ch
Feedback
የስብዕና ልህቀት

የስብዕና ልህቀት

前往频道在 Telegram
68 961
订阅者
无数据24 小时
-137
-96730

数据加载中...

标签云
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服
进出提及
---
---
---
---
---
---
吸引订阅者
十二月 '25
十二月 '250
在0个频道中
十一月 '25
+4
在0个频道中
Get PRO
十月 '250
在0个频道中
Get PRO
九月 '250
在0个频道中
Get PRO
八月 '250
在0个频道中
Get PRO
七月 '250
在0个频道中
Get PRO
六月 '250
在0个频道中
Get PRO
五月 '250
在0个频道中
Get PRO
四月 '250
在0个频道中
Get PRO
三月 '250
在0个频道中
Get PRO
二月 '250
在0个频道中
Get PRO
一月 '25
+7
在0个频道中
Get PRO
十二月 '24
+904
在1个频道中
Get PRO
十一月 '24
+87
在1个频道中
Get PRO
十月 '24
+183
在1个频道中
Get PRO
九月 '240
在0个频道中
Get PRO
八月 '240
在0个频道中
Get PRO
七月 '240
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+1
在0个频道中
Get PRO
五月 '240
在0个频道中
Get PRO
四月 '240
在0个频道中
Get PRO
三月 '24
+8
在0个频道中
Get PRO
二月 '24
+3
在0个频道中
Get PRO
一月 '240
在0个频道中
Get PRO
十二月 '230
在0个频道中
Get PRO
十一月 '230
在0个频道中
Get PRO
十月 '230
在0个频道中
Get PRO
九月 '230
在0个频道中
Get PRO
八月 '230
在0个频道中
Get PRO
七月 '230
在0个频道中
Get PRO
六月 '230
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+24
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+1
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+10
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+5
在0个频道中
Get PRO
一月 '230
在0个频道中
Get PRO
十二月 '220
在0个频道中
Get PRO
十一月 '220
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+2
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+4
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+1
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+3
在0个频道中
Get PRO
六月 '220
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+209 344
在0个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
15 十二月0
14 十二月0
13 十二月0
12 十二月0
11 十二月0
10 十二月0
09 十二月0
08 十二月0
07 十二月0
06 十二月0
05 十二月0
04 十二月0
03 十二月0
02 十二月0
01 十二月0
频道帖子
ምልከታ‼️ #እየሸለምን ያለነው ሀገር ገንቢዎችን ወይስ ጊዜ❗❗ ገዳዮችን? 👉??«#TikTok_Creative_Award» ከሰሞኑ የተከናወነው የ«TikTok Creative Award» ደማቅ አልባሳት ቅንጦት ና አፍራሽ ተግባራት የታዩበት ሊያሳየን ያልቻለው አንድ አስፈሪ እውነት የሀገራችንን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን ነው። ጥያቄው፡- እየሸለምን ያለነው ሀገር ገንቢዎችን ወይስ ጊዜ ገዳዮችን? የሚለው ነው።ከበለፀጉት ሀገራት ተሞክሮ አንፃር ሲታይ፣ የዘንድሮው ሽልማት ለወጣቱ ያስተላለፈው መልእክት እጅግ አደገኛ ነው። Has to be banned!! ለምን? 1. የቻይናን ጥበብ ወይስ የቻይናን ቆሻሻ? (The Double Standard) የቲክቶክ ባለቤት የሆነችው ቻይና፣ ዓለምን በቴክኖሎጂ የተቆጣጠረችው በመጨፈር አይደለም። ቻይና ለገዛ ወጣቶቿ የምትፈቅደው የቲክቶክ ቅጂ (Douyin)፣ ከ14 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚያሳየው የሳይንስ ሙከራዎችን፣ የሮቦቲክስ ፈጠራዎችን እና የአገር ፍቅር ታሪኮችን ብቻ ነው። ለምን? ምክንያቱም «ነገን የሚረከበው ትውልድ ጭንቅላት በዕውቀት እንጂ መደንዘዝ የለበትም» ብለው ስለሚያምኑ ወደኛ ሲመጣ ግን ነገሩ ተገላቢጦሽ ነው። ሽልማታችን የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የመፅሀፍ እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ወደ ዳር ገፍቶ «ቀልድን» የጀግንነት ማማ ላይ ሰቀለ። ቻይና ለልጆቿ የዕውቀት ወተት ስትግት፣ እኛ ለልጆቻችን በመዝናኛ የተለወሰ መርዝ እየሰጠን ይሆን? ይህንን ቆም ብለን ልንጠይቅ ልንመረምር ይገባል። 2. «Creative» (ፈጠራ) ወይስ «Viral» (ማነጋገሪያ)? ቃላትን በትክክል እንጠቀም። «ፈጠራ» (Creativity) ማለት የህዝብን ችግር የሚፈታ፣ አዲስ እሴት የሚጨምር እና ትውልድን የሚያሻግር ስራ ነው። ስልክን አገላብጦ በመቅረጽ በሺዎች የሚቆጠሩ «ላይክ» ማግኘት ታዋቂነት (Popularity) እንጂ ፈጠራ (Creativity) ሊሆን አይችልም። ባደጉት ሀገራት ሽልማት የሚሰጠው ለይዘት ጥራት እና ለሚያመጣው ለውጥ ነው። እኛ ጋር ግን መስፈርቱ  የቁጥር ጨዋታ ሆነ። ሳይንስን፣ ህክምናን እና ትምህርትን የሚያስተላልፉ ቻናሎች እንደ ሁለተኛ  ሲታዩ፣ ቀላል መዝናኛዎች የክብር ዙፋን ላይ ተቀምጠዋል። እውቀት በ «ላይክ» ብዛት አይለካም፤ እውነትም በ «ሼር» ብዛት አይረጋገጥም። 3. ለወጣቱ የተላለፈው አደገኛ መልእክት (The Wrong Role Models) አንድ ወጣት ይህንን ሽልማት ሲመለከት አእምሮው ውስጥ የሚቀረፀው ምንድን ነው? • "ለካ ክብር ለማግኘት ተምሮ ዲግሪ መያዝ፣ ሌሊት ተቀን ለሀገር የሚጠቅም ምርምር ማድረግ ወይም መፅሀፍ መጻፍ አይጠበቅብኝም።" • "ለካ አቋራጭ መንገድ አለ! ስልኬ ላይ ብጨፍር፣ በቅጽበት 'የዓመቱ ምርጥ' ተብዬ እሸለማለሁ።" ይህ አስተሳሰብ የስራ ባህልን (Work ethic) የሚገድል መርዝ ነው። አሜሪካን፣ ጃፓንን እና ጀርመንን የገነቡት ፊታቸው በላብ የረጠበ ኢንጂነሮች ሐኪሞች ሙህራኖች ና ገበሬዎች እንጂ፣ ካሜራ ፊት የሚሽሞነሞኑ አይደሉም። ወጣቱን ትምህርት እና የሥራ ጎዳና አውጥተን፣ ወደ አቋራጭ መንገድ እየገፋነው ነዉ አገርንም ጭምር! 4. የባህል ወረራ በሽልማት ስም ሽልማቱ ላይ የታየው የአለባበስ እና የቅንጦት ትርኢት፣ የኢትዮጵያን ወጣት ማንነት የሚወክል ነበር? ወይስ የሆሊውድን "Red Carpet" ለመኮረጅ ?  Via:- Dr BEREKET EMMANUEL MD, Author Founder influential youth Ethiopia CEO ==========≠============ @enlighten_ethiopia

3 333190

2
ሃይማኖቶችን እከሳለሁ ፥ የሃይማኖት አባቶችን እወቀሳለሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከአንድ መከራ ወደ ሌላ መከራ እንዲሸጋገር የተፈረደበት ይመስላል። በየእለቱ የማያቋርጥ ሰቆቃን ይጋፈጣል። አንድ አንቅፋት ደጋግሞ ይመታዋል። ባለፉት ጥቂት አመታት በአራቱም አቅጣጫ እሳት እየዘነበ ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ እየተደረገ ያለው ጦርነት ንፁሃንን እየቀጠፈ ቢሆንም ማንም ትኩረት አልሰጠውም። የአማራ ክልሉ ጦርነት እስካሁን መፍትሔ አላገኘም። ትግራይ ከጦርነት ሳታገግም ሌላ ጦርነት እየተደገሰ ነው። በቤንሻንጉል ፥ በጋምቤላ ፥ በሶማሌ ፥ በአፋር... ስላለው ችግር ፍፁም እየተነጋገርን አይደለም። የሃይማኖት አባቶችን መውቀስ እፈልጋለሁ። ሃይማኖትችን እከሳለሁ። ሃይማኖት ተቋማትና መሪዎቹን "በሀገር መከራ እጃችሁ አለበት" ብዬ እከሳለሁ። ይህ ማጋነን አይደለም። በጦርነት ቀጠና አስገድዶ መደፈር መደበኛ ነገር መስሏል። አስገድዶ መድፈር እንደ ጦር መሳሪያ እያገለገለ ነው። የሴቶች ገላ ጦር ሜዳ ሆኗል። ደናግላን በግዳጅ ተነውረዋል። ሚስቶች ከባሎቻቸው ውጭ ወደ ሴትነታቸው ወንድ ገብቷል። ባል ሚስቱን ከፆታዊ ጥቃት ማዳን አልቻለም። አባት ልጁን ከመደፈር አላዳነም። ወንድም እህቱ እንዳትደፈር ከለላ መስጠት አልቻለም። ይህ ለወንድ ታላቅ ውድቀት ነው። በዚህ ሁሉ መሃል የሃይማኖት አባቶችን መውቀስ እፈልጋለሁ። የሃይማኖት ተቋማትን እከሳለሁ። መሐል አገሩ ችግር እየተፈራረቀበት ነው። ፍርድ ይጓደላል ፥ ድሃ ይበደላል። ሙስና ሕጋዊ የሆነ መስሏል። ሰው ሰርቶ መኖር አልቻለም። ቀድሞ ደህና ኑሮ ይኖር የነበረ ዛሬ ወደ ድህነት አረንቋ ተወርውሯል። ኑሮ ተወዷል ተብሎ ብቻ ብሎ መግለፅ ነገሩን ማሳነስ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ማህበራዊ ሃላፊነት የለባቸውም? የሃይማኖት ሰዎች ስለዜጎች አያገባቸውም? ስለፍትህ ግድ የሚሰጠው ማን ነው? የእምነት ተቋማት ለነገ እዳ እያከማቹ ነው። ከማንም ቀድመው ኢ-ፍትሃዊነትን ማውገዝ ግዴታቸው ነበር። ድሃ ሲበደል ፥ ፍርድ ሲጓደል "ይህ ነገር አግባብ አይደለም" የማለት ግዴታ ነበረባቸው። ዜጎች በማንነታቸው ሲጠቁ "ሕግ ይከበር ፥ ይህ ነውር ይቁም" ማለት ግዴታቸው ነበር። ጉልበተኛ ደካማውን ሲጎዳ ዝም ማለት አልነበረባቸውም። ለድምጽ አልባው ድምጽ መሆን ነበረባቸው። ዝም ብለዋል። መናገር የነበረባቸው ዝም ብለዋል። ቀሳውስት ዝም ብለዋል። ፓስተሮች ዝም ብለዋል። ኡስታዞች ዝም ብለዋል። የሃይማኖት አባቶች ዝምታን መርጠዋል። አገር እየተናጋ እነርሱ በዝምታ አድፍጠዋል። ምናልባት ይፈሩ ይሆናል። "ብንናገር እናልቃለን" የሚል ስጋት ይኖርባቸው ይሆናል። ነገር ግን ፈርተው ዝም ያሉቱ ግብዞች መሆናቸውን አሳይተውናል። ለእውነት ሲሉ ዋጋ መክፈል ለእምነት አባት ክብሩ ነው። ከእውነትጋ ተባብሮ ፥ ለፍትህ ድምፅ ሆኖ መከራን መቀበል ለሃይማኖት አባት ጌጡ ነው። የእምነት ተቋማት ፥ የሃይማኖት አባቶች ለደካማው ድምጽ መሆንን ካልወደዱ ስለ ፍትህ የመናገር ሞራል ይኖራቸዋል? ለእውነት ሲሉ ዋጋ ሳይከፍሉ ስለ እውነተኝነት መስበክ ይቻላቸዋል? አምላክ ፍትሃዊ ነው። ፍትሃዊ አምላክን ካመለካችሁ ለደካማው ድምጽ ሁኑ! ይህ እስኪሆን ድረስ የሃይማኖት ተቋማትን እወቅሳለሁ ፥ የሃይማኖት አባቶችን እከሳለሁ። "በዝምታችሁ ኢ-ፍትሃዊነትን ተባብራችኋል ፥ ባለመናገር በደልን አግዛችኋል" ብዬ እከሳቸዋለሁ! Via ተስፋኣብ ተሾመ @Tfanos
4 737
3
..የቀጠለ በዚህ ጊዜ ሽማግሌው በዝግታ ተናገረ፡- ‹‹ለበርካታ ዓመታት በባሃማስ እኖር ነበር።›› ዶ/ር ማይልስ ይህን ጊዜ ፈገግ ብሎ ጥያቄውን አዥጎደጎደ፡- ‹‹እውነትዎን ነው? መቼ ነበር? የትኛው ከተማ?›› ‹‹በዋናው ከተማ ናሳዉ ነበር›› አለ፡ ‹‹በዚያ ሥራዎ ምን ነበር?›› ሌላ ጥያቄ ዶ/ር ማይልስ ወረወረ። ‹‹አስተማሪ ነበርኩ!›› አለ፡ ‹‹ምን ተብሎ የሚጠራው ትምህርት ቤት?›› የዶ/ር ማይልስ የማወቅ ፍላጎት በረታ። ሽማግሌው የትምህርት ቤቱን ስም ጠራለት። ‹‹እንዴ! ጌታዬ እኔም እኮ እዚያ ነበር የተማርኩት›› አለ ዶ/ር ማይልስ። ‹‹አዎ! ምናልባት አንተ አታስታውስኝ እንደሆነ እንጂ እዚያ አስተማሪ ነበርኩ›› አለው። ‹‹ይቅርታ ያድርጉልኝ! በፍፁም ላስታውስዎት አልቻልኩም›› አለ ዶ/ር ማይልስ ወንበሩ ላይ እየተቁነጠነጠ። ‹‹እኔ ሚስተር ሮቢንሰን ነኝ›› አለው፡፡ ዶ/ር ማይልስ ደስታና ድንጋጤ በተቀላቀለ መንፈስ ጮኸ፡- ‹‹ሚስተር ሮቢንሰን!!›› ከዓመታት በፊት የዝንጀሮ ዘር፣ ባርያ፣ ግማሽ ሰው፣ ዘገምተኛና ደደብ በማለት ሲጠራው የኖረው ይህ አስተማሪው እንደነበር በድንገት ትዝ አለው፡፡ ዶ/ር ማይልስ በዚህ ጊዜ ከወንበሩ ተስፈንጥሮ በመነሳት ወደሽማግሌው ተንደረደረ፣ አጠገቡ ደርሶም በሁለት እጆቹ አቅፎ ናፍቆቱን ገለፀለት፡፡ ሽማግሌው ቲቸር ሮቢንሰን ግን በዶ/ር ማይልስ ትከሻ ላይ ጭንቅላቱን አስደግፎ ማልቀስ ጀመረ። በሥፍራው የነበረ ሁሉ እነዚህ ጥቁርና ነጭ ሰዎች በናፍቆት ጉንጭ ለጉንጭ እየተሳሳሙ ተቃቅፈው ሲላቀሱ እንደድራማ እነሱን እየተመለከተ ፈዘዘ። ሽማግሌው ሮቢንሰን፡- ‹‹አዝናለሁ! አዝናለሁ! አዝናለሁ!›› እያለ ደጋግሞ ይቅርታ መጠየቁን ይዞታል። ዶክተር ማይልስ አሁን መሳቅ ጀመረ፡- ‹‹እውነት እንደው ሚስተር ሮቢንሰን በዝንጀሮ፣ የፍጡር ሂደቱን ባልጨረሰ ግማሽ ሰው፣ ደደብ፣ ጠቋራ ባርያ የተፃፈ መጽሐፍ አነበብኩ እያሉኝ ነው? ዝንጀሮ ሕይወቴን ለወጠው እያሉኝ እኮ ነው!?›› ከዚያ በኋላ ሁለቱም ተያይዘው ለረዥም ሰዓት መሳቅ ጀመሩ፡፡ ‹‹ውድ አስተማሪዬ !! ማንኛውንም የሰው ልጅ በድጋሚ ዝቅ አድርገው እንዳይመለከቱ! ፈጣሪ በውስጡ ያስቀመጠው ምን እንደሆነ አያውቁትምና!›› ሲል ዶ/ር ማይልስ የሰንብት ምክር ጣል አደረገ፡፡ ዶ/ር ማይልስ ዝንጀሮ ተብሎ በተሰደበበት በዚያ ትምህርት ቤት ውስጥ ዛሬ አንዱ ማስተማሪያ የእሱ መጽሐፍ ሆኗል፡፡ ወድ አንባቢዬ! ዛሬ በሕይወት ውስጥ የምትገኝበትን ሥፍራ ምን ወይም የት እንደሆነ ማወቅ አልችልም፣ ነገር ግን አንድ እውነት ቢኖር ሰዎች የፈለጉትን ዓይነት በርካታ ስም እየለጠፉብህ ሊጠሩህ ይችላሉ፣ ነገር ግን አንተ ለራስህ ከሰጠኸው አንድ ስም ጋር ፈፅሞ ሊወዳደር እንደማይችል እመን!! የስብዕና ልህቀት @enlighten_ethiopia
7 859
4
"በፍፁም በራስህ ላይ ተስፋ አትቁረጥ" ማይልስ ሞንሮ የአስራ አራት ዓመት ልጅ እያለ በተወለደባት ባሃማስ ደሴት አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ሆኗል። ታዲያ ነጩ ስኮትላንዳዊ አስተማሪ ሚስተር ሮቢንስን በዚያ ትምህርት ቤት የሚማሩ ጥቁሮችን ዘውትር ያላግጥባቸዋል፣ ያንቋሽሻቸዋል፡፡ ‹‹ምንም የማይገባቸው ደደቦች ፣የድንጋይ ራሶች፣ እንስሶች...›› የጥቁሮችን ማንነት የሚገልጥበት የየዕለትት ቋንቋው አድርጎታል። አንድ ቀን የስድቡ ተራ ለማይልስ ደረስ፡- " አንተ ከእንስሳ የተዳቀልክ ግማሽ ዝንጀሮ፣ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂ፣ ጠቋራ ባሪያ፣ በመጥረቢያ ጭንቅላትህን ከፍቼ መጽሐፍትን ብጨምርብህ እንኳን ትምህርቱ አይገባህም› ይኽን የመምህራኑን ውርጅብኝ ያስተናገደው ማይልስ እግረመንገድ የእስከዛሬ የትምህርት ውጤቱን መለስ ብሎ ቢያስበው እውነትም እንደአስተማሪው ነቀፋና ማላገጥ ‹‹F›› ብቻ ሆነበት፡፡ ‹‹በቃ ሚስተር ሮቢንስን እውነቱን ነው፤ ትምህርት ለእኔ አይገባም›› ሲል ከውሳኔ ደርሶ ወደቤቱ አመራ፡፡ ከቤቱ ሲደርስ የሆነበትን ሁሉ ለእናቱ  እያለቀሰ ተርኮ ሲያበቃ ከእንግዲህ ትምህርት ቤት የመመለስ ፍላጎት እንደሌለው ጨምሮ ነገራት፡፡ እናቱ ግን ጠቢብ ሆነች፡፡ እንደሚስተር ሮቢንሰን ስለልጇ ከአንደበቷ ከፉ ቃል አልወጣም ወይም ማይልስ ለራሱ በሰጠው ግምትም አልተቆጣችውም። በዝምታ ወደመኝታ ቤቷ አመራች፤ አፍታም ሳትቆይ ደግሞ በእጇ አንድ መጽሐፍ ጨብጣ ተመለሰች፡፡ ‹‹ማይልስ! እንካ ይሄንን ተቀምጠህ በዕኖና አንብበው›› ፈገግ ብላ ከእጆቹ አኖረችለትና ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ይባላል›› ስትል ደግሞ አስተዋወቀችው፡፡ ማይልስ ከእጆቹ ላይ የተቀመጠውን መጽሐፍ ሽፋኑን አገላብጦ በሚገባ ካጠናው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ውስጡን : ገለጠው፡፡ ዐይኑ ያረፈበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዲህ የሚል ሆኖ አገኘው፡- "እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው መጠን ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው...›› (ኤፌ 3፡20)፡፡ በነጋታው ይህን አጋጣሚ በሚመስል ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሀፍ ቅዱስ ሲገልጥ ያነበበውን ጥቅስ እያሰላሰለ ወደ ትምህርት ቤቱ ማልዶ ገሰገሰ፡፡ ከሦስት ወር በኋላ የፈተና ውጤት ሲነገር በሁሉም ‹‹B›› ማግኘቱ ተነገረው፡፡ ቀጣዩ ሴሜስተር ደርሶ የፈተና ውጤት ተለጠፈ፡፡ ማይልስ በሁሉም ፈተናዎች ‹‹A›› አግኝቷል። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት በነበረው የትምህርት ቤት ቆይታው ከክፍሉ ብቻ ሳይሆን ከትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ሁሉ ልቆ አንደኛ በመውጣት ጨረሰ፡፡ የተማሪዎች ምረቃ ቀን ማይልስ ወደ መድረክ ተጠርቶ የክፍተኛ ማዕረግ ተመራቂነትን ክብር ተቀዳጀ፤ ሽልማትም ተሰጠው። ፈረንጅ ተማሪዎች ሳይቀሩ ከመድረኩ ሥር ተቀምጠው ለማይልስ ያጨበጭባሉ። ማይልስ ሽልማቱን ተቀብሎ በቀጥታ ያመራው ወደ ሚስተር ሮቢንሰን ነበር፡፡ ‹‹እነሆ ውድ መምህሬ! እኔ ግማሽ ዝንጀሮ የሆንኩት ዛሬ ይሄን ሽልማት ለመታሰቢያ ያህል ለአንተ አበረከትሁልህ..›› ፈገግ ብሎ ከእጆቹ አኖረለት ይህ ከተፈፀመ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ማይልስ ወደ ኮሌጅ አምርቶ በአራት ዓመታት ውስጥ ሦስት ባችለር ዲግሪዎችን ተቀበለ፡፡ ከዚያ ቀጠለና በዓመት ከስድስት ወሩ የማስተርስ ዲግሪውን በክብር አገኘ፡፡ ከዚያ በኋላ በመጡት በርካታ ዓመታት ያ የዝንጀሮ ዘር፣ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂ እንዲሁም ደደብ የተባለው ማይልስ አምስት ዶክትሬት ዲግሪዎችን ከአምስት የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለመቀበል በቃ። እንዲሁ ለቁጥር የሚታክቱ ድንቅ መጻሕፍትንም ደርሶ ለዓለም አበረከተ፡፡ አንድ ቀን በለንደን በመሪነት ጥበብ ርዕስ ዙሪያ በተዘጋጀ ሴሚናር ላይ ማይልስ ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ ተገኝቷል። ንግግር አድርጎ ጨርሶ ከሆቴሉ የእንግዳ መቀበያ በተዘጋጀለት ሥፍራ ላይ መጽሐፉን ገዝተው ፊርማውን ከፊት ለፊቱ ተሰልፈው ለሚጠብቁት አንባቢዎቹ ለመፈረም ተቀመጠ፡፡ የሰልፉ ርዝመት መቼም አይነገርም። እየፈረመ፣ እየፈረመ ቆይቶ አንድ በምርኩዝ ድጋፍ የሚጓዝ ሽማግሌ ፈረንጅ ተራው ደረሰና ከፊቱ ቆመ። በመነበብ ብዛት እጅግ ያረጁ፣ ስርዝ ድልዝ በገጾቻቸው የሞላባቸው ሁለት መፅህፍትን ይዟል። ሰውዬው አረማመዱ መጃጀቱን ያሳብቅበታል፡፡ ዶ/ር ማይልስ የመፃህፍቶቹን ማርጀትና በስርዝ ድልዝ መሞላት ተመልክቶ ወደ ፈረንጁ በፈገግታ ቀና አለ፡- ‹‹ጌታዬ! መጽሐፎቼን እንዲህ ሆነው ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ የገዛቸው ሰውዬ በሚገባ አንብቧቸዋል ማለት እኮ ነው! በጣም አድርጌ አመሰግንዎታለሁ!›› ሽማግሌው ሰውዬም፡- ‹‹እነዚህ መጻሕፍት ሕይወቴን እስከወዲያኛው ለውጠውታል›› አሉት። የማይልስ ደስታ አይነገርም፡- "በጣም አመሰግንዎታለሁ! አሁን የተናገሩት ለእኔ ምን ማለት እንደሆነና ሊፈጥርብኝ የቻለውን ስሜት - የሚረዳው ደራሲ የሆነ ብቻ ነው›› ሲል በአክብሮት ምስጋናውን አስቀድሞ ፊርማውን አኑሮ መፃህፍቱን መለሰ፡፡ ሽማግሌው ሰውዬ ግን መፃህፍቱን ተቀብሎ አልሄደም፤ እዚያው እንደቆመ ቀረ። ዶ/ር ማይልስ ከፊቱ ተገትሮ በቀረው ሰው ግራ ተጋብቶ ‹‹ጌታዬ! ከኋላህ ብዙ ሰው ተሰልፎ ፊርማዬን እየጠበቀ ነው፡፡ እባክህ ሥፍራውን ልትለቅላቸው ትችላለህ።" አለው፡፡ ሽማግሌው የሰማው አይመስልም፡፡ አትኩሮቱን ሁሉ ዶ/ር ማይልስ ላይ ጥሎ በአንክሮ ይመለከተዋል። ‹‹ጌታዬ! ወደዚህ ሥፍራ አክብረኽኝ ስለመጣህ፣ እንዲሁም መፃህፍቴን ስለምታነብ አክብሮቴ የላቀ ነው፡፡ ነገር ግን እባክህ ብዙ ሰው ከኋላህ ቆሟል...›› ሲል በድጋሚ ጠየቀው። ሽማግሌው ግን አሁንም በዝምታ ተውጦ እንዳፈጠጠበት ቀረ። በሁኔታው የተጨነቀው ዶ/ር ማይልስ፡- ‹‹ጌታዬ! ችግር ይኖር ይሆን እንዴ? ወይም ልትነግረኝ የፈለግኸው ነገር አለ?›› አለው፡፡ ይቀጥላል ...
6 446
5
የቲክቶክ አዋርድ ፥ እንደ ፖለቲካ ማሳያ * * * በቲክቶክ አዋርድ በኩል ብናጮልቅ የፖለቲካ ንቃተ ህሊናችንን እንመለከታለን። ለቲክቶክ አዋርድ ፥ድምፅ የሚሰጡ ሰዎች ድምፅ የሚሰጡት አቅምን ታሳቢ አድርገው አይደለም። ዋነኛ መስፈርታቸው ቡድንተኝነት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ህዝበኝነት ነው። አንዳንዶች የሃይማኖት ካርድ መዘዋል። የእምነታቸው ተከታይ እንዲያሸንፍ ጠብ እርግፍ ይላሉ። ነገርዬውን ሃይማኖታዊ ተጋድሎ አድርገውታል። ሌሎች የብሔር ካርድን መዘዋል። ለፌደሬሽን ምክር ቤት ተወካይ የሚያቀርቡ ይመስል ተፍ ተፍ እያሉ ነው። እግር ኳስም ጭምር ከውግንና ፖለቲካው አላመለጠም። እግር ኳስ ከውግንና ፖለቲካ የሚለይ መዝናኛ ነው። ነገር ግን የዘንድሮ የቲክቶክ አዋርድ ይህን መርህ ጥሷል። ጥሩ የስፖርት መረጃ አቅራቢ ማነው? ቲክቶክ ላይ ጥሩ የስፖርት መረጃ የሚያቀርቡ ብዙ ሰዎች አሉ። ማሸነፍ ይገባቸዋል። ነገር ግን መራጮች መስፈርታቸው ቡድንተኝነት ነው! "የአርሰናል ደጋፊዎች እገሌን ምረጡ፥ የዩናይትድ ደጋፊዎች ለእንቶኔ ድምፅ ስጡ" ይባላል። መስፈርቱ የቡድን ውግንና ሆኗል። ሌላው የመራጮች ድምፅ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው ፖፑሊስትነት ነው። ጥሩ ይዘት ፈጠራን ከበጎ አድራጎትጋ ይደበላልቁታል። ጥሩ ይዘት የሌለው ግን የደግነት ምልክት ያሳየ ሰው "ባለ ጥሩ ፈጠራ" ተብሎ ድምፅ ይሰጠዋል። እንዴት የሚል ጥያቄ ሲነሳ "ደግ ሰው ነው" ይባላል። ስለ ደግነት መች ተጠየቀ? የቲክቶክ አዋርድ የፖለቲካ ንቃተ ህሊናችንን ይናገራል። ለማህበራዊ ሚዲያ ሽልማት የቡድን ውግንናን ቅድሚያ የሰጠ ሰው የፖለቲካ ምርጫን እንዴት ይመለከተዋል? ለቲክቶክ አዋርድ ከብቃት ይልቅ ሀይማኖት ፥ ብሔር እና የእግርኳስ ቡድን ድጋፍ ዋነኛ መመዘኛ ያደረገ ሰው ፖለቲካን በብቃት ይመዝናል? በፍፁም! ለቲክቶክ አዋርድ ከብቃት ይልቅ በጎ አድራጎትን መስፈርት ያደረገ ሰው ለፖለቲካ ምርጫ መስፈርቱ ምን ይሆናል? እንዲህ አይነት መራጭ ፥ ብቁ ያልሆነ ነገር ግን የደግነትን ጭንብል ያጠለቀ ጮ ሌ አያታልለውም? ዴሞክራሲ ለብዙሃን ድምፅ ዋጋ ይሰጣል። እንደ አቅሚቲ "ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይደረግ" የሚል ጥያቄ አለን። ደግሞም ከፊታችን ምርጫ ይደረጋል። ምርጫው ላይ መንግስት ፍትሃዊ ምርጫ ላያደርግ ይችላል የሚል ጉልህ ስጋት አለ። ስጋቱን እንርሳውና ፍትሃዊ ምርጫ ቢደረግስ? በእርግጥ ፍትሃዊ ምርጫ ቢደረግ ጠቃሚ አካል እንመርጣለን? የምርጫችን መስፈርት ምንድነው? ከብቃት ይልቅ ግለሰባዊ ቸርነት እና ቡድናዊ ውግንናን ቅድሚያ የሚሰጥ ማህበረሰብ ፥ በራሱ ላይ አ ው ሬ ን ይሾማል! Via ተስፋኣብ ተሾመ @Tfanos
9 537