ar
Feedback
YeneTube

YeneTube

الذهاب إلى القناة على Telegram

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

إظهار المزيد
108 095
المشتركون
-12324 ساعات
-5057 أيام
-2 11030 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ የጉዞ ገደቦችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሰፋ አዲስ አዋጅ ማክሰኞ ዕለት ፈርመዋል። በዚህ አዋጅ መሠረት፣ ቀደም ሲል 19 የነበሩት ሙሉ ወይም ከፊል የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው አገራት ቁጥር ወደ 39 እንዲያድግ ተደርጓል። ዋይት ሀውስ እንደገለጸው፣ እርምጃው የተወሰደው ዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት አገራት ተጓዦችን በመለየት እና መረጃን በማጋራት ረገድ "ከፍተኛ የደህንነት ጉድለት" ስላታዩባቸው ነው። ​በፕሬዝዳንቱ አዲስ ውሳኔ መሠረት ሰባት አገራት—ላኦስ፣ ሴራሊዮን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶሪያ—በሙሉ የጉዞ እገዳ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል። በተጨማሪም እንደ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ሴኔጋል እና ዛምቢያ ያሉ 15 አገራት አዲስ የከፊል እገዳ ተጥሎባቸዋል። አዋጁ ከሀገራቱ በተጨማሪ በየፍልስጤም ባለሥልጣን የጉዞ ሰነድ በሚጠቀሙ ግለሰቦች ላይም ገደብ ጥሏል። ​ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን ጥብቅ እርምጃ የወሰዱት በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የብሔራዊ ጥበቃ አባል በአፍጋኒስታን ተወላጅ መገደሉን ተከትሎ የኢሚግሬሽን ቁጥጥሩን ለማጠናከር በሚያደርጉት ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል። ትራምፕ ከጉዞ እገዳው በተጨማሪ የጥገኝነት ጥያቄዎችን ማገዳቸውን እና የተጀመረውን መጠነ ሰፊ ስደተኞችን የማስወጣት ዘመቻ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ​ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አዋጁ ሕጋዊ የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ (Green Card) ያላቸውን እና ቀደም ሲል ቪዛ የተሰጣቸውን ግለሰቦች በተመለከተ የተወሰኑ ልዩ ሁኔታዎችን እንደሚፈቅድ ተመልክቷል። በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 39 አገራት በእገዳው ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል እንደ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ያሉ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ይገኙበታል። Capital @YeneTube
إظهار الكل...
12
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አደረጉ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ማድረጋቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
إظهار الكل...
3
Photo unavailableShow in Telegram
15 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ። ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አሰብ ሆቴል አካባቢ ነው። ናታኒም ፍፁም የተባለው ግለሰብ ከግብረ አበሩ ሚኪያስ ዳባ ጋር በመሆን ምንጩ ያልታወቀ 15 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን በ8 ሺህ ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብር ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሊያውላቸውም ችሏል። ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረገው የአካል ፍተሻም ከኪሳቸው 75 ባለሁለት መቶ ሀሰተኛ ብር በአጠቃላይ 15ሺህ የኢትዮጵያ ሀሰተኛ የብር ኖት ባደረገው ፍተሻ መያዙን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው የቀጠለ መሆኑን የገለፀው የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀሰተኛ የብር ኖት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በመረዳት ፖሊስ መሰል የወንጀል ድርጊትን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ህብረተሰቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበርክት ጥሪ አቅርቧል። Addis Ababa police @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
7
Photo unavailableShow in Telegram
. ❤️ 190,000 (190 ሺ) ገብተናል እናመሰግናለን 🙏 ሁሉም ሰው ያገለገለ እቃውን እየሸጠ ነው - እርሶስ? ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ብቻ መሸጥ እንደሚችሉ ያውቃሉ? መግዛት ከፈለጉ ደግሞ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ። .      ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family . ET Creatives
إظهار الكل...
ጋምቤላ ትኩረት ይፈልጋል በዛሬው ዕለት በጋምቤላ ከተማ 02 በሚገኘው ዋና ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው አንድ የፖሊስ ኮሚሽን መገደሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በከተማዋ ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ 7 ሰዓት አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ምንጮቹ ገልፀዋል። ይህን ተከትሎ ሁኔታው እስኪረጋጋ በከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተከልክሏል ብለዋል። @Fikerassefa @Yenetube
إظهار الكل...
17😭 5😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢሎን መስክ የተጣራ ሃብት 600 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ፎርብስ ይፋ አደረገ። የኢሎን መስክ የተጣራ ሃብት የስፔስ ኤክስ ዋጋ 800 ቢሊየን ዶላር መገመቱንና ለህዘብ ድርሻው ይሸጣል መባሉን ተከትሎ 600 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል። መስክ 500 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ላይ የደረሰ የመጀመሪያው የምድራችን ሰው ባለፈው ጥቅምት ወር የሆነ ሲሆን 600 ቢሊየን ዶላር ላይም የደረሰ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። መስክ የስፔስ ኤክስ የ42% ባለድርሻ ሲሆን የድርጅቱ ዋጋ ግምትና በቀጣይ አመት ለህዝብ ገበያ እንደሚቀርብ ከተነገረ በኋላ የኢሎን መስክ ሃብት በ168 ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 677 ቢሊየን ዶላር ደርሷል። ኢሎን መስክ ከስፔስ ኤክስ በተጨማሪ የቴስላ እና የኤክስ ኤአይ ተቋም ከፍተኛ ባለድርሻ ሲሆን እነዚህም ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው እየጨመረ ይገኛል። የኢሎን መስክን ሃብት መጨመር ተከትሎም የአለማችን 10 ሃብታም ግለሰቦች የያዙት የሃብት መጠን 2.5 ትሪሊየን ዶላር ተሻግሯል። በዚህ አመት ብቻ የአለማችን አስሩ ሃብታሞች ሃብት በ558.9 ቢሊየን ዶላር ጨምሯል ሲባል ዘጠኙ ከአሜሪካ ሲሆኑ ከአስሩ ስምንቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው። በዚህ አመት የኢሎን መስክ ሃብት በ205 ቢሊየን ዶላር ሲጨምር በሁለተኝነት የተቀመጠው የጎግሉ ላሪ ፔጅ ሃብት በዚህ አመት በ96.8 ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 265 ቢሊየን ደርሷል። በሶስተኝነት የጎግሉ ሌላኛው መስራች ሰርጂ ብሪን በ247 ቢሊየን ዶላር ሲቀመጥ የአራተኛ ስፍራውን የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ በ246 ቢሊየን ዶላር ይዞታል። @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
14👍 2
3 መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ በመተት በቤተሰብህ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ እያለች ስታስፈራራ የነበረችን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች ተጠርጣሪዋ አለምነሽ አጉማስ፤ ወንጀሉን ፈፅማለች የተባለው ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ወሎ ሰፈር አካባቢ ከሚገኝ አንድ ፕላዛ ውስጥ ነው። ግለሰቧ በፕላዛው በጽዳት ሰራተኝነት እና በአሳንሰር ተቆጣጣሪነት ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን የግል ተበዳይ በዚሁ ህንጻ ላይ ከሚገኝ የአንድ የግል ድርጅት የፋይናስ ኃላፊ ናቸው። የግል ተበዳይ አቶ ግሩም ነጋሽ ለፖሊስ በሰጡት ቃል እንዳስረዱት የኔሰው የሚባል ግለሰብ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ቢኮሎ ከሚባል አካባቢ እንደሚደውል ገልጸው 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ ልጅህን የሰይጣን መሳቢያ አደርጋታለሁ የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት በማያውቁት ስልክ ተደውሎ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። የግል ተበዳዩ ያቀረቡትን አቤቱታ ተቀብሎ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና የተደወለበትን ስልክ እንዲሁም የማስፈራሪያ መልዕክት ያስተላለፈውን ሰው ድምፅ ማንነት ለመለየት በተደረገ ጥረት ተጠርጣሪዋ የግል ተበዳይን በመከታተል ካጠናች በኋላ ማንነቷን በመደበቅ እና ድምጿን በመቀየር አስፈራርታ 25ሺ ብር  በባንክ እንዲያስገቡላት ካደረገች በኋላ ቀሪ 275ሺ ብር ለማስላክ ስትሞክር የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት መረጃና ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ምርመራ ተጠርጣሪዋ ለመላክ ካዘጋጀችው የማስፈራሪያ  ጽሑፍ የእጅ ስልኳ ላይ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት መሆኑን የላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል። @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
😁 26 16😭 5
Photo unavailableShow in Telegram
  🟦 LinkedIn rental LinkedIn account  አሎት እንግዲያውስ እኛ ጋር ሲመጡ👉   •100-299 connections: $8 በየሳምንቱ   • 300-499 connections: $13 በየሳምንቱ   • 500-999 connections: $15 በየሳምንቱ   • 1000-1999 connections: $20 በየሳምንቱ   • 2000+ connections: $25 በየሳምንቱ 📱በኢትዮጵያ ትልቁ እና ታማኙ የሊንኪደን አካውንት ተከራይ አሁንም በርካታ አካውንቶችን ተከራይቶ ለቢዝነስ አላማ ማስተዳደር ይፈልጋል። 📱ከፍተኛ ኮኔክሽን ወይም ረጅም አመት ያስቆጠሩ አካውንቶች የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ in የእርስዎን አካውንት ደህንነት እንደራሳችን አካውንት አድርገን እንጠብቀዋለን። 📱 የእርስዎን አካውንት ከማከራየት ጎን ለጎን ሰው በመጋበዝዎ ኮሚሽን እንከፍላለን in ስምንት ወር እና 1ዐዐ ኮኔክሽን ዝቅተኛው መስፈርት ነው 📱 ጥራት ያላቸው አካውንቶች እንዲሁም ከ3ዐዐ+ በላይ የሆኑ አካውንቶች welcoming reward ወዲያውኑ ተፈፃሚ ይሆናል። 📱 ዝርዝር መረጃዎችን ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያለዎትን የኮኔክሽን እና የተከፈተበትን አመት 👤Contact Us Now:  📱: @Melech4  ☎️: 0967033154 Our telegram channel 👉 https://t.me/linkedinrent255work
إظهار الكل...
5👍 1🔥 1
Repost from YeneTube
00:40
Video unavailableShow in Telegram
🥁 65% /35% 🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫 🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ     🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ 🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።      🏠  80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ                          🥁ሙሉ  ክፍያ 5,770,050ብር    🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ             🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር ✅ መገልገያዎች 👉 ሁለት  ዘመናዊ  የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች 👉   የመኪና ማቆሚያ ቦታ 👉 ቴራስ   👉  ያልተገደበ  የውሃ አቅርቦት    👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር     👉 የደህንነት ካሜራ     👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም እንዲሁም ⛳️ ገላን ኮንደምንየም 🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ  እየሸጥን እንገኛለን። 🚴🏿‍♂️ይፍጠኑ🚴🏽‍♀️   🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733   ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።     Telegram @momsra16 ይፍጠኑ🗣
إظهار الكل...
12.33 MB
5
Photo unavailableShow in Telegram
ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሠርተፍኬት ሰጠ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም የሚያካሂደውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ 45 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የዕውቅና ሠርተፍኬት መስጠቱን አስታወቀ። ቦርዱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው መረጃ፤ የዕውቅና ሠርተፍኬቱን "በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011" እንዲሁም በ"የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012" መሠረት በተሰጠው ሥልጣን መስጠቱን ገልጿል። በዚህም የቦርዱን መስፈርት አሟልተው የተመረጡት 45 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መጪውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመታዘብ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች፤ የታዛቢዎችን የምዝገባ ሂደት ቀልጣፋ መረጃ አደረጃጀቱንም ዘመናዊ እንዲያደርግ ታስቦ የተዘጋጀው “የበይነ-መረብ ላይ ምዝገባና መረጃ አደረጃጀትን” አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ከጥቅምት 25 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. መስጠቱን አስታውሷል። Via AS @YeneTube @FikerAssefa
إظهار الكل...
😁 16 15👎 2
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ - ዳይናሚክ አክሲዮን ማህበር የስራ ቦታ፡ የሽያጭ እና የግብይት ኃላፊዎች (ብዛት 20 ) ‎አካባቢ፡ አዲስ አበባ ‎🔹 ቁልፍ ኃላፊነቶች ‎የኩባንያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቁ እና መሽምጥ። ‎የመስክ ግብይት እና የደንበኛ ክትትል ማካሄድ። ‎ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የሽያጭ ግቦችን ማሳካት። ‎የዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገበያ ግብረመልስ ሪፖርቶችን ማቅረብ። ‎🔹 መስፈርቶች ‎በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ። ‎እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ እና የማሳመን ክህሎቶች። ‎በጫና ስር የመስራት እና የሽያጭ ግቦችን የማሳካት ችሎታ። ‎በሽያጭ ወይም በማርኬቲንግ ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ነው (ግዴታ አይደለም።) ‎ሐቀኛ፣ ታታሪ እና የመስክ ስራ ለመስራት ፈቃደኛ። ‎🔹 የምናቀርበው ነገር ‎ወርሃዊ ደሞዝ + ማራኪ ኮሚሽን ‎የአፈጻጸም ጉርሻዎች ‎የስልጠና እና የሙያ እድገት እድሎች ‎📩 እንዴት ማመልከት እንደሚቻል (የTalentHub ብቻ) ‎ሁሉም አመልካቾች በTalentHub በኩል ብቻ ማመልከት አለባቸው። https://talenthubethiopia.com/ ‎📍 የቢሮ አድራሻ ‎Megenagna፣ Hibire ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 312፣ አዲስ አበባ‎ ‎📅 የማመልከቻ ቀነ-ገደብ፡ ‎ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ።
إظهار الكل...
15
Photo unavailableShow in Telegram
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ታኅሣሥ 8፤ 2018 ዓ.ም ለፌዴሬሽን እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ንግግር ሊያደርጉ ነው። ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ የ2 ቀናት የሥራ ጉብኝት የሚያካሄዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፤ ንግግር የሚያደርጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሚገኙበት የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መድረክ ላይ ነው። የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ለአባላቱ በላከው “አስቸኳይ” መልዕክት፥ “የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መድረክ ንግግር እንደሚያደርጉ” አስታውቋል። ምክር ቤቱ በዚሁ መልዕክቱ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በከተማው ዙሪያ የሚኖሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ከነገ በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገኙ አሳስቧል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው አንድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ይሄው መልዕክት እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል። የረቡዕውን የጋራ መድረክ በተመለከተ ለገዢው ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተመሳሳይ መልዕክት ቢላክም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካዮች ስለ ጉዳዩ በቀጥታ መረጃ እንዳልደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የነገ በስቲያው የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የፓርላማ ንግግር ዋነኛ ትኩረት ምን እንደሆነ ለምክር ቤት አባላቱ የተባለ ነገር የለም። የህንዱ ኤንዲቲቪ ቴሌቪዥን ጣቢያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የዲሞክራሲ እናት” ባሏት በሀገራቸው ህንድ ጉዞ ላይ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ሀሳባቸውን ለማካፈል “በጉጉት እንደሚጠባበቁ” መግለጻቸውን ዘግቧል። Via Ethiopia Insider @YeneTube @FikerAssefa
إظهار الكل...
42😁 8👎 4🔥 1😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሕፃናት በ12 ዓመታቸው የሞባይል ስልክ እንዲጠቀሙ መፍቀድ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃለ። ሕፃናት በ12 ዓመታቸው የሞባይል ስልክ (ስማርት ስልክ) እንዲይዙ እና እንዲጠቀሙ መፍቀድ ልጆቹን ለድባቴ እንዲዳረጉ፣ ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት ታጋላጭ እንዲሆኑ እና ለእንቅልፍ እጦት እንደሚዳርጋቸው አንድ ጥናት አመልክቷል። አዳጊዎች በረጅም ጊዜ ሂደት የአዕምሮ ዕድገት እና ጤና በተመለከተ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ከ10 ሺህ ሰዎች መረጃ በመሰብሰብ ነበር ጥናቱ በአሜሪካ ብሔራዊ የጤና እንስቲቲዩት ድጋፍ የተከናወነው። በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፊላደልፊያ የሕፃናት ሆስፒታል እና የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ በመሆን ነበር ሕፃናት የሞባይል ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ መፈቀድ የሚያስከትልው ጉዳት ምንድነው የሚለውን ጉዳይ ለመለየት እና የመፍትሔዎችን ለመጠቆም ጥናቱን ሲያከናውኑ የቆዩት። ዩኒቨርሲቲዎቹ ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሆኑ ሕፃናት ዘመናዊ ስልክ እንዲጠቀሙ መፍቀድ ከአእምሮ በሽታ እና ከመጠን በላይ ውፍረት ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው በዚሁ በሠሩት ጥናት ማረጋገጥ ችለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
13🔥 1😁 1😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ! የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዙ ተሰምቷል፡፡የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ድርጅቱ አሳውቋል፡፡ ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ህገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል። ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙም ታዟል።አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ አይቻልም ተብሏል። @YeneTube @FikerAssefa
إظهار الكل...
27👍 9😭 7👎 2🔥 1😁 1
Repost from YeneTube
00:40
Video unavailableShow in Telegram
🥁 65% /35% 🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫 🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ     🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ 🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።      🏠  80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ                          🥁ሙሉ  ክፍያ 5,770,050ብር    🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ             🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር ✅ መገልገያዎች 👉 ሁለት  ዘመናዊ  የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች 👉   የመኪና ማቆሚያ ቦታ 👉 ቴራስ   👉  ያልተገደበ  የውሃ አቅርቦት    👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር     👉 የደህንነት ካሜራ     👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም እንዲሁም ⛳️ ገላን ኮንደምንየም 🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ  እየሸጥን እንገኛለን። 🚴🏿‍♂️ይፍጠኑ🚴🏽‍♀️   🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733   ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።     Telegram @momsra16 ይፍጠኑ🗣
إظهار الكل...
12.33 MB
3👎 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ የ ኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የኢራንን የመከላከያ ስኬቶች ማሳያ ጎበኘ! በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በቴህራን የኢራንን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ስኬቶችን የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ጎብኝቷል። ጉብኝቱ ከከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት ጋር የተደረገውን ስብሰባ ተከትሎ የመጣ ሲሆን ልዑካን ቡድኑ ትናንት እሑድ በኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በሚገኘው የሀገሪቱ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ስኬቶች ላይ ያተኮረውን ኤግዚብሽን ተዘዋውሮ መጎብኘቱ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ወደ ቴህራን የተጓዙት በኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሞሃመድ ባገር ጋሊባፍ ይፋዊ ግብዣ ነው። በጉብኝቱ ወቅት፣ ልዑካን ቡድኑ በኢራን የመከላከያ ዘርፍ ስላሉት የቅርብ ጊዜ ዕድገቶች ማብራሪያ የቀረበለት ሲሆን፣ በኢራን ባለሙያዎችና ኢንዱስትሪዎች የተመረቱ የተለያዩ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ተመልክቷል። በጉብኝቱ ላይ ከተገኙ ባለስልጣናት መካከል የፍትህ ስርዓት ኃላፊ ግሆላም-ሆሴይን ሞህሰኒ ኤጄይ፣ ፕሬዝዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ይገኙበታል ሲል የኢራኑ መህር የዜና ወኪል ዘግቧል። @YeneTube @FikerAssefa
إظهار الكل...
21😁 12🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ለአጥንት ስብራት እና ለአካል ጉዳት ከሚዳርጉ ምክንያቶች ውስጥ የትራፊክ አደጋ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙ ተገለጸ። የኢትዮጵያ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ሀኪሞች ማህበር ፀሐፊ ዶ/ር ንጉሱ ገ/ዮሐንስ፤ ጉዳቶችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጥንትና የሰውነት ጉዳት እየደረሰ የሚገኘው በተሽከርካሪዎች በተለይም በሞተር ሳይክሎች እና በጋሪዎች በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች መሆኑን ገልፀዋል። ይህንን ችግር ለመለየትና መፍትሄ ለመስጠት እንዲቻልም በሀዋሳ የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የአደጋ መዝገብ ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ነግረውናል። ይህ ስርዓት አደጋዎች እንዴት እና የት አካባቢ በብዛት እንደሚከሰቱ ለማወቅ የሚያስችል መረጃ እንደሌለ በመታመኑ የተጀመረ ጥናት መሆኑን አንስተዋል። አብዛኛው ህብረተሰብ ወደ ወጌሻ የመሄድ ልምድ ስላለው ባህላዊውን የአጥንት ህክምና ከዘመናዊው ጋር ማስተሳሰር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መስራት እንደሚገባም ነው የገለፁት። ይህም ወጌሻዎች መሰረታዊ ስልጠና አግኝተው ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ጉዳት ወደ ጤና ተቋም ሪፈር የሚያደርጉበትን አሰራር ለመፍጠር በመታቀዱ ነው ብለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
16😭 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ! የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል። @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
11👍 1
በነዳጅ እጥረት የተነሳ ሰራተኞቻንን እያሰናበትን ነው›› ሲሉ በትግራይ ክልል የሚገኙ የማደያ ባለቤቶች ተናገሩ፡፡ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወደትግራይ የሚገባው ነዳጅ መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን አስታውቀዋል፡፡ በትግራይ የሚገኘው የተባበሩት ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ አቶ አታክልቲ ሀይሉና የቶታል ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጁ አቶ ኪሮስ አባይ በሰጡት መግለጫ የክልሉ ወርሀዊ የነዳጅ በጀት 15 ሚሊዮን ሊትር መሆኑን ገልፀው አሁን ግን እየገባ ያለው ከአንድ ሚሊዮን ሊትር በታች መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የነዳጅ አቅርቦቱ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር አውስተው ነገር ግን በ2017 መጠኑ እየቀነሰ መሄዱንና አሁን በ2018 ደግሞ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡ ችግሩ እንዲፈታ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ቢያቀርቡም አጥጋቢ መልስ ሊያገኙ አለመቻላቸውንም አስታውቀዋል፡፡ የተባበሩት ማደያ ስራ አስኪያጁ አቶ አታክልቲ ሲናገሩ ‹‹በተፈጠረው እጥረት የተነሳ ከመስከረም ወር አንስቶ ደመወዝ መክፈል አቅቶናል፡፡ ስለዚህም ሰራተኞቻችንን እያሰናበትን ነው፡፡›› በማለት ገልፀው ሰራተኞቹ መደበኛ ስራ ሲጀምሩ እንደሚመለሱ በመግለፅ እንዲያርፉ ማድረግ መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡ የማደያ ባለቤቶቹ እንዳሉት በመስከረም ወር አንድ ቦቴ ነዳጅ የተቀበሉ ሲሆን በቀጣይነት ሌላ አንድ ቦቴ የደረሳቸው ደግሞ በህዳር ወር ነው፡፡ ካለው እጥረት የተነሳም ያላቸውን ነዳጅ ለአምቡላንስ፣ ለክልልና ለዞን የመንግስት ቢሮዎችና ለሰላምና ደህንነት ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት ማደል መጀመራቸውን  አስረድተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም የህዝብ ትራንስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት መቆሙን ገልፀው ችግሩ የፌዴራል መንግስት በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከ180 ብር እስከ 240 ብር እየተሸጠ መሆኑን ያስታወቁት የማደያ ባለቤቶቹ የትራንስፖርት ታሪፍም እስከ 70 ፐርሰንት መጨመሩን ገልፀዋል፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
إظهار الكل...
18
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ - ዳይናሚክ አክሲዮን ማህበር የስራ ቦታ፡ የሽያጭ እና የግብይት ኃላፊዎች (ብዛት 20 ) ‎አካባቢ፡ አዲስ አበባ ‎🔹 ቁልፍ ኃላፊነቶች ‎የኩባንያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቁ እና መሽምጥ። ‎የመስክ ግብይት እና የደንበኛ ክትትል ማካሄድ። ‎ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የሽያጭ ግቦችን ማሳካት። ‎የዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገበያ ግብረመልስ ሪፖርቶችን ማቅረብ። ‎🔹 መስፈርቶች ‎በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ። ‎እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ እና የማሳመን ክህሎቶች። ‎በጫና ስር የመስራት እና የሽያጭ ግቦችን የማሳካት ችሎታ። ‎በሽያጭ ወይም በማርኬቲንግ ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ነው (ግዴታ አይደለም።) ‎ሐቀኛ፣ ታታሪ እና የመስክ ስራ ለመስራት ፈቃደኛ። ‎🔹 የምናቀርበው ነገር ‎ወርሃዊ ደሞዝ + ማራኪ ኮሚሽን ‎የአፈጻጸም ጉርሻዎች ‎የስልጠና እና የሙያ እድገት እድሎች ‎📩 እንዴት ማመልከት እንደሚቻል (የTalentHub ብቻ) ‎ሁሉም አመልካቾች በTalentHub በኩል ብቻ ማመልከት አለባቸው። https://talenthubethiopia.com/ ‎📍 የቢሮ አድራሻ ‎Megenagna፣ Hibire ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 312፣ አዲስ አበባ‎ ‎📅 የማመልከቻ ቀነ-ገደብ፡ ‎ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ።
إظهار الكل...
5👍 1