121 286
订阅者
-2624 小时
-1667 天
-98030 天
帖子存档
አስቸኳይ የቁርኣን ኡስታዝ ይፈለጋል
መርከዝ አት_ተውሒድ የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከል አዳሪ የቁርኣን ሂፍዝ ኣስተማሪ ይፈልጋል።
የስራ ሁኔታ ፡ አዳሪ ሙሉ ጊዜ
ብዛት፡ 1
ጾታ፡ ወንድ
እድሜ ከ22 በላይ
ቁርኣን በጥሩ ሁኔታ የሐፈዘ እና የተስተካከለ ተጅዊድ ያለው
✅ ለመርከዙ ተማሪዎች አህካሙ አት-ተጅዊድ ማስቀራት የሚችል
➡️ ለመርከዙ ህግና ደንብ ፍቃደኛ የሆነ።
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሚከተለው አድራሻ በመላክ ማመልከት ትችላላችሁ:-
@Selwamoham
@Abumusab1570
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከሀረዊ ዘመን በኋላ የመጡ አስሱናህ ኪታብ፣ የ0ብደላህ ብነ አሕመድ እንደሆነ የመሰከሩ ዓሊሞች ናቸው። ስለዚህ ሀረዊን ጨምሮ በድምሩ 26 ዓሊሞች "አስሱናህ" ኪታብ የ0ብደላህ ብነ ኢማም አሕመድ እንደሆነ ዘረዘርኩኝ ማለት ነው። ያ የቅጥ /ፈት አምባሳደርስ ምን ይላል? ይሄው ንግግሩ ቃል በቃል፦
"መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይህ ኪታብ የዐብደላህ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ መጽሀፉ በጥንት ዘመን የብልሹ አስተሳሰብ አጋፋሪዎች የተፈበረከ፣ ከይዘትም አኳያ ብዙ ነዉር የተሸከመ መሆኑ ታዉቆ በዑለሞች ዉድቅ [ተደርጓል።]"
እስኪ ይሄንን ነውር ጌጡ ተመልከቱ! ያለው ምርጫ ሁለት ነው። ወይ ይሄ ሁሉ ዑለማእ ኪታቡ የ0ብደላህ ብነ ኢማም አሕመድ እንደሆነ ማረጋገጣቸውን ሳያውቅ በድፍረት የሚዘባርቅ ጥራዝ ነጠቅ ነው። ወይ ደግሞ እውነታውን እያወቀ አይኑን በጨው አጥቦ የሚቀ/ጥፍ ቆርጦ ቀጥል ነው። የጣፈጠውን ማንሳት ይችላል። እኔ ግን ሁለቱንም ነውር የተሸከመ፣ የሌሎችን ማምታቻ ሳያጣራ የሚጓፍፍ፣ በእልህ እየተነዳ አይኑን ጨፍኖ የሚቀ/ጥፍ እንደሆነ ካረጋገጥኩ ቆይቻለሁ።
በነገራችን ላይ
1. ኸጢብ አልበግዳዲይ ያሰፈሩት የኪታቡ ሰነድ ከሀረዊ ሰነድ የተለየ ነው። ይህም የሐሰን ታጁንና የማጭበርበር ሞዴሎቹን ቅጥፈት ይበልጥ እርቃን የሚያስቀር ነው።
2. ዘሀቢም እንዲሁ ከሀረዊ ሰነድ በተለየ ሶሒሕ ሰነድ ዘርዝረው ኪታቡ የ0ብደላህ እንደሆነ አስፈረዋል። [አልዐርሽ፡ 162] አስታውሱ! ሐሰን ታጁ የኢማሙ አሕመድን "አርረድ 0ለ'ዘናዲቃ" ኪታብ ለማስተባበል ዘሀቢ ላይ ሲመረኮዝ ነበር። እዚህ ደግሞ የዘሀቢ ምስክርነት ላይ አይኑን ጨፍኗል። ለምን? የሚሾፍረው ስሜት ስለሆነ። ለዚያም ነው እንዲህ የሚለው፦
"በእርግጥም ይህ ኪታብ ‹ኪታቡ ሱና› ሳይሆን ኢማም ሙሀመድ ዛሂዱል ከዉሰሪ (እስከ 1371 ዓ.ሂ) እንዳሉት ‹‹ኪታቡ ዘይግ›› (የጥመት መጽሀፍ) ነዉ፡፡"
መልስ፦
1ኛ፦ ፊርዐውንም ለህዝቦቹ ቀጥተኛ መንገድ ላይ ናችሁ፣ ሙሳ እንዳያሳስታችሁ ብሎ ነበር። የነዚህም ስራ እንዲሁ ነው።
2ኛ፦ ኢማም ብሎ የጠቀሰው ከውሠሪ እጅግ በርካታ ዑለማኦችን የሚያንቋሽሽ ነው። እነ ኢብኑ ተይሚያና ኢብኑል ቀይማማ ጭራሽ ሙስሊም አይደሉም እያለ የዱ/ርየ ስድብ ነው የሚያዘንብባቸው። ከነሱ አልፎ ኢማሙ ማሊክን፣ ሻፊዒይን፣ ኢማሙ አሕመድን፣ ቡኻሪን፣ ዳሪሚን፣ ኢብኑ ኹዘይማን፣ ኢብኑ አቢ ሸይባን፣ አቡበክር አልመሩዚን፣ ኢብኑ አቢ ሓቲምን፣ ዳረቁጥኒይን፣ ኢብኑ በጧህን፣ ኸጢቡል በግዳዲይን፣ አቡ ኑ0ይምን፣ ኢብኑ ሐጀርን፣ ... ክፉኛ የሚያብጠለጥል የብል ^ግና ቋት ነው። ሐሰን ታጁ ይሄንን ሁለ ነገሩ የረከሰ ጀህሚይ ነው ኢማም እያለ ለነውረኛ ተግባሩ እማኝ የሚያደርገው። ግም ለግም አብረህ አዝግም ነው ነገሩ።
3ኛ፦ በነገራችን ላይ ይሄ ከውሠሪ አንድ ከሐሰን ታጁ የሚሻልበት ነጥብ አለው። እንደሱ አስሱናህ ኪታብ የዐብደላህ ብነ አሕመድ መሆኑን አልሸመጠጠም። ይልቁንም የሳቸው መሆኑን አምኖ ከዚያ ግን እሳቸውም ኪታባቸውም ላይ የስድብ ናዳ ነው ያወረደባቸው። [መቃላት፡ 408]
#ማምታቻ_አምስት፡ "ኪታቡ አቡ ሐኒፋን የሚነካ ብዙ ንግግሮችን ይዟል" ብሏል።
መልስ፦
1- በመጀመሪያ ኪታቡ የዐብደላህ ብነ አሕመድ መሆኑ በትክክለኛ ሰነድ የተዘገበ፣ በታማኝ ዑለማኦች የተረጋገጠ እንደሆነ አይተናል። ይሄ ከሆነ በኋላ አቡ ሐኒፋን የሚነኩት ዘገባዎች ስላሉበት ብቻ ኪታቡ የዐብደላህ አይደለም አይባልም። ይሄ የማገናዘብ ችግር ነው።
2- በዚህ ኪታብ ውስጥ ያሉ አቡ ሐኒፋን የሚነኩት ዘገባዎች አልዒለል በተሰኘው ሌላኛው የዐብደላህ ብነ አሕመድ ኪታብም ውስጥ ይገኛሉ። እንደለመድከው ዒለልም የሳቸው አይደለም በል ደግሞ!
3- አሱናህ ኪታብ አቡ ሐኒፋን የሚነኩት ዘገባዎችን በመያዝ ብቸኛ አይደለም። የቡኻሪ "አታሪኹል ከቢር"፣ የሐርብ አልኪርማኒይ ዐቂዳ፣ የመሩዚይ "አኽባሩ ሹዩኽ"፣ የጁዘጃኒይ "አሕዋሉ ሪጃል"፣ የአቡ ኑዐይም "ሒልየቱል አውሊያእ"፣ የዑቀይሊይ "አዱ0ፋእ"፣ የበይሀቂይ "መናቂቡ ሻፊዒይ"፣ የላለካኢይ "አሱናህ"፣ የኸጢብ "ታሪኹ በግዳድ"፣ የኢብኑ አቢ ሸይባ "አልሙሶነፍ"፣ የየዕቁብ አልፈሰዊይ "አልመዕሪፋ ወታሪኽ"፣ የኢብኑ ሒባን "አልመጅሩሒን"፣ የኢብኑ አቢ ሓቲም "ኣዳቡ ሻፊዒይ" እና "ተቅዲመቱ አልጀርሕ ወተዕዲል"፣ የኩሰጅ መሳኢል፣ የኢብኑ ዐብዲል በር "አልኢንቲቃእ"፣ የኢብኑል ጀውዚ "ሙንተዞም"፣ ወዘተ. አቡ ሐኒፋን የሚነኩ በርካታ ዘገባዎችን ይዘዋል።
እነዚህ ሁሉ ኪታቦች በዚህ ዘገባቸው የተነሳ ፈጠራ ናቸው ልትል ነው? እስኪ ስንቱን ኪታብ የፈጠራ ነው እያልክ እንደምትዘልቅ እናያለን። ታዲያ የዐብደላህ ብነ አሕመድን "አስሱና" ምንድነው ልዩ የሚያደርገው?
4- እንዲያውም የምትከተሏቸው እና የምታጠቅሷቸው አሽ0ሪዮች ጭምር አቡ ሐኒፋን በሃይለኛ እየነቀፉ ፅፈዋል። ለምሳሌ፦
4.1. መዝሀባችንን ያደራጀ ነው የምትለው አቡል ሐሰን አልአሽ0ሪይ፦ አቡ ሐኒፋና ጓዶቹ ሙርጂአ ናቸው ብሏል። [መቃላቱል ኢስላሚዪን፡ 1/119]
4.2. ጁወይኒይ፦ አቡ ሐኒፋህ በጭራሽ ከሙጅተሂዶች አልነበረም። ምክንያቱም 0ረብኛም፣ ሐዲሥም፣ የፊቅህ መሰረታዊ ህጎችንም የሚያውቅ አልነበረም። ከባድ ኢርጃእ ነበረበት፣ በዚህ የተነሳ ሁለት ጊዜ ተውበት እንዲያደርግ ተደርጓል ይላል። [አልቡርሃን ፊ ኡሱሊል ፊቅህ፡ 2/873]
4.3. የምታወድሱት፣ ሑጀቱል ኢስላም፣ ሙጀዲድ፣ የምትሉት አቡ ሓሚድ አልገዛሊይ:- ከጁወይኒ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ትችት አቡ ሐኒፋ ላይ የሰነዘረ ሲሆን ከፊቅህ መርሆዎች ጋር በሚቃረን መልኩ አጉል ብልጣብልጥ ለመሆን የሚሞክር እንጂ አዋቂ አይደለም ይላል። [አልመንኹል፡ 581]
4.4. ኢብኑል ጀውዚይ፦ አቡ ሐኒፋን መተቸት ሁሉም የተስማማበት ነው ብሏል። ሰበቡንም ሲጠቅስ ከፊሎቹ በዐቂዳው፣ ከፊሎቹ በዘገባው፣ ከፊሎቹ ደግሞ ሶሒሕ ሐዲሦችን በሚቃረን መልኩ ግላዊ አስተያየቶችን በማራመዱ የተነሳ ነው ካለ በኋላ መረጃዎችን ዘርዝሯል። [አልሙንተዞም፡ 3/23]
እና አቡ ሐኒፋን ከተቹማ አሽ0ሪይ ብሎ ኢማም፣ ጁወይኒ ብሎ ሰው፣ ገዛሊይ ብሎ ሑጀቱል ኢስላም፣ ኢብኑል ጀውዚ ብሎ ዓሊም የለም ትላለህ ወይ? ወይም ኪታቦቻቸው የነሱ ሳይሆኑ ለተንኮል የተዘጋጁ የፈጠራ ስራ ናቸው ትላለህ? በገዛ ገመድህ ባትታነቅ ይሻልሃል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 23/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሐሰን ታጁ ውዥንብር በአስሱና ኪታብ ላይ
~
የአላህን ሲፋት እና መሰረታዊ የኢስላም 0ቂዳን ከሚያሳዩ በጥንት የሰለፍ አባቶች ከተዘጋጁ በርካታ ስራዎች ውስጥ አንዱ የኢማሙ አሕመድ ልጅ በሆኑት ዐብዱላህ የተዘጋጀው "ኪታቡ ሱንና"፣ በሌላ ስሙ "ኪታቡ 'ረድ 0ለል ጀህሚያ" ነው። ሱሀይብ አስሰቃር የተባለ ጀህሚይ ይሄ ኪታብ በሳቸው ስም የተቀጠፈ እንጂ የሳቸው ስራ አይደለም ይላል። ይሄ ሰው ከስሙ በፊት ዳል አለች፤ ዶክተር ለማለት። ይቺ ከስም ቀድማ የምትቀመጥ ዳል አንዳንዴ ደጅጃል ማለት ትሆናለች። ሐሰን ታጁ በቅርቡ የፃፈውን በቅጥፈት የተሞላ አርቲ ቡርቲ ቢያንስ ከፊሉን ከዚህ የቅጥ ፈት ዘመዱ ነው የወሰደው። "ወፍ ካ'ምሳያዋ ጋር ትበራለች።"
የሐሰን ታጁ አላማ እንዲህ አይነት ውዥንብር የነዙ ሰዎችን ስራ ገልብጦ በማምጣት ሁለት፣ ሶስት ኪታቦች ላይ ብዥታ ከነዛ በኋላ የሰለፎችን 0ቂዳ እንዳለ በንዲህ አይነት የፈጠራ ስራ ላይ የተገነባ እንደሆነ አድርጎ ማሳየት ነው። በመሰረቱ በዚህ ላይ የተዘጋጁ ኪታቦች ብዙ ስለሆኑ ይሄ ኪታብ ከነጭራሹ ባይኖር እንኳ የሚቀይረው ነገር የለም። ስንቱን ኪታብ የፈጠራ ነው እያለ ይዘልቃል? ሌላው ሁሉ ቢቀር ኢማሙ ቲርሚዚይ ዛሬ እነ ሐሰን ታጁ የሚያራምዱትን የማራቆት መዝሀብ የሰለፎች ሳይሆን የጀህሚያ መንገድ እንደሆነ አስረግጠው ይናገራሉ። መቼስ ሱነኑ ቲርሚዚንም የፈጠራ ስራ ነው ሊል አይቻለውም፣ ከሱ የማይጠበቅ ነገር ባይኖርም።
ወደ ኪታቡ ሱንና እንመለስና ሐሰን ታጁ፡ የ0ብደላህ ብነ አሕመድ አይደለም እያለ የነዛቸውን ማምታቻዎች እንመልከት።
#ማምታቻ_አንድ፡ {ኪታቡ የተላለፈባቸዉ #የመጀመሪያዎቹ ሁለት የሰነድ እርከኖች ያልታወቁ ስብዕናዎችን የያዘ በመሆኑ በዐብደላህ እብን አህመድ ስም የተሰራጨዉ ኪታብ ዉድቅ ነዉ} ብሏል።
መልስ፦
* የተባሉት ሁለቱ ዘጋቢዎች ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም አልሀረዊ እና አቡ ነድር ሙሐመድ ብኑል ሐሰን አስሲምሳር ናቸው። የመጀመሪያው የኢብኑ ሒባን ሸይኽ ሲሆን ታማኝና ብቁ እንደሆነ ለይተው መድበውታል። [አሥሢቃት፡ 7/33] ሁለተኛው የአቡ የዕቁብ አልቀራብ ሸይኽ ሲሆን በሰፊው ዘግቦለታል። አቡ ዘር አልሀረዊም "ታማኝ" /ሢቀህ/ ነው ብሎታል። [አልሙዕጀም፡ 390፣ ቁ. 249] አቡ ዘር ተማሪውና የሃገሩ ልጅ ስለሆነ ጠንቅቆ ያውቀዋል። እንዳትጠራጠሩት አሽ0ሪይ ነው።
* ደግሞም ኪታቡ ከሀረዊ መስመር በተጨማሪ በሉንባኒይ፣ በኸላል፣ የ0ብደላህ ብኑ አሕመድ ተማሪ በሆኑት አሕመድ ብኑ ሰልማን አነጃድ፣ በሙሳ አልኻቃኒይ እና በኢስማዒል አልኹጦቢይ በኩል፣ በድምሩ በስድስት የተለያዩ መስመሮች ነው የመጣው። ስለዚህ የሀረዊ መስመር ደካማ ቢሆን እንኳ ሌሎች አሉ ማለት ነው።
ስለዚህ "ኪታቡ ሱንና" ከሰነድ አንፃር የ0ብደላህ ብነ አሕመድ ለመሆኑ አስተማማኝ መረጃ ስላለው የሐሰን ታጁ ማምታቻ ባየር ላይ ተኖ ይቀራል። ይህንን ያዙና ልክ ሰነድ እንደሚያከብር ሰው ያለ ሰነድ ምንም ልንወስድ እንደማይገባ የሚያሳስቡ የሰለፎችን ንግግር መጠቃቀሱን አስቡት። አምታታው በከተማው!
በኪታቡ ሰነድ ላይ ዝርዝር የፈለገ በአምስት ክፍል ከቀረበው የ0ብደላህ አልበራክ توثيق أسانيد كتب العقيدة الإسلامية ጥናት ሶስተኛውን ይመልከት።
#ማምታቻ_ሁለት፡ "ኪታቡን በስም በመጥቀስ ቀዳሚዉ በ597 ሂ ያረፉት እብንል ጀዉዚ ናቸዉ" ብሏል።
መልስ፦ ይሄ ነጭ ውሸት ነው። ከሳቸው በፊት፡
1- አልኸጢብ (463 ሂ. የሞቱ) በታሪኹ በግዳድ፣
2- አቡ መንሱር መዕመር ብኑ አሕመድ አልአስበሃኒይ (514 ሂ.) [አልሑጃህ ፊ በያኒል መሐጀህ፡ 1/ 258] እና
3- ቀውዋሙ ሱንና አቡል ቃሲም አልአስበሃኒይ (535 ሂ.) [አልሑጃህ፡ 2/532]
ኪታቡን በግልፅ በስም ጠቅሰውት እናገኛለን።
#ማምታቻ_ሶስት፡ {ኪታቡን በስም ባይጠቅሱም በመጽሀፉ ዉስጥ የተካተቱ ጥቂት ዘገባዎችን በመጽሀፋቸዉ ዉስጥ በማካተት በኩል በዘመን ቀዳሚዉ በ418 ዓ.ሂ አካባቢ ያረፉት ላሊካኢ ናቸዉ} ብሏል።
መልስ፦
ይህም ግልፅ ቅጥፈት ነው።
1- ኢብኑ መንደህ (310 ሂ.) በሶስት ኪታቦቻቸው (ረድ 0ለል ጀህሚያ፣ አልኢማን፣ አተውሒድ]፣
2- ኸላል (311 ሂ.) [በአስሱና ኪታባቸው በጣም ብዙ ቦታ ላይ]
3- አሕመድ ብኑ ሰልማን አነጃድ (348 ሂ.) [አረድ ዐላ መን የቁል አል ቁርኣን መኽሉቕ]
4- ኣጁሪይ (360 ሂ.) [አሽሸሪዐህ]
5- አቡ ሸይኽ (369 ሂ.) [አልሑጃህ ፊ በያኒል መሐጀህ፡ 2/532]
6- ዳረቁጥኒይ (385 ሂ.) [አርሩእያ፡ 282፣ 283፣ 284]
7- ኢብኑ ሻሂን (385 ሂ.) [አልኪታቡ ለጢፍ፡ 30፣ 31]
8- ኢብኑ በጧህ (387 ሂ.) [አልኢባናህ፡ 146፣ 412፣ 414፣ 484]
እነዚህ ሁሉም የኪታቡን ዘገባዎች በኪታቦቻቸው ውስጥ ያሰፈሩ ከላለካኢይ በፊት ያለፉ ዑለማኦች ናቸው።
#ማምታቻ_አራት፡ "መጽሀፉ በዑለሞች ውድቅ የተደረገ ነው" ብሏል።
የሱው ብጤ የቅርብ ጊዜ ወናፎችን ሊጠቅስ ካልሆነ በስተቀር ይሄ ከእውነት የራቀ ሙግት ነው። እንዲያውም ይሄ ኪታብ በስም ጠቅሶ ያስተባበለ እስከ ቅርብ ዘመን አንድም አልነበረም። ይልቁንም እሱ ከሚለው በተቃራኒ ኪታቡ የ0ብደላህ ብነ አሕመድ እንደሆነ የጠቆሙ/ የመሰከሩ 11 ዑለማኦችን አሳልፌያለሁ። ልጨምር፦
1- ላለካኢይ (418 ሂ.) [ሸርሑ ኡሱሊ አህሊ ሱናህ፡ ብዙ ቦታ]
2- ሲጅዚይ (444 ሂ.) [አረድ ዐላ መን አንከረል ሐርፍ ወስሶውት፡ 166፣ 169]]
3- አቡ የዕላ (458 ሂ.) [ኢብጧሉ ተእዊላት፡ 348]
4- በይሀቂይ (458 ሂ.) [አልአስማእ፡ 319]
5- ኢብኑል በንና (471 ሂ.) [አልሙኽታር፡ ብዙ ቦታ]
በጠቅላላ 16!! ልብ በሉ! ሐሰን ታጁ ዘንድ አስሱናህ ኪታብ ማለት አቡ ኢስማዒል አልሀረዊይ የጣዖት 0ቂዳቸውን ለማፅናት በኢማም 0ብደላህ ስም ሆነ ብለው ፈጥረው ያዘጋጁት ኪታብ እንደሆነ የሚገመት ነው። አቡ ኢስማዒል አልሀረዊይ የሞቱት በ481 እንደሆነ ያዙ። እነዚህ የዘረዘርኳቸው 16 ዓሊሞች "አስሱናህ" ኪታብ የ0ብደላህ ብነ ኢማም አሕመድ እንደሆነ ያረጋገጡ ሲሆኑ ሁሉም፣ እደግመዋለሁ ሁሉም ከአቡ ኢስማዒል አልሀረዊይ በፊት የሞቱ ናቸው። ይሄ ሬሳ አምላኪ እነዚህን ሁሉ ከተራራ የከበዱ ዑለማኦችን ነው የጣዖታዊ ዐቂዳ ተከታይ ያደረጋቸው። በነገራችን ላይ አቡ ኢስማዒል አልሀረዊይ ጣዖት አምላኪ ሊሆኑ ቀርቶ በዘገባ ታማኝነታቸው ላይ የሚታሙ አይደሉም። ዑለማኦች፣ "ኢማም"፣ "ሸይኹል ኢስላም" እያሉ አወድሰዋቸዋል። ይሄ ዋልጌ ግን ለጣዖት አምልኮ የቅጥፈት ኪታብ የሚያዘጋጅ እያላቸው ነው። የሸይኹ ትልቁ "ጥፋት" ሐሰን ታጁ በሚያራምደው የ "አሽ0ሪያ"/ የአሕባሽ መዝሀብ ላይ የተሰላ ሰይፍ ነበሩ።
በተጨማሪም፡
1- ኢብኑ አቢ የዕላ (526 ሂ.) [ጦበቃቱል ሐናቢላ፡ 1/185]
2- ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ.) [አልዒለሉል ሙተናሂያ፡ 1/41]
3- ኢብኑ ቁዳማ (600 ሂ.) በሶስት ኪታቦቻቸው
4- ኢብኑ ተይሚያ (728 ሂ.) [5/387]፣ [ደርእ፡ 1/69፣ 7/108]
5- አዘሀቢይ (748 ሂ.) [አልዐርሽ፡ 162] [አልዑሉው፡ 1/346]፣ [ታሪኹል ኢስላም፡ 5/1028]፣ [አሲየር፡ 8/10፣ 13/523]
6- ኢብኑል ቀዪም (751 ሂ.) [አልጁዩሽ፡ 91] [ዛዱል መዓድ፡ 3/592]
7- ኢብኑ ከሢር (774 ሂ.) [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 16/168]
8- ኢብኑ ረጀብ (795 ሂ.) [አተኽዊፍ ሚነናር፡ 249]
9- ኢብኑ ሐጀር (852 ሂ.) [ፈትሑል ባሪ፡ 13/381]
ሱረቱ ከ አል-ፊል እስከ አል-መሰድ ትርጉም
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
ሱረቱ_ከ_አል_ፊል_እስከ_አል_መሰድ_ትርጉም.mp321.74 MB
የወንድማችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጉዳይን በተመለከተ ።
ጉዳዩ ከጀርባ ዲስክ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ትንሽ ትእግስትን የሚፈልግ ነው ። በሽታው በባህሪው እረፍትን የሚፈልግ እና ባስ ሻል እያለ የሚመላለስ ነው ። በተጨማሪ ጉዳዩ ከኛ አስተያየት ይልቅ የልዩ ባለሞያዎችን ቁርጠኛ ውሳኔ የሚፈልግ ነውና ይህ እስኪገኝ ድረስ መታገሱ እና አለመቸኮሉ የሚመከር ነው ። በቅርብ ያሉ ወንድሞችም ዝምታቸው ከዚህ የመነጨ እንጂ ከቸከልተኝነት አይደለም ።በየግዜውም በጉዳዩ ላይ ከራሱ ጋር እያወራን እና እየመከርን ነው ….
የሐኪም ቁርጠኛ ውሳኔ በተገኘ ግዜ ማድረግ ያለብንን ከማድረግ ወደሇላ አንልም - በአሏህ ፈቃድ !!
በአሏህ ፈቃድ በቅርቡ ውሳኒያቸውን እንሰማለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን ።
በተረፈ እንደ መፍትሄ የሚታሰቡ ሰርጀሪ እና የመሳሰሉ ነገሮችን ባንቸኩልባቸውና አሁንም ለባለሞያ ብንተዋቸው ጥሩ ነው ።
እስከዛው በዱዓ !!
https://t.me/msirage4
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
1- ኢብኑ ተይሚያ ይህንን ኪታብ አስመልክተው በተናገሩበት እንዲህ ብለዋል፦
"وقد ذكره الخلال في كتاب السنة والقاضي أبو يعلي و أبو الفضل التميمي و أبو الوفاء بن عقيل وغير واحد من أصحاب أحمد ولم ينفه أحد منهم عنه"
"በርግጥም አልኸላል በ'ኪታቡ ሱናህ' ውስጥ፣ ቃዲ አቡ የዕላ፣ አቡል-ፈድል አት-ተሚሚይ፣ አቡል-ወፋእ ኢብኑ ዐቂል እና ሌሎች በርካታ የአሕመድ ባልደረቦች የጠቀሱት ሲሆን፣ ከነሱ ውስጥ ማንም የሳቸው መሆኑን አላስተባበለም።" [ደርኡ ተዓሩዲል ዐቅል፡ 1/121]
2- ኢብኑል ቀዪምም እንዲሁ ለዘሀቢ ጥርጣሬ ምላሽ በሚመስል መልኩ እንዲህ ብለዋል፦
"ولم يسمع عن أحد من متقدمي أصحابه ولا متأخريهم طعن فيه"
"ከቀደምቶቹም ይሁን ከኋለኞቹ የአሕመድ ባልደረቦች ውስጥ ከአንድ እንኳ በሱ (በኪታቡ) ላይ ማንቋሸሽ አልተሰማም።" [አልጁዩሽ፡ 130]
3- አሰፋሪኒይ ይህንን የኢማሙ አሕመድ ኪታብ የመዝሀቡ ታላላቅ አኢማዎች ጠቅሰውታል ብለዋል። [ለዋሚዑል አንዋር፡ 1/66-67]
ኪታቡ ላይ ከሰነድ አንፃር ከውሠሪ የተባለ ሁለ ነገሩ የከረፋ ጀህ ^ሚይ ያነሳው ማምታቻ አለ። ይሄ የቆርጦ ቅጠላው አምባሳደር ስላላነሳው ለጊዜው አላነሳውም። በቀጣይ አላህ ከፈቀደ የ0ብደላህ ብን ኢማም አሕመድን "አስሱናህ" ኪታብ የቅጥ ^ፈት ስራ ነው ብሎ በቸከቸከበት ላይ ልመለስ እችላለሁ፣ ምናልባት ከቻልኩኝ ። ሌሊቱን ከህመሜ ጋር እየታገልኩ ነው ይህንንም የፃፍኩት።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 23/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
