ar
Feedback
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

الذهاب إلى القناة على Telegram

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

إظهار المزيد
222 280
المشتركون
-13524 ساؚات
-6137 أيام
-2 27430 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል በጋዛ የነበሩ ከ700 በላይ የውሃ ጉድጓዶችን ማውደሟ ተነገረ‼️ እስራኤል በጋዛ ጦርነት በጋዛ የሚገኝን 85 በመቶ የውሃ ጉድጓድ ማውደሟን የከተማዋ ባልስልጣናት አሳውቀዋል። የውሃ ጉድጓዶቹ በመውደማቸውም በጋዛ በነፍስ ወከፍ ከጦርነቱ በፊት 90 ሊትር በቀን የነበረው ድርሻ ወደ 15 ሊትር መውረዱ ተነግሯል። የእስራኤል ጦርነት በጋዛ ከተማን የሚያጠጡ 3 የውሃ ምንጮችን ያጠቃ ሲሆን ከእነዚህ የውሃ ምንጮች የሚገኘው ውሃ ከአንድ አመት በፊት በ35 በመቶ መቀነሱ ተነግሮ ነበር። የጋዛ የከርሰምድር ውሃ በቀን 262,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃን ለከተማዋ የሚያቀርብ ሲሆን በጦርነቱ በደርስባቸውም ጉዳት የሚያመርቱት የውሃ መጠን በቀን ከ93,000 ኪዩቢክ ሜትር በታች ሆኖ ነበር። የጨው ውሃን ከሚያጣሩ የጋዛ ማጣሪያዎች መካከል በቀን 10,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚያጣራው ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ ሲሆን ሌሎቹም የማጣራት አቅማቸው ከግማሽ በላይ ቀንሷል። ጋዛ ካጋጠማት የውሃ ችግር በተጨማሪ በጦርነቱ 2 ሚሊየን ሜትር የፍሳሽ ማስወገጃ በመውደሙ ቆሻሻ ውሃ ወደተቀረው የውሃ አካል እየገባ እየገባ መሆኑንም አስታውቃለች። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 172😭 127🕊 16😡 16👍 10😁 3🎉 2
Photo unavailableShow in Telegram
👉ሙሉኮከብ ሪል እስቴት እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል 👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ áŠĽáŠ“ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ 👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው ።        🔸2 ሊፍት       🔸️የከርሰ ምድር ውሃ       🔸️backup ጀነኔተር       🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3200 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል። 👉ባለ አንደ መኝታ  82ካሬ  👉ባለ ሁለት መኝታ  96ካሬ  ,99ካሬ áŠĽáŠ“ 105ካሬ 👉ባለ ሶሰት መኝታ  120ካሬ  ,124ካሬ  እና 127ካሬ  👉ባለ አራት መኝታ  182 ካሬ 25% ቅድመ ክፍያ እና 60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው 👉ለዲያስፖራ 20/80 የባንክ ብድር የተመቻቸ 📣በ መሀል CMC መሪ መኖሪያ ቤቶን ይግዙ። ለበለጠ መረጃ 💁‍♂📞 0984323293 💁‍♂📞0919261500        
إظهار الكل...
❤ 25🙏 1
የጤና ሚኒስቴር ተከናዉኗል ባለዉ የዘረመል ምርመራ፣ ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ ከተማ መከሰቱ የተገለጸው የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል‼️ ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ተደርጓል ባለዉ ምርመራ ከቀናት በፊት በበሽታዉ መጠርጣራቸዉን ካሳወቀዉ 8 ሰዎች ዉጪ አዲስ በበሽታው የተጠረጠረ አለመገኘቱን ገልጿል። ቫይረሱን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከር የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ክልሉ መላኩን ጠቁሟል። በምርመራው መሰረት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው የቫይረስ ዝርያ ከዚህ በፊት በሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለው መሆኑ ታውቋል። ይህን ተከትሎ በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ተቋቁሞ የምላሽ ስራዎች እየተስተባበሩ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል። በ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የሚመራዉ የአለም ጤና ድርጅት በጂንካ አካባቢ የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመከላከል 300 ሺህ ዶላር ከድርጅቱ አስቸኳይ ፈንድ በኩል መልቀቃቸውን መግለፃቸው ይታወሳል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 256👍 33🕊 14🔥 10😁 6😭 5👌 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኤርትራን "የግዛት አንድነት ጥሰቶች" በተመለከተ መንግሥት የያዘው "የመታቀብ" አቋም "ሁሌም እንደማይቀጥል" ዶ/ር ጌዲዮን አሳሰቡ‼️ ኤርትራ በኢትዮጵያ "ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት" ላይ የምትፈጽማቸው "ጥሰቶችን" በተመለከተ የፌደራል መንግሥት የያዘው እርምጃ ከመውሰድ "የመታቀብ" አካሄድ "ሁሌም የሚቀጥል እና ገደብ የለሽ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት" የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ። ዶ/ር ጌዲዮን፤ ኢትዮጵያ "ከኤርትራ መገንጠል በፊት እና በኋላ" በአሰብ ወደብ ላይ "ባፈሰሰችው ከፍተኛ ሀብት ምክንያት"፤ አሰብ በፌደራል መንግሥት "በዋነኛነት ቅድሚያ የሚሰጠው" ጉዳይ እንደሆነ መግለጻቸውም ተዘግቧል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ይህንን የተናገሩት ትናንት ሐሙስ ኅዳር 4/2018 ዓ.ም. "ሆርን ሪቪው" የተባለው ቲንክ ታንክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባካሄደው የፖሊሲ ፎረም ላይ ነው። ዶ/ር ጌዲዮን፤ አምባሳደሮችን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች በታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ በአፍሪካ ቀንድ የታዩ ሰሞነኛ ሁኔታዎች በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥትን ፖሊሲ እና ምልከታ አቅርበዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ በተለይም ያተኮረው በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ላይ ነው።በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ለዘመናት የዘለቀው ግጭት መነሻ ከድንበር ውዝግብ ወይም ከባህር በር ፍላጎት የተሻገረ መሆኑን እንዳብራሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ ባወጣው የዶ/ር ጌዲዮን ሙሉ ንግግር ላይ ሰፍሯል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 218👍 45😁 23👏 7🤝 7😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
👉ሙሉኮከብ ሪል እስቴት እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል 👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ áŠĽáŠ“ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ 👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው ።        🔸2 ሊፍት       🔸️የከርሰ ምድር ውሃ       🔸️backup ጀነኔተር       🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3200 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል። 👉ባለ አንደ መኝታ  82ካሬ  👉ባለ ሁለት መኝታ  96ካሬ  ,99ካሬ áŠĽáŠ“ 105ካሬ 👉ባለ ሶሰት መኝታ  120ካሬ  ,124ካሬ  እና 127ካሬ  👉ባለ አራት መኝታ  182 ካሬ 25% ቅድመ ክፍያ እና 60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው 👉ለዲያስፖራ 20/80 የባንክ ብድር የተመቻቸ 📣በ መሀል CMC መሪ መኖሪያ ቤቶን ይግዙ። ለበለጠ መረጃ 💁‍♂📞 0984323293 💁‍♂📞0919261500        
إظهار الكل...
❤ 29🔥 2🤝 2
10ኛው የአፍሪካ ሕብረት-ተመድ የጋራ ዓመታዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል‼️ በ2026 የሚካሄደውን 10ኛውን የአፍሪካ ሕብረት-ተመድ ዓመታዊ ኮንፈረንስ አዲስ አበባ እንደምታስተናግድ ተገለጸ። የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም፣ የደኅንነት እና የዘላቂ ልማት አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል። 9ኛው የአፍሪካ ሕብረት-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓመታዊ ኮንፈረንስ ኒው ዮርክ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ተካሂዷል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኮንፈረንሱን በጋራ መርተዋል። መሪዎቹ በአፍሪካ ሕብረት እና በተመድ መካከል ያለው ዘላቂ አጋርነት ለዓለም አቀፍ ሰላም፣ ደኅንነት እና ዘላቂ ልማት የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን አረጋግጠዋል። የትጥቅ ግጭቶች፣ ሰብዓዊ ቀውሶች እና የዓለም አቀፍ ሕግ መሸርሸር ላይ ጥልቅ ስጋታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ለቀውሶቹ መፍትሔ ለመስጠት ፖለቲካዊ እና የውይይት መፍትሔዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በሊቢያ፣ በታላላቅ ሐይቆች ቀጣና፣ በሳህል እና በመላው አፍሪካ የሚካሄዱ አፍሪካ-መር የሰላም ሂደቶችን ለመደገፍ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል። የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይልም ለሥራው በቂ ፋይናንስ የሚያገኝበት መንገድ ሊመቻች እንደሚገባ በውይይታቸው አንስተዋል። በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ፣ በአየር ንብረት እርምጃ እና ሁሉን አቀፍ ልማት በተለይም በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እና በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ውጤቶች ላይ ትብብርን ማጎልበት እንደሚገባም ገልጸዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 192😁 16👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
👉ሙሉኮከብ ሪል እስቴት እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል 👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ áŠĽáŠ“ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ 👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው ።        🔸2 ሊፍት       🔸️የከርሰ ምድር ውሃ       🔸️backup ጀነኔተር       🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3200 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል። 👉ባለ አንደ መኝታ  82ካሬ  👉ባለ ሁለት መኝታ  96ካሬ  ,99ካሬ áŠĽáŠ“ 105ካሬ 👉ባለ ሶሰት መኝታ  120ካሬ  ,124ካሬ  እና 127ካሬ  👉ባለ አራት መኝታ  182 ካሬ 25% ቅድመ ክፍያ እና 60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው 👉ለዲያስፖራ 20/80 የባንክ ብድር የተመቻቸ 📣በ መሀል CMC መሪ መኖሪያ ቤቶን ይግዙ። ለበለጠ መረጃ 💁‍♂📞 0984323293 💁‍♂📞0919261500        
إظهار الكل...
❤ 19👍 2
የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ህዳር 21 ይከበራል‼️ የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ መግለጫ ሰጥተዋል። ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በመግለጫቸው፤ ኢትዮጵያ እንደ አየር ኃይል ያሉ ዘመናዊ ተቋማት ከገነቡ ሀገራት አንዷ ነች ብለዋል። ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሀገር ናት ያሉት ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ከአፍሪካ ቀድማ ዘመናዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የገነባች ሀገር መሆኗን ገልፀዋል። ከእነዚህ ተቋማት መካከል የኢፌዴሪ አየር ኃይል አንዱ መሆኑን ጠቁመው፤ ተቋሙ እራሱን በሰው ሀይል፣ በውጊያ መሰረተ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች እያጠናከረ ነው ብለዋል። የዘንድሮ 90ኛ የአየር ኃይሉ የምስረታ በዓል ህዳር 21 ቀን በተለያዩ መርኃ ግብሮች በድምቀት እንደሚከበር ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገልጸዋል። የምስረታ በዓሉ በተለያዩ ሁነቶች እና ትርዒቶች እንደሚከበርም ጠቅሰዋል። የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግም ህዳር 21 "ለአየር ኃይል ዕድገት በሙሉ አቅሜ እሮጣለሁ" በሚል ሀሳብ በቢሾፍቱ ከተማ የ10 ኪ.ሜ ዓለምአቀፍ የጎዳና ሩጫ ይካሄዳል ተብሏል። በመግለጫው የተገኙት የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ፤ የሩጫ ውድድሩ ጨምሮ ሌሎች ሁነቶች ለከተማዋ ገጽታ እና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን በበኩላቸው፤ በዚህ የጎዳና ሩጫ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ተሳታፊዎች ጨምሮ ከ25ሺ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ብለዋል። ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ በቋሚነት እንደሚዘጋጅም ተጠቅሷል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 219👍 29😁 25🤝 6😱 3🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
👉ሙሉኮከብ ሪል እስቴት እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል 👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ áŠĽáŠ“ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ 👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው ።        🔸2 ሊፍት       🔸️የከርሰ ምድር ውሃ       🔸️backup ጀነኔተር       🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3200 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል። 👉ባለ አንደ መኝታ  82ካሬ  👉ባለ ሁለት መኝታ  96ካሬ  ,99ካሬ áŠĽáŠ“ 105ካሬ 👉ባለ ሶሰት መኝታ  120ካሬ  ,124ካሬ  እና 127ካሬ  👉ባለ አራት መኝታ  182 ካሬ 25% ቅድመ ክፍያ እና 60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው 👉ለዲያስፖራ 20/80 የባንክ ብድር የተመቻቸ 📣በ መሀል CMC መሪ መኖሪያ ቤቶን ይግዙ። ለበለጠ መረጃ 💁‍♂📞 0984323293 💁‍♂📞0919261500        
إظهار الكل...
❤ 27
የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አፈጻጸም ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት፣ በተለይ በአከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የሚሰላውን አማራጭ አነስተኛ ግብር በተመለከተ ከፍተኛ እፎይታ የሚሰጥ ማብራሪያ ሰጥቷል‼️ ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል የንግዱን ማህበረሰብ አስጨንቆ የነበረውን የትርፍ ህዳግ (Profit Margin) ግዴታ የሚያነሳ በመሆኑ በነጋዴዎች ዘንድ በደስታ ተቀባይነትን አግኝቷል። በሚኒስቴሩ ማብራሪያ መሰረት፣ የአከፋፋዮች አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚሰላበት መንገድ ግልጽ ሆኗል። በዚህ መሰረት ፤  ጅምላ ሻጭ/አከፋፋይ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው ጋር ባደረገው ውል የሚሸጥበት ዋጋ እና የሚያገኘው መቶኛ (ትርፍ ህዳግ) በግልጽ የተወሰነ ከሆነ፣ አማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በጠቅላላ የሽያጭ ገቢው ላይ ሳይሆን፣ በውል ወይም በሕግ በተፈቀደለት የትርፍ መቶኛ ላይ ብቻ ይሆናል ተብሏል። ይህ አዲስ አፈጻጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ ማትረፍ አለባችሁ በሚል ያስቀመጠው ግዴታ በንግዱ ላይ የፈጠረውን ጫና የሚያቃልል ነው። ይሁንና፣ ይህንን ውሳኔ ለመጠቀም አከፋፋዩ የመሸጫ ዋጋ እና የትርፍ ህዳግ በውል መወሰኑን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ለግብር ባለስልጣናት ማቅረብ ይኖርበታል። ይህን የገንዘብ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተከትሎ ነጋዴዎች ለካፒታል ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፣ ውሳኔው የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ እና ከገበያ እውነታ ጋር የሚጣጣም ፍትሃዊ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አከፋፋይ "የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ አትርፉ ማለቱ እኛ የማንችለውና ንግዱን ለከፍተኛ መቀዛቀዝ የዳረገ ነበር። አሁን የገንዘብ ሚኒስቴር 'በውል የተቀበሉትን የትርፍ ህዳግ ተቀበሉ' ሲል ለገቢዎች ሚኒስቴር ያሳወቀው ነገር ትልቅ እፎይታ እና መተንፈሻ ሰጥቶናል።" ሲሉ አድንቀዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን ማብራሪያ የሰጠው የአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ገና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ በመሆኑ በአዋጁ ላይ የተፈጠረውን ግልጽነት የጎደለው ሁኔታ ለማስተካከል መሆኑ ተጠቁሟል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 179👍 18🕊 8😡 7🤝 5👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
❤ 10
Photo unavailableShow in Telegram
👉ሙሉኮከብ ሪል እስቴት እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል 👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ áŠĽáŠ“ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ 👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው ።        🔸2 ሊፍት       🔸️የከርሰ ምድር ውሃ       🔸️backup ጀነኔተር       🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3200 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል። 👉ባለ አንደ መኝታ  82ካሬ  👉ባለ ሁለት መኝታ  96ካሬ  ,99ካሬ áŠĽáŠ“ 105ካሬ 👉ባለ ሶሰት መኝታ  120ካሬ  ,124ካሬ  እና 127ካሬ  👉ባለ አራት መኝታ  182 ካሬ 25% ቅድመ ክፍያ እና 60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው 👉ለዲያስፖራ 20/80 የባንክ ብድር የተመቻቸ 📣በ መሀል CMC መሪ መኖሪያ ቤቶን ይግዙ። ለበለጠ መረጃ 💁‍♂📞 0984323293 💁‍♂📞0919261500        
إظهار الكل...
❤ 24👍 1
ለብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት የሥራ መመሪያ ተጠናቀቀ‼️ ለብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና የፓርቲው ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት የሥራ መመሪያ በስኬት ፍፃሜውን ማግኘቱን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋናው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ አስታወቁ። "በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሐሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከጥቅምት 19 እስከ 30 በአዳማ እና በአዲስ አበባ ከተሞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሲሰጥ ቆይቷል። በሥልጠናው ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የፓርቲው አመራሮች እንደተሳተፉበት አቶ አደም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመላክተዋል። ሥልጠናው የአስተሳሰብ አንድነት ከመፍጠር እና የተግባር አፈፃፀምን ከማላቅ አኳያ እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ የተገኘበት እና ፓርቲው እውነተኛ የኅብረ ብሔራዊነት ተምሳሌት መሆኑም በተጨባጭ የተንፀባረቀበት ነበር ሲሉም ገልጸዋል። የሥልጠና መርሀ ግብሩ ከዝግጅት እስከ ገለጻ፣ የቡድን ውይይት፣ ተሞክሮ ልውውጥ፣ የልማት ሥራዎች የመስክ ጉብኝት እና ማጠቃለያ ድረስ ዓላማውን በሚገባ አሳክቶ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታውን ለተወጡ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። በዚህም አስተባባሪዎችን፣ አሰልጣኞችን፣ አወያዮችን፣ የፀጥታ ተቋማትን፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ልዩ ልዩ ተቋማቱን አመስግነዋል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሥልጠናው ተሳታፊ አመራሮችም ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስገና ያገኙ ናቸው። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 228😁 38😭 16👌 11💔 5😡 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የምርጫ ቦርድ የጌታቸው ረዳን 'ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ' ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ለሕዝብ ይፋ አደረገ‼️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን በመጠቀም፣ በአቶ ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ አመራር የቀረበለትን የአዲስ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል ቦርዱ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት፣ የምዝገባ ጥያቄው የቀረበለት ፓርቲ "ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት)" በሚል ስያሜ ሲሆን፣ በእንግሊዝኛ ደግሞ "Tigray Democratic Solidarity Party (Solidarity)" በመባል ይታወቃል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ያደረገው "በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011" መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት ስላለው እንደሆነ የገለፀ ሲሆን በዚኹ መሠረት እነአቶ ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ “ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ወይም Tigray Democratic Solidarity Party (Solidarity)“ በሚል ስያሜ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ፤ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 መሠረት በፓርቲው ስም፣ ዐርማ ወይም ሌሎች ጉዳዮች ተቃውሞ ያለው ሰው፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከዛሬ ከጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርብ ቦርዱ አሳውቋል፡፡ ©የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 215😁 43👍 36👌 6😱 4🎉 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
إظهار الكل...
❤ 26👍 1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎርጎራ ጣናነሽ-፪ን በይፋ ሥራ አስጀመሩ‼️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎርጎራ ጣናነሽ-፪ ጀልባን በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። ጀልባዋ በጣና ውሃ ላይ እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኢኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት። አክለውም፥ ከ180 ተጓዦች በላይ የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ-፪ ለጉብኝት፣ ለመዝናናት እና አስደማሚውን የጣና ሐይቅ የተፈጥሮ ከባቢ ለመጎብኘት ወደ ጎርጎራ ኢኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ የበለጠ ምቹ አድርጋዋለች ብለዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 232👍 50😁 38😭 13🙏 7💔 6😱 4
ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ‼️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰላማዊው እና ፖለቲካዊው ሂደት የሚያናጉ ክስተቶች እንዲሁም የፕሪቶሪያን ስምምነት የሚጎዱ እንቅስቃሴዎችን እየተመለከትን ነው። ትግራይን ለማናጋትና እርስ በእርስ እንድንጣላ ሆን ተብሎ በአፋር ውስጥ ታጣቂዎች እንዲደራጁ፣ እንዲታጠቁ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር እና ድጋፍ በመስጠት እንዲሁም ተልዕኮ በመስጠት በትግራይ ላይ ተደጋጋሚ የወሰን ጥሰት እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል አሁንም እየተደረገ ነው። ይህ "ሓራ መሬት(ነፃ መሬት)" በሚል ስም በአፋር የሚገኝ ታጣቂ ኃይል ባለፈው ዓመት በተደጋጋሚ በዚህ ዓመት ደግሞ ቀደም ብሎ በኮነባና አብዓላ አቅጣጫ በተደጋጋሚ የመተንኮስ ተግባር ሲፈጽም ቆይቷል። በመቀጠልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በደቡብ ትግራይ ራያ አዘቦና ራያ ጨርጨር ከሕዝብና ባለሃብቶች ጋር የያዘውን የልማት ውይይት ለማደናቀፍ ሲባል ከመጋሌ እና ቶንሳ ተነስተው ደደርባ እና ጸሓፍቲ ገረብአገው ድረስ በመሄድ የአስተዳደሩ አመራሮች ያልፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው የመቐለ-መኾኒ መሾመር ላይ ሁከት ሊፈጥሩ የሚችሉ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል። የትግራይ ሕዝብ እና ጊዜያዊ አስተዳደር ግን የውስጥ ችግሮቻችን በውይይት ለመፍታት እና ለሁለቱም ሕዝቦች ወንድማማችነት እና ጉርብትና ክብር በመስጠት፣ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በመነሳት ሁኔታውን ከመግለጽ ተቆጥበው ቆይተዋል። አሁንም ቢሆን በትግራይ በኩል ሁከት ወይም አለመረጋጋት እንዲፈጠር በፍጹም አይፈልግም። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ችግር እየፈጠረ ያለው አካል ተመልሶ ከሳሽ በመሆን ትናንት ረቡዕ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ል የብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአፋር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች ወደ አፋር መሬት ዘልቀው በመግባት ጥቃት እንደፈጸሙ ገልጿል። ይሁን እንጂ ይህ መግለጫ መሠረት የሌለው ሲሆን የተረገጠ የአፋር ወሰን እንደሌለ እና በተቃራኒው እየተፈጸመ ያለው ተግባር ለሰላማዊ እና ታሪካዊ የወንድማማችነት እና የጉርብትና ግንኙነት የማይመጥን እንዲሁም በመኸር ወቅት የትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ክፋት መሆኑ ግልጽ ነው። በፌዴራል መንግሥት በኩል የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ባለመፈጸሙ ሰላማዊ ሂደቱን እና መተማመንን ከመጉዳት አልፎ የሕዝባችን መከራ እና ስቃይ እንዲቀጥል የሚያደርግ ሲሆን፣ በውጤቱም ሰላማዊውን ፖለቲካዊ ትግል የሚያናጋ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያንና የአካባቢውን ሰላም የሚያናጋ እና ያልተፈለገ ዳግም ጥፋት የሚያስከትል የጥፋት መንገድ ነው። ስለሆነም የፕሪቶሪያ ውል ያለ መዘግየት እንዲፈጸም፣ የትግራይ ሕገ መንግሥታዊ ወሰን እንዲረጋገጥ እና ሕዝባችን ደኅንነቱ ተጠብቆ ወደ ቀዬው እንዲመለስ እንዲደረግ እንዲሁም በግዳጅ ትግራይን ለማዳከም የሚደረገው እንቅስቃሴ ታርሞ በተረጋጋ መንገድ ወደ ውይይት እና መፍትሔ እንድንገባ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል። በሌላ በኩል የሚታዩትን ችግሮች እንደ ዕድል በመጠቀም የውስጥ ችግራችን እንዲወሳሰብ ትግራይ ዳግም የጦርነት ሜዳ እንድትሆን ለማድረግ ሆን ተብሎም ሆነ ባለማወቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የትግራይ እና የሕዝቧ መሠረታዊ ጥቅም እና ደኅንነት በአጠቃላይ የሚጎዳ ተግባር ነው። ስለዚህ አንዱንም ይሁን ሌላውን እየደገፉና እያበረታቱ ትግራይን የጦር ሜዳ ለማድረግ የምትጥሩ አካላት የተለያዩ ምክንያቶችን በመጠቀም በውስጣችን ጥርጣሬ እንዲሰፍን የምትሠሩና ትዕዛዝ ተቀባዮች የሆናችሁ አካላት ከድርጊታችሁ እንዲቆጠቡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በጥብቅ ያሳስባል። የትግራይ ችግር በዘላቂነት የሚፈታው በትግራይ እና በትግራዋይ ነው የሚል ጽኑ እምነት ያለው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በውስጣዊ ፖለቲካዊ ችግር የሐሳብ ልዩነት መፈጠሩ መደበኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ችግራችን በውይይት እና በመግባባት ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እያረጋገጠ ልዩነት ያለው የታጠቀ ይሁን ያልታጠቀ ሁሉም አካል ከውይይት እና ከመግባባት ውጭ ትግራይን የሚጠቅም ሌላ መፍትሔ እንደሌለ ይገነዘባል። በኃይል እና ሕይወት በመክፈል የሚለወጥ ሁኔታ አይኖርም። አሁንም ቢሆን ዘላቂ ደኅንነትና ቋሚ ሰላም በተአማኒነት የሚረጋገጠው የፕሪቶሪያ ውልን አጥብቆ በመፈጸም መሆኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በጽኑ ያምናል። ስለሆነም ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር እና የፕሪቶሪያን ውል ያለ መዘግየት ለመፈጸም ዝግጁነቱን በድጋሚ ያረጋግጣል። በመጨረሻም መላው የትግራይ ሕዝብ በውስጥም ሆነ በውጭ  አሁን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለመጠበቅ እና ለማጠናከር እንዲሁም ብሔራዊ አንድነትን ለማደላደል እንዲታገል በማሳሰብ በዚህ እና በዚያ በሚበተን ወሬ ከትግራይ ጦርነት ተጠቃሚ ነን ብለው እንቅልፍ በሚያጡ ነውረኞች በሚፈጠረው አለመረጋጋት ሳይረበሹ ተረጋግተው በዕለታዊ ሥራቸው ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲረባረቡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ባለፉት ጊዜያት ከሕዝባችን ፍትሐዊ ጥያቄ ጎን በመቆም የሕዝቡ መከራ እንዲሰማ የ ዘር ማጥፋት ጦርነቱ በፕሪቶሪያ ውል እንዲቆም ታሪካዊ አስተዋጽኦ አበርክታችኋል። የትግራይ ሕዝብና ጊዜያዊ አስተዳደር ምስጋናቸውን እየገለጹ አሁንም ቢሆን የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ እንዲፈጸም እና ዘላቂና ቋሚ ሰላም ደኅንነት በኢትዮጵያ እና በአካባቢው እንዲረጋገጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦአችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ል መቐለ @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 271😁 33👍 13🕊 9😱 8🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
❤ 8
Photo unavailableShow in Telegram
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን 70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ 0957504151 0995232706
إظهار الكل...
❤ 17
Photo unavailableShow in Telegram
ፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ‼️ ከጥፋቱ የማይመረው ጉጅሌው የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በመግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 በመደብደብ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል። በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም የአዛውንቶች የህወሓት ጉጅሌ በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል። ይህ የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም ጉጅሌው ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል። ይህ ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው ተስፋ ቢሱ የህወሓት ጉጅሌ ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የዜጎች ደህንነትና የወሰኑን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራስን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ እንገልፃለን። በተያያዘ ዜና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በፌስቡክ ገፃቸው የህወሓት ጦር አፋር ድረስ ዘልቆ ጦርነት መክፈቱን አረጋግጠዋል። በጉዳዩ ላይ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ስለትንኮሳው ከፌዴራል መንግስትም ፣ ከህወሓት እንዲሁም ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል የተባለ ነገር የለም። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
❤ 280😭 76😁 25👍 24😡 8😱 7🔥 4