127 753
المشتركون
-1624 ساعات
-287 أيام
-65030 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU
75ኛ የምስረታ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡
ዩኒቨርሲቲው 75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን በተያዘው ህዳር እና ታህሳስ ወር በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚያከብር መግለፁ ይታወቃል።
የበዓሉ አካል የሆነ የባለድርሻ አካላት ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲዎች የእግር ኳስ ውድድር ይጀመራል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ75 ዓመታት ጉዞ የተሰነደበት መፅሐፍ ይመረቃል፡፡ የተቋሙን አጠቃላይ ጉዞ እና የወደፊት ርዕይ የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጅ መሆኑም ተጠቁሟል። የፓናል ውይይቶች፣ ሴሚናሮች፣ የእግር ጉዞ እና ሌሎች በርካታ ኹነቶች እንደሚካሔዱ ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 18-24/2018 ዓ.ም ለሚከበረው የቀድሞ ተማሪዎች ሳምንት (Alumni Week) በመላው ዓለም ለሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን በ https://alumni.aau.edu.et/register ድረ-ገፅ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
ያመልክቱ!
ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ስልጠናው በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀን መርሐግብር የሚወስዱ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።
የምዝገባ ጊዜ፦
ከህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት
ኦንላይን የመመዝገቢያ ሊንኮች፦
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/Y7Hksp5Ymk7Nx7d9A
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfQcnu1ThOSSsUp9d3XI80NszyyETOwtJPxWNRh68izA7Gd2A/viewform?usp=header
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DebarkUniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡
ለህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን ጥሪ ያራዘመው ዩኒቨርሲቲው፤ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 16 እና 17/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡
ትምህርት ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#InjibaraUniversity
በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) በትምህርት ሚኒስቴር ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 09-10/2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#BahirDarUniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ የኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡
ራስ ገዝ እንዲሆኑ በመንግሥት ከተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እና ሌሎች ተግባራትን በማካተት የደረሰበትን ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት አሰራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DebreBerhanUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦ በተመደባችሁበት ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ሁለት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DebreMarkosUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-L የሚጀምር እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-B የሚጀምር በቡሬ ካምፓስ፤ ሌሎች የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ10ኛ ክፍል እና የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቃችሀብት ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት መረጃን በተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት (HEMIS) እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡
በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ህዳር 16/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፥ ሁሉም ተቋማት መረጃቸውን በተዘጋጀው ሲስተም ላይ የማስገባት ግዴታ እንዳለባቸው ይገልጻል።
በመሆኑም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ሁሉም መረጃዎች ተሟልተውና በየተቋሙ አመራር ተረጋግጠው እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሲስተሙ (http://hemis.ethernet.edu.et) እንዲያስገቡ ጠይቋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ይህን ተከታትሎ የማስፈፀም ኃላፊነት እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን፤ መረጃውን የማያስገቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግሥት በሚሰጡ አገልግሎቶች እንደማይስተናገዱ ተጠቁሟል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#WerabeUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ከህዳር 21 እስከ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ድረስ registrar.wru.edu.et የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የተጠየቁ መረጃዎችን እንድትሞሉ ይጠበቅባችኋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡
ስልጠናው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡
የምዝገባ መስፈርት፦
በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች እና ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት መስኮች በመምህርነት ሙያ መሰልጠን የሚፈልጉ
የምዝገባ ጊዜ
ከዛሬ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት
የምዝገባ ቦታ
ከስር በተገለፁ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን ዝርዝር ለማግኘት https://shorturl.at/N8e0s ላይ በመግባት “አማራጭ የመምህራን ስልጠና ትምህርት አይነቶች” የሚለውን በማውረድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዩኒቨርሲቲ መመዝገቢያ ሊንኮች፦
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/JZG12devyUvDe3v6
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/.../1FAIpQLSfQcnu1ThO.../viewform...
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9
የስልጠና ፕሮግራሙ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ በቀን መርሐግብር የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#UniversityOfGondar
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
የምዝገባ ቦታ፦
የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ በአጼ ፋሲል ግቢ ይከናወናል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#SamaraUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#WoldiaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ የቅርብ ጊዜ አራት ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ የማበልፀጊያ ማዕከላት ጥምረት (Ethiopian University Incubation Center Alliance - EUICA) ተመስርቷል።
የዩኒቨርሲቲዎች የማበፀጊያ ማዕከላት በግብርና፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጤና፣ በቱሪዝም፣ በአየር ንብረት እና በሌሎችም የፈጠራ ሥራዎች አበርክቷቸውን ለማሳደግ የጥምረቱ መመስረት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#TVTI
ለ2018 የትምህርት ዘመን በደረጃ VII (የሁለተኛ ዲግሪ) እና በደረጃ VI (የመጀመሪያ ዲግሪ) ትምህርት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንድትሰለጥኑ በክልሎች ተመልምላችሁ ስም ዝርዝራችሁ የተላከ ሰልጣኞች ምዝገባ ከህዳር 15-17/2018 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
#1Days
1 ቀን ቀረዉ 🏃♂🏃♂
የ ተለያዩ ድርጅቶችን ኔትዎርክ ሰብራችሁ ምትገቡበት የ RED TEAMING ስልጠና ምዝገባ ጥቂት ሰዓታት ቀሩት
በ ኢትዮጵያ 🇪🇹 የመጀመርያ የሆነዉን እድል ከማለፉ በፊት ተጠቀሙበት❤️
➡️አሁኑኑ ይመዝገቡ: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt
ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com
#GTCRT @geeztechgroup
