TIKVAH-SPORT
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469
إظهار المزيد272 336
المشتركون
-1924 ساعات
+3617 أيام
+1 50830 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
NUR TECHNOLOGIES
አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ የሆኑ ላፕቶፓች
☑️HP
☑️Lenovo
☑️Dell
☑️Microsoft Surface
☑️MacBook
☑️Gaming Laptops
☑️Iphone & Samsung Phones
☑️Tablets
በተመጣጣኝ ዋጋ ከሙሉ ዋስትና ጋር እናቀርባለን።
ለበለጠ መረጃ ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
Join Our Telegram Channel for more Information
📱📱📱📱📱📱📱📱📱📱
https://t.me/NurTechnologies
📞0911646359
አድራሻ - ቦሌ መድኃኒለም ሰላም ሲቲ ሞል ፊት ለፊት ለአሚር ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
❤ 36
Photo unavailableShow in Telegram
ቀጣዩ የማድሪድ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?
ስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ትላንት ካስመዘገቡት ድል በኋላ ለአሁኑ ከሀላፊነታቸው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ቀጣዩ የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ለአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተነግሯል።
አሰልጣኙ በእይታ ውስጥ መሆናቸው ሲገለፅ ቆይታቸው በቀጣይ ሳምንታት እና ቀጣይ ውጤት ይወሰናል።
አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚሰናበቱ ከሆነ ቀጣዩ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ የሚሆኑት የወጣት ቡድኑ አሰልጣኝ አልቫሮ አርቤሎኣ እንደሆኑ ተገልጿል።
ሪያል ማድሪድ ከአሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን አና የርገን ክሎፕ ይልቅ አሰልጣኝ አልቫሮ አርቤሎኣን ይመርጣል ተብሏል።
የዘገባው ባለቤት ፋብሪዝዮ ሮማኖ ነው።
❤ 157😁 32👎 13👍 7🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቪንሴንት ኮምፓኒ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተባሉ !
የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ የቤልጅየም የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማት " Raymond Goethals Trophy " ማሸነፍ ችለዋል።
የአሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ወላጅ አባት የልጃቸውን የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማት ተቀብለዋል።
አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በሰጡት አስተያየት “ ትልቅ ክብር ነው ይህ ሽልማት ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው “ ሲሉ ተናግረዋል።
❤ 206👏 43👍 16👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
“ ዳኞች የማድሪድ ስጋት ናቸው “ ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ
የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ስፔን ውስጥ ያለውን ዳኝነት ለክለባቸው “ ስጋት “ ሲሉ ገልፀውታል።
“ የሪያል ማድሪድ ትልቁ ስጋት ስፔን ውስጥ ያለው የዳኝነት ሁኔታ ነው “ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ስለ ትላንቱ ጨዋታ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ " ባለፈው አመት ሪያል ማድሪድ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲሉ ያስፈራሩ ዳኛ ናቸው የመሩት “ብለዋል።
አክለውም “ በአለም እግርኳስ ታሪክ ትልቁ ቅሌት የሆነውን የኔጌሬራ ኬዝ እንዴት መርሳት እንችላለን “ ሲሉ ተጨማሪ ሀሳብ አንስተዋል።
“ በዚህ የዳኝነት ቅሌት እኛ ብቻ ሳንሆን ብዙ ክለቦች እንደተጎዱ እርግጠኞች ነን ፤ በዚህ ተጎድተው የወረዱም አሉ “ ሲሉ ጉዳዩ ሌሎች ክለቦችንም እንደሚመለከት ጠቁመዋል።
😁 199❤ 139👍 19👎 10🤩 5
Photo unavailableShow in Telegram
ፍሬንች ሞንታና ሞሮኮ ደርሷል !
በሞሮኮ ካዛብላንካ የተወለደው አሜሪካዊ ራፐር ፍሬንች ሞንታና ለአፍሪካ ዋንጫው ወደ ትውልድ ሀገሩ ሞሮኮ አምርቷል።
አሜሪካዊ የሂፕ ሀፕ አቀንቃኝ ፍሬንች ሞንታና ከሞሮኳዊው አርቲስት ሬድዋን ጋር ተጣምሮ የአፍሪካ ዋንጫውን አዲስ ዜማ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅነት ያለው ፍሬንች ሞንታና የአፍሪካ ዋንጫው አካል መሆኑ ውድድሩ አለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ ተጨማሪ እድል ይፈጥራል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 182👎 48👏 12👍 7😁 5
Photo unavailableShow in Telegram
ቲያጎ ሲልቫ ወደ አውሮፓ ሊመለስ ነው !
ብራዚላዊው የኋላ መስመር ተሰላፊ ቲያጎ ሲልቫ ከፍሉሚኔንስ ጋር ለመለያየት መወሰኑ ተገልጿል።
ተጨዋቹ የቡድን አጋሮቹን መሰናበቱ ሲገለፅ በቀጣይ ቀናት ወደ አውሮፓ በመመለስ የአውሮፓ ክለብ ሊቀላቀል መሆኑ ተነግሯል።
ተጨዋቹ እስከ አለም ዋንጫው እየተጫወተ ለመቆየት የአውሮፓ ሊግ ክለብ ለመቀላቀል እንደፈለገ ተዘግቧል።
የ 41ዓመቱ ቲያጎ ሲልቫ በቀጣይ አላማው በ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር ብራዚልን መወከል መሆኑ ተገልጿል።
🔥 171❤ 100👍 32😁 12👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
ሩበን አሞሪም አጨዋወታቸውን ሊቀይሩ ነው !
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የማንችስተር ዩናይትድን የአጨዋወት ዘይቤ ለመቀየር በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
አሰልጣኙ የአማድ ዲያሎ እና ብሪያን ምቤሞን አለመኖር ተከትሎ አጨዋወታቸውን ወደ 4-3-3 ለመቀየር መዘጋጀታቸው ተነግሯል።
ሩበን አሞሪም ባለፈው ሳምንት ከዎልቭስ ጨዋታ በፊት ለተጨዋቾቹ አጨዋወታችን እንቀይራለን በማለት ማሳወቃቸው ነው የተገለጸው።
ባለፈው ሳምንት ቡድኑ የ 4-3-3 አጨዋወት ላይ በትኩረት ሲዘጋጅ እንደነበር ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ከዛሬው የበርንማውዝ ጨዋታ በፊት የነበረው አብዛኛው የቡድኑ ዝግጅትም አራት ተከላካዮች ላይ መሰረት ያደረገ ታክቲካል አሰላለፍ ላይ እንደነበር ተጠቁሟል።
❤ 399😁 155👍 44🙏 9👏 4🔥 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያቀኑ ነው !
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ቃዲሲያ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስን በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።
አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስን ከወራት በፊት ከሴልቲክ ሀላፊነት ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ ያለ ስራ ይገኛሉ።
የቀድሞ የሊቨርፑል እና ሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ አል ቃዲሲያን ለመረከብ ወደ ሳውዲ አረቢያ አቅንተዋል።
አል ቃዲሲያ በሳውዲ አረቢያ ሊግ 1️⃣7️⃣ ነጥቦችን በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
❤ 127👍 11😁 10
Photo unavailableShow in Telegram
ካርሎ አንቾሎቲ ውላቸውን ሊያራዝሙ ነው !
የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በብሔራዊ ቡድኑ ያላቸውን ኮንትራት ለማራዘም መቃረባቸው ተገልጿል።
አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በብሔራዊ ቡድኑ እስከ 2030 ለመቆየት ውላቸውን እንደሚያራዝሙ ተነግሯል።
የ 66ዓመቱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ባለፈው ግንቦት ወር የብራዚል ብሔራዊ ቡድንን እስከ 2026 አለም ዋንጫ መጨረሻ መረከባቸው ይታወሳል።
❤ 155👏 16😁 4🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ ዋንጫው ምን አዲስ ነገር እንመለከታለን ?
ሞሮኮ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የስፖርት ቀጥታ ስርጭት ስርዓት ትሞክራለች።
የአፍሪካ ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ " 4K HDR " ከፍተኛ ጥራት ባለው ምስል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።
የቀጥታ ስርጭቱ ከተለያዩ ማዕዘኖች የሚቀርፁ በራሪ ካሜራ እና ድሮኖችን እንደሚያካትት ተነግሯል።
የውድድሩ ስርጭት ከአለም ዋንጫ ጋር የሚቀራረብ ፕሮዳክሽን እንደሚኖረው ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
👍 435❤ 128👏 60🔥 9😁 3
በሞሮኮ ያለው የአየር ሁኔታ ምን ይመስላል ?
የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከቀናት በኋላ በሞሮኮ መካሄድ ይጀመራል።
በውድድሩ የሚካፈሉ ብሔራዊ ቡድኖች በተዘጋጀላቸው ማረፊያ መቀመጫቸውን በማድረግ ዝግጅት ጀምረዋል።
በሞሮኮ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ ዝናብ ፤ ጎርፍ እና ነጎድጓድ እንደሚስተዋል ተገልጿል።
በምዕራብ ሞሮኮ በምትገኘው የባሕር ዳርቻ ከተማ ሳፊ በድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ምክንያት 22 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።
በአፍሪካ ዋንጫው ወቅትም በሞርኮ ቀዝቃዛማ የአየር ንብረት እንደሚኖር ይጠበቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 168🙏 32😢 18🔥 4🤔 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
“ የሚተቹን ተጨዋቾች እነሱ ሲለቁ የነበረው ቡድን ያለ ይመስላቸዋል “ ሩበን አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የክለቡ የቀድሞ ተጨዋቾች ስለ ክለቡ በቂ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል።
በቀድሞ ተጨዋቾች ስለደረሰባቸው ትችት የተጠየቁት አሰልጣኙ “ ስለ ክለቡ ሙሉ መረጃ የላቸውም “ ሲሉ መልሰዋል።
“ ተጨዋቾቹ የሚያዩት እነሱ ሲለቁ የነበረውን ሁልጊዜ የሚያሸንፈውን ቡድን ነው ፤ አሁን በክለቡ ነገሮች አስቸጋሪ ናቸው “ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
ስለ ኮቢ ማይኖ የተጠየቁት አሞሪም “ የምንጫወተው በሁለት አማካይ ነው በእሱ ቦታ ያለው ፈርናንዴዝ ነው እሱን ከአሰላለፍ ማውጣት አንችልም “ብለዋል።
“ አሁን ያለብን ችግር ኮቢ ማይኖ ተጠባባቂ መሆኑ ሳይሆን ጨዋታዎች አለማሸነፋችን ነው “ ሩበን አሞሪም
❤ 356😁 128👍 29👎 19👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሎስ ብላንኮዎቹ ወደ ድል ተመልሰዋል !
ሪያል ማድሪድ ከዲፖርቲቮ አላቬስ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ እና ሮድሪጎ ሲያስቆጥሩ የዲፖርቲቮ አላቬስን ጎል ቪሴንቴ ከመረብ አሳርፏል።
የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተሰላፊ ኪሊያን ምባፔ በሊጉ 1️⃣7️⃣ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።
ሮድሪጎ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ ሪያል ማድሪድ :- 39 ነጥብ
1️⃣2️⃣ ዲፖርቲቮ አላቬስ:- 18 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዳሜ - ሪያል ማድሪድ ከ ሲቪያ
ቅዳሜ - ኦሳሱና ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 275👎 23👍 19🙏 13🥰 5🤬 4🔥 3😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
ጁቬንቱስ ድል አድርጓል !
ጁቬንቱስ ከቦሎኛ ጋር ያደረገውን የጣሊያን ሴርያ መርሐ ግብር 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የጁቬንቱስን የማሸነፊያ ግብ ሁዋን ካባል ከመረብ አሳርፏል።
ጁቬንቱስ ካለፉት አስራ አንድ ጨዋታዎች በአንዱ ጨዋታ ነው የተሸነፈው።
ኬናን ይልዲዝ በውድድር አመቱ ሰባተኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
5️⃣ ጁቬንቱስ :- 26 ነጥብ
6️⃣ ቦሎኛ :- 25 ነጥብ
በቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዳሜ - ጁቬንቱስ ከ ሮማ
እሁድ - ቦሎኛ ከ ሳሱሎ ( ከሁለት ሳምንት በኋላ )
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 114🙏 5👍 4🔥 2🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
“ ጆታን ለዘለዓለም አስታውሰዋለሁ “ ሄንደርሰን
እንግሊዛዊው ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን ብሬንትፎርድ ከሊድስ አቻ ሲለያይ ለክለቡ የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል።
ጆርዳን ሄንደርሰን ግቡን ካስቆጠረ በኋላ የዲያጎ ጆታን ደስታ አገላለጽ ተጠቅሞ ነበር ደስታውን የገለፀው።
ከጨዋታው በኋላ ቃሉን የሰጠው ሄንደርሰን “ ከጥቂት ቀናት በፊት ልደቱ ነበር ፤ እሱ ምርጥ ጓደኛ ነው ሁልጊዜም አስታውሰዋለሁ “ ሲል ተደምጧል።
አክሎም “ ከጆታ መሞት በኋላ የሊቨርፑል ተጨዋቾች በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉ መገመት አልችልም “ ብሏል።
❤ 482😢 105👏 16👍 12🔥 7🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢንተር ሚላን የሴርያው መሪ ሆነዋል !
ኢንተር ሚላን ከጂኖኣ ጋር ያደረገውን የጣልያን ሴርያ መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ላውታሮ ማርቲኖዝ እና ቢሴክ ሲያስቆጥሩ ለጂኖኣ ቪቲንሀ ከመረብ አሳርፏል።
ኢንተር ሚላን ማሸነፉን ተከትሎ የሴርያውን መሪነት ተረክበዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ኢንተር ሚላን :- 33 ነጥብ
1️⃣6️⃣ ጂኖኣ :- 14 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
እሁድ - አታላንታ ከ ኢንተር ሚላን
እሁድ - ጂኖኣ ከ አታላንታ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 113🤔 37👍 17🔥 5
Photo unavailableShow in Telegram
ባየር ሙኒክ ነጥብ ጥሏል !
በጀርመን ቡንደስሊጋ የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ከሜንዝ ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
የባየር ሙኒክን ግቦች ሌናርት ካርል እና ሀሪ ኬን ሲያስቆጥሩ ለሜንዝ ፖቱልስኪ እና ሊ ከመረብ አሳርፈዋል።
ባየር ሙኒክ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ሁለተኛ ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል።
እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ሀሪ ኬን በውድድር ዘመኑ 1️⃣8️⃣ኛ የሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ባየር ሙኒክ :- 38 ነጥብ
1️⃣8️⃣ ሜንዝ :- 7 ነጥብ
እሁድ - ሄደንሄም ከ ባየር ሙኒክ
እሁድ - ሜንዝ ከ ሴንት ፓውሊ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 151👎 20👍 15😁 14👏 7🔥 5🥰 4😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
ዩናይትድ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት ያገኝ ይሆን ?
ማንችስተር ዩናይትድ ወሳኝ ተጨዋቾቹ ብሪያን ምቤሞ ፣ አማድ ዲያሎ እና ናስር ማዝራዊን ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ይልካል።
ፊፋ ክለቦች ተጨዋቾቹን ለአፍሪካ ዋንጫው በነገው ዕለት የመልቀቅ ግዴታ እንዳለባቸው አሳውቋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በነገው ዕለት ከበርንማውዝ ጋር የሚጫወት ሲሆን ተጨዋቾቹ መሳተፋቸው እስካሁን አልተረጋገጠም።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከቀናት በፊት የተጫዋቾቹን በጨዋታው መሳተፍ እስካሁን አላወቅኩም ነበር ያሉት።
ሌሎች ክለቦች ነገ ያጫውታሉ ?
የስፔኑ ክለብ ሪያል ቤቲስ ጨዋታውን የሚያደረገው በተመሳሳይ በነገው ዕለት ሲሆን አፍሪካውያን ተጨዋቾችን ልኳል።
በቡድኑ ያሉት ሞሮኳዊ ተጨዋቾች ሶፍያን አምራባት እና ኢዛልዙሊ በነገው ዕለት ለክለባቸው ግልጋሎት አይሰጡም።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
❤ 199😢 48😁 38👍 21👎 3🙏 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዳን በርን ወደ ሆስፒታል ተወስዷል !
የኒውካስል ዩናይትዱ ተከላካይ ዳን በርን በዛሬው የሰንደርላንድ ጨዋታ በጎን አጥንቱ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ነበር።
ተጨዋቹ በጉዳቱ ምክንያት በመጀመሪያው አጋማሽ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል።
ዳን በርን በጉዳቱ ምክንያት ለመተንፈስ መቸገሩን ተከትሎ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተነግሯል።
ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የኒውካስል አሰልጣኝ ኤዲ ሀው “ በርን ወደ ሆስፒታል ተወስዷል ደህና እንደሚሆን ሙሉ ተስፋ አለን “ ብለዋል።
❤ 207😢 122🙏 31👍 13😱 8
Photo unavailableShow in Telegram
“ በምርጥ ብቃታችን ላይ አይደለንም “ ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ የክሪስታል ፓላስን ሜዳ “ እጅግ አስቸጋሪ ቦታ “ ሲሉ ገልፀውታል።
“ በጣም አስቸጋሪ ቦታ ነው “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ “ ኳስ ካጣህ በአስገራሚ ሁኔታ ያጠቁሀል ነገርግን እኛ ታጋሽ ነበርን “ ብለዋል።
ስለ ቡድናቸው ወቅታዊ ቁመና የተነሳላቸው አሰልጣኙ “ “ አሁንም ገና በምርጥ ብቃታችን ላይ አንገኝም “ ሲሉ ገልጸዋል።
“ ፊል ፎደን ዛሬ ጥሩ አልተጫወተም ብዙ ኳሱችን አሳጥቷል በእያንዳንዱ ንኪኪ ሲቸኩል ነበር “ ፔፕ ጋርዲዮላ
❤ 376😁 194🔥 20👎 19🙏 7👏 5👍 3😱 2
