አዲስ ነገር መረጃ
الذهاب إلى القناة على Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
إظهار المزيد103 408
المشتركون
-6824 ساعات
-937 أيام
+16730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ኢሎን መስክ በፎርብስ መረጃ መሠረት ከ$600 ቢሊዮን በላይ ሀብት በማፍራት በታሪክ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል
ለዚህ ዋና አስተዋፅዖ ያደረጉት ቴስላ ፣ ስፔስኤክስ እና xAI የገበያ ካፒታላይዜሽን እድገት ነው።
ከዚህ ቀደም ስፔስኤክስ ለአይፒኦ (IPO-Initial Public Offering) ለመዘጋጀት ባንኮችን መምረጥ መጀመሯ ተዘግቦ ነበር—ይህ የሽያጭ ሂደት የተሳካ ከሆነ መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮኔር ሊሆን ይችላል።
❤ 7🤪 2
በሰው ዘንድ የተናቁትን በማክበር ይታወቃል🙏
በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን በገዳመ አስቄጥስና በደብረ ሲሐት ይታወቃል፡፡
ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ያፈራባት ታላቁዋ የቅዱሳን ስፍራ ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን በቅድስናው ደቀ መዛሙርትን ወልዶባታል፡፡ ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ይጠራል:: ዘመነ ጻድቃን በሚባለው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ዓለምን ንቆ፣ ገና በወጣትነቱ የመነነ ቅዱስ አባት፣ ስም አጠራሩ የከበረ፣ በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው፡፡ "አባ ዳንኤል ዘገዳመ አስቄጥስም" ይሰኛል፡፡ ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለማችን ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም በስፋትም አንደኛ ገዳም ነው፡፡ ሁሌም በገዳሙ አበ ምኔት ሆነው የሚሾሙት አበው የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው፡፡
ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ ያልነበረው ትጉሁ አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በሁዋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል፡፡ ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ፣ ድውያንን ሲፈውስ፣ ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል፡፡ ሌሊት ጭው ወዳለው በረሃ ወርዶ የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድራል፡፡ በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል፡፡ ከእነዚህ ሥውራን ቅዱሳን መካከልም ለ38 ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረችው እሥራኤላዊቷ ቅድስት ዓመተ ክርስቶስና መንግስቷን ትታ በሥውር የኖረችው ቅድስት በጥሪቃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም በማክበሩም ይታወቃል፡፡ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀነ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ" ብለው የናቋቸውን ቅዱስ ምሕርካንና በሴቶች ገዳም "እብድ" ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል፡፡ በእርሱ ዘመን ይሰራጭ ለነበረ ጦማረ ልዮን ለሚባል ኬልቄዶናዊ የኑፋቄ ደብዳቤ በትጋት ምላሽ ሲሰጥ የነበረ ታላቅ ሐዋርያም ነበር አባ ዳንኤል፡፡ አንድ ቀንም በንጉሡ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ከወታደሩ ቀምቶ በመቅደዱ ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል፡፡ አውሎጊስ የሚባል ደሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ ጻድቁ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ደሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ፡፡ ጌታም በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታዬ" ሲለው ጌታችን ሃብትን ሰጠው፤ ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ፡፡
ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት፡፡ ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው፡፡ እመቤታችን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች:: "ልጄ ሆይ ማር!" አለችው፡፡ ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ፣ አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው፡፡ በአንድ ወቅት ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም ሊዘርፍ ገባ፡፡ ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ ስለበራ ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል፡፡ አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ ታሕሳስ 7 ዐርፏል፡፡
ገዳማውያን ድንቅ ስራቸውና የጸሎታቸው ኃይል ይህን ያህል ድንቅ ተአምር ያርጋል፡፡ በዓታቸውን ስናጸና ገዳማቸውን ስንደግፍም የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 11
Photo unavailableShow in Telegram
በህንድ ባል ሚስቱን በእባብ አስነድፎ ከገደለ በኋላ ከሶስት አመት በኋላ እውነታው ታወቀበት
አንድ ባል ሚስቱን ከገደለ በኋላ ሌላ አሳዛኝ ክስተት ለማስመሰል በመሞከር ዱካውን ለመደበቅ ሞክሯል በሚል ህንድ ውስጥ መያዙን ኤንዲቲቪ ዘግቧል።
ሚዲያው እንደዘገበው ሩፔሽ አምበርካር ከሦስት ጓደኞቹ ጋር አሴሮ፣ መርዘኛ እባብ ወደ ቤት አምጥቶ፣ እሷ ተኝታ ሳለች ሆን ብሎ ሚስቱ ላይ አስቀመጠው። በእባቡ በመነከሷም ሕይወቷ አለፈ።
ለሦስት ዓመታት ያህል ሩፔሽ፣ ጓደኞቹና ተባባሪዎቹ በአጋጣሚ የተፈጠረ አደጋ መሆኑን ሁሉም እንዲያምኑ ማድረግ ችለዋል። ከጥቂት ዓመታት በኋላ አንድ መርማሪ ጉዳዩን መልሶ አይቶ በምስክርነቱ ውስጥ ልዩነቶችን በማስተዋሉ በመጨረሻም ሰውዬው ተጋለጠ።
@Addis_News
@Addis_News
👏 25❤ 24😨 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንግሊዝኛ ቋንቋን ቤትዎ ቁጭ ብለው ይማሩ
Mark Language Academy
የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመናገር ክህሎትዎን ወይም ችሎታዎን የትም ሳይሄዱ ቤትዎ ቁጭ ብለው Face to Face በ Zoom, በቴሌግራም Video Call ወይም Google meet ላይ መማር ይችላሉ
እንዲሁም አስገራሚ ለውጥ ያመጣሉ
✅ Speaking ( ንግግር)
✅ Listening ( ማዳመጥ)
✅ Grammar ( ሰዋሰው )
✅ How to read and Write ( መፃፍ ና ማንበብ )
ሁሉንም በ5 ወር ውስጥ ብቻ ይቻሉና ራስዎን ይለውጡ
ከ ሰርተፍኬት ጋር ......
ለመመዝገብ ያናግሩን 👇
@MarkEngAcademy
☎️ 0908880599
❤ 6
ጋምቤላ ትኩረት ይፈልጋል
በዛሬው ዕለት በጋምቤላ ከተማ 02 በሚገኘው ዋና ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው አንድ የፖሊስ ኮሚሽን መገደሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በከተማዋ ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ 7 ሰዓት አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ምንጮቹ ገልፀዋል።
ይህን ተከትሎ ሁኔታው እስኪረጋጋ በከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተከልክሏል ብለዋል።
@Fikerassefa @Yenetube
❤ 8👍 7😢 7
Photo unavailableShow in Telegram
"ፀልዩልኝ" ማስተር አብነት
በማህበራዊ አስተዋፅኦው ስሙ ከፍ ብሎ የሚነሳው ማስተር አብነት "ፀልዩልኝ" ብሏል።ወንድማችን ማስተር አብነት አሞኛል ሲል ተደምጧል።
"ህመሜን ለማንም መናገር አልፈልግም ግን ደግሞ ሰውነት ይታያል።ሁላችሁም ፀልዩልኝ "ብሏል።ማስተር አብነት በርካቶች የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ ካሉበት ችግር እንዲወጡ የድርሻው እየተወጣ የሚገኝ ብርቱ ወጣት ነው።
@seledadotio
@seledadotio
🙏 126❤ 38👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
👨💼 እቤትዎ ሆነው ስራ መስራት ይፈልጋሉ?👍
⌛🖥 የኦንላይን ስራዎች የሚሰሩበት እና እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎችን የሚያገኙበት አሪፍ አፕልኬሽን፤ ባሉበት ቦታ ሆነው በስልኮ በቀላሉ የሚሰሩበት እና በየወሩ ተከፋይ የሚሆኑበት አፕ❗️
💥🎮በቀላሉ ከታች ባለው ሊንክ አፑን ዳውንሎድ በማድረግ መስራት እና መጠቀም ትችላላችሁ።
📱📱 DOWNLOAD ለማድረግ 📱📱
🔽🔽🔽🔽
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.habeshanjobs.habeshanjobs
⚡️ @Habeshan_Jobs_Com
⚡️ @Habeshan_Jobs_Com
❤ 4
Photo unavailableShow in Telegram
እንግሊዝኛ ቋንቋን ቤትዎ ቁጭ ብለው ይማሩ
Mark Language Academy
የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመናገር ክህሎትዎን ወይም ችሎታዎን የትም ሳይሄዱ ቤትዎ ቁጭ ብለው Face to Face በ Zoom, በቴሌግራም Video Call ወይም Google meet ላይ መማር ይችላሉ
እንዲሁም አስገራሚ ለውጥ ያመጣሉ
✅ Speaking ( ንግግር)
✅ Listening ( ማዳመጥ)
✅ Grammar ( ሰዋሰው )
✅ How to read and Write ( መፃፍ ና ማንበብ )
ሁሉንም በ5 ወር ውስጥ ብቻ ይቻሉና ራስዎን ይለውጡ
ከ ሰርተፍኬት ጋር ......
ለመመዝገብ ያናግሩን 👇
@MarkEngAcademy
☎️ 0908880599
Photo unavailableShow in Telegram
በብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር 154 ብር ከ77 ሳንቲም ተሽጧል።
በዚህ 12ኛ ዙር ጨረታ 50 ሚልየን ዶላር
ቀርቦ የነበረ ሲሆን 13 ባንኮች ጨረታውን አሸንፈዋል።
@seledadotio
@seledadotio
🤪 13❤ 8
Photo unavailableShow in Telegram
በሙስና የተጠረጠሩ የኤሌክትሪክ ሠራተኞች ተቀጡ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ በ54 ሠራተኞቹ ላይ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት በዲጂታል አማራጮች ከህብረተሰቡ በደረሱ ጥቆማዎች መሰረት ነው እርምጃው የተወሰደው።
በዚህም መሰረት 5 ሰራተኞች ከስራ ሲሰናበቱ፣ 37ቱ የደመወዝ ቅጣት፣ 12ቱ ደግሞ ከቦታ ዝውውር እና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።
ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚያጋጥሟቸውን የሙስና ችግሮች በተቋሙ የዲጂታል መተግበሪያዎች በኩል ጥቆማ መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ተቋሙ አሳስቧል።
@seledadotio
@seledadotio
👍 15❤ 11
Photo unavailableShow in Telegram
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ቀጠናውን እየረበሸ ነው - ኢሳይያስ አፈወርቂ
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ወደ ሳውዲ አቅንተው ከሳውዲው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ለአንድ ሚዲያ በሰጡት ቃለምልልስ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ከበርካታ ሀገራት የጦር መሳሪያ እየጎረፈለት ይገኛል ያሉ ሲሆን ይህ ሀይል ለሱዳን እንዲሁም ለቀጠናው ከባድ ስጋት ደንቅኗል ሲሉ መናገራቸውን አዩ ዘሀበሻ ተመልክቷል።
ፈጥኖ ደራሽ ጦሩ በሱዳን ሲቪሊያንን እየገደለ ነው፣ አስገድዶ መድፈር እየፈፀመ ነው፤ ለዚህ ሀይል የሚደረገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ መቆም እንዳለበት ለሳውዲው አልጋ ወራሽ እንደተናገሩ በቃለምልልሳቸው ላይ አንስተዋል።
ኤርትራ ለሱዳኑ ወታደራዊ መሪ አልቡርሃን ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ተከትሎ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በኤርትራ ላይ እርምጃ እንደሚስድ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 22🤣 10💯 1
የሀጅ ጉዞ ምዝገባ
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2018 የሀጅ ጉዞ ምዝገባ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ምክር ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ የምዝገባ ሰነዶችን አሟልተው ለሚገኙ የሃጅ ተጓዦች ምዝገባቸውን በ30 ደቂቃ ውስጥ ጨርሰው እንዲመለሱ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።
ለምዝገባ የተሰጠው ጊዜ አናሳ በመሆኑ እንዲሁም አሁን ላይ የሚቀሩት ቀናት ከ40 ያነሱ ቀናት በመሆናቸው ሁጃጆች ከወዲሁ አስፈላጊ የሚባሉ ሰነዶችን በማሟላት ወደ ምዝገባ ተቋማት በመሄድ እንዲያጠናቅቁም ጠይቋል።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 12🤣 5
Photo unavailableShow in Telegram
ባል በማኅበራዊ ሚዲያ የሌሎች ሴቶችን ፎቶ 'መውደድ' ወይም like ማድረግ የጋብቻን መሠረት የሚያፈርስ ተግባር ነው ተባለ
በቱርክ ውስጥ በቅርቡ የተሰጠው አንድ የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚፈጸሙ ድርጊቶች በፍቺ ክሶች ውስጥ ከፍተኛ የሕግ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኗል።
ከካይሰሪ ከተማ የመጣች አንዲት ሴት ባሏ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሌሎች ሴቶችን ፎቶ በተደጋጋሚ Like ማድረጉ የጋብቻን ክብር የሚያጎድፍና መተማመንን የሚጎዳ መሆኑን በመግለጽ ባሏን ከሰሰች።
ፍርድ ቤቱ የባለቤቱን የኦንላይን እንቅስቃሴ መረመረና ሚስቱ ያቀረበችውን ክስ ተቀብሏል። ዳኞቹም ባልየው በትዳሩ መፍረስ ላይ 'ከባድ ጥፋተኛ' መሆኑን በመወሰን ለሚስቱ ካሳና የፍች ቀለብ እንዲከፍል ትዕዛዝ አስተላለፈዋል።
ዳኞቹ ፎቶ 'መውደድ' በቀጥታ የዝሙት ድርጊት ባይሆንም፣ በትዳር ውስጥ ያለውን ሥነ ልቦናዊ መተማመን የሚያዳክም እና የጋብቻን መረጋጋት የሚያናጋ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።
ይህ ታሪካዊ ውሳኔ በቱርክ ውስጥ የዲጂታል ባህሪዎች በፍቺ ጉዳዮች ላይ ከባድ የሕግ ውጤት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ያረጋገጠ ሲሆን፣ የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ አዲስ አቅጣጫ ጠቋሚ ሆኗል።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 25🤣 6👏 4🥱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቦርዱ ለ45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች ዕውቅና ሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሠርቲፊኬት ሰጥቷል።
ለታዛቢዎቹ ዕውቅናው የተሰጠው ቦርዱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሲሆን፤ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡና መሥፈርቱን ላሟሉ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሠርቲፊኬት መስጠቱ ተገልጿል።
ቦርዱ ቀደም ሲል 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች፤ የታዛቢዎችን የምዝገባ ሂደት ቀልጣፋ መረጃ አደረጃጀቱንም ዘመናዊ እንዲያደርግ ታስቦ የተዘጋጀው “የበይነ-መረብ ላይ ምዝገባና መረጃ አደረጃጀትን” አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱን አስታውሷል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
🤪 7❤ 6
የሃይማኖት ነገር ቁሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊና በሃይማኖት ሆኖ በመንፈሳዊነት የሚታወቅና የሚታመን ነው።
ሥላሴ፣ ሠለሰ ሶስት አደረገ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን፤ ሥላሴ ማለት ሶስትነት ማለት ነው። ለምሣሌ ሰዎች በጸበል ይድናሉ፡፡ አንዱ ጸበል ሁሉን አይነት በሽታ ይፈውሳል፡፡ በዓለም ሕክምና ግን የአንደኛው መድኃኒት ለአንዱ መርዝ ነው፡፡ መንፈሳዊው ሕክምና ጸበል ግን ጤነኛ ቢጠጣው መጠበቂያ፣ ሕሙም ቢጠጣው ፈውስ ነው፡፡
የሥላሴን አኗኗር በስጋዊ ስሌት የማንመረምረውም መንፈሳዊ በመሆኑ ነው፡፡ የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት ስንማር ከሂሳብ ቀመር ሕግ አስተሳሰብ ነጻ መሆን ያሻል። ምክንያቱም መንፈሳዊዉ ጥበብ ሥጋዊዉን ጥበብ ወይም ፍልስፍና ይመረምረዋል እንጅ መንፈሳዊ ጥበብና ምሥጢር በዓለማዊ ዕውቀትና ምርምር ሊደረስበት አይቻልምና።
በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን፣ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ አምላክ ቅድስት ሥላሴ፡፡ በዘፍጥረት 18÷1 “እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ ስር ለአብርሐም ተገለጠለት። አብርሐምም ዓይኑን አነሳና ሦስት ሰዎችን አየ” የሚል ቃል አለ፡፡ ይህ ድንቅ ምስጢር እግዚአብሔር በሶስትነቱ በሰዎች አምሳል ለአብርሐም መገለጡን በቁጥር ሶሰት ብሎ ያስረዳል። አንዳንዶች ይህ ሀሳብ ስለሥላሴ አይደለም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ መጽሐፉ ግን “እግዚአብሔር ከሶስት ሰዎች ጋር ወይም ከሁለት መላእክት ጋር ተገለጠለት” አይልም። ወይም መላእክትም ሆኑ ሰዎች በዚህ ሥም አይጠሩም፤ በኢሳ 42÷8 “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው! ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም።” ይላልና፡፡ በማያወላዳ ሁኔታ ሦስት ሰዎችን አየ” ብሎ ለይቶ ስለተናገረ እግዚአብሔር ሦስትነት ያለው መሆኑን በግልጽ ያስረዳል።
የቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ከዓለም በፊት የነበረ ስም ነው እንጂ ኋላ የተገኘ አይደለም፡፡ ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ የእግዚአብሔርን አንድነት በባህርይ፣ በህልውና፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ በመፍጠር በመሳሰሉት፡፡ የሰው ነፍስ የቅድስት ሥላሴ ምሳሌ ናት፡፡ ይኸውም አብ በልብ፣ ወልድ በቃል፣ መንፈስ ቅዱስ በእስትፋስ ይመሰላሉ፡፡ በእግዚአብሔርነቱ፤ ልብ፣ ቃል፣ ሕይወት አለ። ነፍስ ሶስት ባህርያት ቢኖሯትም አንድ እንደምትባል እግዚአብሔርም ሶስት ስም፤ ሶስት ግብር፤ ሶስት አካል፤ ቢኖረውም አንድ አምላክ እንጅ ሶስት አማልክት አይባልም፡፡ ሥላሴ የሚለው ስም የአንድነትና የሶስትነት ስም ነው፡፡ በስም፣ በግብርና በአካል ሶስት እንላለን፡፡
በመዝሙር 138÷7 እንደተጻፈው በሁሉ የመላ ነውና፡፡ “ከመንፈስህ ወዴት እሔዳለሁ፤ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ውቅያኖስም ጥልቅ ብወርድም በዚያ ትገኛለህ፤ እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ ከአጽናፍ አጽናፍ ብበርም እጅህ በዚያ ትመራኛለች ቀኝህም ትይዘኛለች” ይላል፡፡ ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈሰ ቅዱስ ለየራሳቸው ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል፣ አላቸው። አካል በአጠቃላይ ሙሉው የሰውነታችን ክፍል ነው። የፍጡራን አካል የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚመጠን፤ የሚወሰን፣ ሲሆን የሥላሴ አካል ግን፤ የማይታይ ፣ በእጅ የማይዳሰስ፣ በቦታ የማይወሰን፣ በሁሉም ምሉዕ ነው። የቅድስት ሥላሴ ምሕረትና ቸርነት አይለየን፡፡
ገዳማውያኑ ይህን ምሕረትና ቸርነት ተስፋ አድርገው ይተጋሉና ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 39🙏 4🤪 4
የሱዳን ቀውስ፡ በወርቅ እያበራ፣ በረሃብ እያለቀሰ
ሱዳን በዘር ማጽዳት፣ አስገድዶ መድፈር፣ 4.3 ሚሊዮን የሚሆኑ የተፈናቀሉ ሰዎች እና በከባድ የምግብ ቀውስ የተመታች የአፍሪካ ሀገር ነች።
በሱዳን ባለው የዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ቢያንስ 150,000 ሰዎች ተገድለዋል። በዚህ ሁኔታ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሱዳንን በዓለም ላይ እጅግ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ያለባት ሀገር አድርጎ አውጇል።
በዚህች ሀገር ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ማዕድናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቶን ወርቅ አለ።
በተጨማሪም፣ በነዳጅ በበለፀገችው ሱዳን ውስጥ በእነዚህ በጥቁር ገበያ በተሸጡት ሀብቶች የተገኘው ገንዘብ በርስ በእርስ ጦርነቱ ውስጥ ሚና እየተጫወተ ነው። ወርቁ ቢኖርም በአስተዳደር መጓደል እና በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ ቢያንስ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች በረሃብ እየተሰቃዩ ነው።
የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ታሪክ
ሱዳንከፈረንጆቹ እስከ 1956 ድረስ በእንግሊዝ እና በግብፅ ትተዳደር ነበር። በግብፅ እርዳታ ሀገሪቱ ጥር 1956 ነፃነቷን አገኘች። ከዚያ በኋላ በደቡብ ሱዳን እና በአሁንዋ ሱዳን መካከል የዘር እና የሃይማኖት ግጭት የነበረ ሲሆን ረጅም ግጭት ተፈጠረ። በ1983 ፕሬዝዳንት ጃዓፋር ኑማን የእስልምናን ሸሪዓ ህግ ሲያስተዋውቁ ከደቡብ ሱዳን ጋር ከባድ የእርስ በእርስ ጦርነት ተጀመረ።
በዚህ ሁኔታ የሱዳን ወታደራዊ እና እስላማዊ የፖለቲካ መሪዎች ያቀዱት መፈንቅለ መንግስት ተካሄደ። ኦማር አልበሽር ሰኔ 1989 በመፈንቅለ መንግስቱ ሱዳን ውስጥ ስልጣን ያዙ። በወቅቱ አልበሽር በሱዳን ጦር ሰራዊት ደህንነት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ያለው መኮንን ነበሩ። መፈንቅለ መንግስቱን የመሩት እሳቸው ነበሩ።
ነገር ግን በ2019 አልበሽር አሰቃቂ እጣ ፈንታ ውጤቶችን መቀበል ነበረባቸው። በ2019 በሱዳን በእርሳቸው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ። በዚህም ምክንያት ጦር ሠራዊቱ በሌላ መፈንቅለ መንግስት ፕሬዝዳንቱን ገለበጠ። ሆኖም፣ ተራው ሕዝብ ዲሞክራሲ እንሰፍን በመጠየቅ ተቃውሞውን ቀጠለ። በተቃውሞው ጫና የሠራዊቱና የሲቪል አስተዳደሩ በጋራ ተነሳሽነት መንግሥት የተቋቋመ ቢሆንም፣ ያ መንግሥትም በጥቅምት 2021 በሌላ መፈንቅለ መንግስት ተወገደ።
ከመፈንቅለ መንግስቱ ጀርባ የነበሩት ሁለቱ ዋና ዋና ሰዎች ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና ጄኔራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ናቸው። ጄኔራል አል-ቡርሃን የሱዳን የታጠቁ ኃይሎች (ሠራዊቱ) መሪ እና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ናቸው። ሃምዳን ዳጋሎ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) አዛዥ ናቸው። በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች መሠረት፣ ይህ መጥፎ ስም ያተረፈው ከፊል ወታደራዊ ኃይል (RSF) በሱዳን ውስጥ የተለያዩ ሰብአዊ ወንጀሎችን እየፈፀመ ነው። የቡርሃን እና የዳጋሎ ኃይሎች ለሱዳን ቀውስ ተጠያቂ ናቸው።
የጦርነቱ ዋና አቅርቦቶች ወርቅ እና ነዳጅ ናቸው
በሱዳን ውስጥ በተገኙ የተለያዩ ማዕድናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቶን ወርቅ ተከማችቷል ተብሎ ይነገራል። በተጨማሪም፣ ተጨማሪ ማዕድናት ሳይገኙ አሉ ። በሱዳን ውስጥ ትልቁ የወርቅ ማዕድን ቦታ ጀበል አመር ነው። ማዕድኑ በቀጥታ በRSF ቁጥጥር ስር ነው። ከዳጋሎ ቤተሰብ ጋር የተቆራኘው አል-ጁናይድ ኩባንያ ማዕድኑን ሲያስተዳድር ቆይቷል። በተጨማሪም በዳርፉር እና በደቡብ ኮርዶፋን ክልሎች ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የወርቅ ማዕድናት በአሁኑ ጊዜ በRSF ቁጥጥር ስር ናቸው።
በ2024 RSF ከእነዚህ ማዕድናት ቢያንስ 10 ቶን ወርቅ አውጥቷል፣ የገበያ ዋጋውም 860 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው። ሁለቱ ትልልቅ ገዢዎች የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ግብፅ ናቸው። ከዚህ ወርቅ ውስጥ 80 በመቶው በህገ-ወጥ መንገድ ይዘዋወራል። ለህገ-ወጥ ዝውውር በጣም የታወቀው መንገድ ከዳርፉር ድንበር ክልል ወደ ግብፅ በኢትዮጵያ በኩል ነው።
ሌላው ከዳርፉር ድንበር ክልል ወደ ሊቢያ ከዚያም ወደ ኤሚሬትስ ነው። በተጨማሪም RSF በታኅሣሥ መጀመሪያ የሱዳንን ትልቁ የነዳጅ መስክ የሆነውን ሄግሊግን ተቆጣጥሯል። ዜጎችን ለመግደል እየዋለ ያለው መሳሪያ በወርቅና በነዳጅ ገንዘብ እየተገዛ ነው።
አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ እና የዋጋ ግሽበት
ግጭቱ በመላው ሱዳን ከ150,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል። ረሃብ በሀገሪቱ ተስፋፍቷል። ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችም ተደፍረዋል።
ዓለም አቀፉ የስደት ድርጅት (IOM) እንደገለጸው በሱዳን ውስጥ 30 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ 9.6 ሚሊዮን የሚሆኑት በውስጥ ተፈናቃዮች ሲሆኑ፣ 4.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎረቤት አገሮች ተሰደዋል።
በተጨማሪም ከ700,000 በላይ ሕጻናት በከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ሲሆን ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሱዳን ፓውንድ ያለማቋረጥ ዋጋው እየቀነሰ ነው። በ2025 በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት 113 በመቶ ደርሷል።
የዩኒሴፍ ባለስልጣን ቴድ ቻይባን እንደተናገሩት በችግሩ በከፋ ሁኔታ የተጎዱት ህጻናት ናቸው። ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በረሃብ ስጋት ውስጥ ሲሆኑ፣ 14 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው፣ ይህም በሱዳን ውስጥ ካሉት ህጻናት አራት አምስተኛው ነው። በሰሜን ዳርፉር ብቻ በዚህ ዓመት 150,000 ሕጻናት በከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።
ምንጭ፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር/ቢቢሲ/አልጀዚራ
@Addis_News
@Addis_News
❤ 23😢 12
