108 095
订阅者
-12324 小时
-5057 天
-2 11030 天
帖子存档
ጦርነትን ለማስወገድ እንሰራለን፣ ለሰላም ብለን የምንሸጠው ግዛት ግን የለም"ፕሬዘደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ይህን ያሉት 'የትግራይን ህልውና እና ደህንነት ለማረጋገጥ!' በሚል መሪ ሃሳብ ከታኅሣሥ 02/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ በቆየው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአመራር አቅጣጫዎች፣ እቅዶች እና አፈጻጸም ላይ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው።
ትግራይ በተለያዩ ዘርፎች እጅግ በጣም አስቸጋሪ እና ጫና የበዛበት ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች ያሉት ፕሬዝደንት ታደሰ ወረደ፣ ያለን ምርጫ እነዚህን ተግዳሮቶች ተቋቁመን መውጣት ነው ብለዋል።
በተለያዩ መንገዶች እገዳው እንዲጨምር እና እንዲወሳሰብ የሚያደርጉ ብዙ እንቅስቃሴዎች አሉ፤ በመሆኑም የአደጋው መጠን ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይሄዳል፣ በመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ያለው ጫና መጨመሩ፣ በፍትህ እና ዳኝነት ላይ ያለው ውስብስብ ችግር፣ ያለን ደካማ ኢኮኖሚ፣ ስርአታዊ የሚመስል የሙስና ችግር፣ ተጠናክሮ የሚቀጥለው እገዳ እና በውስጣችን ሆነው የሚሰሩ አካላት በመጨመራቸው የተጋላጭነታችን መጠን በእጥፍ እንዲጨምር አድርጎታል ሲሉ ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዳሉት ደግሞ "ተቸገርኩ ብለህ ብትጮህ የሚሰማህ በሌለበት ዓለም አቀፍ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።
ሀገራት የራሳቸውን ፍላጎት የሚያስቀድሙበት፣ ብትሞትም የሚሰማህ በሌለበት እና ለሰብአዊነት የሚሰጠው ትኩረት በቀነሰበት ዓለም አቀፍ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል።
ለዚህ መፍትሄውም በውስጣችን በምንፈጥረው አቅም ነው ሲሉ ፕሬዝደንት ታደሰ ገልጸዋል።
አደጋዎችን ተሸክሞ በማይቀጥልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው፤ እነዚህንም መፍታት የምንችለው አንድ በመሆን፣ በመረጋጋት እንዲሁም በራሳችን አቅም ብቻ ነው ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ አንድ ከሆንን እና አቅም ከገነባን የመሰማት አቅማችንና የመደራደር አቅማችን ከፍ ያደርጋል ብለዋል።
በተጨማሪም ጀነራል ታደሰ ወረደ የበጋን መምጣት በመጠበቅ እና የመኸርን ምርት መጨመር በመምከር የሚለካ የኢኮኖሚ ጥንካሬ የለም ያሉ ሲሆን፣ ጠንካራ አቅም የሚኖረው ጠንካራ ኢኮኖሚ ሲገነባ እና በዝናብ ላይ ጥገኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ሲገነባ ነው ብለዋል።
ከጎረቤት ክልሎችና ከፌደራል መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት በአግባቡ እንሰራበታለን ያሉት ፕሬዝደንት ታደሰ፣ የሚኖረንና የምንፈጥረው ግንኙነት ግን በአቻ ለአቻ መርህ፣ በራስ መተሳሰርና መደጋገፍ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብለዋል።
በጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ የቀረበው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአመራር አቅጣጫዎች እና እቅዶች ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጎበት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ቀጣይ የአመራር አቅጣጫዎችና አፈጻጸማቸው ተብራርተው በሙሉ ድምፅ ጸድቆ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው መድረክ ትናንት ታኅሣሥ 04/2018 ዓ.ም ተጠናቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 44😁 2
Repost from YeneTube
00:40
视频不可用在 Telegram 中显示
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
12.33 MB
❤ 10👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
በአዲስ አበባ የውስጥ ለውስጥ መንገድ አጥሮች እንዲነሱ የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን አስጠነቀቀ፡፡
በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ ግለሰቦች መንገዶቹን በሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት እንዲያደርጉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።
ባለሥልጣኑ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በሕገወጥ መንገድ በግለሰቦች ታጥረው የተዘጉ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ይህ ሕገወጥ ድርጊት የሕብረተሰቡን በመንገድ ሀብት የመጠቀም መብት ከመጋፋቱም በላይ፣ የትራፊክ እንቅስቃሴው እንዲስተጓጎል አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑን አክሎ አስታውቋል።
በመሆኑም፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ አካላት በሙሉ ከቅዳሜ ታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ መንገድ የዘጉበትን አጥር እንዲያነሱ እና መንገዱን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል።
በሁሉም የከተማዋ ማዕዘናት መጠነ-ሰፊ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጸው ባለስልጣኑ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጥር የማያነሱ አካላት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 25👎 3😁 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የአሜሪካዊቷ ሚኒስትር ክሪስቲ ኖም ውሳኔ በቦስተን ከተማ ለምትኖረው ኢትዮጵያዊቷ ነርስ *ሜላት ገብረ እግዚያብሔር “መርዶ” ሆኖባታል።
የአሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ ሆምላንድ ሴኪዩሪቲ (Department of Homeland Security) ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ከትላንት በስቲያ አርብ ያስተላለፉት ውሳኔ፤ እንደ እርሷ ሁሉ “ጊዜያዊ ከለላ” አግኝተው በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አስደንግጧል።
የ54 ዓመቷ ሚኒስትር የአርብ ዕለት ውሳኔ፤ ሜላትን ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ከለላ ያሳጣ ነው። ውሳኔው ይፋ ከተደረገ በኋላ ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር አጭር ቆይታ የነበራት ሜላት “እንዴት እንደምተኛም አላውቅም” ስትል ጭንቀቷን አጋርታለች።
ሜላትን ለጭንቀት እና ፍርሃት የዳረጋት ውሳኔ የተላለፈው፤ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለው ሁኔታ “ጊዜያዊ ከለላ” ለመስጠት የሚያስፈልገውን “ቅድመ ሁኔታ” እንደ ቀደሙት ጊዜያት “የሚያሟላ አይደለም” በሚል ምክንያት ነው። በአሜሪካ ለተወሰነ ጊዜ መቆየት የሚያስችለውን “ጊዜያዊ ከለላ” የሚያገኙት፤ ግጭት እየተካሄደባቸው ከሚገኙ፣ የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌሎች ፖለቲካዊ ቀውሶች ከገጠማቸው ሀገራት ለሚጓዙ ዜጎች ነው።
ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ወደ ትውልድ ሀገራቸው በግዳጅ ከመመለስ በህግ የሚጠበቁ ሲሆን በአሜሪካ ለመስራት የሚያስችላቸው ፈቃድ ያገኛሉ። ኢትዮጵያውያን ይህን የሰብአዊ ጥበቃ ያገኙት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ወቅት በታህሳስ 2015 ዓ.ም ነበር።
በወቅቱ ከለላውን ለማግኘት ብቁ የሆኑ 26,700 ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ይገኛሉ ተብሎ ይገመት ነበር።
🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16779/
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 29🔥 3👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
.
በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ
✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family
ET Creatives
❤ 8
Repost from YeneTube
照片不可用在 Telegram 中显示
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ - ዳይናሚክ አክሲዮን ማህበር
የስራ ቦታ፡ የሽያጭ እና የግብይት ኃላፊዎች (ብዛት 20 )
አካባቢ፡ አዲስ አበባ
🔹 ቁልፍ ኃላፊነቶች
የኩባንያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቁ እና መሽምጥ።
የመስክ ግብይት እና የደንበኛ ክትትል ማካሄድ።
ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የሽያጭ ግቦችን ማሳካት።
የዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገበያ ግብረመልስ ሪፖርቶችን ማቅረብ።
🔹 መስፈርቶች
በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ።
እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ እና የማሳመን ክህሎቶች።
በጫና ስር የመስራት እና የሽያጭ ግቦችን የማሳካት ችሎታ።
በሽያጭ ወይም በማርኬቲንግ ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ነው (ግዴታ አይደለም።)
ሐቀኛ፣ ታታሪ እና የመስክ ስራ ለመስራት ፈቃደኛ።
🔹 የምናቀርበው ነገር
ወርሃዊ ደሞዝ + ማራኪ ኮሚሽን
የአፈጻጸም ጉርሻዎች
የስልጠና እና የሙያ እድገት እድሎች
📩 እንዴት ማመልከት እንደሚቻል (የTalentHub ብቻ)
ሁሉም አመልካቾች በTalentHub በኩል ብቻ ማመልከት አለባቸው።
https://talenthubethiopia.com/
📍 የቢሮ አድራሻ
Megenagna፣ Hibire ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 312፣ አዲስ አበባ
📅 የማመልከቻ ቀነ-ገደብ፡
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ።
❤ 23👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያውያን ሲሰጥ የነበረውን ከለላ አቋረጠ!
የአሜሪካ መንግሥት ከሦስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያውያን በጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ በአገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ የፈቀደበትን አሠራር እንዲያበቃ አደረገ።የአሜሪካ መንግሥት ይህንን ጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ መብት የሚሰጠው በአገራቸው ግጭት፣ የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌላ ለደኅንነታቸው አስጊ የሆነ የተለየ ክስተት ካለባቸው አገራት ለመጡ ስደተኞች ነው።
በዚህ የጥገኝነት መብት ውስጥ ተቀባይነት የሚያገኙ ስደተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲሠሩ እና ከአገር እንዳይባረሩ የሚያደርግ ጊዜያዊ ከለላን ያገኛሉ።
ይህ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሲሰጥ የነበረው ጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ አሁን በስደተኞች ላይ ጠንከር ያለ አቋም በሚያራምዱት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር እንዲያበቃ ተደርጓል።ውሳኔው ይፋ የተደረገው የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅነንት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖም የመንግሥት ውሳኔዎች በሚወጡበት የፌደራል መንግሥቱ መድረክ ላይ ባወጡት ማስታወቂያ ነው።
"የአገሪቱን ሁኔታ በመመርመር እና ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግሥት አካላት ጋር በመመካከር ኃላፊዋ ኢትዮጵያ ለጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን የማታሟላ ናት የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል" በማለት ውሳኔውን አሳውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/clyddz42p4vo
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 19😭 18👍 6🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
"አሰብን በጋራ መጠቀም አለብን'' ኤርትራኖች ሞኞች ናቸው! ''አምባሳደር ጀኔራል ባጫ ደበሌ።
የሚያስቡ ከሆነ አሰብን በጋራ ጥቅም ማዋል'' ለጋራ ጥቅም ካላዋልክ ደግሞ አይቀርም እናመጣዋለን። አሰብን አስቀራለሁ ስትል ይጠፋል። በውጊያ የመሄድ ፍላጎት የለንም፣ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንሄዳለን።
የነሱ ሃሳብ ኢትዮጵያን በማመስ ኤርትራ በሰላም ትኖራለች የሚል ፖሊሲ ነው ያላቸው። ይህ ደግሞ የሞኞች ፓሊሲ ነው አንተ የሰው ቤት እየበጠበጥክ በሰላም አትኖርም ሰውን ሰላም አሳጥተህ አንተ በሰላም አትኖርም።
አንተ መስታወት ቤት ውስጥ ቁጭ ብለህ ድንጋይ ብትወረውር ምን ሊያመጣ እንደሚችል ይታወቃልና የኢትዮጵያ የባህር በር የማገኘት ጉዳይ ምንም ጥርጥር የለውም"።
አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 57😁 45👍 9👎 4🔥 1
Repost from YeneTube
00:40
视频不可用在 Telegram 中显示
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
12.33 MB
❤ 8👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ኤርትራ ከኢጋድ አባልነቷ መውጣቷን አስታወቀች!
"ኢጋድ የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የማያሳካ ሆኗል"
ኤርትራ ከድርጅቱ ለመውጣት የወሰነችውን ውሳኔ በይፋ ለኢጋድ ዋና ጸሐፊ አሳውቃለች ሲል የአገሪቱ የኢንፎሜሽን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡
ኤርትራ እ.ኤ.አ. በ1993 የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እንደገና ሲደራጅ ጀምሮ ቁልፍ ሚና መጫወቷን ያስታወሰው መግለጫው፣ ጥምረቱ በሂደት የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የማያሳካ ሆኗል ሲል ተችቷል፡፡
“ከጎርጎሮሳውያኑ 2005 ዓ.ም ወዲህ፣ ኢጋድ የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የሚያሟላ ሳይሆን፣ ጉዳት የሚያስከትል ሚና ተጫውቷል፡፡ በተለይም ኢላማ ለተደረጉ አባል አገራት፣ኤርትራ ላይ በልዩ ሁኔታ መሣሪያ ሆኗል። እነዚህ ያልተገቡ ድርጊቶች ኤርትራን እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 2007 አባልነቷን እንድታግድ አስገድዷታል።” ብሏል መግለጫው፡፡
ኤርትራ ድርጅቱ ስህተቶቹን ያርማል በሚል ተስፋ እ.ኤ.አ. ሰኔ 2023 አባልነቷን ማስቀጠሏን የጠቀሰው መግለጫው፣ ኢጋድን በሕግ የተሰጡትን ግዴታዎች ባለመወጣት እንደሚከስ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
የኤርትራ የኢንፎሜሽን ሚኒስቴር፤ “በዚህ ሁኔታ ኤርትራ ሕጋዊ ሥልጣኑንና ኃላፊነቱን ካጣ፣ ለሁሉም አባላቱ የሚታይ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ከማያስገኝ እንዲሁም ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽኦ ካላደረገ ድርጅት አባልነቷን ለማቋረጥ ተገድዳለች።” ብሏል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 25😁 8👎 2
照片不可用在 Telegram 中显示
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለአልጄርስ ስምምነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቀረቡ!
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአልጀርስ የሰላም ስምምነት 25ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ በተከናወነበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለስምምነቱ ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ፀሐፊው በቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱጃሪክ በኩል የሰጡት መግለጫ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት እንደገና ባየለበት ወቅት ነው።
ታህሳስ 3 ቀን 1993 ዓ.ም የተፈረመው የአልጀርስ ስምምነት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በይፋ ያስቆመ ሲሆን፣ የድንበር ማካለል ዘዴዎችን ከመዘርጋቱ በተጨማሪ የሁለቱንም ሀገራት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት አረጋግጧል።
ዋና ጸሐፊው ስምምነቱን ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል ሰላማዊ ግንኙነትን መሠረት ያደረገ “ወሳኝ ማዕቀፍ” በማለት ገልጸውታል።
ጉተሬዝ በተጨማሪም፣ ከሰባት ዓመታት በፊት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ መግለጫ አማካኝነት ለሰላም የገቡትን ቁርጠኝነት ያደሱበትን ሁኔታ አስታውሰው፣ ይህም የውይይትና የትብብርን ዋጋ የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።
ውጥረቱ እንደገና እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ ዋና ጸሐፊው ሁለቱም አገራት በአልጀርስ ስምምነት ውስጥ የተካተተውን ዘላቂ ሰላምና የሉዓላዊነት እንዲሁም የግዛት አንድነት ራዕይ ዳግም እንዲያረጋግጡ የጠየቁ ሲሆን የትብብርና የመልካም ጉርብትና ግንኙነቶችን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያና ኤርትራ “ለሁሉም በሚጠቅም” መልኩ የልማት ትብብርን ለመከተል ከቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ጋር መሥራታቸውን እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 29😁 6👎 2😭 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ግሎባል ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ከቀነ ገደቡ በፊት ማሟላቱን ገለጸ።
ግሎባል ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን በማሳደግ ብር 5 ቢሊየን ማድረስ መቻሉን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልጸዋል፡፡
ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፃር የ1መቶ2 በመቶ ዕድገት ማሳየት መቻሉንም ነዉ የተናገሩት፡፡
ባንኮች ካፒታላቸዉን 5 ቢሊየን ብር እንዲያደርሱ በብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን መመሪያ ከጊዜ ገደቡ በፊት ማሳካት መቻሉን አንስተዋል፡፡
ግሎባል ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት 5.56 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት የተመዘገበው ከባለፈው ዓመት ከተመዘገበው ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።
በተዘጋው በጀት ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ሃብት 34.4 ቢሊየን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር የ42 በመቶ ዕድገት ማሳየት መቻሉንና በበጀት ዓመቱ 7.53 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰበሰብ መቻሉ ተገልጿል።
ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ41 በመቶ ብልጫ በማሳየት የባንኩን አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን ወደ ብር 25.75 ቢሊየን ማድረሱ ተነግሯል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ፣ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ1.17 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን አስታዉቋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 24🔥 1
Repost from YeneTube
00:40
视频不可用在 Telegram 中显示
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
12.33 MB
Repost from YeneTube
照片不可用在 Telegram 中显示
ሁሉም ሰው እየሸጠ ነው - እርሶስ?
ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ይሽጡ። መግዛት ከፈለጉ ደግሞ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ
✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family
ET Creatives
"ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን" ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው
ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን ሲሉ የትግራዩ ጀነራል ተናገሩ። ለአመታት በአዲስአበባ ታስረው የነበሩት የቀድሞው የሜቴክ ሀላፊ ጀኔራል ክንፈ ዳኘው አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተው ተከስተዋል። “የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባርነት ወይስ እንደ ኤርትራ ነፃነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ጀነራል ክንፈ ዳኘው የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ይልቅ ከኤርትራ ነፃነት እንደሚያገኝ አዲስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡ ጀነራሉ ብራኸ ከተሰኘ የዩቱዩብ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባርነት ወይስ ኤርትራ ነፃነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከእስር ከተፈቱ በኋላ አልፎ አልፎ አነጋገሪ ሀሳቦችን በመሰንዘር የሚታወቁት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ትግራይ ነፃ ሀገር መሆን አለባት የሚለውን አቋማቸውን ደግመውታል፡፡ እንደ ጀነራሉ እምነት ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆና መቀጠል የሚበጃት ስላልፎነ፣ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ወደ ቅድመ ጦርነት ሁኔታ እየተመለሰች ያለችው ትግራይ የኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ስር መግባት እንደሌለባትም ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡ በትግራይ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ብቸኛ የግንኙነት የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው ያሉት ሲሆን፣ ከዚያ ውጭ ምንም አይነት ማሰሪያ የለም ብለዋል፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስተዳደር ይልቅ፣ ከኤርትራ ጋር መወዳጀት እንደሚሻለቸውም ጠቁመዋል፡፡ የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራም ይሁን ከፋኖ ኃይሎች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት፣ ስልታዊ ወይስ ቋሚ የሚለውን ጉዳይ በግልጽ መበየን እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡
ትግራይ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት ብለው የሚያምኑት ጀነራሉ፣ የሚፈጸመውን በፖለቲካዊ ቁርጠንነትና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የትግራይን ሀገርነት ለማደናቀፍ የሚንቃቀስ አካል ካለ ለመመከት ወይም ለኃይል አማራጭ ለመጨረስ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡
ስለ አሁናዊ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይና ኤርትራ ውጥረት የተጠየቀት ጀነራሉ፣ ግጭት ከተቀሰቀሰ የውክልና ጦርነት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥት መካከል በባህር በር ጉዳይ ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ፣ ሌሎች ኃይሎችን በውክልና የሚያሳትፍ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
በቀጠናው የሚቀሰቀስ ጦርነት በባህሪው የውክልና ጦርነት ያሉት ጀነራሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ያነሳው የቀይ ባህር ጥያቄ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ፍላጎት ነው ሲሊም ያጣጥላሉ፡፡ ምንም እንኳን ጀነራሉ ጥያቄ የውክልና ጉዳይ ነው ቢሉም፣ ኢትዮጵያ መፍትሔ ያላገኘ ታሪካዊ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ እንደላት ይታወቃል፡፡
|
ጀነራሉ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሊቀሰቀስ ይችላል ያሉት ጦርነት፣ ትግራይን የወጊያ ማዕከል ሊያደርግ እንደሚችለም ጠቁመዋል፡፡ ትግራይ የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የውክልና ጦር ሜዳ እንዳትሆን ከወዲሁ ስልታዊ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጀነራሉ መክረዋል፡፡
ሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች ትግራይን ወደ ሀገርነት ለማሸጋገር በጋራ መቆም እንዳለባቸው ጀነራሉ መክረዋል፡፡ የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው ያሉትን የመገንጠል አጀንዳ እንደሚያቀነቅኑ ይታወቃል፡፡
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 62😁 52👎 20🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
መምህሯን አስገድደው የደፈሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሀርቡ ጂባት ቀበሌ ውስጥ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል የፈፀሙት ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ
የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ በዬራ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት 1ኛ ተከሳሽ ማሞ ዘነበ
2ኛ ተከሳሽ ቢቂላ ፍቃዱ የካቲት 27ቀን 2017 ዓ.ም ከለሊቱ 7ሰዓት ድርጊቱን መፈጸማቸው ተገልጿል ። ተጎጂዋ በመምህርነት ሞያ ስታገለግል የነበረች ሲሆን በር ሰብረው በመግባት የግብረ ስጋ ድፍረት በደል እንደፈፀሙባት በማስረጃ ተረጋግጧል።
ሁለቱ ተከሳሾች በመምህሯ ላይ ድርጊቱን ከፈፀሙ በኋላ ወዲያው ለፖሊስ ደውላ በማሳወቋ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጎጂዋ የጤና ምርመራ የተደረገላት ሲሆን በውጤቱም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል በግዳጅ እንደተፈፀመባት መረጋገጡም ከጤና ተቋም የተገኘው ማስረጃ ማረጋገጡን ገልፀዋል ።
ፖሊስ በመምህሯ ላይ የተፈፀመውን የግብረ ስጋ ድፍረት በደል በማስረጃዎች አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኳል።
አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን ማስረጃ ተመልክቶ በወንጀል ህግ ቁጥር 620 እና 605 መሰረት ክስ የመሰረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 39ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች የሃይል ድርጊት በመጠቀም አስገድደው የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀማቸውከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት በማስከተላቸው እያንዳዳቸው በአስራ አንድ አመት እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ በዬራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
ብስራት FM
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 30👎 11
ከሀገራችን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አንዱ የሆነውን ቲክቶክ በመጠቀም ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችና ምስሎችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ግለሠቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።
በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ስነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ ዜና በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባራትና ትውልድን ለማነጽ መጠቀም ሲገባ ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ።
@Yenetube @Fikerassefa
ከሀገራችን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አንዱ የሆነውን ቲክቶክ በመጠቀም ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችና ምስሎችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ግለሠቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።
በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ስነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ ዜና በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባራትና ትውልድን ለማነጽ መጠቀም ሲገባ ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ።
@Yenetube @Fikerassefa
照片不可用在 Telegram 中显示
የአሜሪካ ኮንግሬስ አባል ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በሌሎች እምነት አማኞች ላይ እየተፈጸመ ነዉ ላሉት ጥቃት ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ ተባለ
በአሜሪካ ኮንግሬስ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባሉ ኤርል በዲ ካርተር፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የሓይማኖት ተከታይ ማኅበረሰቦች ላይ ይፈጽሙቸዋል ላሉት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ አሜሪካ ማዕቀብ እንድትጥል የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አቀረቡ።
ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ፣ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም እና ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የተመረጡ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሁሉንም ዲፕሎማሲ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙ ይጠይቃል።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የሌሎች ኃይማኖቶች ተከታዮች የጦር ወንጀልና ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎች እንደተፈጸሙባቸው የሚያሳዩ ሁኔታዎች መኖራቸውንም የውሳኔ ሃሳቡ ይገልጣል።
Via ዋዜማ
@Yenetube @Fikerassefa
👍 135❤ 28😁 9👎 1😭 1
