ch
Feedback
YeneTube

YeneTube

前往频道在 Telegram

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

显示更多
108 065
订阅者
-12324 小时
-5057
-2 11030
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
አይ ኤም ኤፍ እና ኢትዮጵያ በባለሙያዎች ደረጃ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ላይ ደረሱ፣ ይህም ኢትዮጵያ 261 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንድታገኝ ያስችላታል ተብሏል! ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አራተኛው ዙር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታወቀ። ስምምነቱ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አመራርና የቦርድ አስፈጻሚ አካል የመጨረሻውን ይሁንታ ካገኘ በኋላ ወደ 261 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንዲለቀቅ ያስችላል ተብሏል። አይ.ኤም.ኤፍ ይህን ያስታወቀው ትናንት ታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው። ስምምነቱ የተደረሰው ከጥቅምት 20 - ህዳር 4/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የተካሄዱትን ውይይቶች ተከትሎ ሲሆን፣ ከህዳር 24- 26/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በበይነ-መረብና በአካል በተደረጉ ተጨማሪ ስብሰባዎች ተጠናቋል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እንዳስታወቀው፣ ስምምነቱ ቀደም ሲል በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የጸደቀው እና 3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አካል ነው። ቀጣዩ ዙር ብድር ሲለቀቅ፣ ተቋሙ ከአጠቃላይ ብድሩ ውስጥ እስካሁን ለአገሪቱ የለቀቀው የገንዘብ መጠን 2.134 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል። የአይ.ኤም.ኤፍ ልዑክ መሪ የሆኑት አልቫሮ ፒሪስ፣ በቅርቡ የወጡ መረጃዎች “ከ2024 አጋማሽ ወዲህ የተፋጠነ ዕድገት” መኖሩን እንደሚያሳዩ ገልጸዋል። Via AS @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
👎 33 21👍 3😭 2
የታጠቁ አካላት የሰላም መንገድን እንዲመርጡ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ። የአማራ ክልል ሕዝብ ከዚህ በላይ ጦርነት እያደረሰ ያለውን ችግር መሸከም ስለማይችል አሁንም ድረስ የታጠቁ አካላት የሰላም መንገድን እንዲመርጡ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቅርበዋል። በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ የአፋሕድ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሰጥተዋል። የአማራ ሕዝብን ጥያቄ እናስመልሳለን ብለን ወደ ጫካ ብንገባም ትግላችን የአማራ ሕዝብ ጠል በሆኑ እና ኢትዮጵያ እንድትፈርስ በሚፈልጉ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጠላቶች እጅ መውደቁ ድርጅቱ ወደ ሰላም ስምምነቱ መምጣቱን አመራሮቹ ገልጸዋል። አፋሕድ ወደ ትጥቅ ትግል ከገባበት ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የአማራ ክልል ሕዝብ በሰላም መንቀሳቀስ የማይችልበት ደረጃ መድረሱን እና ከትምህርት፣ ከጤና እና ሌሎችም አገልግሎቶች ውጭ ሆኖ ከፍተኛ ችግር ማስተናገዱንም የአፋሕድ ምክትል የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ እና የወሎ ቤተ አማራ ጠቅላይ ግዛት እዝ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ኢያሱ አበራ ተናግሯል። የትኛውም ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንጂ በጦርነት የሚፈታ ባለመሆኑ እንዲሁም የክልሉ ሕዝብ በሰላም እጦት ከሚደርስበት ችግር እንዲወጣ ድርጅቱ የሰላም ስምምነቱን መፈረሙንም ገልጿል። “እስከመቼ ነው ጦርነት ውስጥ የምንቆየው?” የሚል ጥያቄ በድርጅቱ ውስጥ በየደረጃው ካሉ ሠራዊት አባላት ጥያቄ ሲነሣ እንደነበር የገለጸው የአፋሕድ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ፋይናስ ኃላፊ፣ አሁን የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተገቢ መሆኑን አረጋግጧል። በተደረሰው ስምምነትም ሁላችንም ደስተኞች ነን ሲልም ገልጿል። የድርጅቱ የጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የወሎ ቤተ አማራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አስተዳደር እና ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ግርማ እጅጋየሁ፣ አማራ ጠል ወይም ኢትዮጵያ ጠል የሆኑት ህወሓት እና ሻዕቢያ ከግብጽ ተልዕኮ ተቀብለው የአማራ ክልልን የማተራመስ አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ አካሄዳችን ትክክል አይደለም ብለን ወደ ድርድር መጥተናል ብሏል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
😁 47 30👍 7👎 1🔥 1
3
照片不可用在 Telegram 中显示
እጅ የሰጡ የፋኖ ታጣቂዎች በአዲስአበባ ሰሞኑን በቡድን ከነትጥቃቸው ሰላም ይሽለናል በማለት እጃቸውን ለመከላኪያ ሰራዊት የሰጡት የፋኖ አመራሮችና ታጣቂዎች በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ መግለጭ እየሰጡ እንደሚገኝ ታውቋል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
😁 71 16👎 12👀 3👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ትራምፕ 1 ሚሊየን ዶላር 'ጎልደን ካርድ' ቪዛን በይፋ አስጀመሩ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢያንስ 1 ሚሊየን ዶላር መክፈል ለሚችሉ ሐብታም የውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጥ ‘ጎልደን ካርድ’ ቪዛን በይፋ አስጀምረዋል። ቪዛ ካርዱ አመልካቾች ብቁ መሆናቸው ከተረጋገጠ “በቀጥታ የአሜሪካ ዜጋ መሆን የሚችሉበትን መንገድ ይከፍትላቸዋል” ተብሏል። ትራምፕ ቪዛውን ካስተዋወቁ በኋላ “እጅግ አስደናቂ ነገር” በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል። ቀደም ብሎ ይፋ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ ቪዛ ካርድ ለአሜሪካ“ተጨባጭ ጥቅም” ያስገኛሉ የተባሉ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል። አዲሱ የትራምፕ ቪዛ ዋሺንግተን ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ዘመቻ በጀመረችበት፣ ለሥራ ቪዛ የሚከፈለው ገንዘብ እንዲጨምር እና ሰነድ አልባ ስደተኞችን የማባረር እርምጃ በጀመረችበት ወቅት የተዋወቀ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
25👎 14😁 3😭 1
照片不可用在 Telegram 中显示
እግድ ከተጣለባቸው ዘጠኝ የ #ዶቼ_ቬለ ዘጋቢዎች መካከል የሰባቱ ሲነሳ ሁለት ጋዜጠኞች በዘላቂነት መታገዳቸውን ጣቢያው አስታወቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ኢትዮጵያ ከሚገኙት የዶይቸቬለ ዘጠኝ ዘጋቢዎች መካከል በሰባቱ ላይ የጣለውን እገዳ ማንሳቱን ጣቢያው አስታወቀ። ሆኖም ጣቢያው ሁለቱ ሠራተኞቹ በዘለቂነት ከሥራ መታገዳቸውን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን መስማቱን ገልፆ "እርምጃውን አጥብቆ አውግዟል"። አያይዞም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ስህተት አለባቸው ያላቸው ዘገባዎች አልያም የኢትዮጵያ ሕግን የሚጥሱ የሚላቸውን ማስረጃ እንዲያቀርብ ዶይቸ ቬለ በድጋሚ መጠየቁን ከጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ለ #ዶቸ_ቬለ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ዘገባ እንዳይሰሩ ጊዜያዊ እግድ የተጣለባቸው ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም ነበር። ጣቢያው በወቅቱ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ "የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በፃፈዉ ደብዳቤዉ ዶቼ ቬለና ወኪሎቹን የኢትዮጵያን ሕግና ደንብ ጥሰዋል፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን አያከብሩም በማለት ወቅሷል" ሲል ገልፆ ነበር። የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) በበኩሉ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዶይቼ ቬለ አማርኛ ዘጠኝ ጋዜጠኞች በጊዜያዊነት ማገዱን በጽኑ ማውገዙ ይታወሳል። ውሳኔውም በአስቸኳይ እንዲቀለበስ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ፌዴሬሽኑ ይህንን እርምጃ የዶይቼ ቬለን ዘገባ “ዝም ለማሰኘትና በተለይም በአማራ ክልል ውስጥ ስላለው ግጭት ኢትዮጵያውያን ገለልተኛ መረጃ እንዳያገኙ ለመገደብ የታሰበ የማስፈራሪያ ድርጊት ነው” ሲል በወቅቱ ማስታወቁ አይዘነጋም። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
14😁 3
አሻም ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ ስርጭት ማቆሙን አሳወቀ 📌 ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል። #Ethiopia | አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተችበት ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ስታደርስ ቆይታለች፡፡ ይሁን እንጂ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ስራዋን ለመቀጠል አቅም ስለሌላት በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ባለፉት 8 ዓመታት ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋር አብራችሁ ለዘለቃችሁ ለውድ ተመልካቶቻችንና ተከታታዮቻችን ልባዊ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
😭 24 22👍 3😁 1
የትራንስፖርት ታሪፍ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተፈፃኒ ሳይሆን መቆየቱን ተናገሩ‼️ “በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሺያ ይደረጋል” የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች፤ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከሦስት ጊዜ በላይ  ጭማሪ ቢደረግም የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል።  የታሪፍ ማሻሺያ እንዲደረግላቸው ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉንም ገልጸዋል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሺያ የተደረገላቸው የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 80 ብር በሚሸጥበት ወቅት እንደነበር ኢቲዮቲዩብ ያነጋገራቸው የታክሲ አሽከርካሪዎች አስታውቀዋል። ሆኖም የነዳጅ ዋጋ ከሦስት ጊዜ  በላይ ጭማሪ ያደረገ ቢሆንም የታሪፍ ማሻሺያው ግን ሳይስተካከል መቆየቱን ገልጸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን የታክሲ አሽከርካሪ እንደገለጹት ከሆነ “ ታሪፉን እንዲያስተካክሉልን የትራንስፖርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል። የነዳጅ ዋጋ ሦስት ጊዜ ተሻሽሏል። [በሦስቱ ዙሮች] ከ 80 ብር ወደ 121 ብር ጨምሯል። በዚህ ጊዜ ምንም የታክሲ ታሪፍ ማሻሺያ አልተደረገም” በማለት አስረድተዋል። ዛሬ ታኀሳስ 1/2018 ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ተሻሽሎ ቀርቧል። ከ ቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ  121 ብር ሲሸጥ የነበረውን አንድ ሊትር ቤንዚን 8 ብር ከ 12 ሳንቲም ጨምሮ በ 129.12 ብር መሸጥ ጀምሯል። ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲንም በተመሳሳይ ዋጋ እንዲሸጡ መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ ካደረገው መረጃ ላይ ተመልክተናል። በዚህ ሁኔታ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ የትራንስፖርት ታሪፍ ሳይሻሻል መቅረቱ ጫና ውስጥ ከትቶናል የሚሉት ጣቢያችን ያነጋገራቸው የታክሲ ሾፌሮች “በጥቂት ሳምንታት አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ይደረጋል ብንባልም ተግባራዊ አልተደረገልንም” ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዴኤታ አቶ በሪኦ ሐሰን “መጥተው ይጠይቁ እኔ ጋር” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተውናል። ሆኖም  ኢትዮቲዩብ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኙው መረጃ እንደሚያመላክተው በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት ወስጥ ዐዲስ የትራንፖርት ታሪፍ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገንዝቧል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
24👎 7😁 1
照片不可用在 Telegram 中显示
照片不可用在 Telegram 中显示
Repost from YeneTube
00:40
视频不可用在 Telegram 中显示
🥁 65% /35% 🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫 🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ     🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ 🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።      🏠  80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ                          🥁ሙሉ  ክፍያ 5,770,050ብር    🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ             🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር ✅ መገልገያዎች 👉 ሁለት  ዘመናዊ  የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች 👉   የመኪና ማቆሚያ ቦታ 👉 ቴራስ   👉  ያልተገደበ  የውሃ አቅርቦት    👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር     👉 የደህንነት ካሜራ     👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም እንዲሁም ⛳️ ገላን ኮንደምንየም 🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ  እየሸጥን እንገኛለን። 🚴🏿‍♂️ይፍጠኑ🚴🏽‍♀️   🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733   ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።     Telegram @momsra16 ይፍጠኑ🗣
显示全部...
12.33 MB
5👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ሁሉም ሰው እየሸጠ ነው - እርሶስ? ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ይሽጡ። መግዛት ከፈለጉ ደግሞ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family ET Creatives
显示全部...
8
照片不可用在 Telegram 中显示
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳወቀ! የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል። አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ‎ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል። ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህል ለመጫን የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል። @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
👎 98 82👍 41😁 13🔥 2👀 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀመረ የፋይናንስ ዘርፍ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን አስመልክቶ ለፋና ዲጂታል የላከው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2030 ውስጥ አንዱና ዋናው አስቻይ ምሰሶ ሆኖ ተቀምጧል። ለተለያዩ ዘርፎች አገልግሎትን ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር፤ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና ለዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት መሠረት በመጣል በኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ሒደት ዋነኛ አስቻይ እንዲሆን ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፋይዳን መሰረት አድርጎ የሚሰጡ የፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎቶችን የማቀናጀት ሀገራዊ ግብን ለማሳካት በትግበራው ላይ በሰፊው እየሰራ እንደሆነም ይታወቃል። በዛሬው እለትም ለፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን አንድ ርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ፋይዳ ዲጂታል የማንነት መረጃ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር (harmonization) ስራን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
👎 22 19🔥 2😭 2👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀን ከ3 እስከ 4 ለወሲባዊና አካላዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች አገልግሎት ያገኛሉ ተባለ  አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ካለፉት አምስት ዓመታት አንስቶ ከክልሉ ሴቶች ጉዳይ ጋር በመተባበር እንዲሁም  ዩኒሴፍ በሚያገኘዉ ድጋፍ የአንድ መስኮት አገልግሎት በማቋቋም  አካላዊና ወሲባዊ ጥቃት ለሚደርስባቸዉ ሴቶችና ህፃናት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታዉቋል ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መርቀኒ አወድ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ሆስፒታሉ በቀን ወሲባዊና አካላዊ ጥቃት ለሚደርስባቸዉ ከ3 እስከ 4 ለሚሆኑ ሴቶችና ህፃናት የአንድ መስኮት አገልግሎት ይሰጣል ። ባለፉት 4 ወራት ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ 218 ሴቶችና ህፃናት አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዉ ፤ከዚህ ዉስጥ ስድስቱ ህፃናት ሲሆን የተቀሩት ከ18 ዓመት የዕድሜ ክልል በታችና በላይ የሆናቸዉ ናቸዉ ብለዋል ። ይህ የአንድ መስኮት አገልግሎት በዉስጡ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ፣ጠቅላላ ሀኪም ፣ነርስ ፣የፖሊስ አካል ፣አቃቤ ህግና ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶች የእርግዝናና የኤችአይቪ ምርመራ እንዲሁም ሌሎችንም ህክምናዎች እንዲያገኙ ከተደረገ በኃላ ወዲያዉኑ ጉዳያቸዉ በህግ ይታይላቸዋል ተብሏል ። ይህም መጉላላትን በማስቀረት ዉሳኔዎች በፍጥነት እንዲሰጡ የሚኖረዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ ያሉት ዳይሬክተሩ አልፎ አልፎ የግብረሰዶም ጥቃት የሚደርስባቸዉ ወንዶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልፀዋል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
16😭 2
照片不可用在 Telegram 中显示
የቀድሞው የአደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ! የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል። የፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ፣ አቶ ምትኩ ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር በመሆን የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴን ጨምሮ በርካታ የምግብ እርዳታ ቁሳቁሶችን ከመጋዘን በማውጣት ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ አስረድቷል። በተጨማሪም፣ ከ472 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲከፈል በማድረግ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።ፍርድ ቤቱ አቶ ምትኩ ካሳን በተጨማሪም፣ በሕገ ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ምንጩን ደብቀው ሕጋዊ አስመስለው በማቅረብ ወንጀል ከልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ እና ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ጋር ተከሰው ጥፋተኛ መሆናቸውን ወስኗል። በዚህም መሰረት፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል የ8 ዓመት ከ4 ወር እስራት ሲፈረድባቸው፣ ልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ ደግሞ የ5 ዓመት እስራት ተበይኖባቸዋል። Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
15👍 4
00:40
视频不可用在 Telegram 中显示
🥁 65% /35% 🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫 🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ     🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ 🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።      🏠  80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ                          🥁ሙሉ  ክፍያ 5,770,050ብር    🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ             🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር ✅ መገልገያዎች 👉 ሁለት  ዘመናዊ  የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች 👉   የመኪና ማቆሚያ ቦታ 👉 ቴራስ   👉  ያልተገደበ  የውሃ አቅርቦት    👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር     👉 የደህንነት ካሜራ     👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም እንዲሁም ⛳️ ገላን ኮንደምንየም 🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ  እየሸጥን እንገኛለን። 🚴🏿‍♂️ይፍጠኑ🚴🏽‍♀️   🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733   ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።     Telegram @momsra16 ይፍጠኑ🗣
显示全部...
12.33 MB
8👍 1🔥 1
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ነው ይፋ ያደረገው። የአውሮፕላን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግን ጭማሪ ተደርጎበታል። - ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር - ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር - ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር እንዲሸጡ ተወስኗል @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
😭 23 19
照片不可用在 Telegram 中显示
"በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር የለም!" ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር እንደማይኖር፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር)፣ ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይየ30 በመቶ ግብር ይጣላል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር መቆየቱን፣ ነገር ግን ይህ መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል። ገንዘብ ሚኒስቴርን ጨምሮ በጉዳዩ ላይ በየትኛውም የመንግሥት አካል የተሰጠ መግለጫ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይጣላል የተባለው ግብር በማኅበራዊ ሚዲያው ላይየተፈጠረ እንጂ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንም የሚያውቀው ከዚህ ወር ጀምሮ የሚጣል ምንም ዓይነት የግብር ጭማሪ እንደማይደረግና መንግሥትም ይህን የማድረግ ዕሳቤ እንደሌለው መሆኑን ተናግረዋል። ‹‹በሐሰተኛ መረጃ የተነሳ ኅብረተሰቡ ላልተገባ ሠልፍና እንግልት እየተዳረገ ይገኛል፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ያለ ምንም ይፋዊ የመንግሥት ውሳኔ ከወጣው የነዳጅ ዋጋ ውጪ ያለ አግባብ ጭማሪ የሚያደርጉ የነዳጅ አከፋፍይ ኩባንያዎችና ማደያዎች ተጠያቂ እንደሚደረጉም አሳስበዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በመደበኛ ሁኔታ ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን፣ ነገር ግን በዚህ ሐሰተኛ መረጃ ምክንያት ፍጆታ ላይ ጭማሪ መፍጠሩን ገልጸዋል። የተናፈሰው መረጃ ስህተት መሆኑን ለነዳጅ ኩባንያዎችና ማደያዎች በተደጋጋሚ እያሳወቁ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኩባንያዎች ባልተፈለገ መንገድ ተታለው ከጂቡቲ የተረከቡትን ነዳጅ ላልተገባ ጥቅም የማዋል ዕሳቤ እንዳይፈጠርባቸው በድጋሚ አሳስበዋል። @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
48😁 11
照片不可用在 Telegram 中显示
የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡ በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል። "ጊፋታ" በወላይታ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡ ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል። @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
👍 24 12😁 8👎 1