይ ከለላ የነበራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜጎችን መብትም ማንሳቷ ይታወሳል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
照片不可用在 Telegram 中显示
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ያለውን ስራ ለማስፋፋት 138 ሚሊየን ዶላር ተበድሯል። የቴሌኮም ገበያው ለውጪ ተቋማት ክፍት መሆኑን ተከትሎ ከጥቂት አመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ የገባው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ያለውን ስራ ለማስፋፋት ከስታንዳርድ ባንክ 138 ሚሊየን ዶላር ተበድሯል። ሳፋሪኮም ባገኘው ብድር በኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎቶችን እና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት እንደሚሰራ ተነግሯል። ስታንዳርድ ባንክ ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲቀላቀል አማካሪና የገንዘብ ፈንድ ያደረገ ባንክ ሲሆን በሃብት(Assets )የአፍሪካ ግዙፉ ባንክ ነው። የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ አላማቸው ወጣቶች፣ ስራ ፈጣሪዎች እና የተገለሉ ማህበረሰቦች በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንዲሳተፉ በማድረግና በ2030 የታሰበው የጋራ ብልፅግና እንዲደረስ የብዙሃንን ህይወት መለወጥ እንደሆነ ተናግረዋል። ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊየን በላይ ንቁ ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን የ4ጂ የኢንተርኔት አገልግሎቱን ለግማሽ ያህሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽ አድርጓል። ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ከገባ በኋላ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም እና የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት መሰረተ ልማቶች ላይም ከ2.27 ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት አድርጓል። ዘገባው የተገኘው የTuko News ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
64🤬 5👍 4
照片不可用在 Telegram 中显示
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!! 🌟አያት ግራንድ ሞል ✨ 3000 የንግድ ሱቆች ✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ ✨ከ 24 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው ✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል 🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ 🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ  በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!! 💥ለበለጠ መረጃ በ 251944856735 በቀጥታ @tegegne123 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
显示全部...
3
照片不可用在 Telegram 中显示
ቻይና ኮንዶምን ጨምሮ በተለያዩ የወሊድ መከላከያዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መጣል ልትጀምር ነው። ቻይና ከፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮ የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶችና ምርቶች ከታክስ ነፃ እንደማይሆኑና የ13 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሚጣልባቸው አስታውቃለች። ቻይና ከ1980 እስከ 2015 ጥንዶች አንድ ልጅ ብቻ እንዲኖራቸው ታደርግ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ በ2015 ወደ ሁለት ልጆች ከዛም በ2021 ይህንኑ ቁጥር ወደ ሶስት ከፍ አድርጋ ነበር። የሚወለዱ ህፃናትን ቁጥር በእነዚህ ጊዜያት ለመቀነስም የወሊድ መከላከያ ከ30 አመታት በላይ ከታክስ ነፃ ሆኖ ነበር። በ2024 9.5 ሚሊየን ህፃናት በቻይና ሲወለዱ በ2019 ከተወለዱት 14.7 ሚሊየን ህፃናት አንድ ሶስተኛው ብቻ እንደማለት ነበር። የሞት ቁጥር ከሚወለዱት የበለጠባት ቻይና ብዙ ህዝብ የሚኖርባት የሚለውን ስያሜም በ2023 በህንድ ተነጥቃለች። በ2020 በቻይና በአጠቃላይ 5.4 ቢሊየን ኮንዶሞች ጥቅም ላይ ሲውሉ ባለፉት ተከታታይ 11 አመታትም ጭማሪ አሳይቷል። በ2022 በቻይና 9% የሚሆኑ ጥንዶች ኮንዶም ይጠቀሙ ነበር ሲባል ታክስ መጣሉ የወሊድ መከላከያዎችን ቢያስወድድም ልጅ ለማሳደግ ከሚወጣው ወጪ አንፃር ኢምንት በመሆኑ ውልደት ላይ ያን ያህል ተፅዕኖ አይፈጥርም ተብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ የታክስ ጭማሪው ሰዎችን ለተላላፊ በሽታዎች እንዳያጋልጥ ተሰግቷል። ዘገባው የዩሮ ኒውስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
🤣 40 28🤔 7👍 2
#እንድታውቁት " [በአዲስ አበባ] በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ አካላት በሙሉ፤ ከቅዳሜ ታህሳስ 4 ቀን 2018 ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት፤ መንገድ የዘጉበትን አጥር እንዲያነሱና መንገዱን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲያደርጉ በጥብቅ እያሳሰበ፤ በተጠቀሰው የጊዜ ደገብ ውስጥ አጥር የማያነሱ አካላትን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል፡፡" - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
97👍 60👎 13
照片不可用在 Telegram 中显示
📱ብድር ለመውሰድ ቀላል መንገድ ይፈልጋሉ? Digaf MFI ብለው ከፕላይ ስቶር /playstore/ በማውረድ ብድር ማመልከት ይችላሉ፡፡ በስልክዎ ብቻ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ እና የብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ! 👉 አሁን ይዉሰዱ | ቀላል | ፈጣን | ተደራሽ 📥 መተግበሪያውን አሁን ይጫኑ እና ብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.digaf.digafselfapp ለበለጠ መረጃ  ደሞ 6575 ላይ ይደውሉ! ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ
显示全部...
7
照片不可用在 Telegram 中显示
አባይ ሆምስ ስመ ጥሩ እና ገናናው አባይ ቴክ ለረጅም ዓመታት የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሌግዠሪ ዶፕሌክስ ቤቶችን በ ፍላሚንጎ ሰርቶ እንዳስረከበ ይታወቃል አሁን ደግሞ በመሃል ሜክሲኮ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቅዎችን ለሽያጭ  አውጥተናል። ለመኖሪያ አልያም አትርፈው ለመሸጥ የሚመርጡት 👉 የሳይት አድራሻ :- በመሃል ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ 👉 ቅድመ ክፍያ 10% 👉 ባለ 1 መኝታ 👉 ባለ 2 መኝታ 👉 ባለ 3 መኝታ 👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች በ10, 14, 33.6, 50.4 ካሬ ጀምሮ በተጨማሪም  እንደ አከፋፈሎ ከ 10-20 % ቅናሽ ይደረግሎታል 📍ሜክሲኮ ለበለጠ መረጃ በ 09-38-95-23-23
显示全部...
9
照片不可用在 Telegram 中显示
ኢኮዋስ ከፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮ የአየር ትራንስፖርት ታክስን ሊቀንስ ነው። የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ አባል ሃገራት በቀጣናቸው የአየር ትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ ከፈረንጆቹ ጥር 1 2026 ጀምሮ በአቪየሽን ዘርፉ ከመንገደኞች እና ደህንነት ጋር በተያያዘ የሚጣለውን ታክስ በ25% ለመቀነስ ተስማምተዋል። ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ለመጓዝ ከፍተኛ ወጪ መጠየቁ ቱሪዝምና ንግድን አዳክሟል ያለው ኢኮዋስ የታክስ ቅነሳው ትስስርን እንደሚያጠናክርና ቀጣናው ላይ ጠንካራ አየር መንገዶች እንዲኖሩ እንደሚያደርግ ገልጿል። ኢኮዋስ በሁሉም አባል ሃገራት የስምምነቱን አፈፃፀም እንደሚመለከትና እንደሚቆጣጠርም ጨምሮ ገልጿል። ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
34👍 6
照片不可用在 Telegram 中显示
ደቡብ አፍሪካ 14 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሃገሯ ሊገቡ ሲሉ በኤርፖርት መያዟን አስታውቃለች። የደቡብ አፍሪካ የድንበር አስተዳደር ባለስልጣን 5 ወንድና 9 ሴት ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ወደ "OR Tambo" አለም አቀፍ ኤርፖርት ቢደርሱም የመጡበት መንገድ አጠራጣሪ ሆኖ ስላገኘው ለተጨማሪ ምርመራ እንደያዛቸው ገልጿል። አስተዳደሩ የኢትዮጵያውያኑ ጉዞ ከሰዎች ዝውውር ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ያለ ሲሆን በተደረገ የመጀመሪያ ምርመራ ሰዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተመልሰው በህገወጥ መንገድ ከመግባታቸው በፊት ወደ ሌሎች ጎረቤት ሃገራት ለመሻገር የተደረገ ጥረት እንደሆነ ገልጿል። አስተዳደሩ በመንገደኞቹ የጉዞ መረጃ ላይ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን ስላገኘ በኤርፖርት ተለይተው ለምርመራ መወሰዳቸውን አንስቷል። የደቡብ አፍሪካ የድንበር አስተዳደር በሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ወደ ሃገሩ በተጭበረበረ ቪዛ ሊገቡ የነበሩ 16 የባንግላዴሽ ዜጎችንም ይዣለሁ ብሏል። ደቡብ አፍሪካ በእነዚህ 30 ሰዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ መጀመሯን የገለፀች ሲሆን የሰዎችን ዝውውር ለመቆጣጠር የደህንነት እርምጃዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፃለች። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
58😢 24👎 6🤣 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ደቡብ ሱዳን የሄግሊግ የነዳጅ መስመርን ለመጠበቅ ጦሯን ወደ ሱዳን መላኳን ገለፀች። ከቀናት በፊት የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋነኛ የነዳጅ መስመሩን መቆጣጠሩ መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን ደቡብ ሱዳን ይህንን ዋነኛ የነዳጅ መስመር ለመጠበቅ ጦሯን መላኳን አስታውቃለች። የደቡብ ሱዳን የመከላከያ ኃይል አዛዡ ጀነራል ፖል ናንግ የደቡብ ሱዳን ጦር በነዳጅ መስመሩ እንዲሰፍር የተደረገው ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ከሱዳን ጦር መሪው ጀነራል አልቡርሃን እና ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ጀነራል ዳጋሎ ጋር ተነጋግረው ከተስማሙ በኋላ ስለመሆኑ ገልፀዋል። ሶስቱ አካላት የነዳጅ መስመሩ ለሁለቱም ሃገራት አስፈላጊ ስለመሆኑ በማመናቸው መጠበቅ እንዳለበት ስለተስማሙ የደቡብ ሱዳን ጦር ሄግሊግ ስለመሆኑ ጀነራሉ ገልፀዋል። ከደቡብ ሱዳን የሚወጣው ነዳጅም በተሳካ መልኩ በመስመሩ ተጓጉዞ በፖርት ሱዳን በኩል ለውጪ ገበያ እየቀረበ ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ዘገባው የአልአረቢያ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
36🤔 7🤣 5👍 4🕊 1
照片不可用在 Telegram 中显示
አሜሪካ ወደ ሃገሯ ያለ ቪዛ የሚገቡ ጎብኚዎች የ5 አመት የማህበራዊ ሚዲያ ታሪካቸውን እንዲያሳዩ ለመጠየቅ ማቀዷ ተነገረ። ወደ አሜሪካ ያለ ቪዛ መግባት የሚችሉ ጎብኚዎች የማህበራዊ ሚዲያ ተግባራቸውን፣ የኢሜይል አካውንታቸውንና የቤተሰብ ታሪካቸውን ለመጠየቅ መታቀዱ ተሰምቷል። ከነዚህ ያለ ቪዛ ወደ አሜሪካ መግባት ከሚችሉ ሃገራት የሚመጡ መንገደኞች የ5 አመት የማህበራዊ ሚዲያ ታሪካቸው ሲታይ የሃገራቱ ቁጥር እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ኳታር፣ እስራኤልና ጃፓንን ጨምሮ 42 መሆኑ ተዘግቧል። በተጨማሪ ጎብኚዎቹ ባለፉት 5 አመታት የተጠቀሙትን የስልክ ቁጥርና ባለፉት 10 አመታት የተጠቀሟቸውን የኢሜይል አድራሻዎች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። ጎብኚዎቹ ከእነዚህ መረጃዎች በተጨማሪነትም እንደ አሻራ እና ዲኤንኤ ያሉ የባዮሜትሪክ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ታቅዷል። በቪዛ ወደ አሜሪካ በሚመጡ ሰዎች ላይ የማህበራዊ ሚዲያ መረጃቸውን እንዲያቀርቡ መደረግ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ያለ ቪዛ የሚገቡትን በተመለከተ የወጣው ፖሊሲ ላይ በሚቀጥሉት 2 ወራት ውስጥ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች ሃሳባቸውን እንዲሰጡም ተጠይቀዋል። ዘገባው የአልጄዚራ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
52🤣 22👎 8👏 5😢 2
照片不可用在 Telegram 中显示
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ 🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄 🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት 💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር 💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር 💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ 🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ) 💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር 💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር 💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር - በግንባታ ላይ የሚገኙ ይደውሉልን የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ! ☎️0900025097 #telegram (@SamuelMERITRealtor) https://t.me/addisapartmentforu
显示全部...
24😢 3👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(IMF) ለኢትዮጵያ የ261 ሚሊየን ዶላር ብድር ለመልቀቅ ተስማማ። የገንዘብ ተቋሙ እና የኢትዮጵያ አመራሮች የአራት አመቱን የ3.4 ቢሊየን ዶላር የተራዘመ የብድር ማዕቀፍ በተመለከተ አራተኛ ግምገማ አድርገው ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በአመራሮች ደረጃ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎም ኢትዮጵያ ከተቋሙ የ261 ሚሊየን ዶላር ብድር ይለቀቅላታል ተብሎ ይጠበቃል። በሐምሌ ወር 2016 ስምምነቱ ከተጀመረ በኋላ ጥሩ የማክሮ ኢኮኖሚክ ውጤቶች እየታዩ ነው ያለው ተቋሙ ከፈረንጆቹ 2024 አጋማሽ ጀምሮ በወርቅ፣ ኤሌክትሪክ እና ግብርና ምርቶች የታገዘ ፈጣን እድገት እየተመዘገበ ነው ብሏል። አይኤምኤፍ የዋጋ ንረት ቀንሷል፣ የመንግስት ገቢ ጨምሯል እንደዚሁም ለውጪ የሚቀርበው ምርትም አድጓል ብሏል። ጠንካራ የገንዘብ ፖሊሲ የዋጋ መረጋጋትን ለማምጣት ቁልፍ ነው ያለው የገንዘብ ተቋሙ የውጪ ምንዛሬ ገበያው ላይ ውድድርና አገልግሎትን ለማሻሻል ቀሪ ስራዎች ያስፈልጋል ብሏል። የገንዘብ ተቋሙ የ261 ሚሊየን ዶላር ብድር የሚለቀቀው የተቋሙ ቦርድ ሲያፀድቀው ሲሆን ብድሩ በቦርዱ ፀድቆ ሲለቀቅ በዚህ የብድር ማዕቀፍ ስር ለኢትዮጵያ እስካሁን የተሰጣትን ብድርም 2.134 ቢሊየን ዶላር ያደርሰዋል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
👎 173 66😢 37🤬 14🤣 10👏 5💔 5
照片不可用在 Telegram 中显示
#Update የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኬንያ እና አሜሪካ መካከል የተፈፀመውን የጤና ስምምነት አገደ። ኬንያ እና አሜሪካ ባሳለፍነው ሳምንት የ2.5 ቢሊየን ዶላር የጤና ስምምነት መፈራረማቸው ሲታወስ ሩዋንዳም ተመሳሳይ የጤና ስምምነት ፈፅማ ነበር። ፍርድ ቤቱ ስምምነቱን ያገደው የኬንያውያን የግለሰብ መረጃዎች በስምምነቱ መሰረት ተላልፈው ይሰጣሉ በሚል ነው። ስምምነቱ ሲፈፀም ከመጀመሪያውም የመረጃ ማጋራትን በተመለከተ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሙሉ ክርክር መስማት እስከሚጀምርበት የፈረንጆቹ የካቲት 12 ድረስ ውሳኔው እንዲታገድ ወስኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ተመሳሳይ የአምስት አመት የጤና ስምምነቶችን መፈፀም ቀጥላለች። ኡጋንዳ ተመሳሳይ የ2.3 ቢሊየን ዶላር ስምምነት ስትፈፅም ከዚህ ውስጥ አሜሪካ እንደ ወባ፣ ኤድስና ቲቢ ያሉ በሽታዎችን ለመዋጋት 1.7 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ታደርጋለች። በተመሳሳይ ከሌሴቶ ጋር የ364 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ሲፈፀም ከዚህ ውስጥ 232 ሚሊየን ዶላሩ በአሜሪካ ይሸፈናል። አሜሪካ አሜሪካን ቀዳሚ ያደረገ የጤያ ስትራቴጂ በትራምፕ አስተዳደር ስር ይፋ ካደረገች በኋላ የምትሰጠው የጤና ድጋፍ አሰጣጥ የተቀየረ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ መንግስታዊ ላልሆነ ተቋማት የሚሰጥ ገንዘብ እንደሌለና ቀጥታ ለመንግስት እንደሚሰጥ መግለጿ ይታወሳል። አሜሪካ ከእነዚህ የአፍሪካ ሃገራት ጋር የተፈራረመቻቸው የአምስት አመት የጤና ስምምነቶችን ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም ጋር እንደምትፈራረም መገለፀለ ይታወሳል። ዘገባዎቹ ከቢቢሲና ከስቴት ዲፓርትመንት የተገኙ ናቸው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
71👍 29👎 5👏 5🤔 3😢 3
照片不可用在 Telegram 中显示
የአውስትራሊያ የህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ እገዳ ወደ ትግበራ ገብቷል። አውስትራሊያ እድሜያቸው ከ16 አመት በታች የሆኑ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ ማዘጋጀቷ የሚታወስ ሲሆን ህጉ ወደ ስራ ገብቷል። 10 የሚሆኑት ትላልቆቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከእኩለ ለሊት ጀምሮ ህፃናትን እንዲያግዱ የታዘዙ ሲሆን ይህንን ካላደረጉ እያንዳንዳቸው 33 ሚሊየን ዶላር ይቀጣሉ። የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለህፃናት ባስተላለፉት መልዕክት " ስልካችሁን "Scroll" ከምታደርጉ አዲስ ስፖርት ጀምሩ፣ አዲስ የሙዚቃ መሳሪያ ተማሪ ወይም በሼልፋችሁ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ተቀምጦ የነበረን መፅሐፍ አንብቡ፤ ከምንም በላይ ደግሞ ከጓደኞቻችሁና ቤተሰቦቻችሁ ጋር የጋራ ጊዜ አሳልፉ" ብለዋል። እድሜን ማዕከል ያደረገ እገዳ በአለማችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገበረችው አውስትራሊያ ለአሁኑ እገዳው በ10 መተግበሪያዎች ላይ እንደሆነ አስታውቃለች። የአውስትራሊያ ትግበራ ተመሳሳይ እገዳን መከተል ለሚፈልጉ ሃገራት ትምህርት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። መረጃው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
84👏 38👎 1🤝 1
照片不可用在 Telegram 中显示
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!! 🌟አያት ግራንድ ሞል ✨ 3000 የንግድ ሱቆች ✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ ✨ከ 24 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው ✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል 🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ 🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ  በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!! 💥ለበለጠ መረጃ በ 251944856735 በቀጥታ @tegegne123 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
显示全部...
8🤣 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ዲሞክራቲክ ኮንጎ በ25 አመት ውስጥ መጥፎ የተባለውን የኮሌራ ወረርሽኝ እያስተናገደች ትገኛለች። 2025 ከገባ ወዲህ በዲሞክራቲክ ኮንጎ 64,427 ሰዎች በኮሌራ ሲያዙ 1,888 ሞቶች ተመዝግበዋል። ከተያዙት መካከል 14,818 ያህሉ ህፃናት ሲሆኑ ከሚመዘገበው 4 ሞት መካከልም አንዱ የህፃን ልጅ ሞት ነው። ዩኒሴፍ ይህ የኮሌራ ወረርሽኝ በሃገሪቱ ከ25 አመታት በኋላ የተከሰተ መጥፎው ወረርሽኝ ነው ብሎታል። ኮንጎ ካሏት 26 ግዛቶች በ17ቱ ወረርሽኙ መከሰቱ ሲነገር ዩኒሴፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቋል። በአፍሪካ ዝቅተኛው ምጣኔ በሆነውና 43 በመቶ ህዝቧ ብቻ መሰረታዊ የሚባል የውሃ አገልግሎት የሚያገኝባት ኮንጎ በሃገሯ ያለው ግጭት የበሽታውን ስርጭት ጨምሯል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
19😢 15👍 1🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በመንግስታዊ ስልኮች ላይ ቲክቶክ ቢታገድም የቲክቶክ አካውንት ከፍተዋል። በ2023 የወቅቱ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሪሺ ሱናክ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ቲክቶክ በመንግስታዊ ስልኮች ላይ እንዳይሰራ አግደው ነበር። ቲክቶክ አሁንም በመንግስት ስልኮች ላይ ታግዶ ይቀጥላል ሲባል የጠቅላይ ሚኒስቴሩ አካውንት እንዲሰራ የደህንነት መከላከያዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ተብሏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃለ አቀባይ የቲክቶክ አካውንቱ መከፈት ሰፊ ህዝብ ለመድረስ ያስችላል ብለዋል። ቲክቶክ በተደጋጋሚ በተለያዩ ምክንያቶች የደህንነት ጥያቄ የሚነሳበት ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ ታግዶ እንደነበርና አሁንም ብዙ ክርክሮች በደህንነቱ ዙሪያ እንደሚነሱ ይታወቃል። ዘገባው የዘ ኢንዲፔንደንት ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
🤣 35 15