ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
الذهاب إلى القناة على Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
إظهار المزيد166 291
المشتركون
-1624 ساعات
-397 أيام
+20730 أيام
أرشيف المشاركات
ግሩም ድንቅ ነህ
ግሩም ድንቅ ነህ አምላኬ ግሩም ድንቅ ነህ
ግሩም ድንቅ ነህ ጌታዬ ግሩም ድንቅ ነህ
ሰው የጣለውን ከምድር ከፍ ታደርጋለህ
የተረሳውን አምላኬ ታስታውሳለህ
አዝከቤተ ሳይዳ ያነሳል ባልጋ ያለውን መጠመቅ ሽቶ እረዳት ወገን ያጣውን ካጢያተኛው ቤት ይገባል እራት ሊበላ በቀል አያውቅም ጌታዬ ከፍቅር ሌላ እንዳምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንዳማኑኤል ማንም የለም /2/
አዝየበደለውን አይንቅም ያነሳል በእጁ ፍፁም ይራራል በእውነት ጌታ ለልጁ ከሳምራዊው ጋር ይውላል እንደ ጉዋደኛ ሁሉን በፍቅር የሚያስብ ታማኝ እረኛ እንዳምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንደ አማኑኤል ማንም የለም /2/
አዝሰው የናቀውን አንስቶ ሾሞ ያከብራል ዘይት አፍሶ ባርያውን በእጁ ይቀባል አክሊል ይደፋል አንስቶ ላጎነበሰው ክብርና ጋሻ መከታ ዝናር ሊሆነው እንደ አምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንደ አማኑኤል ማንም የለም /2/
አዝያዘነውን ሰው ያፅናናል ፍቅር እየዘራ ያነሳለታል የጭንቁን ግዙፍ ተራራ ደግሞ አይኖርም በቤቱ የእስር ቀንበር እርሱን ተማምኖ የቆመ ከመቅደሱ ስር እንደ አምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንደ አማኑኤል ማንም የለም /2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ግሩም_ድንቅ_ነህ_ዘማሪ_ዳግማዊ_ደርቤ_2018_የአእላፍት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ.m4a5.86 MB
❤ 198🥰 7🕊 4🔥 2
ታህሣሥ 1 /፩/በዚችም ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዮሐንስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ ነው። ይህም የከበረ ቀሲስ የሆነ የገምኑዲ አገር ሰው ነው በዘመኑም የቅዱሳን ሰማዕታት የሰርጊስና የባኮስ ቤተ ክርስቲያናቸው ተሠራች ዳግመኛም የአቡቂርና የዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በምስር መሰብሰቢያ ቅጽር አጠገብ ተሠራች ያነፃቸውም ስሙ እንድርያስ የሚባል እግዚአብሔርን የሚፈራ ያዕቆባዊ አንድ የግብጽ ሰው ነው። እርሱም ለመርዋን ልጅ ለገዢው ለንጉሥ አብደል ጸሐፊው ነው። ይህም አባ ዮሐንስ የወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን በእስክንድርያ አገር በታወቀ ቃምስ በሚባል ቦታ የሠራ ነው። በዚህ በንጉሥ አብደል ዘመንም ሦስት ዓመት ያህል ጽኑ ረኃብ ሆነ ይህም አባት ለድኆች ለጦም አዳሪዎችና ለችግረኞች የሚያስብ ሆነ በየሳምንቱም አራት ጊዜ ወርቅና ብር እንጀራም ይሰጣቸዋል አብዝቶ የሚራራ መመጽወትን የሚወድ በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ነውና። በዘመኑም ንጉሥ ይዜድ ሙቶ በርሱ ፈንታ መርዋን ነገሠ ይህም አባት በማርቆስ ወንበር ዘጠኝ ዓመት ኖረ በሰላምም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 183🕊 11
ወትቤሎ
ወትቤሎ ይኩነኒ/2/
በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ
በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ/2/
የአእላፋት ዝማሬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ወትቤሎ_ይኵነኒ_2018_የአእላፍት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.m4a1.67 MB
❤ 71🥰 6🕊 3
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
አለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ
አዝኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ሥሉስ ያሉህ መላዕክት በራማ የሚያመሰኑህ ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና ትንቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/2/
አዝቅዱሱን መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ ምን ይዤ ልምጣና በአምላኬ ፊት ልስገድ ወደ ላይ በሰማይ ወደ ታች በጥልቀት አምላኬ የት አለ የማትገኝበት ጌታ ሆይ የት አለ የማትገኝበት
አዝበኪዳን በፀሎት ቅዳሴ ሰዓታት አንተ የሰጠኸኝ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምን አለ ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው(2)
አዝሀብትና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው ጤናዬ የሰጠኝ ከአንተ በቀር ማነው በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በምን_ደስ_ላሰኝህ_ዘማሪ_ዳግማዊ_ደርቤ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር.m4a4.34 MB
❤ 246🕊 12🥰 7🔥 4
ሕዳር 30/፴/አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሠላሳ በዚች ቀን የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አካክዮስ አረፈ ። ይህም ቅዱስ ቸር የሆነ ምሁር ነው አምላክ ያጻፋቸውንም መጻሕፍት ቃላቸውን አሳምሮ የሚተረጉም አዋቂ ነው በቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያንም ቅስና ተሹሞ ነበር ። በኬልቄዶንም ስብሰባ በሆነ ጊዜ ይህ አባት በጉባኤው ውስጥ በሆነው ሁሉ ደስ አላለውም ስለ እውቀቱም እንዲመጣ በፈለጉት ጊዜ እርሱ አሞኛል ብሎ ስለራሱ ምክንያት ሰጠ ። የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት እንጣልዮስም በአረፈ ጊዜ በቁስጥንጥንያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ። በተሾመ ጊዜም ከብቻው እግዚአብሔር በቀር ማንም ሊአስወግደው የማይችል የጥልና የመለያየት የማይድን በሽታ በፍቅር አንድ አደረገ :: ዜናውም በሮማውያን ኤጲስቆጶሳት ዘንድ በተሰማ ጊዜ አባ አካክዮስን ከቁስጥንጥንያ መንበር አሳደዱት በቀናች ሃይማኖት እንደ ፀና በደሴት ውስጥ አረፈ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 197🕊 9🥰 6
Photo unavailableShow in Telegram
ኅዳር ፳፱ /29/በዚችም ዕለት የተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ (የሰማዕታት መጨረሻ) የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት። ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው። ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ጴጥሮስ" አለችው። ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ። ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ጴጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት። ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር᎓᎓ ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ᎓᎓ አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው። ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ። ብዙ ተአምራትንም ሠራ። በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ጵጵስናው ላይ አልተቀመጠም:: በኋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ። ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ። በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ። ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ። ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ። ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 264🕊 20🥰 6
መድኃኔዓለም
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አዝአላስብም አልፈዋለሁ ብዬ ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
አዝየቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
አዝትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ
አዝእየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መድኃኔዓለም_የለም_የሚሳነው_ዘማሪት_ሲስተር_ሕይወት_ተፈራ_2018_የአእላፍት_ዝማሬ_መዝሙር.m4a3.87 MB
❤ 140🥰 14🕊 4
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
√
አንዳንድ አጋጣሚዎች በሕይወታችን
ትልቁን ለውጥ ሊፈጥሩ ወይም የሆነ
ነገርን ሳናስብ ድንገት እንድንወደው
ሊያደርጉን ይችላሉ ።
Green Bird Tech የሚሰጣቸው
ኮርሶችም ምናልባት እንዲሁ ሳይሆኑ
አይቀሩም 🤗
ምንም መነሻ ዕውቀት ይዛችሁ ኑ
አንልም ፣ ይልቅ ከምንም ተነስታቹ
የትም ድረሱ ነው ሀሳባችን ።
የማያግባባን አንድ ነገር ብቻ ነው
አ
ለ
መ
ሥ
ራ
ት
አያግባባንም ብቻ ሳይሆን
አያዛልቀንም ጭምር 🤫
ማወቅ ለሚፈልግና ለሚተጋ ግን
የምንነፍገው አንዳች ነገር የለንም።
√
የውሳኔ ሰው ሁኑ
ዛሬውኑ ተመዝገቡ
ይህንን ሁሉ ባንድ ጊዜ
አስተምረን እስከቤታቹ
እንሸኛቹሃለን 😄
• Laptop
• Internet
• በቂ ጊዜ
አላችሁ ?
ይሄው
@Greenbirdtechnology
ላይ አሁኑኑ ተመዝገቡ
@greenbirdtechs
@greenbirdtechs
የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
❤ 57🔥 4🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
➛ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ልብሰ ስብሐት ማሰፊያ የሚውል መንፈሳዊ ዕጣ በ100 ብር ብቻ በመቁረጥ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ።
➟ ዳሽን ባንክ፦ 5542906694011
ከላይ ባለው ባንክ ቁጥር 100 ብር ብቻ በመላክ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ።
ትኬት ለመግዛት እነዚህን ስልኮች ይጠቀሙ
+251909837170
+251962913061
ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
2018 ዓ.ም
❤ 79
Photo unavailableShow in Telegram
✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
➛ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ልብሰ ስብሐት ማሰፊያ የሚውል መንፈሳዊ ዕጣ በ100 ብር ብቻ በመቁረጥ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ።
➟ ዳሽን ባንክ፦ 5542906694011
ከላይ ባለው ባንክ ቁጥር 100 ብር ብቻ በመላክ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ።
ትኬት ለመግዛት እነዚህን ስልኮች ይጠቀሙ
+251909837170
+251962913061
ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
2018 ዓ.ም
ሕዳር 28/፳፰/በዚች ቀን የሀገረ ኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ሰረባሞን በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ በተወለደ ጊዜ በአባቱ ስም ስምዖን ብለው ጠሩት አባቱም ሲሞት ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ። መልአክም ተገለጸለትና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ እንዲሔድ አዘዘው እንዳዘዘውም ሔደ። እርሱም የጌታችንን ሰው የመሆኑን ምሥጢር ገለጠለት ግን ዘመዶቹ የሆኑ አይሁድን ስለፈራ በኢየሩሳሌም አገር የክርስትና ጥምቀትን ሊአጠምቀው አልደፈረም። ኤጲስቆጶሱም ስለርሱ ምን እንደሚያደርግ ሲያስብ እመቤታችን ተገልጣለት ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎናስ እንዲልከው አዘዘችው። ሰረባሞንም እየተጓዘ ሳለ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ቀደም ብሎ በሰው አምሳል ወደ ቴዎናስ ቀርቦ ስለ ቅዱስ ሰረባሞን አስረዳው ሰረባሞንም በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕግ አስተምሮ የከበረች የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው። ከዚህም በኋላ ኒቅዮስ ለሚባል አገር ኤጲስቆጶስነት ሾመው። እግዚአብሔርም ከሀገረ ስብከቱ ጣዖታትን ደመሰሰ ዳግመኛም አብን ወልድን መንፈስ ቅዱስን አንድ አካል የሚያደርግ የሰባልዮስን ስድብ አስወገደ። ዲዮቅልጥያኖስም ስለ ቅዱስ ሰረባሞን በሰማ ጊዜ በብዙ ዓይነት ሥቃይ አሠቃየው። ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ምክንያት በጌታችን እንዳያምኑ ንጉሡ ፈርቶ ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያ ቅዱስ ሰረባሞንንም ለሀገሩ ደቡብ ወደ ሆነ ቦታ ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወስደው በክብር ገነዙትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆች ተአምራት ሆኑ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
« አሁን ያለሁበት ሁኔታ በጥቂቱ 😁 »
እያወራን ያለንው ስለምናደርገው እውነታ ነው
• Laptop
• Internet
• በቂ ጊዜ
አላችሁ ?
ይሄው አሁን ተመዝገቡ ባለሙያ ሁኑ
@Greenbirdtechnology
√ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
√ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500
√ ቤታቹ ሆናቹ ብቻ
ብቁ ግራፊክስ ዲዛይነር ሁኑ
ደግሞም Video Editing Course
ተሸለሙ
1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ
2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ
3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ
የኮርስ ቀናት
ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00
እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00
3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ
ምሽት 2:00 - 4:00
@greenbirdtechs
@greenbirdtechs
የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
❤ 39🔥 4
መረቤን በአሳ የመላ
መረቤን በአሳ የመላ /2/
ማን አለ ከአምላኬ ሌላ /2/
ነገር ሁሉ ውብ የሚሆነው
ባንተ ነው ጌታ ባንተ ነው /2/
አዝበስምህ ስንጀምር ፍፃሜያችን ያምራል እጅህ ከኛ ጋራ በጥበብ ይሰራል ከቶ ያላንተ ፈቃድ ማን ከዚህ ደረሰ ደስ ብሎት ያደረ ተድላን የቀመሰ
አዝከብዙ ድንቢጦች እበልጥብሀለሁ የማትዘነጋኝ ነህ ይህንን አውቃለው የግራው መንገዴን በቀኝ የምትመራ እስተካከላለው ስሆን ካንተ ጋራ
አዝአቤኔዘር አለ ሳሙኤል በቋንቋው በጨለማው ዘመን ስለረዳኸው አንተን የታመነ ሲሳዩ ይበዛል ባዶውን የመጣ አፍሶ ይመለሳል
አዝመኝታው ይሞቃል እንጀራው ያጠግባል እግዚአብሔር ካለበት ኑሮ ይደላደላል ብዙ ብንበለፅግ እልፍ ቢኖረን ፀጋው ከሌለበት አይደምቅም ድንኳን ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
6082726593_1 (19).mp36.14 MB
❤ 136🥰 5🕊 1
